የሀገር ጥበብ Yehager Tibeb

የሀገር ጥበብ Yehager Tibeb Ethiopian trafiotional clothes
(1)

ኮንዶሚኒየም መኖር ችግር ነው! ሁሉም ዶሮና በጉን በሩ ላይ አስሮ ብሎካችንን ኤልፎራ አስመስሏታል። እኔም ትናንት ሚስቴ በግ ካልገዛህ እያለች ስትነተርከኝ ጥቂት ብር ይዤ በግ ልገዛ ብወጣ አ...
07/01/2021

ኮንዶሚኒየም መኖር ችግር ነው! ሁሉም ዶሮና በጉን በሩ ላይ አስሮ ብሎካችንን ኤልፎራ አስመስሏታል። እኔም ትናንት ሚስቴ በግ ካልገዛህ እያለች ስትነተርከኝ ጥቂት ብር ይዤ በግ ልገዛ ብወጣ አንድ ቀውላላ በግ ነጋዴ ሁለት ፊታቸው ላይ ከባድ ድብርት የሚታይባቸውን ከሲታ በጎች ይዞ ቆሞ አገኘሁና ጠጋ ብዬ
«ልትሸጣቸው ነው?» አልኩት
«እና ሐገር ላስጎበኛቸው ነው ካገሬ ይዣቸው የወጣሁት?» አለኝ
«እንደው ኩነኔ አይሆንም እነዚህን መግደል?» ስለው ፈጠን ብሎ
«አንቀህ ነው እንዴ ምትገድላቸው?» አለኝ
«አይ ያው በቢላም ቢሆን ...» ብዬ ሳልጨርስ
«ወንድሜ ካሳዘኑህ ውሰድና በጉዲፈቻ አሳድጋቸው» አለኝ
«እሺ ስንት ነች እቺ?» አልኩት ወደአንዷ እየጠቆምኩ
«በግ ታውቃለህ ማለት ነው። በጣም አስተዋይ በግ ነች እሷ» ብሎ ጀርባዋን መታ መታ ሲያደርጋት ወደጎን ፍንግል አለችና አቧራዋን አራግፋ ተነሳች።
«እኔ አስተውሎቷ ምን ይሰራልኛል ላስተምራት አይደለም እኮ ምወስዳት» ስለው
«ሁለት ሺ ብር ክፈል» አለኝ
«ሁለት ሺ ብርማ አታወጣም»
«በርግጥ ላታወጣ ትችላለች ነገር ግን እኔ ሁለት ሺ ብር ነው የሚያስፈልገኝ»
«ቀንስና ልውሰድልህ» አልኩት
«አይ ወዳጄ በጓን ግን አይተሃታል? ውስጠ ወይራ እኮ ነች። መፍዘዟን አትይ። በዚያ ላይ በእንክብካቤ ነው ያደለብኳት»
«ጭራሽ ደልባ ነው እንዲህ የከሳችው?»
«አዎና! በርግጥ እኔ ስብእናዋ ላይ ነው የሰራሁት። በጥሩ ስነምግባር ነው ያሳደግኋት» አለኝ ቆፍጠን ብሎ። ሳቄን ለመቆጣጠር እየሞከርኩ
«አንድ ሺ ብር ትሸጥልኛለ ...?» ብዬ ሳልጨርስ
«ውሰዳት!» አለኝ በደስታ ተሞልቶ።
ምነው ዝም ባልኩ ብዬ በይሉኝታ አንድ ሺ ብር ሰጥቼው በጓን ይዤ ልሄድ ስል መራመድ አቅቷት በቀስታ ስታዘግም
«ቃሬዛ ቢኖርኮ ደግ ነበር» አለኝ ሰውዬው በጉን በሃዘን እየሸኘ።
ተበሳጭቼ ዝም ብዬው ስሄድ
«ወንድሜ እንደው ለነፍስ ትሆንሃለች መጀመሪያ የህክምና እርዳታ አርግላት» አለኝ
መንገድ ላይ በጓን ያየ ሁሉ ከንፈሩን እየመጠጠ ያልፋል። አንዳንዱ እኔን እያየ አንገቱን በሃዘን ይነቀንቃል። በግ ላርድ ሳይሆን እንደአብርሃም ልጄን ልሰዋ ይዤ እየሄድኩ ነው ያስመሰሉት። ሽምቅቅ እንዳልኩ ቤት ደረስኩ። ሚስቴ በጓን እንዳየቻት
«ምንድነው ይዘህብኝ የመጣኸው?» ብላ ጮኸች። በጩኸቷ ከኔ ይልቅ የደነገጠችው በጓ ነች። አይኗን አስለምልማ መሬት ወደቀች! የመጀመሪያ ደረጃ እርዳታ ላደርግላት ሞከርኩ። አልነቃ ስትለኝ በአፌ ትንፋሽ ልሰጣት ሳጎነብስ ሚስቴ
«በዚህ አፍህ እኔ ከንፈር ጋር ድርሽ እንደማትል እወቀው!» ስትለኝ ቀና ብዬ መጨረሻዋን ማየት ጀመርኩ ..
ውይይ! አረፈች! በጣም የሚያሳዝን ሁኔታ ነው የገጠመኝ ጎበዝ።
ለሚስቴ «ያ ሙታን አስነሳለሁ ሚለው ነብይ ጋር ይዘናት እንሂድ ይሆን?» ስላት
«እሱ አክስቱ ሞታ ክፍለሐገር ሄዷል» አለችኝ። እሺ ምን ተሻለኝ ጓዶቼ?
«ቆይ ግን ...የግድ ስጋዋን ለመብላት እኛ ልንገድላት ይገባል እንዴ? ያው ሞት ሞት ነው። በቢላም ሞተች በድንጋጤ ያው መሞቷ አይቀርም!» ስል ሚስቴ ሶስት ግዜ አማትባ «በል አውጥተህ ጣል» አለች።
እኔ ግን ተስፋ አልቆረጥኩም! እቺን በግ እኮ ስጋዋን ፈልጌ ሳይሆን እንደበግ እንድትተውን ነው የገዛኋት። አክተር ደሞ አይሞትም
ኦህህህህህ! ተመስገን!
ነቅታለች ጎዶች «እልልልል ...» (አሉ እትዬ ዘርፌ የቤት እቃ (ማማሰያ ሳይቀር) እየሰረቀ ያሰለቻቸው ልጃቸው ሲታሰር)
እንዲህ ነው እንጂ በግ! ዝም ብሎ መሞት አለንዴ? እኛ ሳንፈቅድላትማ አትሞታትም! አልኩ ለሚስቴ (አንዳንዴኮ እንደ አፍሪካ መሪዎች ሚያደርገኝ ነገር አለ። ተመልሳ ሳትወድቅ ብሬክ ላርጋት።

