Gaarummaa ፡መልካምነት

Gaarummaa ፡መልካምነት Educational

08/12/2022

“በችግሩ ምክንያት ቤተ ክርስቲያን እጅግ እየተጎዳች ነው፡፡" ምሥራቅ ወለጋ ሀገረ ስብከት

ከሰሞኑ በምሥራቅ ወለጋ ንጹሐንን መሠረት ያደረገ ጥቃት እየተፈጸመ እንደሚገኝ በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ እየተገለጸ ይገኛል። ምንም እንኳን ከመንግሥት የተሰጠ ይፋዊ መግለጫ ባይኖርም የተለያዩ የሀገር ውስጥና የውጪ መገናኛ ብዙኃን እየዘገቡት ይገኛሉ።

በዚህም የምሥራቅ ወለጋ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ አባ ወልደ ገብርኤል አበበ እንደገለጹት “ኔትወርክ በአለመሥራቱና የትራንስፖርት አገልግሎት በመቋረጡ ምክንያት ቤተ ክርስቲያን እና ምእመናን ያሉበትን ሁኔታ ማወቅ አዳጋች እንደሆነባቸው” አስረድተዋል።

ነገር ግን የጊዳ አያና ወረዳ ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጅ እንደተገደሉ እንዲሁም ኪረሙ ወረዳ ላይ ከሚገኘው በዓለ ወልድ ቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች መካከል ፀሐፊው ብቻ ሲቀር ሁሉም እንደተገደሉ በመረጃ ደረጃ እንደደረሳቸው ገልጸዋል።

የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ አክለውም ጥቃቱ ቤተ ክርስቲያንን መሠረት ያደረገ ነው ለማለት ባያስደፍርም በዚያ ውስጥ ግን ቤተ ክርስቲያን እጅግ እየተጎዳች እንደሆነ ተናግረዋል። ጥቃቱ እስከ አሁን ድረስ መቀጠሉን የአስረዱት ሥራ አስኪያጁ በአካባቢው በተደጋጋሚ ጊዜ የሚፈጸመውን ችግር ለሚመለከታቸው አካላት ማሳወቃቸውንም ጨምረው ገልጸዋል። መረጃው የተሚማ ነው፡፡

++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++
የማኅበረ ቅዱሳን ብሮድካስት አገልግሎት
የምናውቀውን እንናገራለን ያየነውንም እንመሰክራለን!

የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://www.youtube.com/user/EOTCMK?s....
የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ ፤ ፈጣን መረጃዎችን ያግኙ
https://t.me/+SjwkW1oiAsZDLLX0
አጫጭር ትምህርታዊ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት የቲክ ቶክ አማራጫችንን ይመልከቱ
https://www.tiktok.com/?lang=en

10/10/2022

ሰማዕቷ ቅድስት አርሴማ

በከሀዲው ዲዮቅልጥያኖስ ዘመነ መንግሥት ንጉሡ መልኳ (ሥነ ላህይዋ) ውብ የሆነች ብላቴና ሊያገባ ወዶ መልእክተኞችን መርጠው ያመጡለት ዘንድ ላከ። እነርሱም መላ ሀገሪቱን ሲያስሱ ከቆዩ በኋላ ንጽሕት ቅድስት አርሴማ እናታችንን በአንድ በሮሜ ባለ ገዳም ውስጥ ከሌሎች ደናግል ጋር አገኟትና ሥዕሏን ስለው ለንጉሡ ላኩለት። ብፅዕት እናታችን ቅድስት ንጽሕት መርዓተ ክርስቶስ ቅድስት አርሴማም ሥነ ላህይዋ እጅጉን ልዩ የሆነ መልከ መልካም ነበረች።

