15/07/2025
ታሪካችንን እናካፍላችሁ፣ እነዚህ በሁለት ቋንቋ የተፃፋ የልጆች መፃህፍት አሁን ገበያ ላይ ይገኛሉ።
ይህ የአመታት ህልም እውን እንዲሆን የተለያዩ ኢትዬጵያውያን ፃህፍት አስተዋፅኦቸውን አበርክተውበታል። እነዚህ በሁለት ቋንቋ የተፃፋት የልጆች መፃህፍት የሀገራችን ኢትዬጵያን ሰፊ ባህል ፣ እሴቶች እና የእስተሳሰብ ውቅር ይዳስሳሉ።
እነዚህ መፃህፍት እንደ ተረት ብቻ የተፃፋ አይደሉም። ለሁሉም ወላጅ በተለይ ደግሞ ከሀገራቸው እና ባህላቸው ርቀው ላሉ ወላጆች ፣ የኢትዮጵያዊነትን የበለፀገ ባህል በልጆቻችን ለማስረፅ እንድንችል የቀረበ ስጦታ ነው።
1. የዳዊት ህልም ሰማይ
የመፅሀፍ ታሪክ የሚያጠነጥነው በአንድ የዘጠኝ ዓመት ታዳጊ ህይወት ነው። ዳዊት ይባላል የአእምሮ ሳይንስ ተመራማሪ እና የጠፈር ሳይንስ መሀንዲስ መሆንን ያልማል። አዲስ አበባ ዙሪያ ከሚገኙት ከፍታ ቦታዎች ላይ ነው ያደገው። ወላጆቹ የሚነግሩትን መሳጭ ታሪኮች እና ከኢትዬጵያ ሰማይ ላይ የሚሆኑትን ክስተቶች በቅርበት እያየ በዚህ ውስጥ ወደፊቱን ያቅዳል።
ዳዊት በእነዚህ 36 ውብ ገፆች ውስጥ ራሱን ከምድር ከፍ አድርጎ ከክዋክብት እና ሮኬቶች ጋር ራሱን ያልማል። ስለሀገሩ፣ ስለማነቱ እንዲሁም ስለ ውደፊት እጣፈንታው ፍንትው ባለ ስዕል ያልማል።
👉 የዳዊት ህልም ሰማይ መፅሀፍን አሁኑኑ ከአማዞን ድረ ገፅ ላይ ይዘዙ።
https://www.amazon.com/dp/B0FH8ZC917
🌿 2.አቢ እና ትልቁ የቡና ዛፍ
ይህ ታሪክ አንባቢን ወደ አንድ ጥንታዊ የኢትዬጵያ የቡና ጫካ ይወስዳል። በዛም አቢ የተባለ ልጅ ከአንድ ጥበበኛ የቡና ዛፍ ጋር የሚኖረውን ውሎ እናያለን ። ይህ ተአምረኛ የቡና ዛፍ እንዴት ተረት እንደሚያወራ እና በቅጠሎቹም እንደሚዘምር እያየን ከተፈጥሮ ጋር እንዴት መቆራኘት እንደሚገባን እንዲሁም ደግሞ ተፍጥሮንም ሆነ ቤተሰባችንን እንዴት ማዳመጥ እንደሚገባን እየነገረን የደግነትንም ዋጋ ያስተምረናል።
👉 አቢ እና ትልቁ የቡና ዛፍ መፅሀፍን አሁኑኑ ከአማዞን ድረ ገፅ ላይ ይዘዙ።
https://www.amazon.com/dp/B0FGYFDY7J
እነዚህ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተፃፋ ታሪኮች የተፃፋት ከድንግል ኢትዮጵያዊ ታሪኮች በመነሳት ሲሆን ልጆቻችን ባሉበት ሆነው የኢትዮጵያዊነትን ስሜት ያጣጥማሉ።
እነዚህ መፃህፍት ተራ ገፆችን የተሸከሙ አይደሉም። ልጆቻችን ባህላቸውን እና እና የጥልቅ አስተሳሰብ ባለቤትነታቸውን ትተው በባእድ ባህል እንዳይጠለፋ ድልድይ በመሆን፣ ቋንቋቸውን ሳይ ተው አርቆ የማለም ጥበብን በውስጣቸው ለማኖር ታቅዶ የተፃፈ ነው።
💡እነዚህ መፃህፍት ለማን ናቸው፣
* የሀገራቸውን ባህል እና እሴት ለልጆቻቸው ለማስተዋወቅ ለሚፈልጉ በውጭ ሀገር ለሚኖሩ ወላጆች
* የእማርኛ ቋንቋ ችሎታቸውን ለሚያሻሽሉ ልጆች
* በትምህርት ቤቶች ውስጥ አፍሪካዊ ተረቶችን ለሚያስተምሩ መምህራን እና ተማሪዎች
* እነሳሽ እና እነቃቂ ተረቶችን ለሚጠቀሙ ወላጆች
📚 ሁሉም መፃህፍት በ አማዞን ድረ ገፅ ወይም መተግበሪያ ላይ ይገኛሉ።
መነሻቸውን የሚያውቁ ልጆች እና ትውልድ በጋራ እንገንባ። ራዕያችንን ለማሳካት በምናደርገው ጉዞ ላይ ከጎናችን በመቆምዎ እናመሰግናለን።
#አማርኛናእንግሊዝኛ