02/01/2021
31/12/2020

ራሺያ ውስጥ አንድ ሰነፍ ወታደር አለ፡፡ በቃ ኢላማውን ጠብቆ ተኩሶ መትቶ
አያውቅም፡፡ ሁሌ ይተኩሳል፤ ሁሌ ይስታል፡ ከእለታት አንድ ቀን አለቃው በጣም ተናደደና ሠራዊቱን ሰበሰበ፡፡
“ጓዶች፤ ይሄ ወታደር በተደጋጋሚ ኢላማውን ያልጠበቀ ተኩስ በመተኮስ
ይታወቃል፡፡ ወታደር አልሞ የጠላቱን ልብ በጥይት ካልነደለ ምኑን ወታደር ይባላል?” አለ የሰነፉን ወታደር ክንድ ይዞ፡፡ ተሰብሳቢው በሆታ “ኧረ አይባልም” አለ፡፡ “ይሄ ሰነፍ ስንፍናውን እንዳያጋባብን ሊቀጣ ይገባል፡፡ ቅጣቱንም ራሱ በራሱ ይወስዳል…” ይልና ራሱን እንዲያጠፋ ይወስናል፡፡
ሰነፉ ወታደርም ሰወር ካለ ስፍራ ይገባና ጥይት ይተኩሳል፡፡ ከደቂቃዎች በኋላ
ግን ሰነፉ ወታደር ይመለሳል - ወደ ካምፑ፡፡ አዛዡ ቱግ ብሎ “አንተ ራስህን አጥፋ ብዬህ አልነበረ?” ሲለው...
“ጌታዬ ራሴን ስቼው ነው!” አለ 😄

🌼🌼🌼መልካም አዲስ አመት 🌼🌼🌼        💚💛❤ ኢትዮጵያዬ💚💛❤
11/09/2020

🌼🌼🌼መልካም አዲስ አመት 🌼🌼🌼
💚💛❤ ኢትዮጵያዬ💚💛❤

ሰውን ለመርዳት የግድ እስኪተርፈን ድረስ መጠበቅ የለብንም:: ካለን ላይ ማካፈል የበለጠ ዋጋ አለው።              💚💛❤
27/06/2020

