29/04/2026
የአሸዋ ላይ እግድና የግብዞች ጩኸት፦
የዲሲው ጎግና ማጎግ፦ የመቅደሱ አውሬና የፎርፌው ማኅተም
********************************************
ሚያዝያ 21 ቀን 2018 ዓ.ም
April 29, 2025 (GC)
በዋሽንግተን ዲሲ ሰማይ ሥር፣ በቅንጡ ቪላዎች በስተጀርባ የሚከናወነው ድራማ ከሺህ ዓመታት በፊት በነቢዩ ሕዝቅኤልና በሐዋርያው ዮሐንስ የታየው ያ "የጎግ እና ማጎግ" ውጊያ ዳግም መከሰቱን የሚያበስር ነው:: የአቡኑ የሥራ ቦታም እና የጀሌዎቻቸው መቅደስ ሳይሆን፣ ነቢዩ ሕዝቅኤል በምዕራፍ ፰ ላይ እንዳየው "በጨለማ ውስጥ የሚደረግ የርኩሰት ምክር ቤት" ነው፡፡
ዋሽንግተን ዲሲ – የነፃነት አደባባይ፣ የዕውቀት ማዕከልና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ከተማ ናት፡፡ በዚህች ታላቅ ከተማ የሚኖረው ኢትዮጵያዊ ምዕመን ደግሞ የሠለጠነ፣ መጽሐፍትን የመረመረና በነፍሱ የሚቀልድበትንና ነፍሱን የሚፈውሰውን ለይቶ የሚያውቅ ነው፡፡ ታዲያ በዚህ ምዕመን መካከል ሆኖ ''ሳልመንና ሰላጣ" እያጠቡ ወንጌልን መሸፈን ይቻላልን? በዋሽንግተን ዲሲ ሰማይ ሥር ያሉት የዘመኑ ይሁዳዎች ለሃይማኖት ቀናኢ ሆነው ሳይሆን፣ የሚከተሉት አራት እርኩሰቶቻቸው እንዳይጋለጡባቸው ነው፦ እነዚህ ጥቂት ስብስቦች በቅንነት እና በእምነት በውጪው ዓለማት በቤተክርስቲያንን መዋቅር ያሉትን እውነተኛ አገልጋይ ካህናት አባቶችን አይወክሉም!
በእነዚህ "የዘመኑ ሄሮድሶች" ላይ እንደሚከተለው
አራት ነጥቦችን አቀርባለሁ ፡፡
፩. ዘረኝነት፦ የጥላቻ መሐንዲሶች
እነዚህ በዋሽንግተን ዲሲ ሰማይ ሥር ያሉት ጥቂት የዘመኑ ይሁዳዎች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን እንደ መንፈሳዊ ተቋም ሳይሆን እንደ "ጎሳ ማኅበር" የሚመለከቱ ዘረኞች ናቸው፡፡ እስኪ ፍረዱ ሁሉንም ሰዎች ያካተቱ ናቸውን? ወይስ እነማን ናቸው ያሉት፡፡ ዛሬ እኛ መጥተን "ኢትዮጵያዊነትንና ፣ ሰላምን ክርስቶሳዊ ፍቅርን" ስንሰብክ፣ ዘረኝነታቸው እንዳይጋለጥ ደነገጡ፡፡ እነዚህ ስብስቦች የቤተክርስቲያንን መዋቅር እንደ ጋሻ በመጠቀም፣ በውስጡ የዘረኝነትን መርዝ ይረጫሉ።
ወንድሙን የሚጠላ ጳጳስ በመቅደሱ ሲቆም፣ ያ ቦታ የጸሎት ቤት ሳይሆን የ"ጎግና ማጎግ" የጦር ሜዳ ይሆናል:: ዘረኝነት በበገነበት ልብ ውስጥ መንፈስ ቅዱስ የለም፤ ያለው የአውሬው ማኅተም ብቻ ነው፡፡
፪. መተተኝነት፦ ከዲያቢሎስ ጋር ተዋርሶ
ሕዝብን የማደንዘዝ ጥበብ ሕዝቅኤል በመቅደሱ ግድግዳ ላይ "የተሳሉ ርኩስ ምስሎችንና የሚሰግዱላቸውን ሽማግሌዎች" እንዳየ (ሕዝ ፰፡፲)፣ ዛሬም በዲሲ ቪላዎች ውስጥ በወንጌል ፋንታ "በሽንኩርት ቁሌትና በሰላጣ ቪዲዮ" በተለያዩ ተዋርሶ ሕዝብን የሚያደነዝዝ መተት ነግሷል:: ይህ ሕዝብን የማደንዘዝ ጥበብ የመተት መንፈስ ነው—የምዕመኑን ነፍስ እንደ ሥጋ የሚመጥጥ፣ ዕውቀቱን ፣ ገንዘቡን የሚሰልብና ወደ ድንቁርና የሚመራ ነው :: በእነዚህ ሰዎች ጓዳ ያለው "የርኩሰት መተት" እየተቃጠለ መሆኑን በደም ደብዳቤያቸው " ማረጋገጥ ይቻላል
