Dere Essa

Dere Essa ICT

የታሰረ የመንግሥት ሠራተኛ የደሞዝ መብት በአዲሱ አዋጅ (1334/2016)አንድ ሠራተኛ በወንጀል ተጠርጥሮ በቁጥጥር ሥር ቢውል ወይም በጊዜ ቀጠሮ ቢታሰር የሚከተሉት ሕጋዊ መብቶች አሉት፦1️⃣...
12/07/2026

የታሰረ የመንግሥት ሠራተኛ የደሞዝ መብት በአዲሱ አዋጅ (1334/2016)

አንድ ሠራተኛ በወንጀል ተጠርጥሮ በቁጥጥር ሥር ቢውል ወይም በጊዜ ቀጠሮ ቢታሰር የሚከተሉት ሕጋዊ መብቶች አሉት፦

1️⃣ የግማሽ ደሞዝ ክፍያ (50%)

ሠራተኛው በቁጥጥር ሥር በዋለበት ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ለ 3 ወራት ድረስ የመሠረታዊ ደሞዙን 50% የማግኘት መብት አለው።

ተቋሙ "ሥራ አልገባህም" በሚል ምክንያት ደሞዝ ሙሉ በሙሉ ሊያቆም አይችልም።

2️⃣ የጊዜ ገደብ (3 ወራት)

እስሩ ከ 3 ወራት በላይ የሚቆይ ከሆነ ግን፣ ከሦስተኛው ወር በኋላ ያለው ክፍያ ይታገዳል።

ነገር ግን ሠራተኛው በነፃ ከተለቀቀ የታገደው ደሞዝ በሙሉ ይታሰባል።

3️⃣ በነፃ ሲለቀቅ የሚከፈል ካሳ

ሠራተኛው በነፃ ከተለቀቀ ወይም ክሱ ከተቋረጠ፦

ሳይከፈለው የቀረው 50% ደሞዝ በአንድ ጊዜ ተሰልቶ ይከፈለዋል።

በእስር የቆየበት ጊዜ እንደ ሥራ ዘመን ይቆጠርለታል።

ወደ ቀድሞ ሥራው የመመለስ ሙሉ መብት አለው።

4️⃣ ደሞዝ ሙሉ በሙሉ የሚቆመው መቼ ነው?

ሠራተኛው በፍርድ ቤት ጥፋተኛ ተብሎ የእስራት ፍርድ ሲበየንበት ብቻ ተቋሙ የሥራ ውሉን አቋርጦ ደሞዝ ሊያቆም ይችላል።

መንግሥት መሥሪያ ቤቱ በአዲሱ አዋጅ መሠረት ሠራተኛው እስካልተፈረደበት ድረስ ደሞዝ አልከፍልም ማለት አይችልም! ግማሽ ደሞዙን የመክፈል ግዴታ አለበት

17/06/2026

ሊቀ መልእክት ቅዱስ ሚካኤል የልባችሁን መልካም መሻት ይሙላላችሁ🙏

የስሙ ትርጓሜም “እንደ እግዚአብሔር ያለ ማን ነው” ማለት ሲሆን የ7 ሊቃነ መላዕክት አለቃቸው ነው ቅዱ ሚካኤል። ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት በመዝሙር 33÷7 “የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል ያድናቸውማል” ይለናል፡፡ ከእግዚአብሔር ዙፋን ስር ትዕዛዝ በወጣ ግዜ ኪሩቤል ተቀብለው ለሱራፌል ያስተላልፋሉ፤ ሱራፌልም ለሚካኤልና ለገብርኤል ለሩፋኤልም ያደርሳሉ፡፡ ሚካኤል ለፍጥረቱ በጎም ይሁን ክፉ ትዕዛዙን ይፈጽሙ ዘንድ መላዕክትን ያዛቸዋል፤ መላዕክቱም ሁሉ አቤቱ የእጅህን ስራ አታጥፋ እያሉ ቀንና ከማታ ይለምናሉ። በዓለም ፍፃሜም ስለህዝቡ የሚቆመው ሚካኤል ይነሳል። በማለት በምዕራፍ 12÷1 ጽፎልናል፡፡ በራዕይ 8÷3 “የቅዱሳኑ ፀሎት ከዕጣኑ ጢስ ጋር ከመልአኩ እጅ ወደ እግዚአብሔር ፊት ወጣ” ተብሎ እንደተጻፈውም መላዕክት የቅዱሳኑን ጸሎት ወደ እግዚአብሔር ያሳርጋሉ፡፡

