30/07/2026
ስህተት የመሥራት ፍርሃት እርምጃ ከመውሰድ ሲያግዳችሁ
የውድቀት ወይም የተሳሳተ ውሳኔ የማሳለፍ ፍርሃት ወደፊት እንዳትራመዱ የሚያስራችሁ ከሆነ፣ ጥንቃቄያችሁ እንደ ጥንካሬ ማገልገሉ ቀርቶ እንቅፋት ሆኖባችኋል ማለት ነው።
ከዚህ አይነቱ ስህተት ራስን ለመጠበቅ፣ ማድረግ በፈለጋችሁት ሁኔታ ዙሪያ በሚገባ ማሰብ፣ ማቀድና ሊደርስ የሚችለውን ችግር ተሻግሮ የመሄጃ ዝግጅት ማድረግ አስፈላጊ ነው፡፡
አንድን ነገር ለማድረግ ያደረባችሁ ጉጉት ሚዛናዊ ጥንቃቄ እንዳታደርጉ ከገፋፋችሁ
ነገሩን ለማከናወን ያላችሁ መነሳሳት ከማቻኮሉ የተነሳ ያለ ጥበብ፣ እቅድ ወይም ያለ በቂ ዝግጅት በጥድፊያ እንድትራመዱ የሚያደርጋችሁ ከሆነ፣ እርምጃችሁ ጉዳት የሚያስከትል ሊሆን ይችላል፡፡
ከዚህ አይነቱ ስህተት ራስን ለመጠበቅ፣ ለጋለው ስሜታችሁ ጊዜን መስጠት፣ በሁኔታው ዙሪያ የበሰሉ ሰዎችን ማማከርና እውነታ-ተኮር እቅዶችን ማውጣት አስፈላጊ ነው፡፡
ዋናው መርህ ሚዛንን መጠበቅ ነው፦ በድፍረት እርምጃ ውሰዱ፣ ነገር ግን ከማስተዋልና ከጥንቃቄ ጋር ይሁን።
መልካም ምሽት! Eyob Mamo