11/11/2017
ከምዕራፍ 1-5 ላላነበባችሁ ድጋሚ የተለጠፈ
ልብ ሲያፈቅር(ጀምስ ፓንቴ)
ክፍል አንድ
መስከረም1/1982
ዕድሜዬን በትክክል አላውቀውም፡፡አብራኝ የምትኖረው እናቴ አስራ ሁለት ዓመቴ እንደሆነ ነግራኛለች፡፡ከእናቴ ተፋቶ ሌላ ቦታ ከሌላ ሴት ጋር የሚኖረው አባቴ ደግሞ አስር ዓመቴ እንደሆነ ሲያወራ ሰምቼዋለው፡፡ለምን ሁለት የተለያየ ዕድሜ ሊኖረኝ እንደቻለ ሳስብ በትንሿ አዕምሮዬ የሆነ መላ ምት ብልጭ አለልኝ፡፡
እናቴ ያረዘመችው-የእኔን ሆድ ለመሙላት አረቄ ስታወጣ…ጠላ ስትጠምቅ..ጉልት ስትቸረችር እያንዳንዱ ቀን የኑሮ ሸክም እኔን ፊት ለፊቶ እያየች ስለምትሸከም ከክብደቱ የተነሳ በእያንዳንዱ ነጠላ ቀን ላይ የተወሰነ ሰዓት ጨምራ እየደመረች ይሆናል፡፡የመከራ ቀን እረጅም አይደል፡፡
አባቴ ያሳጠረው-ከእናቴ ከተለያየ አምስት ዓመት ሆኖታል፡፡ ፡፡ ከእናቴ ጋር አይነጋገሩም፡፡እንደውም በአጋጣሚ መንገድ ላይ ሲገናኙ ይገለማመጣሉ፡፡ እና አባቴ እኔን የሚያገኘኝ በእሱ ሰፈር ሳልፍ ወይንም በእኛ ሰፈር ሲያልፍ ባጋጣሚ መንገድ ላይ ነው፡፡ይሄ አጋጣሚ የሚከሰተው በሶስት ወር ወይም በአራት ወር አንዴ ነው፡፡አባቴ ለእኔ የሚያወጣው ወጪ ለእንቁጣጣሽ የሚገዛልኝ ሰልባጅ ልብስ እና በረባርሶ ጫማ ነው፡፡ሌላው ከእሱ የማገኘው ጥቅም ዘወትር በሰፈርም ሆነ በትምርት ቤት ለመጠሪያ የምጠቀምበት ስሙ ነው፡፡ስለሆነ እኔን በተመለከተ ካለበት ቀላል ጫና አንጻር ዕድሜዬ አጥሮ ቢታየው አይፈረድበትም
እንግዲህ በዚህ አወዛጋቢ ዕድሜ ላይ ሆኜ ነው ባለ ብዙ ብር የሆንኩት ፡፡የገቢ ምንጬ የዘመን መለወጫ በዓሉ ነው፡፤በስዕል ችሎታዬ በሰፈሩ ተወዳዳሪ ስለሌለኝ ስድስት ለሚሆኑ የሰፈር ጎደኞቼ ዛሬ ያዞሮቸውን የወረቀት ላይ አበቦች የሳልኩላቸው እኔ ነኝ፡፡ለዚህም ልፋቴ ከእያንዳኝዱ 0.75 ሳንቲም በድምሩ አራት ብር ከሃምሳ አግንቼያለው፡፡ማታ ከጎደኞቼ ጋር በመንደራችን በመዞር ከጨፈርኩት ሆያ..ሆዬ ሁለት ብር ከስልሳ ሳንቲም፤ዛሬ ለሊት በማውቃቸውም ሆነ በማላውቃቸው ቤት እራሴ ካዞርኮቸው የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ያላቸው የወረቀት ላይ አበቦች የሸቀልኩት ሶስት ብር ከሰባ ሳንቲም ጠቅላላ ሲደመር አስር ብር ከሰማንያ ሳንቲም ይሆናል፡፡ታዲያ ይታያችሁ ይሄን ያህል ገንዘብ እናቴ እንኳን ያላት አይመስለንም፡፡ዳሩ ምን ያርጋል በእኔ ላይ ወሰን አልባ መብት ያላት እናቴ በአንድ ብር ቅንጥብጣቢ ሥጋ ገዝታ ከሰራችው ወጥ ሆዴ እስኪነረት ካጠገበችኝ ቡኃላ ስምንቱን ብር ተረከበቺኝ፡፡
‹‹አይ የእኔ ልጅ ጎበዝ እኮ ነው፡፡ደብተሩን መግዣ ቻለ›› በሚል ሰበብ ብሬን ዘረፈችኝ፡፡የእኔ ደብተር መግዣ ከሁለት ብር በላይ እንደማይፈጅ አውቃለው ቀሪው እንግዲህ የእሷን የገንዘብ ቦርሳ የሚያደልብ መሆኑ ነው፡፡ከተቃወምኮት በእጄ ላይ የቀረችውን ሁለት ብር ከሰማኒያዬን ተቀብላ ዱላ እንደምትመርቅልኝ በደመነፍስ ስለተገለፀልኝ የተቆዘረውን ሆዴን እና የቀረችውን ገንዘቤን ይዤ እቤቱን ትቼላት ወጣው፡፡
ወደ ሰፈራችን ሜዳ ስደርስ አብዛኞቹ ጎደኞቼ ተሰብስበዋል ፡፡ሁሉም ፊት ላይ የሚታየው ደስታ በሌላ ጊዜ ሚደገም አይመስለም፡፡ግማሹ ከረሜላ ይመጣል ፡፡አንዳንዱ ሸንኮራ ያኝካል፡፡ ቀሪው ደግሞ ኮሾሮ ይኮረሽማል፡፡ልቀላቀላቸው አልፈለግኩም ምክንያቱም ከሳዕታት በፊት ከሁሉም የበለጥኩ ሀብታም ነበርኩ፡፡ ቅድም ዙሪያቸው እየተንጐራደድኩ ያን ሁሉ ብሬን ስቆጥር በአድናቆት በቅናት እና በአክብሮት ከበው ሲመለከቱኝ ነበር፡፡አሁን ደግሞ ተቀላቅዬያቸው የሀብቴ መጠን ከሰማይ ወደ ምድር እንዲህ እንደተሸቀነጠረ ቢረዱ … በተራቸው በንቀት ስሜት ዙሪያዬን ከበው እንደሚያሾፉብኝ ከልምድ ስለማውቅ ሳያዩኝ ብቻዬን ወደ ዋናው ከተማ ተጎዝኩ፡፡
