21/09/2026
ዑምራ በኢስላም በግንባር ቀደምትነት ከሚከናወኑ የአምልኮ ሥርዓቶች አንዱ ሲሆን፣ በመካ በሚገኘው በመስጂዱል ሀራም ውስጥ የሚፈጸም የኢባዳ ዓይነት ነው። ትንሿ ሐጅ በመባልም ይታወቃል።
ዋና ዋና ምሰሶዎች
• ኢሕራም: ከሚቃት ወሰን ሲደርሱ የንጽህና ዝግጅት አድርጎ ኒያ ማድረግ።
• ጦዋፍ: ካዕባን ሰባት ጊዜ መዞር።
• ሰዕይ: በሶፋ እና በመርዋ መካከል ሰባት ጊዜ መመላለስ።
እንዲሁም ጸጉርን መላጨት ወይም ማሳጠር ሥርዓቱን ያጠናቅቃል።
ትሩፋት:
• ኃጢአትን ያስተሰርያል።
• ድህነትን ያስወግዳል።
• የአላህ እንግዳ ያስብላል።
በዓመቱ በማንኛውም ጊዜ መፈጸም የሚቻል ሲሆን፣ በረመዳን ወር የሚደረግ ዑምራ ከነቢዩ ጋር ከተደረገ ሐጂ ጋር እኩል ዋጋ እንዳለው ይገለጻል።
#ዑምራ #ሙስሊም #ኡስታዝኑሩቱርኪ😊 #መካ TURKI