A.Kassa

A.Kassa ማር ተጣርቶና ሳይጣራ እና የወተት ውጤቶች (ቅቤ ተነጥሮና ሳይ?

23/01/2023

ማኅበረ ቅዱሳን ሰንበት ት/ቤቶች፣ ማኅበራት፣ ካህናት፣ ምእመናን እና የሚመለከተው የመንግስት አካል ለቤተ ክርስቲያን ዘብ እንዲቆሙም ጠየቀ::

(ባላገሩ ቴሌቭዥን፣ 15/2015፣ አዲስ አበባ)

ሕገ ወጥ "ሢመተ ጳጳሳት" ጉዳይ አስመልክቶ መግለጫ አውጥቷል።

የመግለጫው ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል፦

"መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ።" ሐዋ 20፣ 28

የማኅበረ ቅዱሳን ወቅታዊ መግለጫ

በትናንትናው ዕለት ጥር 14 ቀን 2015 ሲመተ "ኤጲስ ቆጶሳት" በሚል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ለመክፈል በተፈጸመ ድርጊት ጥልቅ ሐዘን ተሰምቶናል። ድርጊቱ በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ከታዩት አሳዛኝ መከፋፈሎች ሁሉ የተለየ መልክ ያለው ነው። ምንም እንኳን የመከፋፈል ጥሩ እና ምክንያታዊ የሆነ ባይኖርም ይኼኛውን ተመሳሳይነትም ሆነ ተወዳዳሪ ያለ አይስልም።

• ቀኖናዊት እና ሐዋርያዊት የሆነችውን ቤተ ክርስቲያን ቀኖና እና ሥርዓት የጣሰ መሆኑ

•በሕገ ቤተ ክርስቲያን ሲመተ ኤጲስ ቆጰሳትን በተመለከተ በግልጽ የተቀመጠውን ሕግ ሙሉ በሙሉ የጣሰ መሆኑ

• ከዚህ በፊት በታሪችን በፖለካዊ ለውጥ ምክንያት ተከስቶ የቆየው ሲኖዶሳዊ መፋፈል በዕርቅ መፈጸሙን እንደ ምሳሴ በመውሰድ፤ እኛም የፈለግነውን ከፈጸምን በኋላ ነገሩን በዕርቅ በመቋጨት የሾምናቸውን ይዘን እንቀላቀላለን የሚል ተገቢ ያልሆነ ስሌትን ታሳቢ እንዳደረገ የሚነገርለት መሆኑ

• በዐለም የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ቋንቋን እና ብሔርን መሠረት አድርጎ መለያየትን ማምጣት በማያወላውል መንገድ የተወገ እና የተጠላ መሆኑ ቢታወቅም በእኛ ሀገር ግን በሃይማኖታዊ ሥርዓት ሳይሆን ልክ እንደ ፖለቲካ መብት ሲቀነቀን የቆየ እና አሁንም ያን መንገድ የተከተለ መሆኑ

• በቤተ ክርስቲያናችን የአገልግሎት ሒደት በተለያዩ ወቅቶች እና ጊዜያት በሃይማኖታዊ አስተምህሮ ስሕተት፣ በሕግ ጥሰት እና በመሳሰሉት የተለያዩ የጥፋት ታሪክ ያላቸውን ሰዎች ያካተተ መሆኑ

• በአስተዳደር ሂደት የኩርፊያ ስሜት ያላቸውን ያካተተ መሆኑ እና

• ሿሚዎቹ ለዚህ መዓረግ ያበቃቻቸውን እና ክርስቶሳዊ አደራ የሰጠቻቸውን ቤተ ክርስቲያን ንቀው እና ቸል ብለው ራሳቸውን ከአንድ ብሔር እንደሆኑ የሚቆጥሩ እና ሃይማኖታችንና ቤተ ክርስቲያናችንን በዚሁ መንገድ አደረጃጀት እና አሠራር እንዲኖራት በሚደረግ እንቅስቃሴ ውስጥ የነበሩ መሆናቸው ምሳሌ እና ተወዳዳሪ የሌለው ጥፋት ለመሆኑ ማሳያዎች ሊሆኑ ይችላሉ።

በዚህም ምክንያት በሁኔታው ከልብ ማዘናችን አስቀድመን እየገጽን፤ ማኅበሩ እንደተቋም ያለውን አቋም እንደሚከተለ ይልጻል፦

1. ይህ ድርጊት ብዙ ነገሮች የታጨቁበት እና ብዙ ውጤቶችንም ሊያስከትል የሚችል እንደመሆኑ በተገቢው ትኩረት እና ፍጥነት ከቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ እንደሚሰጥበት ተስፋ እናደርጋለን።