ለነገሩ ይቆይ እንጂ እስከ ነገ ጥዋት ሁሉም አሁን ከያዙት ገንዘብ ቢያንስ ዘጠና ፐርሰንቱን እንደሚዘረፍ እርግጠኛ ነኝ፡፡ ምክንያቱም የሁሉም እናት የእናቴ ጎደኞች እና የእሷው ቢጤዎች ስለሁኑ፡፡
ከሄድኩበት ተመልሼ ወደ እቤት የገባውት ከምሽቱ ሶስት ሰዓት ነበር፡፡ ያመሸው እንዳይመስላችሁ እንደውም አውድ-አመት ስለሆነ ነው በጊዜ የገባውት፡፡ እኔም ሆንኩ የሰፈር ጎደኞቼ ወደ ቤት እንድንገባ የሚፈቀድልን ከምሽቱ አምስት ሰዓት የገበያ ቀን ከሆነ ደግሞ ሰባት ሰዓት ካለፈ ቡኃላ ነው፡፡ ደጃፉን ተሸግሬ ወደ አንድ ክፍል ቤታችን ስገባ ሶስት ዘወትር የማውቃቸው ሰዎች አረቄ ከግስላ ሲጋራ ጋር ቀላቅለው… ሌሎች አራት ሰዎች ደግሞ አረቄውን ብቻ ይጎነጫሉ፡፡ ከመካከላቸው ሁለቱ ሴቶች ናቸው፡፡ እናቴ እንደ ምሰሶ መሀከል ወለል ላይ ዘወትር ከቦታው የማይነቃነቀውን ጀበና እና ረከቦት ከፊቶ ጎልታ ከአንዱ ወደ አንዱ ዓይኖን ታቁለጨልጫለች ፡፡እቤቱ እንደ ወትሮው በአረቄ ሽታ…በትንባሆ ሽታ…በላብ ሽታ…በጫማ ሽታ (ከጥቂት ጫማ ሚመጭ )አብዛኞቹ እቤታችን የሚመጡት ደንበኞች ጫማ የላቸውም ወይም ሆነ ብለው አያረጉም፡፡
‹‹ጎረምሳሽ መጣ አለ›› በተኮላተፈ ንግግር ጋሪ ነጂው ደቻሳ፡፡ምንም ሳልመልስ ከእናቴ ጀርባ ባለችው ባልተያዘች ኩርሲ ላይ ተቀመጥኩ፡፡ ደቻሳን አልወደውም፡፡እሱ ደግሞ ፈርዶበት ከእኛ ቤት አይወጣም፡፡ እንደውም አልፎ አልፎ ከእናቴ ጋር ያድራል፡፡ ለነገሩ እሱ ብቻ አይደለም አሁን እዚህ እቤት ውስጥ ካሉት ሰዎች እንኮን ሦስቱ በተለያየ ቀን እዚሁ ቤት ከእናቴ ጋር አድረዋል፡፡ የእሱ ከሌሎቹ የሚለየው ግን አንደኛ ደጋግሞ ማደሩ… ሁለተኛ በማንኮራፋት እኔን እንቅልፍ መንሳቱ… ሦስተኛ ማንኮራፋቱን ሲያቆም እናቴን ከገደብ በላይ ማስለፍለፉ ናቸው፡፡ ዛሬ ዓመት በዓሉን በማስመልከት ይመስለኛል አራት ሰዓት ተኩል ላይ እቤታችን ባዶ ሆነ፡፡‹‹ደክሞኛል ባክህ ወንበሮቹን አንድ ቦታ ሰብስባቸው›› አለችኝ እኔም ከእሷ በላይ ቢደክመኝም ትዕዛዞን እምቢ ማለት ስለማልደፍር በተጨማሪም ከብድርብሱ ውስጥ ፈጥኜ መግባት ስለፈለግኩ እንዳለቺኚ አደረግኩ ፡፡እሷም ጠረግ ጠረግ አደረገችና ተጣጥፎ የታሰረውን ፍራሽ ፈታ መሀል ወለል ላይ ዘርግታ መሀሉ የተቦተረፈ አንሶላ አንጥፋ አባቴ ጥሎን ከመሄዱ በፊት ከእናቴ ጋር አብረው ይለብሱት የነበረ ብርድልብስ ደረበችበት፡፡አለሚቱ ጋር ደርሼ መጣው እራትህን ብላና ተኛ ብላኝ ወጣች፡፡
ተንደርድሬ በሩን ከውስጥ ቀረቀርኩት፡፡ መብላት አላሰኘኝም፡፡ ከጃኬቴ ስር የደበቅኩትን ዕቃ አወጣው፡፡ ልብሴን ጠቅላላ አወለቅኩ እናቴ ከተወቸችልኝ ሁለት ብር ከሰማንያ ሳንቲም ቀንሼ የገዛውትን ፓንቴን ለመሞከር ነው፡፡ አጠለቅኩት ትንሽ ሰፋ ቢለኝም በውስጤ የጫረብኝ ደስታ መጠን አልባ ነበር፡፡የፓንት ባለቤት መሆን ከሁለት አመት በላይ በውስጤ የተብላላ ምኞት ነበር፡፡ይሄንን ምኞት በውስጤ እንዳበቅል ዘሩን የዘራችብኝ በለጡ ነች፡፡ በለጡ ማለት ቢያንስ በአምስት አመት የምትበልጠኝ የእጅ ስራ መምህራችን ልጅ ነች፡፡ በለጡን በጣም ወዳታለው፡፡ እሷን በምወዳት መጠን ልክ ደግሞ አባቶን እጠላቸዋለዋለው፡፡እሳቸውን ብቸቻ ሳይሆን እሮብን ቀን እጠላለው፡፡ምክንያቱም የእጅስራ ክፍለ ጊዜ ያለን ዕሮብ ቀን ነው፡፡ዳንቴል ስሩ…ሹራብ ስሩ..ኩርሲ ስሩ..