አይሁድ ጌታን ሲሰቅሉት መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል በአይሁድ ስራ አዝኖ በቁጣ ሰይፉን አወጣ፤ ቅዱስ ሚካኤል ግን በእግዚአብሔር ትዕግስት ተገርሞ፣ ፈጣሪን ፍጡራን ሰቀሉት እያለ በአርምሞና በትዕግስት አያቸው ይላል ድርሳኑ። ቅዱስ ሚካኤል ሰኔ 12 ቀን ዲያቢሎስን አሸንፎ በምትኩ ሊቀ መላዕክት ሆኖ የተሾመበትና አፎምያንም የረዳበት ቀን ስለሆነ በታላቅ ሥርዓት ይከበራል። ህዳር 12 ሕዝበ እስራኤልን በክንፎቹ ጥላ ከበረሃው ፀሐይ ከልሎ ከግብጽ ምድር እየመራና እየጠበቀ ከንዓን ያገባበት ዕለት ነው። መላዕክቱ በክንፋቸው የእግዚአብሔር ስም ስለተፃፈበት ህዝቡን ይጠብቃሉ፤ የመላዕክቱን ስም የመጨረሻውን ፊደል ስናይ ኤል ብሎ ይጨርሳል፡፡ ሚካ-ኤል ገብር-ኤል ኡራ-ኤል፡፡ ይህም “ስሜ በሱ ላይ ነውና” እንደሚል የእግዚአብሔር የምህረት ስም ስለሆነና በክንፎቻቸው ስለተፃፉ መላዕክቱ ይጠብቁናል።

“በመንገድህ ሁሉ ይጠብቁህ ዘንድ መላእክቱን ስለአንተ ያዛቸዋል፤ እግርህም በድንጋይ እንዳይሰናከል በእጆቻቸው ያነሱሃል” ተብሎም በመዝሙር 90÷11 ተጽፋልና አህዛብን ጭምር ያለጊዜያቸው እንዳይሞቱ መላዕክት ይጠብቋቸዋል፡፡ በትንቢተ ዳንኤል 10÷13 እና 10÷21 ደግሞ የስሙ ትርጉም እግዚአብሔር ዳኛዬ ነው የተባለው ነብዩ ቅዱስ ዳንኤልም ስለ ቅዱስ ሚካኤል እንዲህ ሲናገር ከዋነኞቹ አለቆች አንዱ ሚካኤል ሊረዳኝ መጣ፣ በተዘጋ ጉድጓድ ሲያጽናናው ደግሞ “ከሚካኤል በቀር የሚያጽናናኝ የለም” አለ፡፡

ሊቀ መልእክት ቅዱስ ሚካኤል የልባችሁን መልካም መሻት ይሙላላችሁ🙏

17/06/2026
17/06/2026

🌹🥰🌹🥰🌹

ትክክል ነህ በጣም ክፉ ሰው ነው።
26/05/2026

ትክክል ነህ በጣም ክፉ ሰው ነው።

ዲታ ወረዳ የደሳለኝ ዶሳ የገንባውን ጥላቻ ህንፃ አሁን የመጣው አመለ ሸጋው አስተዳደር ጥላቻ ግንቡን በዘመናዊ ዱሮን እየደበደቡ ይገኛሉ አሁን ባለው አንድነት ኃይል የተቀላቀሉ እርምጃ እየተወሰደ ይገኛል።

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dere Essa posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share