Sle Anebebnachew Metsaft Enawra

Sle Anebebnachew Metsaft Enawra Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Sle Anebebnachew Metsaft Enawra, Addis Ababa.

02/09/2023

Best picture

02/09/2023

Oromia-My Country

05/02/2023
20/01/2023

✨የሳምንቱ ምርጥ ምርጥ አባባሎች✨
🇪🇹 አመራር በጉልበት ሳይሆን በጥበብ ነው

1⃣📍ሰዎች የሚያስቡትን ለማወቅ ከሚናገሩት ይልቅ የሚያደርጉትን አስተዉል።

2⃣📍ተፈጥሮ፣ ጊዜና ትዕግስት ሶስት ታላላቅ ሐኪሞች ናቸው።

3⃣📍ፍቅር፣ ገንዘብና ህመም ሚስጥር ሆነው መቆየት
አይችሉም፤ በፍጥነት ራሳቸው

4⃣📍እውነት ጫማውን እስከምታጠልቅ ድረስ ሃሰት በፍጥነት
ታዛመታለች።

5⃣📍ከፊትህ ስላለው መንገድ ለማወቅ በመንገዱ ያለፉትን ጠይቅ።

6⃣📍ጎረቤቶችህ እነማን እንደሆኑ ሳታውቅ ቤት አትግዛ።

7⃣📍ፀሓይ የምትወጣው ለሁሉ ነው።

8⃣📍ፀጥ ያለ ባህር አዞ የለውም ብለህ አታስብ።

9⃣📍ውድቀት ከባድ ቢሆንም ለመነሳት አለመሞከር ደሞ የከፋ ነው።

🔟📍 በጨለማ ሁሉም ቀለሞች አንድ ናቸው።

🌟የትኛው አባባል ተመቻችሁ🌟

💫Lik€~comment💫
Share
ሸር

05/01/2023

የሞት ፍርድ ያስቀረው ሀኪም መኖሪያ ቤት
===
ሰዎች ወደ አዲስ ቦታ ሲሄዱ እንደየዝንባሌያቸው መጎብኘት የሚፈልጓቸው ቦታቸው አሉ። ወደ ለንደን ከተማ ስሄድ የሞት ፍርድ ያስቀረውን ሀኪም መኖሪያ ቤት ለመጎብኘት ወስኜ ነበር። ቀኑ በረዷማ ቢሆንም፣ ቦታው ራቅ ያለ ቢሆንም በ1923 በህክምና የኖቤል ሽልማትን ያገኘው ሀኪም ቤት ተገኘሁ።

በ1920 ዶ/ር ፍሬድሪክ ባንቲንግ ለተማሪዎቹ 'ሌክቸር' ሲያዘጋጅ ስለ ጣፊያ ብዙ መፅሀፍት አነበበ። በዚን ጊዜ ስለ ስኳር ህመም የሚታወቀው ሳይንስ ስለ ምልክቶቹና ስለሚያስከትለው ጉዳት ብቻ ነው እንጂ ስለህክምናው ምንም የሚታወቅ ነገር አልነበረም። ስለዚህ በዛን ዘመን በልጅነት የሚጀምር የስኳር ህመም (Type I Diabetes) የተገኘበት ሰው የሞት ፍርድ እንደተፈረደበት ሰው ያለው እድል በወራት እድሜ እስከሚሞት ቀኑን መቁጠር ነበረ። ዶ/ር ባንቲንግ ለተማሪዎቹ የሚያስተምረውን እያብሰለሰለ ወደ አልጋው ይሄዳል። ነገር ግን እንቅልፍ እንቢ አለው። ድንገት አንድ ሀሳብ መጣለት እና ከአልጋው ላይ ተፈናጥሮ ተነሳ።

"ከሰውነት ውጭ ኢንሱሊን ማምረት ቢቻል የስኳር ህመምን ማከም ይቻላል" ብሎ አሰበ። ከዛ ምርምር ማድረግ ጀመረ። ምርምሩ ተሳካለትና የሞት ፍርድ ይመስል የነበረውን ሁኔታ ወደ ሚታከም ህመም ለወጠው። የፋርማሲ ፋብሪካዎች አዲሱን ግኝት በብዙ ሚሊየን ብሮች ገዝተው ባለቤትነቱን እንዲያዛውርላቸው ለመኑት፤ አስለመኑት። ዶ/ር ባንቲንግ ግን "ያገኘሁት ግኝት እንደሸቀጥ እንዲሸጥ ሳይሆን ሁሉም የአለም ዜጎች እንዲጠቀሙበት ነው።" ብሎ የባለቤትነት ፈቃዱን ለህዝብ ሰጠ። የፋርማሲ ባለንብረቶች ግን "የመድሀኒት ባለቤትነትን መሸጥ ነው እንጂ በነፃ ማስተላለፍ አይቻልም!" ብለው አስቸገሩ።
ዶ/ር ባንቲንግ "እንግዲያውስ ለህዝቡ በአንድ ዶላር ሸጨዋለሁ።" ብሎ አሳልፎ ሰጠ።

ለንደን ኦንታሪዮ የሚገኘው የዶ/ር ባንቲንግ መኖሪያ ቤት አሁን ሙዚየም ሆኗል። አስጎብኚዎቹ ወደ ስልሳዎቹ የሚጠጉ የነፃ አገልግሎት የሚሰጡ የስኳር ህመም መድሀኒት የሚወስዱ ሴቶች ነበሩ። የዶ/ር ባንቲንግ አልጋ፣ ምርምር የሰራበት ማክሮስኮፕ፣ መድሀኒት የቀመመባቸው ብልቃጦች አሉ። እንደነገሩኝ እራሳቸው ወይም ቤተሰባቸው የስኳር ህመም ያለባቸው ሰዎች ከአለም ዙሪያ ለመጎብኘት ይመጣሉ።

ጉብኝቴን ጨርሼ ስወጣ ስለ አእምሮ ህክምና ማሰብ ጀመርኩ። አንዳንድ የአእምሮ ህመሞች ዛሬ ባለው ሳይንስ ውጤታማ ህክምና የላቸውም። ለአንዳንዶቹ ህመሞች የሚሰጡት መድሀኒቶች የጎንዮሽ ጉዳቶች አላቸው። ነገ ግን የተሻለ መድሀኒት ይመጣል። ዛሬ አይታከምም የተባሉት ነገሮች ነገ ይታከማሉ።

ያለ አእምሮ ጤና፤ ጤና የለም!
ዶ/ር ዮናስ ላቀው

03/01/2023
31/12/2022

https://youtu.be/FJNyz01_16A Teddy Yo is a well known Ethiopian singer and song writer whose music is contemporary and able to attract the youth. Last

Address

Addis Ababa

Telephone

+251919808899

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Sle Anebebnachew Metsaft Enawra posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Sle Anebebnachew Metsaft Enawra:

Shortcuts

Share