ብለው ያዙናል ፡፡እንዴት እንደሚሰራ ግን አንድም ቀን አሳይተውን አያውቁም፡፡መስራት ሲያቅተን ግን ጭንቅላታችን እስኪቆስል በኩርኩም ያበግኑናል፡፡በአርጩሜ ይዠልጡናል፡፡እኔ ደግሞ የዘወትር ደበኛቸው ነኝ፡፡በቃ እጅስራ ምባል ነገር አይሳካልኝም፡፡ወደ ፓንቱ ታሪክ ልመለስ እና የምወዳት በለጡ ዓመቱን ሙሉ እየቀያረቸች የምታደርጋቸው ሦስት ፓንቶች አሎት፡፡አንድ ጀልጃላ ዘጠኝ ቁጥር የተጻፈበት የስፖርት ቁምጣ ፤ሁለተኛው እኔ በጣም የምወድላት ሮዝ ቀለም ያለው ከሰውነቶ ጋር ልጥፍ የሚል እና በጣም የሚያሳምራት ሲሆን ሦስተኛው ግን የፋብሪካ ውጤት አይመስለኝም… በቡኒ ክር በኪሮሽ የተሰራ ነው፡፡ እርግጠኛ ባልሆንም ተማሪዎች ሰርተው ካስረከቡት የእጅ ስራ ውጤት ውስጥ ምርጡን በማርክ ለውጠው አምጥተው የሸለሞት አባቶ ይመስሉኛል ፡፡እና የፓንት ፍቅር የተጠናወተኝ በዚህች በለጡ ምክንያት ነው፡፡ የሚገርመው ሰፈር ውስጥ ሆነ ትምህርት ቤት ሳያት የትኛውን ፓንቶን እንዳደረገች መቀመጫዋን ለደቂቃ በማየት ብቻ እለያለው፡፡
ዛሬ ግን ይሄው ምኞቴ ተሳክቶ ከእሷ ጎን ቁጭ ብዬ ልብሴን በድፍረት አወላልቄ በደስታ ውሀ ውስጥ መንቦጫረቅ እችላለው ፡፡ በጣም የሚያምር ፓንት ነው ያለኝ ፡፡ለዛውም ጀምስ ፓንት፡፡ ፊት ለፊት ላይ የተለጠፈለት ሰዓት መሰል ጌጥ ደግሞ ይበልጥ አሳምሮታል፡፡ ሰዓት መሰል ያለኩት ቅርፁን እንጂ መልኩን አላልኩም ቀለሙ ወርቃማ ነው፡፡ ያብረቀርቃል፡፡ እዛው ለሰዕታት ተገትሬ የእኔን አዲሱን ፓንት በዓይኖቼ… የበለጡን ፓንት ደግሞ በምናቤ አድንቄ ሳልጨርስ በሩ ተንኮኮ፡፡ ቶሎ ብዬ ፓንቴን አውልቄ እን በምተኛበት ቦት ብርድ ልብስ ውስጥ ሸጎጥኩትና መላመላዬ ሄጄ ከፈትኩላት፡፡ ‹‹አልተኛህም እንዴ?›› አለችኝ፡፡
‹‹ እንቅልፍ አልወሰደኝም››
‹‹ በደምብ አልተራገጥክማ››
ዝም አልኮት እና ቀስ ብዬ ብርድ ልብሱን ገልጬ ተከናነብኩ፡፡ እናቴ እንደ ዘወትሮ በራፉንም መስኮቱንም ቀርቅራ በሁለቱም ላይ ትሪዎችን አንጠልጥላ በቀጥታ ከጎኔ ተኛች ፡፡ቀሚሶን አውልቃ አረንጎዴ የሻማ የውስጥ ልብሲን እያንሾሾች፡፡ወዲያው ነበር እንቅልፍ የወሰዳት፡፡ የሰፈራችን ሀብታም ሴት እትዬ ጥሩ ሁል ጊዜ እንቅልፍ እምቢ አለኝ እያሉ ሲማረሩ እሰማለው፡፡ እናቴ ግን አንድም ቀን ስለ ዕንቅልፍ ስትጨነቅ ሰምቼ አላውቅም፡፡ ብርድ ልብሱን በደምቡ ለብሳ እንኮን ሳትጨርስ ነው ዓይኖ የሚጨፈነው፡፡ለነገሩ እኔም እንደእሷው ነኝ፡፡ ዛሬን ሳይጨምር ማለቴ ነው፡፡ ዛሬማ እንቅልፍ ሚወስደኝ አይመስለኝም፡፡ ምን አልባት እማማ ጥሩ በየቀኑ አዳዲስ ፓንት እየገዙ ስለእሱ እያሰቡ ይሁን እንዴ እንቅልፍ የማይወስዳቸው ስል አሰብኩ፡፡ፓንቴን ቀስ ብዬ መልሼ አጠለኩት፡፡ ከእናቴ እና ከበለጡ እኩል የሁንኩ ከአባቴ ደግሞ ጠበለጥኩ መስሎ ተሰማኝ፡፡ምክንያቱም አባቴ እኔ እስከማውቀው ድረስ ከእኛ ጋር በሚኖርበት ጊዜ ፓንት አልነበረውም፡፡
ልብ ሲያፈቅር(ጀምስ ፓንቴ)
ምዕራፍ ሁለት
መስከረም 2/1982
ከተለመደው ትንሽ ጠንከር ያለ የእናቴ ተንከትካች ሳቅ ነበር ከእነንቅልፌ ያባነነኝ ፡፡ዓይኖቼን ስገልጥ ስሬ ቆማ እየተንፈረፈረች ሆዶን ይዛ ታስካካለች፡፡ ብርድ ልብሱን ገፋኝ በእጆ ይዛዋለች፡፡‹‹ኪ..ኪ..ኪኪ..ኪ…እውነትም ጎርምሰህልኛል ..ጉድ ነው፡፡›› ተገለፀልኝ ስለፓንቴ እያወራች እንደሆነ ገባኝ፡፡
‹‹ እስቲ እስቲ ቁም››
ቀጫጫ እጆቼን በስራ በደለደሉ እጆቾ ጨምድዳ አቆመችኝ፡፡
‹‹ከየት አመጣኸው?›› በትኩረት አገላብጣ ካየችኝ ቡኃላ ጠየቀችኝ
‹‹ገዛውት››
‹‹ ኦሆ..ሆ ገዛውት… ወገኛ ነህ… ገና ቂጥህን አስተካክለህ መጥረግ ሳትችል ብታንታ…የአባቱ ቢጤ ሸርሙጣ…..››
‹‹....እስቲ..እስቲ…ደግሞ የትልቅ ሰው ይመስላል ፡፡ሰፍቶሀል፡፡››