ሰውን ለመርዳት የግድ እስኪተርፈን ድረስ መጠበቅ የለብንም:: ካለን ላይ ማካፈል የበለጠ ዋጋ አለው።
💚💛❤

በአንድ ወቅት ቢል ጌትስን “ካንተ የሚበልጥ ሃብታም አለ ወይ?” (ልብ በሉ ቢል ጌትስ ቁጥር አንድ ሃብታም በነበረበት ወቅት ነው) ተብሎ ተጠይቆ የሰጠውን አስገራሚ ምላሽ blogpost በMy...
17/06/2020

በአንድ ወቅት ቢል ጌትስን “ካንተ የሚበልጥ ሃብታም አለ ወይ?” (ልብ በሉ ቢል ጌትስ ቁጥር አንድ ሃብታም በነበረበት ወቅት ነው) ተብሎ ተጠይቆ የሰጠውን አስገራሚ ምላሽ blogpost በMy Life Chapter ገፁ ላይ በ2017 አስነብቦ ነበር:: ምላሹ መሳጭና አስተማሪ ስለሆነ እንዲህ አቅርቤዋለሁ።

“ከብዙ ዓመት በፊት ነው: ኒውዮርክ ኤርፓርት ውስጥ ጋዜጣዎችን ሳይ አንዱ ጋዜጣ ላይ የተፃፈውን ርዕስ ወደድኩትና ጋዜጣውን ልገዛው ፈለኩ:: ነገር ግን ምንም ገንዘብ አልነበረኝም እና ጋዜጣውን አስቀምጬ ስሄድ ያ ጋዜጣ ሻጭ ጥቁር ልጅ ጠራኝና ‘ይህ ጋዜጣ ያንተ ነው:: ውሰደው::’ አለኝ:: ‘ምንም ገንዘብ የለኝም ልገዛክ አልችልም’ ስለው ‘ምን ችግር የለውም ውሰደው’ ብሎ ጋዜጣውን ሰጠኝ::

ከ3 ወር በሗላ እዛው ኤፓርት ሄድኩኝ እና እዛ ጋዜጣ ሻጭ ልጅ ጋር ተገናኜን:: በአጋጣሚ አሁንም ልገዛ ፈልጌ ገንዘብ አልነበረኝም:: አሁንም ልጁ ጋዜጣውን በነፃ ሰጠኝ:: አሁንስ ደግሜ ልቀበልክ ብለው ‘ምንም ችግር የለውም ውስደው ሰጥቼሃለሁ’ ብሎ ጋዜጣውን በነፃ ለሁለተኛ ጊዜ ሰጠኝ።
ከ19 ዓመት በሗላ ሃብታም እንዲሁም ታዋቂ ሆንኩ:: በዚህ ጊዜ ልጁን አግኝቼ ብድሩን ልመልስለት ማፈላለኩ ጀመርኩ:: ከአንድ ወር ፍለጋ በሗላ እገኘሁት:: ‘ማን እንደሆንኩ ታውቃለህ?’ ብዬ ጠየኩት እሱም ‘አዎ ዝነኛው: ሃብታሙ ቢል ጌትስ ነክ’ አለኝ:: እኔም ‘ከብዙ አመት በሗላ ሁለት ጋዜጦች በነፃ ሰጥተህኛል: እናም ብድርክን ልመልስልክ እፈልጋለሁ:: ስለዚህ የምትፈልገውን ነገር ሁሉ ንገረኝና ላድርግልህ’ አልኩት:: እሱም ‘ምንም ነገር ብታደርግልኝ ብድሬን መመለስ አትችልም’ አለኝ::’ እኔም በጣም ተገርሜ ‘ለምን?’ አልኩት:: እሱም ‘እኔ የሰጠሁህ ደሃ እያለሁ ካለኝ ላይ ቀንሼ ነው:: አንተ ግን የምትሰጠኝ ሃብታም ሆነክ ከተረፈክ ላይ ነው:: ስለዚክ ብድሬን ልትመልስ አትችልም::’ አለኝ::
በርግጠኝነት ያ ልጅ ከኔ የበለጠ ሃብታም ነው:: “
ምን ለማለት ነው ሰውን ለመርዳት የግድ እስኪተርፈን ድረስ መጠበቅ የለብንም:: ካለን ላይ ማካፈል የበለጠ ዋጋ አለው።

በቅንነት ያድርጉ።

💚
15/06/2020

💚

❤👌
13/06/2020

❤👌

ሰናይ ቀን💚💛❤
05/06/2020

ሰናይ ቀን
💚💛❤

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የሀገር ጥበብ Yehager Tibeb posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category