፫. ቁማርተኝነት፦ የመቅደሱ ነጋዴዎች
የአውሬው መንፈስ አንዱ መገለጫ ሰውነትን ማርከስ ነው፡፡ በዲሲ ቅንጡ ቪላዎች ውስጥ የሚፈጸመው የርኩሰትና የሴሰኝነት ሕይወት፣ ቃለ እግዚአብሔርን ከመተርጎም ይልቅ የሥጋን ፈቃድ የሚያረካው የእነዚህ ሰዎች ኑሮ የአደባባይ ምስጢር ነው:: ሐዋርያት ''ማዕድ ለማገልገል ቃሉን አንተወውም'' (ሐዋ 6 ፡2) እንዳሉት ሁሉ ፣ በመቅደስ ቆሞ የነፍስ ሐኪም መሆን ሲገባቸው፣ በየቪላው እየዞሩ "ሰላጣ" እያሳዩ ራሳቸውን ለነውር ዳረጉ፡፡ በራዕይ ዮሐንስ ላይ እንደተጠቀሰው "በምድር ነጋዴዎች" የተሞላችው ባቢሎን፣ ዛሬ በዲሲ ቤተክርስቲያን መልክ መጥታለች:: የምዕመኑ መባ ለመንፈሳዊ አገልግሎት ሳይሆን ለቁማር መቆመሪያ እየዋለ ነው:: ሰይጣን ከወጣ የቁማር መቆመሪያው "መባ" ይደርቅብናል ብለው ስለሰጉ፣ ገና አሜሪካ ልንመጣ ነው ስንል በደብዳቤያቸው ዘለፉ ይጀምራሉ፡፡ እባብ እግሩን ደብቆ ይሄዳል፤ እነዚህም "ነጋዴዎች" ክህነታቸውን ደብቀው ካሲኖ ይሄዳሉ::
"እስኪ ፍረዱ!" ጥቂት የሚሆኑ እውነተኛ አባቶችን የማይወክሉ በዲሲ አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ በዲያቆንና በካህን ስም ብቻ ቁጭ ብለው፣ ውዳሴ ማርያም በቃል የማይደግሙ ማታ ማታ በየትኛው ካሲኖ (Casino) እንደሚውሉ ዲሲ የሚያውቀው የአደባባይ ምስጢር ነው፡፡ የምዕመኑ መባ ለመንፈሳዊ አገልግሎት ሳይሆን ለ"ቁማር" መቆመሪያ እየዋለ ነው:: ዛሬ ለማገድና ለማሳገድ የሚሮጡ ሰዎች የመቅደሱን ገንዘብ በካሲኖ ጠረጴዛ ላይ የሚበትኑ "የዘመኑ ይሁዳዎች" ናቸው::
፬. ነውረኝነት፦ የታሪክ ወጭት ሰባሪዎች
ርኩስነታቸው እንዳይጋለጥ "ደብዳቤ" በማዘጋጀት የእውነትን ብርሃን ለመጋረድ አምስት የተለያዩ ጊዜያት ሞከሩ። ግን አልቻሉም ደግሞም አይችሉም! አንድ ጳጳስ በሐዋርያዊ ግዴታው መቅደስ መገኘት ሲገባው፣ በደብዳቤያቸው "ውሻ" እና "ተኩላ" የሚሉ ቃላትን መጠቀማቸው ራሱ የንግግር ነውር (Gutter Language) ነው:: "ከውስጥ ያለው ነውር በአፍ ይወጣል'' እንዲሉ!
የዲሲ ሕዝብ ሆይ! ፈርዖን ሙሴን ለማገድ ሞክሮ ነበር፤ ነገር ግን የቀይ ባሕር ማዕበል ፈርዖንንና ጀሌዎቹን በላቸው:: ዛሬም በጻፉት "የደም ደብዳቤ" በገዛ ራሳቸው ላይ ፍርድን አምጥተዋል::
ዘረኝነት፣ መተተኝነት፣ ቁማርተኝነት፣ ነውረኝነትና ሴሰኝነት የነገሠበት መንበር፣ የእግዚአብሔርን አገልጋይ ሊያግድ አይችልም:: ይህ ደብዳቤ በዲሲው ጓዳ ያለውን ርኩሰት ለዓለም ያጋለጠ "የውድቀት ማኒፌስቶ" ነው፡፡
ጭልፋ መስቀልን አያሸንፍም!
ሽንኩርትም ዕጣኑን አያጠፋም!
እኛም የኃያሉ አምላካችን የእግዚአብሔር ጥበቃና ምሕረት አብሮን እስካለ ድረስ፤ እንደተያዝን አንቀርም፡፡ ከታሰርንበት እንፈታለን፤ ከወደቅንበትም እንነሣለን!
╭══•|❀:✞✟✞❀|•══╮
✥┈┈••●◉✞◉●••┈••✥
ከመልአከ ኃይል ቀሲስ ኃይለመለኮት ግርማ ወንድሙ
21/08/2018 ዓ.ም
ከአሜሪካ 🇺🇸 ዋሺንግተን ዲሲ መንፈሳዊነት ይብለጥ!
✥┈┈••●◉✞◉●••┈┈✥
╰══•|❀:✞✟✞❀|•══╯