Ebrahim Balanigo

Ebrahim Balanigo We make and diskaas

04/07/2022

|| የዘንድሮ የሃጅ የጸጥታ ሃይሎች አስገራሚ ዝግጅት

09/04/2022
07/04/2022

ኢትዮጵያ በሃይማኖትም ሆነ በፖለቲካው ሴኩላሪዝምን ተግብራ አታውቅም!

©Musa Adem oumer

የማንነት ፖለቲካ እንደ ሽንኩርት ነው አንዱን ቅርፊት በገፈፈከው ቁጥር ሌላው ወጥቶ ይጠብቀሃል። በቅንነት እና በእውነተኛ ፍትህ ካልሆነ በስተቀር በማጭበርበር፤ በማስመሰል እና ፖሊሲዎችን ተገን በማድረግ ለማስተዳደር መሞከር የጉዳዩን ክብደት ካለመገንዘብ ወይ ደግሞ በማን አለብኝነት የሚታለፍ አይደለም መዘዙ ብዙ ነውና።

ሴኩላሪዝም ሃይማኖትን ተው ማለት አይደለም!
አንብቦ መረዳት እንደሚቻለው ሴኩላሪዝም ሃይማኖቶች በትምህርትና ሌሎች ማህበራዊ ጉዳዮች የፖሊሲና የአፈፃፀም ሂደቶችን Influence ማድረግ የለባቸውም ማለት እንጂ ሃይማኖት አልባ ማህበረሰብ መፍጠር ማለት አይደለም።

ሀገራችን ለሌሎች ክብር በሰጠህ ቁጥር ክብር የምታጣበት ሀገር መሆን የለባትም ተከባብረን ለሁላችንም የምትሆን ሀገር ነው መገንባት ያለብን።

እስቲ የተወሰኑ የሃይማኖት ጥያቄዎችን ላንሳ

1/የሁላችንም ቀዳማዊት እመቤት ከአራት ኪሎ ቤተመንግስት የመዝሙር ነጠላ ዜማ አልጋበዙንም?

2/የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር የሁሉንም ሃይማኖቶች ቃላቶች አብዩዝ በሚያደርግ ልክ በፓስተር ቶን ፖለቲካን አልጋቱንም?

3/ በሁሉም የመንግሥት መስሪያ ቤቶች ማለት በሚቻል መልኩ የመንግስት ሠራተኞች በተለይ ፀሃፊዎች ወይ ቅድስ ማሪያም ወይ ደግሞ የኢየሱስን ፎቶ በትልቁ ለጥፈው አልተቀመጡምን?

4/ከዚህም እጅግ በባሰ መልኩ በመስሪያ ቤት ረደጃ የሚካኤልን ፀበል ፃድቅ ተዘጋጅቶ ቢሮ አይዘጋምን?

5/ከዚህ እጅግ በተቃረነ መልኩ ማንም እርኩስ የሚጨፍርበት በአብዮት አደባባይ ህዝበ ሙስሊሙ ፆሙን ውሎ ስለ ሀገሩ እየፀለየ ለሰላሳ ደቂቃ ተሰብስቤ ላፍጥር ስል ውሻ አልተደረገም?

6/ኢትዮጵያዊነቱን ለነዛ የዜግነት መዳቢዎች ለማረጋገጥ "ግድቡ የኔነው" በማለት በሚልዮኖች ብር አላዋጣምን?

7/በሁሉም ትምህርት ቤቶች አብይ ፆም ገብቷል ተብሎ የሁሉም የተማሪውች ምግብ ወደ የፆም ምግብ አልተቀየረምን?

8/አሁን ረመዳን ስለገባ ሁሉም ተማሪዎች መመገቡን አቁሟልን?

9/አስተዳዳሪው ፓርቲ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ኃላፊዎች ሳይቀር በማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት አልያዘምን?

10/መንግስት ብቸኛውን የሙስሊሞች ተቋም በሆነው የመጅስሊስ እና የሸሪዓ ፍርድ ቤቶች ውስጥ ግልፅ በሆነ ሁኔታ ጣልቃ አልገባምን?

11/ ይህ ሁሉ ሃይማኖታዊ ትርዒቶች በሚፈፀምበት ሀገር ላይ ስለ ሴኩላሪዝም ማውራት እንዴትስ ይቻለናል?

አላበዛባችሁም ብዬ እንጂ ሺህ ጉዳዮችን መዘርዘር ይቻላል አለመናገር ደግሞ አለማወቃችንን አያመለክትም። ተማሪዎች ሶሏታቸውን ይስገዱ፣ ፆማቸውን ይፁሙ፤ ሂጃባቸውንም ይልበሱ፣ ትምህታቸውን ይማሩ ይህ ማንንም አይጎዳም። አትሰግዱም እያልን ይሀው መዓት ከሰማይ እየወረደብን ነውና እንንቃ!

12/03/2022
10/03/2022

2ሺ ዶላር ደርሰናል። በርግጥ ባሰብነው ልክ እየሄደልን አደለም። ቢያስንስ 10ሺ ሆኖ መዋል ነበረበት። አሁንም ቢሆን እገዛችሁን አጠናክራችሁ ቀጥሉበት። እኛ የምንለምነው ለግል ጉዳያችን አይደለም።
ለኢትዮጵያና ለህዝቦቿ የሚሆን ተቋም እናቁም እያልን ነው። የለገሳችሁን ሁሉ ምስጋናችን ይድረሳችሁ !

ጎፈንድሚ 👇
https://t.co/JRxCbqfKpB

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
1000459697482
_
አቢሲኒያ ባንክ
91346311
ስም ለሁሉም ባንኮች መሀመድ አልአሩሲ
ሱሌማን አብደላ

08/03/2022

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ebrahim Balanigo posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share