የዚህን ጊዜ ሰውነቴ ቀዘቀዘብኝ፡፡ ከለኝ ልምድ እናቴ የሆነ እርምጃ መውሰድ ስትፈልግ ያንን እርምጃ የሚደግፍ ንግግር ታስቀድማለች፡፡ የትልቅ ሰው ነው ያለችው ምንአልባት ለራሷ ልታደርገው ይሆን እንዴ ? የሚል ፍርሀት አንቀጠቀጠኝ፡፡ ህልሜ ሁሉ ሲከስም ታየኝ፡፡ ብዙም ሳይቆይ ግን የእናቴን መቀመጫ በጎሪጥ አይቼ ተፅናናው፡፡ ከጉልበቶ በላይ እሺ ብሎ እንደማያልፍት እርግጠኛ ስለሆንኩ፡፡ግን ከቁጣዋ ጋር ተያይዞ አንድ ነገር ብልጭ አለልኝ፡፡ ምን አልባት አባቴ ከእኛ ጋር ሲኖር ፓንት ያልነበረው እናቴ ሸርሙጣ ብላ እንዳትሰድበው ፈርቶ ይሆን ስል አሰብኩ፡፡ ሊሆን ይችላል፡፡
ደግነቱ ጎረቤት ጠብ ተነስቶ ጩኸት ስለቀለጠ ወሬ የምትወደው እናቴ ተንደርድራ በባዶ እግሮ እቤቱን ለቃ ወጣች፡፡ እኔም ከመመለሷ በፊት በፍጥነት በጀምስ ፓንቴ ላይ ሱሪዬን ደርቤ የቀሩኝን ሳንቲሞች መኖራቸውን አረጋግጬ ወደ ጎደኞቼ ሄድኩ፡፡ ሦስት ሆነው ሲጫወቱ አገኘዋቸው፡፡ እና አራተኛ ሆኜ ተቀላቀልኮቸው፡፡ ከመካከላችን አንዱ‹‹ ኳስ እንጫወት›› አለ እኔ ሌላ ሀሳብ አቀረብኩ
‹‹ወንዝ እንሂድ››
‹‹ለምን? ››ሌለኛው ጠየቀ
‹‹ልንዋኝ ነዋ››
‹‹በዚህ ጥዋት፤ ይቀዘቀዛል እኮ!››
ተከራከርኩ ‹‹አይቀዘቅዝም አንድ አላማ ሸንኮራ ገዝተን እየበላን እንሂድ››
‹‹ባክህ እኔ ምንም ሳንቲም የለኝም ሁሉንም እናቴ ወሰደችብኝ››
‹‹የእኔንም ወሰደችብኝ… ሃምሳ ሳንቲም ብቻ ነው ደብቄ ያስቀረውት›› ሌለኛው ተናገረ
አላልኮችሁም ትናንትናውኑ ነበር ይሄ የንብረት ነጠቃ ሁሉንም ጎደኞቼን እንደሚያጋጥማቸው የተነበይኩት
‹‹ሸንኮራውን የምገዛው እኔ ነኝ ››
የሸንኮራውን ግብዣ ሳቀርብ ሁሉም ተስማሙ፡፡ ግን በመገረም ነበር እና በመጠራጠር መሀል ተሰንቅረው ነበር እሺ ያሉኝ፡፡ ምን ቸር እንዳደረገኝ ግራ ገብቶቸዋል፡፡በስምምነታችን መሰረት በሀምሳ ሳንቲም በማውጣት አንድ አላማ ሸንኮራ ገዝቼ አራት ቦታ ቆራርጬ አንድ አንድ አከፋፈልኮቸው እና እሱን እየገመጥን ወደ ወንዝ አመራን፡፡ እንደደረስን ተዝናንቼ ድንጋይ ላይ ቁጭ አልኩ ሁሉም በየተራ እያወላለቁ መላመላቸውን ወንዝ ውስጥ ለመዋኘት ገቡ፡፡ ናቅኮቸው፡፡ ያልተገረዘ ወሸላቸውን (እርግጥ እኔም አልተገረዝኩም)ተመለከትኩ የበላይነት ተሰማኝ፡፡
‹‹ይዘኸን መጥተኸ ቁጭ ትላለኸ እንዴ አውልቀኸ አትዋኝም? ›› አለኝ ከጎደኞቼ አንዱ
‹‹መጣው ፀሀዬን እስክትወጣ እየጠበቅኩ ነው›› አልኩት
ፀሀዬ በደንብ ፍንትው ብላ ማቃጠል ጀምራለች‹‹ ፈሪ ፈርተህ ነው አለኝ ››ሌለኛው ሳቁን ገታ አድርጎ፡፡ እኔ ግን ፈርቼ አልነበረም፡፡ ፀሀዬ እስክትወጣ ነው የያልኩትም ይህቺ የምታቃጥለዋን ሳይሆን የእኔዋን ፀሀይ ማለቴ ነበር፡፡ ድንገት ውሀ ልትቀዳ፣ልብስ ልታጥብ ወይንም ልትዋኝ ብትመጣ ብዬ በጉጉት እየጠበቅኮት ነው
ጎደኞቼንም ሆነ እሷን በአንዴ ለማስገረም ፡፡የእኔ ፀሀይ በለጡ ግን ብቅ ልትል አልቻለችም ፡፡ስለዚህ የእሷ ለነገ ይደርሳል አልኩና በመጀመሪያ ከላይ የለበስኩትን ሹራብ ቀጥሎ በዝግታ ሱሪዬን አወለቅኩ፡፡ ቅድሚያ ያየኝ ጥጋብ የሚባለው ጎደኛዬ ነው፡፡ እነዛ ጭል ጭል የሚሉ ዓይኖቹን በለጠጣቸው፡፡ በገረሜታ‹‹ እንዴ ተመልከቱ…ተመልከቱ በማለት አዋጅ አስነገረ›› እየተሸቀዳደሙ ወደ እኔ በመምጣት ከበቡኝ፡፡ በእጃቸው እየዳበሱ ዙሪያዬን እየተሸከረከሩ ተመለከቱልኝ፡፡ አደነቁልኝ፡፡ በመጨረሻም አንድ አንዴ እንዳስለብሳቸው ለመኑኝ፡፡ ፍቃደኛ አልሆንኩም፡፡ ሁሉም አኮረፉኝ፡፡ እኔ ሳልዋኝ ልብሳቸውን መልበስ ጀመሩ፡፡ እኔም እነሱን የማስጎምጀት እንጂ የመዋኘት ፍላጎት ስላልነበረኝ ቅሬታ አልተሰማኝም፡፡ ልብሴን ለብሼ በኩራት ከኃላ ተከተልኮቸው፡፡ የተበሳጩት ቀንተውብኝ እንደሆነ ስለገመትኩ ደስ አለኝ፡፡ ሰፈር እስክንደርስ አላናገሩኝም፡፡ አንድ ሰዓት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ግን የአስደናቂ ፓንት ባለቤት መሆኔ በሰፈራችን ሁሉ ተወራ እያንዳንዱ ውሪ እየመጣ ሱሪዬን ዝቅ እያደረግኩ እንዳሳየው ሲለምኑኝ እኔም ይሄንን ሳደርግ ዋልኩ፡፡ በክብር እና በእርካታ፡፡ በለጡ ዘንድ ወሬው ደርሶ ይሆን ስል አሰብኩ፡፡ማረጋገጥ ግን አልቻልኩም፡፡