ንጉሡም ይህን ሥዕል እንዳየ በልቡ በእጅጉ ፈቀዳ፤ እንዲያመጡለትም አዘዘ። ይህን እንደሰሙ እኒያ ደናግልና ቅድስት አርሴማ የገዳሙም እመምኔት የሆነችው ቅድስት አጋታ ሸሽተው ወደ አርማንያ ሄዱ። በዚያም ሳሉ ንጉሥ ድርጣድስ የሚገዛው ግዛቱ ነበርና ከንጉሡ ድዮቅልጥያኖስ መልእክት ደርሶት ሲያስፈልጋት ከደናግሉ ጋራ አገኛቸው። እርሱም በመልከ መልካምነቷ በእጅጉ ተስቦ እንዲህ ያለችቱንማ ለራስ ነው እንጂ ማን ሞኝ አለ በሚል ለንጉሡ ድዮቅልጥያኖስ መሥጠቱን ትቶ ለራሱ እዚያው አኖራት። ከደናግሉም ጋራ ካሠራቸው በኋላ ቅድስት እናታችንን ብዙ ሊያታልላት ሞከረ። እርሷ ግን በመንፈሳዊ ሕይወቷ ፍጹም ጥብዓት ያለባት ራሷንም ለቸሩ አምላካችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ሙሽራ ያደረገች ናትና ለሰማያዊ ሙሽርነቷ የታመነች ሆነች። ንጉሡም ደጋግሞ ቢሞክር አልሆንለት አለ። በኋላም እመ ምኔቷን እንድታባብላት ላካት፤ እመ ምኔቷ ግን ይበልጡኑ አጽናናቻት፤ ‹‹አይዞሽ! እንዲ ላለው ምድራዊ ኃላፊ ነገር እንዳትታለይ፤ ሰማያዊ ሙሽርነትሽንና ንጽሕናሽን አጽኚ›› ብላ እንዲያውም ይበልጥ አስጨከነቻት። በኋላም ንጉሡ በግድ ይዞ ሊሄድ ቢል ኃይለ መንፈስ ቅዱስ አድሮባት ነበርና ያንን በጦር የጎለመሰ ሰውነት ያለውን ብርቱ ንጉሥ ከመሬት ፈጠፈጠችው። ንጉሡም አንዲት ትንሽ ወጣት እንደምን ጣለችኝ ብሎ እጅግ አፈረ።

ንጉሡም በዚህ ሁሉ ተቆጥቶ ቅድስት አርሴማን ሥቃይዋን ሊያበዛባት ወዶ እኒያን ደናግል እርሷን ፊት ለፊታቸው አሠራትና አንድ በአንድ አንገታቸውን ቀላቸው። እርሷ ግን ‹‹አይዟችሁ!›› እያለች ታጽናናቸው ነበር። የሚደንቀው ትሰቀቃለች ብሎ ያደረገላት ነገር እንዲያውም ቅዱሳኑ ሰማያዊ አክሊልን ሲቀበሉ ትመለከትበት ነበር። በኋላም ‹‹አንቺንስ እንደሌሎቹ ቶሎ አልገድልሽም›› ብሎ እጅግ ብዙ ሥቃያትን አሠቃያት። ከእነዚህም አንደኛው ሁለቱን ድንግል ጡቶቿን ቆረጠ፤ ይህም አልበቃ ብሎት ሁለቱን ዐይኖቿን አወጣ፤ እርሷም እንዲህ ሳለች እመቤታችን ንጽሕት ድንግል ማርያም የብርሃን ልዩ ዐይኖችን ሰጠቻት። በመጨረሻም ማሠቃየትን በሰለቸ ጊዜ ከእኒያ ከቀሩት ደናግል ጋራ በመስከረም ሃያ ዘጠኝ ቀን አንገቷን ሰየፈና ሁላቸውም የሰማዕትነትን የድል አክሊል ተቀዳጁ። እኒህም ቁጥራቸው ሰባ አምስት ወንዶችና ሠላሳ ዘጠኝ ሴቶች ነበሩ።

