03/09/2026
ሥለ ምታገባው ሰው ጸልይ
ጸሎት ለተዘጉ ብዙ በሮች ሁሉ ቁልፍ ነው:: ካላንኳኳን የሚከፈትልን በር የለም:: ጋብቻ ወደ ተባለ ትልቅ ተቋም ከመግባትህ በፊት፣ ነገሮችን ሁሉ በጊዜው ውብ አድርጎ የሚሰራው ፈጣሪ ነውና:: መክ 3-11 ነገሮች በጊዜአቸው መልካም እንዲሆኑልህ በጉዳዩ ላይ ትኩረት በመስጠት መንገዱንም ይመራሃልና ደጋግመህ ጸልይ:: መልካም ሚስት በሒሳብ ስሌትና ቀመር አትገኝም::
“ረዳቱ ናትና ፅኑ መጠጊያውም ናትና ልባም ሴትን ያገባ ሰው ተድላ ደስታውን አገኘ” ሲራክ 36-29 ከምታውቃት በላይ፣ የምታፈቅራትን፣ ከምታፈቅራትም በላይ ዘርህን ተቀብላ ስለ ምታስቀጥልልህ አጋርህ፣ እስከ ሽምግልና ለምትቆዩት ውዷ ሚስትህ አብዝተህ ጸልይ::
ይህ ማለት “ከፊት ይልቅ ትጋ" ለማለት እንጂ፣ አንድ ክርስቲያን ይብዛም ይንስም ከጸሎት የተለየ ሕይወት ኖሮት አይደለም:: “ሳታቋርጡ ጸልዩ" እንዲል 1ተሰ 5-17 ጸሎት ከማግባትህ በፊትም፣ በኋለም ፈጣሪ ካንተ ጋርመሆኑን የምታረጋግጥበት፣ ተገዢነትህን የምትገልጽበት፣ ከእጁም በረከት የምታገኝበት የአምልኮህ መገለጫህ ነው::
ስለዚህ አንዳንዴ ሳይሆን ሁልጊዜ ጸልይ:: ምን ዓይነት ትዳር ውስጥ ገባው እያልክ ከማዘንህ በፊት ጸልይ:: በጸሎት ባሕርን ትሻገርበታለህ፣ ድቅድቁን ጨለማ ታቋርጥበታለህ፣ ከጠላትም ታመልጥበታለህና "ጋሻህ" ነው:: ልታገባትም ላታገባትም ትችላለህ፣ አብራችሁ ላትኖሩም፣ ልትወልዱም፣ ላትወልዱም ትችላላቹ:: ይቅርና ሀዘኑን ብቻ ሳይሆን ከአቅም በላይ የሆነን ደስታን መቋቋም የሚቻለው “በጸሎት" ነው::
ስትጸልይ ቅዱሱ መንፈስ ካንተ ጋር ይሆናል:: ይህ መንፈስ እንዳይወሰድብህ አብዝተህ ጸልይ:: ቅዱስ መንፈስ ያለበት ሰው ለሌላም ይተርፋል:: መንፈሱ አለኝ ተብሎም ተምታቶበት፣ትዳር እንዳይምታታም መጠንቀቅ ያስፈልጋል:: በገዛ ሚስትህ በጋብቻህ ውስጥ ለሚፈጠሩ ማንኛውም ጉዳይመፍትሔው እጅህ ላይ ነው:: ያ የሚሆነው ደግሞ መንፈስ ቅዱስ ሲረዳህ ነው:: ቅዱሱ መንፈስ ካልረዳን በቀርየሚረዳንና የሚረዳንን አጋር ማግኘት ይቸግረናል:: መዝ 50-11 የሚጸልዩ ስዎች በሚስቶቻቸው ላይአሲድ አይደፉም:: ያደላቸውማ በትር ቀርቶ የከፋ ቁጣ እንኳ የላቸውም:: ሁሌ በመነጋገር ያምናሉ:: ከዚህም በላይ ደግሞ የጋብቻን ዓላማ ስለሚገነዘቡ ለተጋቡለት ዓላማ ይኖራሉ:: አይሆንም እንጂ ባይሳካ እንኳን ሁሉን “ ለበጎ ነው “ እያሉ ያልፋሉ:: የጸሎት ጥቅሙም ለፈተናዎች ሁሉ መውጫ መንገድ መሆኑም ጭምር ነው:: የምናመልከው ጌታ አሳልፎ አይሰጠንምና::