ከሳምንት ቡኃላ አስደንጋጭ ክስተት አጋጠመኝ፡፡ ጀምስ ፓንቴ የገባበት ጠፋ፡፡ እቤታችን አንድም ያልተበረበረ ቦታ የለም፡፡ ከአስራ አምስት የሚበልጡ በቤታችን የሚገኙ የዓይጥ ጉድጎዶች ሳይቀሩ እየተቆፋፈሩ በተደጋጋሚ ተበረበሩ፡፡ ምንም ፍንጭ ሊገኝ አልቻለም፡፡ በዚህ ክሰተት እኔ ብቻ ሳልሆን እናቴም ክፉኛ ተበሳጭታለች፡፡‹‹እነዚህ እከካም ጎደኞችህ ናቸው ተመቅኘተውህ የሰረቁህ›› አለች እናቴ፡፡ በንግግሮ ደስ አለኝ፡፡ ለካስ አመል ሆኖባት ተቆጣችኝ እንጂ በእኔ ጀምስ ፓንት መግዛት ተደስታ እና ኩራት ተሰምቶት ነበር፡፡
እቤት ውስጥ እንደሌለ እርግጠኛ ስንሆን ፍለጋው ወደ ውጭ ተሸጋገረ፡፡ እናቴ ከሰፈራችን ውሪዎች መካከል በእሷ አመለካከት ስርቆቱን ለመፈጸም ድፍረቱ ዕድሉ እና አጋጣሚው ይኖራቸዋል ብላ የጠረጠረቻቸውን በየስርቻው እየዞረች ሱሪያቸውን እና ቁምጣቸውን እያስወለቀች ፈተሸቻቸው፡፡ ሊገኝ ግን አልቻለም፡፡ ፍተሸው የተካሄደባቸው ልጆች ወላጆች ግን አጉረመረሙ፡፡ እናቴ ግን ቁብም አልሰጣትም፡፡
‹‹ ታዲያ የማንንም ዲቃላ ሱሪ አስወልቄ የልጄን አዲስ ፓንት መስረቅ አለመስረቃቸውን ለመፈተሸ የፍርድ ቤት የፍቃድ ወረቀት ማውጣት ነበረብኝ?›› ሥትል አሽሞጠጠች፡፡
መስከረም 28/82
ከምሽቱ አምስት ሰዓት አከባቢ ወደ ቤት ስገባ ደቻሳ ከእናቴ ጎን ተቀምጦ ሲጎነታትላት ደረስኩ፡፡ ሁለቱም ፊት ለፊት የአረቄ መለኪያ ይታያል፡፡‹‹ ..ኦ ጎረምሳው መጣህ›› አለኝ በተለመደው ቃና አስቀያሚው ደቻሳ፡፡ ምንም አልመለስኩለትም፡፡ ዝም ብዬ ኩርሲ ላይ ተቀመጥኩ፡፡
‹‹ያው እራትህ ሳህኑ ላይ ኦለልህ ብላና ተኛ›› አለችኝ እናቴ የጠቆመችኝን ሰሀን ከፈትኩና የበቆሎ ቂጣ(ጦረሰሾ) በጐመን እየተስገበገብኩ በላውና ጥግ ላይ ወደ ተነጠፈልኝ መኝታዬ ሄጄ ተከናንቤ ተኛው፡፡
‹‹ ዛሬ ነገር አለ›› ስል አሰብኩ፡፡ እናቴ እዚህ ቦታ እንድተኛ ካዘዘችኝ ከሆነ ሰው ጋር ለመተኛት አስባለች ማለት ነው፡፡ ተነስታ በራፉን በመሸንጎሪያ ስትቀረቅር ይሰማኛል፡፡ ደቻሳ አልወጣም፡፡
‹‹በል ሂሳብ ዝጋልኝ››አለችው፡፡
‹‹አንተ ጋር ሰባት ደብል እኔ ጋር አራት ደብል … አስራ አንድ ይሆናል፡፡ አስራ አንዱ ማለት አምስት ብር ከሀምሳ ማለት ነው ›› አለችው፡፡
በእናቴ የሂሳብ ችሎታ ምን ጊዜም እንደተደነቅኩ ነው፡፡ በአባቴ ወጥቼ እንጂ በእሷ ብወጣ ኖሮ እንዲህ በእየለቱ የሂሳብ አስተማሪዬ ጥያቄ መመለስ እያስቸገረኝ አለንጋ አልቀምስም ነበር
‹‹ያው ሀምሳ ሳንቲም መልሺ›› አላት ደቻሳ ባሻካራ ድምፅ
እኔ እንዳልሰማ መሰለኝ ድምጾን ቀንሳ ‹‹የምታድረበትን አምጣ እንጂ›› አለችው፡፡
‹‹ ምን አለበት አንዳንዴ እንኳን የውሽምነት መብቴን ብታከብሪልኝና እንደሰዉ በነፃ ብታሳድሪኝ፡፡››
‹‹ኡኡ..ቴ ድንቄም ውሽማ››
‹‹እንዴት አታፈቅሪኝም ማለት ነው?››
‹‹ወገኛ ነህ ባክህ እኛ በጊዜያችን አፍቅረን… ወሽመን… አደባድበን… ወጥቶልናል፡፡ ስንቱን ሸበላ ስንቱን ጀግና አገላብጠናል፡፡ ምን ታረግ ዛሬ በእርጅናዬ እና በችግሬ ጭርቁስቁስ ብዬ ብታገኘኝ ወንድ የተራብኩ እመስልሀለው የኑሮ ሽንቁሬን ለመድፈን ብዬ እንጄ ..የወሲብ ጥሜን ለማርካት እንዳይመስልህ››
እናቴ ስለ ድሮ ውበቶ እና ስለ ጥንት ውሽሞቾ ማውራት ከጀመረች ሆድ እንደሚብሳት እና በለቅሶ እንደምትደመድመው ስለማውቅ ጨነቀኝ፡፡ ይሄን ሸፋፋም ይበልጥ ጠላውት፡፡