ቅድስት አርሴማ ከሃያ ሰባቱ ደናግል ጋራ ሰማዕትነት ከተቀበለች በኋላ ንጉሡ ድርጣድስ ፈጽሞ ታመመ ታወከ። ቅዱስ ጎርጎርዮስም ሊቀ ጳጳሳትን አስቀድሞ አሥሮት ነበር። (ይኸውም በትውፊት ታላቅ ወንድሟ እንደኾነ ይገራል)። በኋላም ቅዱስ ጎርጎርዮስን ፈታውና ከደዌው ዳነ፤ የቅዱሳን ደናግል እና የቅድስት አርሴማንም የቅዱሳን ሰማዕታቱን ዕፅም ፍልሠታቸው በዚህ በቅዱስ ጎርጎርዮስ እንዲደረግ ሆነ፤ ይህም ታኅሣሥ ስድስት ቀን ነው፡፡ እንዲሁ ደግሞ የእርሷ ማኅበርተኞች የሚባሉ የመቶ ዐሥራ ዘጠኝ ሰማዕታት ዝክራቸው ነው። ከዚያም በስሟ ያማረ ቤተ ክርስቲያን ሠርተው እንዲሁ ያከበሩበት ነውና እናከብረው ዘንድ ይገባናል።

ለእግዚአብሔር አምላካችን በዚህች ድንቅ የክርስቶስ ሙሽራ ቅድስት አርሴማ እና በደናግሉም ሁሉ ጸሎት ይማረን፤ ለዘላለሙ አሜን።

ምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሣር ዘወርኃ መስከረም

14/09/2022

"ኦ ጢሞቴዎስ ዕቀብ ማኅፀንተከ ተገሐሦሙ ለርኩሳን እለ ያመጽኡ ነገረ ከንቶ ወያሴስልዋ ለጽድቅ በሐሰት እስመ እሉ ስሕቱ እምተስፋ ሃይማኖት ጸጋ ምስሌከ አሜን"

" ጢሞቴዎስ ሆይ በውሸት ዕውቀት ከተባለ ለዓለም ከሚመች ከከንቱ መለፍለፍና መከራከር እየራቅህ የተሰጠህን አደራ ጠብቅ ይህ ዕውቀት አለን ብለው አንዳንዶች ስለ እምነት ስተዋልና ጸጋ ከአንተ ጋር ይሁን አሜን"

1ኛ ጢሞ 6:20-21

"አደራ ጥብቅ ሰማይ ሩቅ" እንዲሉ አበው ኑ አደራችንን እንጠብቅ

21/08/2022

➻Nuyi Ortodooksonni yammuu du'aa ka'uu Giiftii keenyaa yaadnu gaaffii nuti gaafannu, "kaateetti moo hin kaane; ol baateetti moo hin baane" jedhu osoo hin taane, "simannaan samii irrattu ishee taasifame maal fakkaata laata?" gaaffii jedhudha. Hiyyeessichi Alaazaar yeroo du'etti ergamoonni gara Abrahaamitti fudhatan yoo jedhame Haadhaa Waaqaa akkamitti kabajaniiru laata? Gara samiitti olbahuun isheef waan guddaa miti. Sababni isaa isheen samii lammaffaa Waaqa samii barruusaatti baatu harka isheen qabdedha. Gara samiitti ol bahuu isheen carra- qabeessi ishee osoo hin taane samichadha. Samiin teessoo isaati; laftis ejjannoo miila isaati; Dubroon Maariyaam garuu haadha Isaati. Teessoo irra haati ni caalti. Qulqulluun Yaaiqoob inni Siruug akka jedhe, 'samiin isa hin deenye; hin guddisne; hin hoosisne, Dubroon garuu kana hunda taasisteetti'. Kanaafuu gara samiitti bahuu isheetiin kabajni isaa samichaaf malee isheef miti.
➻Dhugumayyuu yeroo Giiftiin keenya gara samiitti olbaate simannaan isheef taasifame akkam ture?! Nuyi dhalli namaa haadha keenya kabajuus kunuunsuus kan dandeenyu hamma isheen lafarra jirtuttii fi hamma nuyi jirruttidha. Uumaan 'abbaa fi haadha kee kabaji' jedhe garuu haadha isaa kabajuu kan danda'u lafa qofarratti osoo hin taane samiirrattidhas. Haatisaa gara isaa yoo dhuftu Fayyisaan Addunyaa Kiristoos akkamitti ishee simateera laata?

19/07/2022

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gaarummaa ፡መልካምነት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Gaarummaa ፡መልካምነት:

Shortcuts

Share