በመሆኑም ቤተ ክርስቲያናችን እንደ የትኞቹም ጥንታዊያት እና ሐዋርያዊያት አብያተ ክርስቲያን ቀኖናዊ እና ሐዋርያዊ ክህነቷ ሳይናጋ እና አማኞቹም ሳይረበሹ ተጠብቀ ይኖሩ ዘንድ ቅዱስ ሲኖዶስ ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን ሳይሸራርፍ እና ሳያጓድል ፈጣን ውሳኔ በመወሰን የቤተ ክስቲያኒቱን ቀኖናዊነት እና ሐዋርያዊነት እንደሚያስጠብቅ በታላቅ ተስፋ እንጠብቃለን።

ምእመናንና ለቤተ ክርስቲያናችን አዎንታዊ ሀሳብ እና ድጋፍ ያላችሁ አካላት ሁሉ ያለምንም ሥጋዊ ፖለቲካዊ እና ፍልስፍናዊ ጫና ቀኖና ቤተ ክርስቲያን እንዲጠበቅ የየበኩላችንን ድርሻ እንድንወጣ እናሳስባን።

2 በሀገራችን ዘመናዊው ሕግ ከተተገበረበት ጊዜ ጀምሮ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያ ሕጋዊ ሰውነቷ ታውቆ እና መብቷ ተጠብቆ መቆየቷ የታውቀ ነው። ዛሬ ግን በሀገር ሕግ እንደሌለ በሚያስመስል ሁኔታ አንዳንድ አካት በተደጋጋሚ መብቶቿን ሲዳፈሩ እና ሕገ ጥ ድርጊቶች ሲፈጸሙባት እያስተዋልን ነው።

ይህ ዓይነት ድርጊት ደግሞ በሀገር ላይ ሁከትን ሊመያጣ እና የማኅበረሰብ ሰላምን ሊያናጋ የሚችል እጅግ አደገኛ ድርጊት መሆኑ የታወቀ ነው። ስለዚህም የሚመለከተው የመንግሥት አካል በፍጥነት ድርጊቱን በሕግ ቁጥጥር ስር አውሎ የቤተ ክርስቲያኒቱን ሕጋዊ መብት ማስከበር እና የአማኞቿንም ሆነ አጠቃላይ የዜጎችን ሰላም እንዲያስጠብቅ ጥሪያችንን በትሕትና እናቀርባለን።

3. የቤተ ክርስቲያኒቱ የበላይ አካል ችግሩን ከተፈጸመው ድርጊት ሰፋ አድርጎ በማየት ቤተ ክርስቲያኒቱን ለዚህ ያበቋትን የችግሮች መንሥኤዎች፣ ምክንያቶች፣ ድክመቶ እና ጉድሉቶችን በሙሉ ለመለየት የሚያስችሱ ስብሰባዎችን፣ ጉባኤዎችን እና ጥናቶችን በተከታታይ በማድረግ ዘላቂ እና የማያዳግም መፍትሔዎችን ለመተግበር ሁኔታውን እንዲጠቀምበት በታላቅ ትሕትና እንይቃለን።

ቤተ ክነቱ እንደ ተቋም በዘመናት እስካሁን የሄደባቸው መንገዶች በጊዜ ብዛት ችግሩን እዚህ ደረጃ እንዳደረሱት ሁሉ አሁን በቁርጠኝነት መፍትሔ መስጠት የማይችል ከሆነ በዚህ በከፋ እና ሊመለስ ወደማይችል ጥፋት ላለመድረሳችን ምንም ዋስትና የለንም።

ስለዚህም መዋቅሩ እና ሁሉም የቤተ ክርስቲያን አካላት ነገሮችን በስክነት፣ ጥልቀት እና ተገቢውን ትኩረት በመስጠት ከዛሬ ሳንዘገይ ለዘላቂ ተቋማዊ መፍትሔ እና ቀኖናዊ አንድነት እንድንሠራ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

4 ማኅበራችን ማኀበረ ቅዱሳን ተቋማዊ ተፈጥሮው ቤተ ክርስቲያንን ለማገልገል እና ለሕልውናዋ የሚጠበቅበትን ሁሉ ለማድረግ ነው።

08/12/2022
03/08/2022

Ethiopian organic 🐝Honey

03/06/2022

Address

Addis Ababa
አካበ.1221

Telephone

+251913839382

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when A.Kassa posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to A.Kassa:

Share