እናቴ ቀጠለች… ‹‹አንተ ጠረንገሎ ትከፍላለህ ወይስ ቤቴን ለቀህልኝ ትወጣለህ›› ትዕግስቶ እንዳለቀ የተረዳው ደቻሳም ብሩን ሰጣት፡፡ ስንት እንደሰጣት ግን በመሸፋፈኔ ማወቅ አልቻልኩም፡፡ ሁለቱም እያጉረመረሙ ወደ መኝታቸው ተጓዙ፡፡ በእኔ እና በእነሱ መኝታ መካከል የሁለት ሜትርእና እናቴ የከወ
ከእዛ ቡኃላ ደቻሳ እና እናቴ የከወኑትን ነገር ለእናንተ ለማውራት ለእናቴ ያለኝ ፍቅር አይፈቅድልኝም፡፡ እና ዘልዬዋለው፡፡ብቻ እንደምንም እንቅልፍ ወሰደኝ፡፡
ሊነጋጋ ሲል ስሜ ሲጠራ ሰማው፡፡ ከውጭ ነው፡፡ ትዝ አለኝ ከጎደኞቼ ጋር እስፖርት ለመስራት ተቀጣጥሬ ነበር፡፡በሰፈራችን የእግር ኮስ ቡድን አቆቁመናል፡፡ እየተደናበርኩ ተነሳው እና መብራቱን አበራው፡፡ እናቴ እና ደቻሳ ጅርባቸውን ገጥመው ተኝተዋለ፡፡ልብሴን ለብሼ ልወጣ ስል ዓይኔ የደቻሳ ልብስ ላይ አረፈ፡፡ አንድ የተንሻፈፈች ጠረጵዛ ላይ ተቆልሎል፡፡ ተጠጋውት…‹‹ አዎ እራሱ ነው ››አንሾካሾኩ፡፡ ጀምስ ፓንቴ ፡፡አነሳው እና ወደ ዓይኔ አስጠጋውት፡፡ በጣም ከመቆሸሹ እና ጠርዙ ወደ ላይ ከመሸብሸቡ በስተቀር የራሴው ፓንት ነው፡፡ መልሼ አስቀመጥኩት፡፡ በራፉን ከፈትኩና ጎደኞቼን እንደመመኝ ነግሬያቸው ወደ ውስጥ ተመለስኩ፡፡ መብራቱን አጥፍቼ መኝታዬ ላይ ጋደም ብዬ በጨለማ ውስጥ ምን እርምጃ መውሰድ እንዳለብኝ ሳሰላስል ነጋና እናቴ ስተነሳ ሰማዋት፡፡
‹‹ አንተ ደቻሳ… ተነስ ተጋድመህ ልትውል ነው እንዴ…? እነዚህ ሀሚተኛ ጎረቤቶቼ ሳይነሱ ውጣልኝ›› አለችው፡፡ እየተነጫነጨ ተገለባበጠ እና መልሶ ማንኮራፋት ጀመረ፡፡ እናቴ ማታ አውልቃ የጣለችውን ቀሚስ ለበሰችና ተነሳች፡፡ ድንገት ወደ እኔ አማተረች እና‹‹ እንዴ ምነው ተጎለትክሳ? ‹‹እየጠሩህ አልነበረ እንዴ?››
አልመለስኩላትም፡፡
‹‹አሞሀል እንዴ?››
‹‹ፓንቴን ..››
እየቃዠው ሳይመስላት አይቀርም‹‹ ምንድነው የምታወራው?››
ቆምኩ እና ወደ ጆሮዋ ተጠግቼ በጣቴ ወደ ደቻሳ ልብስ እየጠቆምኩ‹‹ ፓንቴን…ሙታንታዬን..››አልኮት
እየተንደረደረች ሄደችና አነሳችው፡፡ አገላብጣ አየችው፡፡ ዓይኖቾ ፈጠጡ፡፡ ዓይኖቾ እንዲህ ሚፈጡት የንዴት ዛር ሲሰፍርባት መሆኑን ከልምድ አውቃለው፡፡ የለበሰውን ብርድ ልብስ ገፈፈችው በድንጋጤ ባነነ እና በእጆቹ እፍረተ ስጋውን ሸፈነ ..እንትኑ ትልቅ ነው፡፡
‹‹አብደሻል እንዴ?››
‹‹ አንተ ሌባ …አንተ ልክስክስ›› ብላ ፓንቱን ፊቱ ላይ ወረወረችበት፡፡ አነሳና ለመልበስ ሲሞክር መልሳ መነጨቀችው፡፡
‹‹ሙታንታዬን አምጪ››
‹‹ደግሞ ከመቼ ወዲህ ነው እንዳንተ አይነት ሸፋፋ እንዲህ አይነት ቡታነንታ አድርጎ የሚያውቀው? ለመሆኑ ዘር ማንዘርህ ቡታነንታ አድርጎ ያውቃል?››
‹‹እቤቴ አድረህ…በጭኔ ሞነው አልጄን ቡታን… አድርጎ እንኳን አምሮቱ ሳይወጣለት …ምንታደርግ ካንተ አይነት ልክስክስ ጋር የተልከሰከስኩት እኔው ነኝ ወይ ልጅት!››
‹‹ባክሽ አትጩሂብኝ… የልጄ ነው ካልሽ ውሰጂው… መዝረፍ እንደሆነ ልማድሽ ነው›› በማለት እፍረተ ስጋውን መሸፈን እረስቶ እያንጀለጀለ ተነሳና ቦላሌውን በመልበሰ ሹራቡን በማጥለቅ በረባርሶ ጫማውን ደነቀረ እናም እናቴ ፊት ተገተረ፡፡ ድርጊቱን በዝምታ ትከታተለዋለች፡፡
‹‹ክፈቺልኝ ልሂድበት››
‹‹የሰፈሩን ሰው ሁሉ ጠርቼ ሳላዋርድህ የቡታንታውን ሂሳብ ቁጭ አድርግ›› ይሄው ይሄንን በማለት ኪሱ ውስጥ ወሸቀችለት፡፡
‹‹..እንደጀመርከው ውሰድ እና አጨማልቀው…. እ ምን ይሸልሀል?›› እነዛ ወሬ ቀለባቸው የሆነ የሰፈሬን ሰዎች ልጥራቸው ወይስ አራት ብር ቁጭ ታደርጋለህ?››
ደቻሳ ከንዴቱ የተነሳ መናገር ሁሉ አቅቶታል፡፡ አራት ብር አወጣና እጆ ላይ አስቀመጠላት፡፡
‹‹ አዎ ጥሩ መርጠሀል›› በማለት በራፉን ከፈተችለት፡፡ደቻሳም እተራገመ ወጥቶ ሄደ፡፡
እናቴ አሁን ከንዴቶ ቀዝቅዛለች፡፡ ፊቶ ሁሉ በርቶል፡፡
‹‹እማ የገዘውት አኮ 2.50 ነው››አልኮት
