ETH Addis

ETH Addis Entertainment

26/01/2026
26/01/2026
26/01/2026
26/01/2026
Who scored this goal? 🏃‍♂️
17/07/2025

Who scored this goal? 🏃‍♂️

ከ3 ባንኮች 41 ሚሊዮን ብር መዘረፉ ተሰማ‼በአማራ ከልል ሰሜን ሸዋ ዞን ጣርማበር ወረዳ መዘዞ ንዑስ ወረዳ በትላንትናዉ እለት  ከሌሊቱ 7 ሰዓት ላይ ከ3 ባንኮች ከ41 ሚሊዮን ብር በላይ ...
17/07/2025

ከ3 ባንኮች 41 ሚሊዮን ብር መዘረፉ ተሰማ‼

በአማራ ከልል ሰሜን ሸዋ ዞን ጣርማበር ወረዳ መዘዞ ንዑስ ወረዳ በትላንትናዉ እለት ከሌሊቱ 7 ሰዓት ላይ ከ3 ባንኮች ከ41 ሚሊዮን ብር በላይ በታጠቁ ሀይሎች አንደተወሰደ ታውቋል።

በንዑስ ወረዳዉ ከሚገኙ
📌 ከቡና ባንክ 11ሚሊዬን 550ሺህ ብር፣
📌ከፀዳይ ባንክ 1ሚሊዬን 28ሺህ ብር እንዲሁም
📌ከአባይ ባንክ 29 ሚሊዬን 365ሺህ ብር በአጠቃላይ 41ሚሊዬን 943 ሺህ ብር መወሰዱን ወረዳው አሳውቋል።
#ዜና

 #ግብር        #ዜና     የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤቱም የገቢ ግብር ማሻሻያ አዋጅን በ5 ተቃውሞ፣ በ12 ድምጸ ተዓቅቦ በአብላጫ ድምጽ ነው ያፀደቀው።በሕዝብ ተወካዮች ምር ቤት የፕላን...
17/07/2025

#ግብር #ዜና

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤቱም የገቢ ግብር ማሻሻያ አዋጅን በ5 ተቃውሞ፣ በ12 ድምጸ ተዓቅቦ በአብላጫ ድምጽ ነው ያፀደቀው።

በሕዝብ ተወካዮች ምር ቤት የፕላን፣ በጀት እና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ደሳለኝ ወዳጄ የገቢ ግብር አዋጅ ማሻሻያው ከግብር ነጻ የሆነው ከመቀጠር የሚገኘ ገቢ ከፍ እንዲል የተደረገ በመሆኑ ፦
- ዝቅተኛ ገቢ ባላቸው ተቀጣሪዎች ላይ የግብር ጫናው እንደሚቀንስ፤
- የግብር መሰረቱ እንዲሰፋ፤
- መንግስት ከገቢ ግብር የሚያገኘው ገቢ በአንጻራዊ ሁኔታ ከፍ እንዲል አጋዥ መሆኑን አመልክተዋል።

በማሻሻያው ላይ ከበርካታ ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት እንደተደረገበት እና እንደ ቋሚ ኮሚቴም ሰፊ ጊዜ ተወስዶበት የተዘጋጀ ማሻሻያ ነው ብለዋል።

የገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር እዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) በበኩላቸው፣ " ማሻሻያው ለረጅም ጊዜ ውይይት የተደረሀበት እና የሀገራት ልምድ የተወሰደበት ነው። ማሻሻያው ዘመኑን የዋጀ ነው " ሲሉ ተናገረዋል።

አዋጁን የተቃወሙ የምክር ቤት አባላት የገቢ ግብር ማሻሻያው የመንግስት ሠራተኛውን የኑሮ ሁኔታ ታሳቢ ያላደረገ ማሻሻያ በመሆኑ ምክር ቤቱ ማሻሻያውን በድጋሚ እንዲፈትሸው ጠይቀዋል፡፡

የገቢ ግብር አዋጁ ከዚህ ቀደም ሰፊ የክርክር ነጥቦች የተነሳባቸው ጉዳዮች ላይ ማስተካከያ ሳይደረግበት ነው በ5 ተቃውሞ ፣ በ12 ድምጸ ተዓቅዶ በአብላጫ ድምጽ የፀደቀው።

🇪🇹


ትላንት ምሽት 1:52 መቀሌ የደረሰ አውሮፕላን መጠነኛ ጉዳት እንደደረሰበት ታውቋል።ከአዲስ አበባ ወደ መቀሌ በረራ ያደረገው አውሮፕላን ምሽት 1:52ሰዓት አሉላ አባነጋ ኤርፖርት የደረሰው 2...
17/07/2025