የሚጸልዩ ሰዎች ከምድርም ያልፋሉ:: እይታቸው ይቀየራል ስማያዊ ነው:: አይደለም ለሚስት ለሌሎችም ይተርፋሉ:: በጸሎት መጽሐፍ እየጸለዩ ሚስታቸውን በፊክሽን መጽሐፍ አይፈቱም:: ለሚሻግት፣ ለሚቆሽሽ፣ ለእዳሪ ነገርበትንሽ ትልቁ አይጋጩም:: የሚጸልዩ መንፈሳቸው ይሰክናል:: ሊጣሉ፣ ሊደባደቡ፣ ሊሰዳደቡ፣ ሊተዛዘቡ፣ ቂም ሊያያዙ፣ ሊጨቃጨቁና፣ “ልሞክረው” በሚል ሊፋቱ አይጋቡም:: ምክንያቱ ለጸሎት የሚቆሙት ሁሉን በሚያውቅ አምላክ ፊት እንደሆነ ያውቃሉና፣ ምን ይዘው ይቆማሉ?
የሀገሬ ሰው “ባልና ሚስት ከአንድ ምንጭ ይቀዳሉ“ እንዲል የሚጸልዩ ሰዎች የሚስማማቸውን ያገባሉ:: ስትጸልይየምትጸልየዋን ታገኛለህ:: ምናልባት እርሷ ባትጸልይ ባንተ የተነሳ የተባረከቺው ትመጣለች:: ደግሞም ደክመህና ሰንፈህ ባትጸልይ እንኳ የምታበረታታህና የምትጸልይልህን አጋርታገኛለህ:: ጸሎት ለሚመጡ ልጆችም ይጠቅማል:: በትዳርሁሉ ነገር የሚሆነውም፣ የሚታለፈውም፣ “በጸሎት” ነው::
ሁሉ ብቻ በጸሎት ያገኘኸውን ሁሌም ስታከብረው ትኖራለህ:: አብሶ ሚስትህን ተባርካ ካገኘኻት ዘመዴ፣ ዘመንህ ይባረካል:: የተባረከቺውን አገባህ ማለት በደስታህ ሳይሆን በሀዘንህም ውስጥ በረከት ታያለህ:: ብዙ ሀዘኖችህን “እርሷ ባትኖር ኖሮ እንዴት አልፈው ነበር" ያስብልሃል:: የእርሷ መባረክ ለልጆችህ፣ ለጤናህ፣ ለሥራህ ጠቅላላ ለማህበራዊ ኑሮህ ዋስትና ስለ አለው:: ቅድሚያ ሳይታክቱ መጸለይ::
ከዚህ አውነት ተነስተን፣ ከስኬቶችህ ጎን የእርሷ ድጋፍና ጸሎት ወሳኝ ስለሆነ ጋብቻህ የማትጸጸትበት ሊሆን እንዲገባ ቀድመህ ጸልይ:: ስለምታገባው ጸለይክ ማለት ስለ ሀገርም ስለ ምትወልደው ልጅም፤ ስለ ወደፊትህም እየጸለይክ ነው::
ከመጽሐፉ ገጽ 52 - 54 የተወሰደ
መጽሐፉን 4ኪሎ ቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ግራውንድ በሚገኘው ሱቃችን መውሰድ ይችላሉ። ኦሜጋ መጻሕፍት ነን!!!
!!!!!!!!
💎 Telegram: https://t.me/ethiofagos
📍 4ኪሎ ቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ግራውንድ ላይ ያገኙናል።
🇪🇹 Addis Ababa, Ethiopia
📞 0941555550
👉 የቤተክርስቲያንን እውነተኛ የታሪክ አሻራ በሰነድ የተደገፈ እውነታ ለማወቅ ይህንን መጽሐፍ ያንብቡ!
አሁን ይዘዙ!