‹‹ዝም በል አውቄ ነው… ሌላው ወለድ ነው›› አለችኝ፡፡
ብር የያዘው እጆ ላይ ዓይኖቼን ተክዬ ‹‹ በቃ ስጪኝና አሁኑኑ ገዝቼ ልምጣ አልኮት››
ወደ ሳንቲም ማስቀመጫዋ ሄደች እና ሃያ አምስት ሳንቲም አነሳች እና መዳፌ ላይ አስቀምጣ ‹‹አብደላ ሻይ ቤት ሂድና ቁርስህን ብላ… ከአሁን ወዲያ ግን ሙታንታ የሚባል ነገር አያስፈልግህም… እስቲ መጀመሪያ እደግ…››
ፈዝዤ በቆምኩበት ተገትሬ ቀረው…‹‹ ካልፈለግክ ሳንቲሙን መልሰልኝና ማታ የተረፈህ ጦሮሾ ስላለ እሱን ቁርስህን ብላ›› አለችኝ እንደመባነን አልኩና ልክ ደቻሳ እንዳደረገው እቤቱን ለቅቄ ተፈተለኩ ወደ አብደላ ሻይ ቤት ከምንም ይሻላል በማለት አሳንቡሳ ልበላ፡፡
ልብ ሲያፈቅር (ጀምስ ፓንቴ)
ምዕራፍ 3
የበለጡ ታሪክ በጀምስ ፓንቴ ብቻ አላበቃም፡፡ በ14 ዓመቴ ለእሷ ያለኝ ፍቅር 140 ፐርሰንት ደረሰ፡፡ በቃ በህልሜም በውኔም እሷን ብቻ ማለም ጀምሪያለሁ፡፡ ቅዠት ሆናብኛለች፡፡ ደግሞ ወድጄ አይደለም፡፡ የእኔዋ በለጡ 16 ዓመት ሆኗታል፡፡ በቃ አብባለች . . . ጉንጮቿ ምልተዋል . . . ጡቶቿ ፈጠዋል . . . መቀመጫዋ ጠጥሯል . . . እና እራሴን መቆጣጠር ስላቃተኝ እርምጃዬን ወሰድኩ፡፡
ተጨንቄ እና ተጠብቤ ጥንታዊ የፍቅር ደብዳቤ በሦስት ቀን ፅፌ ጨረስኩ፡፡ አንድ ሰፈር ውስጥ ስለምንኖር ደብዳቤውን ለመስጠት ብዙም አልተቸገርኩም፡፡ ከምሽቱ 1፡30 አካባቢ ሱቅ ተልካ ወደ ቤት ስትመለስ አገኘኋት፡፡
‹‹በለጡ››
‹‹አቤት ድርዬው››
በለጡ ዱርዬው ስትለኝ ለምን እንደሆነ እንጃ ደስ ይለኛል፡፡ ዱርዬው የሚለው ቃል እኔ ጋር ሲደርስ ተፈቃሪው . . . ተወዳጁ የሚል ትርጉም ነው የሚሰጠኝ፡፡
‹‹ይሄው አገኝኸኝ እኮ››
ፈራው . . . ሰውነቴ ሁሉ ተንቀጠቀጠብኝ
‹‹ማለቴ . . . ምን መሰለሽ››
‹‹ባክህ ቸኩላለሁ›› ብላ ፊቷን አዙራ መንገዶን ስትቀጥል
‹‹ቆይ አንጂ ሰው ልኮኝ እኮ ነው›› በማለት በፖስታ የታሸገውን ደብዳቤ አውጠቼ ሰጠኋት ‹‹አቃጠሪ . . . ማነው የሰጠህ?›› ብላ መነጨቀችኝ፡፡
‹‹በቀደም የሸኘሽ ልጅ›› በማለት በቆመችበት ጥያት ሄድኩ፡፡
ምን ነካኝ . . . ምን ማለቴ ነው?.... በቀደም የሸኛት ልጅ ማን ነው? ማንም ሲሸኛት አላየሁም፡፡
በማግስቱ
የማልወዳቸው ሁለት ጨበሬ ጓደኞች ጋር ት/ቤት ውስጥ አገኘኋት፡፡
‹‹ሃይ . . . አፌ ላይ ድንገት መጣብኝ
‹‹ሃይ ዱርዬው›› በለጡ መለሰች
ጓደኞች አስጠሊታ ሳቅ ሳቁ፡፡ ፈችኝ በፈጣሪ ምን ያሚያስቅ ንግግር ታደርጋለች ይሄኔ እሷ ዱርዬው ስላለች የሰደበችኝ . . . የተጠየፈችኝ መስሎቸው ይሆናል እኮ፡፡ ምድረ ወረኛ ሁላ፡፡ ለማንኛውም ተላለፍን፡፡ ከወትሮ ብዙም የተለየ ነገር አልተመለከትኩባትም፡፡ ግን በመጠኑ ፊቷ የበራ . . . የፈካ መሰለኝ፡፡ ብሩህ ተስፋ ታየኝ፡፡ ብቻዋን እስካገኛት ተኮልኩ፡፡ ግን የደብዳቤዬን መልስ እንዴት አድርጋ ትሰጠኛለች፡፡ታፍር ይሆናል፡፡ የሆነ ሀሳብ መጣልኝ አልፌያቸው ከሄድኩ በኋላ ተመለስኩ
‹‹በለጡ›› ጠራኋት
‹‹አቤት›› ወደኋላ ዞረች እና ተነጥላ ወደ እኔ ቀረብ አለች፡፡
‹‹መጽሐፍ እንድታውሺኝ ነበር››
‹‹የምን መጽሐፍ››
‹‹አደፍርስ የሚል መጽሐፍ ይዘሽ አይቻለሁ . . . ከት ብላ ሳቀችብኝ፡፡
‹‹ምን ልታደርገው››
‹‹ላነበው ነዋ››
ባክህ እንኳን አንተ የ7ኛ ክፍል ተማሪ ይቅርና እኔም የዘጠነኛ ክፍል የምማረው አንብቤ አልገባኝም፡፡
ሲያበሳጭ . . . ይህቺ በለጡ . . . እኔን በመልክ ትበልጠኛለች . . . በዕድሜ ትበልኛለች . . . በትምህርትን ምን ትበልጠኛለች . . . እኔ በምን ይሆን የምበልጣት ምን አልባት በዱርዬነት ይሆናል፡፡ ዱርዬ ማለት ግን ምን ማለት ነው?