ትላንት ምሽት 1:52 መቀሌ የደረሰ አውሮፕላን መጠነኛ ጉዳት እንደደረሰበት ታውቋል።

ከአዲስ አበባ ወደ መቀሌ በረራ ያደረገው አውሮፕላን ምሽት 1:52ሰዓት አሉላ አባነጋ ኤርፖርት የደረሰው 2 አብራሪዎች እና ሁለት የበረራ አስተናጋጅ 49 ተጓዥ መንገደኞችን ይዞ ሲሆን ለማረፍ ጥቂት ደቂቃዎች ሲቀሩት በአውሮፕላኑ የቀኝ ክንፍ ላይ ቀላል አደጋ እንደደረሰበት ታውቋል።የአይን እማኞች በሰው ላይ የደረሰ አደጋ የለም ብለዋል።

የግብርና ምርቶችን ጨምሮ በተለያዩ የፍጆታ ሸቀጦች ላይ የሚታየው የዋጋ ንረት ገንዘቦችን ከጥቅም ውጭ እያደረጋቸው ይገኛል ተባለ  | በኢትዮጵያ የግብርና ምርቶችን ጨምሮ በተለያዩ የፍጆታ ሸቀ...
17/07/2025

የግብርና ምርቶችን ጨምሮ በተለያዩ የፍጆታ ሸቀጦች ላይ የሚታየው የዋጋ ንረት ገንዘቦችን ከጥቅም ውጭ እያደረጋቸው ይገኛል ተባለ

| በኢትዮጵያ የግብርና ምርቶችን ጨምሮ በተለያዩ የፍጆታ ሸቀጦች ላይ የሚታየው የዋጋ ንረት የገንዘቦችን የመግዛት አቅም እየተፈታተነና አንዳንዶቹንም የመገበያያ ገንዘቦች ከጥቅም ውጭ እያደረጋቸው መሆኑ ተገልጿል፡፡

የፋይናስና የኢንቨስትመንት ባለሙያው አቶ ይርጋ ተስፋዬ ከኢትዮ ኤፍ ኤም ጋር በነበራቸው ቆይታ ፤አሁንላይ በሳንቲሞች የሚሸመቱ ቁሶች ከጠፉ ሰነባብተዋል ብለዋል፡፡

ከአምስ እስከ ሃምሳ ሳንቲም ያሉ የመገበያያ ገንዘቦችም ከገበያ ወጥተዋል ማለት ይቻላልም ነው ያሉት፡፡

አቶ ይርጋ ገንዘቦቹ እየጠፉ ለመምጣታቸው ምክንያቱ የምርቶች ዋጋ መናር ነው ያሉ ሲሆን፤ ፍላጎትና አቅርቦትን ማቀራረብ አንዱ የዋጋ ንረትን ለመቆጣጠር የሚያስችል ዘዴ ነው ሲሉም ተናግረዋል ፡፡

ሌላኛው ጣቢያችን ያነጋገራቸው የፋይናስ ባለሙያው አቶ ጋማቹ ብረሃኑ፤የኢትዮጵያን የገንዘብ የመግዛት አቅም ማሳደግ እስካልተቻለ ድረስ ገንዘቦቻችን ላይ ቁጥር እየጨመርን ነው የምኔደው ብለዋል።

ይህ እንዳይሆን ከወዲሁ ወደ ሀገር ውስጥ የሚገባውን ምርት መቀነስና የሀገር ውስጥ ምርትን ማሳደግ ይገባል ሲሉ ገልፀዋል።

የመሰረታዊ ሸቀጦችና አገልግሎቶች ዋጋ ንረት በዚህ የሚቀጥል ከሆነ አሁን ባሉት ገንዘቦቻችን ብዙ ጊዜ መቆት እንደ ማይቻልም አንስተዋል።

ይሄ ደግሞ እንደሌሎች ሃገራት የራስን ገንዘብ ከአገልግሎት አውጥቶ ዶላርን ወደ ማስገባት ያመራል ይህ ሁኔታ ደግሞ በመጨረሻ ሉአላዊነትን እስከመፈታተን ያደርሳል ሲሉ ጣቢያችን ያነጋገራቸው የፋይናስ ባለሙያዎች አሳስበዋል፡፡

የአሜሪካ መንግስት፣ በሀገሪቱ በከባድ ወንጀሎች ተፈርዶባቸው የነበሩና ዜግነት የሌላቸውን ስደተኞች፣ ወደ ደቡብ አፍሪካዊቷ ትንሽ ሀገር ኤስዋቲኒ (የቀድሞዋ ስዋዚላንድ) ማባረር ጀመረ  | ይህ...
17/07/2025

