05/04/2020
ካነበብኩት የወደድኩት ያስተማረኝ ታሪክ
በኢትዮጵያም ሆነ በተቀረረው ዓለም ብቸኛው አይነስውር ፎቶ አንሺ አብዱ ሀሰን!
አብዱ ሀሰን የዛሬ 30 ዓመት ገደማ ይህችን ዓለም ሲቀላቀል ሁለቱም አይኖቹ አያዩም ነበር፡፡ ሆኖም ተፈጥሮ ብርሃንን ብትነፍገውም ጥበብን ግን አብዝታ ሰጥታዋለች፡፡ አይነ ስውሩ ፎቶ አንሺ አብዱ ሀሰን ሳያይና ሳይመለከት ያልጠቆረ፤ ያልነጣ፤ ያልተዛነፈን ያልተንጋደደ ፎቶ የሚያነሳ ጥበበኛ ነው፡፡ አብዱ ከልጅነቱ ጀምሮ ለፎቶ ጥበብ ልዩ ፍቅር አለው፡፡ ብዙዎችም ቆመው፤ ተቀምጠው፤ ስቀው፤ አኩርፈው፤ ተቃቅፈው ፤ ተለያይተው በአብዱ ካሜራ እራሳቸውን አይተዋል፡፡ ሁሉም ሊባል በሚችል መልኩ በተነሷቸው ፎቶዎች ተደምመዋል፡፡ በተለይም ሰበታ በሚገኘው አይነስውራን ት/ ቤት እያለ የተለያዩ ዝግጅቶችን ፎቶ እያነሳ የትምህርት ቤቱ ቅርስ እንዲሆኑ አድርጓል:: በዚህም በርካታ አድናቆትና ምስጋና ተችሮታል፡፡
‹‹አካል ጉዳተኝነት ከምንም ተግባር አያግድም፤ ካሰቡበት ቦታ መድረስ ይቻላል፤ ዋናው ጥረት ብቻ ነው››
ከፈለግን ምንም ማድረግ ይቻላል
''ምንጭ ቲክቫህ''
መልካም የተባረከና ስኬታማ ቀን ይሁንል✅✅✅✅✅✅✅✅✅✅✅