ተበሳጨው፡፡ ‹‹ምን ችገረሽ፡፡ አንቺ ታውሺኛለሽ ወይስ አታውሸኝም››
‹‹በቃ በቃ አትበሳጭ . . . ማታ እቤት ናና ውሰድ››
‹‹እቤት እማ አልመጣም››
‹‹ምነው?››
‹‹አባትሽ››
ሳቀች፡፡ አባቶን በጣም እንደምፈራቸው ታውቃለች፡፡
‹‹በቃ እዛ ምትጎለትበት ቦታ ይዤልህ እመጣለሁ›› ብላኝ ከጓደኞቿ ጋር እየተሳሳቀች ጥላኝ ሄዳች፡፡ ስለያት እፎይ አልኩ፡፡ ከእሷ ጋር ቆሜ ሳወራ ይጨንቀኛል፡፡ ምፍራት እንደ እጅ ሥራ አስተማሪ አባቶ ነው፡፡ ልዩነቱ እሳቸውን በጥላቻ ሲሆን እሷን በፍቅር ነው፡፡ በነገራችን ላይ ከ 6ኛ ክፈል በላይ የእጅ ሥራ ትምህርት ስለማንማር ከበለጡ አባት ኩርኩም ተገላግያለሁ፡፡
ማታ
በለጡ የቀጠረችኝ ቦታ መቀመጥ የጀመርኩት 11፡00 ሰዓት ላይ ነው፡፡ ከትምህርት ቤት እንደተመለስኩ ደብተሬን ለማስቀመጥ እንኳን ወደቤት አልሄድኩም፡፡ ያልሄድኩበት ዋና ምክንያት ከእናቴ ላለመገናኘት ነው፡፡ ምን ይታወቃል ልክ እንዳየችኝ መጻፍ የምታክል ሽልጦ ወርውራልኝ
‹‹መክሰስህን ብላና . . . ገበያ ሄደህ ቡና ግዛልኝ›› ብትለኝ ወይም
‹‹መክሰስህን ብላና . . . ዛሬ ቦኖ ውሃ ስለሌላ ወንዝ ሄደህ ውሃ ቀድተህልኝ ና›› ብትለኝስ
ወይም
‹‹ መክሰስህን ብላና . . . እራሴን ስላመመኝ ቆንጆ ቡና አፍልተህ አጠጣኝ›› ብትለኝስ
እነዚህን እና የመሳሰሉትን የእናቴን ትዕዛዛት ለመከወን ብዬ ደፋ ቀና ስል በመሀል በለጡ መጥታ ብታጠኝስ፡፡ ለእኔ ትልቅ ኪሳራ አይደል፡፡ ስለዚህ ያለችኝ ቦታ ተጎልቼያለሁ፡፡ ይህ ቦታ እኔ ብቻ ሳልሆን የሰፈራችን ጎረምሶች እንዲሁም የእኔ ቢጤ ውሪዎች ተሰብስበው በመቀመጥ ስለፊልም የሚደሰኩሩበት… ስለ ኳስ የሚከራከሩበት . . . ስለ ፍቅር የሚንሸኳሸኩበት . . . በአካባቢው የምታልፍን ሴት የሚላከፉበት…. አንዳንዴም ቁማር የሚጫወቱበት ቦታ ነው፡፡ የግራር ዛፍ አለ፡፡ ዙሪያው ጠፍጠፋ ድንጋይ መቀመጫዎች ይገኛሉ፡፡ ዛሬ ብቻዬን ነኝ፡፡ ይህ የሆነው በሰፈራችን የሚገኘው የሸምሱ ቪዲዮ ቤት የቆንጆዎችን ፊልም ከ12፡00 ሰዓት ጀምሮ ስለሚያሳይ ነው፡፡ ቆንጆዎቹ ደግሞ የአማርኛ ፊልም እንዳያመልጣችሁ ብሎ ማስታወቂያ ከለጠፈ የወሲብ ፊልም ላሳይ ነውን እንዳያመጣላችሁ ማለቱ ነው፡፡ ይሄን የማያውቅ የእኛ ሠፈር ልጅ የለም፡፡ ምን አልባት በቅርብ ከገጠር የመጣ ፋራ ካልሆነ፡፡
ከ2፡30 ጥበቃ በኋላ አንዱ ሰዓት ገዳማ ሲል በለጡ መጣች
‹‹ዱርዬው . . ምነው ብቻህን?››
‹‹እየጠበኩሽ ነዋ፡፡››
‹‹ቆየህ እንዴ?››
‹‹ብዙም አልቆየሁም›› እውነቴል?››
‹‹ያውእና ሦስት ሰዓት በለጡን መጠበቅ ብዙ ይባላል ? . . በፍፁም
‹‹ያውልህ . . . ደግሞ በጥንቃቄ ያዘው፡፡ ነግሬኸለሁ የአባዬ ነው›› ብላ እጄ ላይ አስቀመጠችልኝ
‹‹ችግር የለም፡፡ ነገ መልስልሻለሁ፡፡››
ከት ብላ ሳቀች፡፡ ‹‹ ኪ .ኪ.ኪኪ››
‹‹ምን ያስቅሻል?››
‹‹ርዕሱን ለማንበብ ነው እንዴ የተዋስከው?››
‹‹አይ ላነበው ነው››
‹‹አረ ባክህ.. ቀልደኛ ነህ፡፡ አንተ በአስር ቀን አንብበህ ታሪኩን ከተረክልኝ እሸልምኃለሁ ብላኝ›› እየሳቀች እንደልማዷ ጥላኝ ሄደች፡፡
ከቆምኩበት ጨለም ያለ ቦታ ተንደርድሬ የመንገድ መብራት ወዳለበት ቦታ ሄድኩኝ፡፡ አዳፍርስን ከመጀመሪያው ገጽ እስከ ማብቂያው ሁለት ጊዜ ገልጬ ጨረስኩት ምንም ውስጡ የለ፡፡ ባዶ ነው፡፡ ባዶ የወረቀት ንብብር፡፡ ምን ዓይነት ነች?፡፡ ይህቺ በለጡ የእኛ ሠፈር ልጅ አይደለችም እንዴ?›› እራሴን ጠየኩ እኔ አሁን መጽሐፍ አውሺኝ ያልኳት ለምን እንደሆነ ለምን አይገባትም፡፡ ከመቼ ወዲህ ነው እኔ ልብወለድ አንብቤ የማውቀው፡፡ የትምህርት መጽሐፍም በግድ ነው፡፡ የእኔ ጥረት የደብዳቤዬን መልስ በመጽሐፍ ውስጥ አድርጋ እንድትመልስልኝ ነበር፡፡ ሶስት ሰዓት ሙሉ ሳልደክም የጠበቅኳት እስከ አሁን እየፃፈች ይሆናል… ቃላት እየመረጠች . . . ግጥም እደረደረች . . እየሰረዘች እየደለዘች ይሆናል ብዬ ነው እንጂ የንባብ ፍቅር አናውዞኝ አልነበረም፡፡
መጽሀፉን በጥንቃቄ አንድይዘው ስታስጠነቅቀኝ ነገ እመልስልሻለሁ ያልኳት እውነቴን ነበር፡፡ እኔ ውስጡ ያለውን ደብዳቤ ከወሰድኩ ምን ያደርግልኛል ብዬ ነበር፡፡ በሽቄ ወደ ቤት ገባሁ፡፡ በንዴት መጽሐፉን ማንበብ ጀመርኩ ያቺ እናቴ ስምንት ሰዓት ከእንቅልፍ ነቅታ መብራቱን አጥፋልኝ ብላ እስክታስገድደኝ ድረስ 55 ገጾችን አንብቤ ነበር፡፡ ይሄ ለእኔ ሪከርድ ነው፡፡ በአንዱ ቀን ያውም ያለ ማቋረጥ 55 ገጽ ማንበብ . . .
በአንዱ ለሊት የምሁርነት መንፈስ ተፅናወተኝ›› ክፍል ስድስት እንዲደርሳችሁ ከታች ያሉትን ስቴፖች ይከተሉ
1ፖስቱን ላይክ ያድርጉ
2ሼር
3part6 ኮመንት ላይ