የአሜሪካ መንግስት፣ በሀገሪቱ በከባድ ወንጀሎች ተፈርዶባቸው የነበሩና ዜግነት የሌላቸውን ስደተኞች፣ ወደ ደቡብ አፍሪካዊቷ ትንሽ ሀገር ኤስዋቲኒ (የቀድሞዋ ስዋዚላንድ) ማባረር ጀመረ

| ይህ አዲስ ፖሊሲ፣ በአሜሪካ ውስጥ ከፍተኛ ውዝግብና የሰብዓዊ መብት ጥያቄዎችን ያስነሳ ሲሆን፣ አስተዳደሩ ከዚህ ቀደም ታይቶ የማይታወቅ የኢሚግሬሽን እርምጃ እየወሰደ መሆኑን ያመላክታል ተብሏል።

እንደ ዛሬው ሲቢኤስ ኒውስ ዘገባ፣ ይህ እርምጃ ዒላማ ያደረገው በአሜሪካ ውስጥ በህጋዊ መንገድ የመኖር ፈቃድ ኖሯቸው ነገር ግን በከባድ ወንጀሎች የተፈረደባቸውን ስደተኞች ነው። የፖሊሲው አወዛጋቢነት የሚጀምረው፣ እነዚህ ተባራሪዎች የኤስዋቲኒ ዜጎች ባለመሆናቸው ነው።

በአዲሱ የ"ሶስተኛ ሀገር" ስምምነት መሰረት፣ የኤስዋቲኒ መንግስት እነዚህን ተባራሪዎች የራሱ ዜጎች ባይሆኑም እንኳ ለመቀበል ተስማምቷል። ይህም አሜሪካ፣ የገዛ ሀገራቸው ሊቀበላቸው ፈቃደኛ ያልሆኑ ወንጀለኞችን የምታስወግድበት አዲስ አማራጭ ሆኖላታል።

የአሜሪካ የሀገር ውስጥ ጸጥታ ጥበቃ መምሪያ (DHS) በሰጠው መግለጫ፣ "ይህ ፖሊሲ አደገኛ ወንጀለኞችን ከአሜሪካ ማህበረሰብ ለማስወገድና የሀገርን ደህንነት ለማስጠበቅ ወሳኝ ነው" ብሏል።

በሌላ በኩል፣ የስደተኞች መብት ተሟጋች ድርጅቶች እርምጃውን በጽኑ አውግዘውታል። "ይህ ፖሊሲ ኢ-ሰብዓዊ ከመሆኑም በላይ፣ አሜሪካ የራሷን ችግር ወደ አንዲት ትንሽ የአፍሪካ ሀገር 'እንደቆሻሻ መጣል' ነው" ሲሉ ተችተዋል። ድርጅቶቹ፣ ይህ አካሄድ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ህግጋትን የሚጥስ ሊሆን እንደሚችልም ስጋታቸውን ገልጸዋል።

የኤስዋቲኒ መንግስት ለምን ይህንን አወዛጋቢ ስምምነት ለማድረግ እንደተስማማ የተሰጠ ዝርዝር መግለጫ የለም። ነገር ግን አንዳንድ ተንታኞች፣ ከስምምነቱ ጀርባ ከአሜሪካ የሚገኝ ከፍተኛ የገንዘብ ድጋፍ ወይም ሌላ የዲፕሎማሲያዊ ማበረታቻ ሊኖር እንደሚችል ይገምታሉ።

ይህ የትራምፕ አስተዳደር አዲስ ፖሊሲ፣ በኢሚግሬሽን ህግጋት አፈጻጸም ላይ የተደረገ ከፍተኛ ለውጥ ሲሆን፣ በቀጣይ ቀናት ተጨማሪ ውይይቶችንና ክርክሮችን እንደሚያስነሳ ይጠበቃል።

በአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ የመጀመርያ ሜዳልያዋን አገኝች  | በናይጄሪያ ዛሬ መካሄድ በጀመረው የአፍሪካ ከ20 እና ከ18 ዓመት በታች የአትሌቲከስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ የብር እና ...
17/07/2025

በአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ የመጀመርያ ሜዳልያዋን አገኝች

| በናይጄሪያ ዛሬ መካሄድ በጀመረው የአፍሪካ ከ20 እና ከ18 ዓመት በታች የአትሌቲከስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ የብር እና የነሃስ ሜዳልያ አግኝታለች፡፡

በሴቶች ከ18 አመት በታች 1500 ሜትር ፍጻሜ አትሌት ኤልሳቤጥ አማረ 2ኛ ስትወጣ ደስታ ታደለ 3ኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች፡፡

በተመሳሳይ ርቀት በወንዶች ከ18 አመት በታች ደግሞ አትሌት ሳሙኤል ገ/ሃዋርያ 3ኛ በመውጣት የነሀስ ሜዳል ባለቤት ሆኗል፡፡

በአንተነህ ሲሳይ

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ETH Addis posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share