Holy Quran ቅዱስ ቁርአን

Holy Quran ቅዱስ ቁርአን ይህ ኢስላማዊ የፌስቡክ ገጽ ቅዱስ ቁርአንን ለሙስሊሙ ማህበረ

ያ አላህ በጎ የምንሰራ  አድርገን::አሚን!SHARE«በጎ ሥራንም ሥሩ፤ አላህ በጎ ሠሪዎችን ይወዳልና፡፡» አል-በቀራህ 195https://www.facebook.com/EthioQuran
11/09/2019

ያ አላህ በጎ የምንሰራ አድርገን::
አሚን!
SHARE
«በጎ ሥራንም ሥሩ፤ አላህ በጎ ሠሪዎችን ይወዳልና፡፡» አል-በቀራህ 195
https://www.facebook.com/EthioQuran

—————————ደስታውን ጋብ አድርገን የተሳሳቱ ትርክቶችን እናርም! —————————  ረቡዕ ምሽት በሚሌኒየም አዳራሽ በተካሄደው ታላቅ የአፍጥር ግብዣም ሆነ ቀደም ብሎ በነበሩት ሂደቶች የትር...
25/05/2019

—————————
ደስታውን ጋብ አድርገን የተሳሳቱ ትርክቶችን እናርም!
—————————
ረቡዕ ምሽት በሚሌኒየም አዳራሽ በተካሄደው ታላቅ የአፍጥር ግብዣም ሆነ ቀደም ብሎ በነበሩት ሂደቶች የትርክት ስህተት መፈጠሩ ግልጽ ሆኗል። Akemel ከትናንት ወዲያ ጥሩ ማስታወሻ አስነብቦናል። Moonirahም በጉዳዩ ላይ ጽፋለች። ሌሎች ጽሑፎችንም አይቻለሁ። በእርግጥም የትርክት ስህተት ተፈጥሯልና አጥርቶ መሄድ ተገቢ ነው። አጫጭር እውነታዎችን እናስቀምጥ እስቲ...
———
እውነታ ❶
ለ7 ዓመታት የታገልነው የመንግሥትን ጣልቃ ገብነት ነው!
———
የድምፃችን ይሰማ ሠላማዊ ትግል ዓላማ በዋነኝነት የመንግሥትን በሃይማኖት ጣልቃ ገብነት መቃወም ነው። በመዝሃቦች መካከል የተደረገ ጸብ አልነበረም። ሆኖም አያውቅም። መንግሥት ከሊባኖስ አንድ በጥባጭ አንጃ አስመጥቶ በግድ ሥልጠና መስጠት እና መስጊዶችን መቀማት በመጀመሩ ያንን አስገድዶ ጠመቃ በመቃወም የተደረገ ትግል ነው። ጸባችን ከእነ ዶ/ር ሽፈራው እና በመጅሊስ ግቢ ካስቀመጧቸው አሻንጉሊቶቻቸው ጋር እንጂ እርስ በእርስ አልነበረም።
———
እውነታ ❷
መጅሊስን የታገልነው ሙሰኛ፣ ከፋፋይ እና የመንግሥት ዕኩይ ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ ስለሆነ ነው!
———
«አሽ‐ሸዕብ ዩሪድ ኢስቃጠል መጅሊስ! (ሕዝቡ መጅሊሱ እንዲወርድ ይፈልጋል!)» በሚል መፈክር ለዓመታት የታገልነው ከመጅሊሱ ጋር የመዝሃብ ጸብ ኖሮን አልነበረም። የመጅሊሱ መዝሃብ «ሣሪቂያ» (ሙሰኝነት) ነበር። ያልመረጥናቸው አመራሮች «መሪ» ተብለው ተቀምጠው ዘረፉን። መብታችንን አስነጠቁን። ተቋማቶቻችንን አስዘጉብን። መንግሥት ከሊባኖስ ያመጣውን ረባሽ አንጃ መጫኛ መሣሪያ ሆኑብን። እኛም ታገልናቸው። የግልም ሆነ የመዝሃብ ጸብ አልነበረንም።
———
እውነታ ❸
ያለፉት 10 ወራት ተቋም የማስተካከል ሂደት የትግላችን መጀመሪያም መጨረሻም አይደለም!
———
ታሪካዊ እና ስኬታማ ሥራ የሠራው 9ኙ ኮሚቴ ሲቋቋም መንግሥት የ«አስታራቂ» ካባ ለብሶ መምጣቱ የተሳሳተ ትርክት ነበር። ዝም የተባለው «ለመንግሥት መውጫ መንገድ መክፈቱ አይከፋም» ከሚል ስሜት በመነጨ እንጂ ትርክቱ ትክክል በመሆኑ አልነበረም። ያም ቢሆን መንግሥት ከለውጡ ወዲህ ሲሠራ የነበረውን የዱሮ ስህተት አምኖ በግላጭ «ንስኃ ገብቻለሁ» ስላለ ብዙ መሸፋፈን አያስፈልገውም ነበር። የደስታ ስሜት ውስጥ ስለነበርን ተዘናጋን ብለን እንለፈው። ዛሬ ላይ በራሳችን አንደበት የተሳሳተ ትርክቱን ማንገሥ ግን ትልቅ ስህተት ይሆናል።
የትግል ታሪካችን በምንወደው፣ በምናከብረው እና በምናወድሰው 9ኙ ኮሚቴ አልተጀመረም። አልተጨረሰምም። ተቋሙን በማስተካከል ሂደት የተፈጠሩት መዝሃባዊ የሐሳብ ልዩነቶች የትግላችን ዋነኛ ገጽታ አልነበሩም። ይልቁንም ያለፉት 10 ወራት ክስተቶች ናቸው። በዑለሞቻችን አስተዋይነት የሠፈነው የመዝሃብ ልዩነት የማሥተዳደር ጥበብ/ስምምነትም ቢሆን ሕዝበ-ሙስሊሙን ወደማያልቅ የመዝሃብ ግጭት ለመምራት የተደረጉ የከሸፉ ሙከራዎች የፈጠሩት የ10 ወራት ውጥረት እንጂ የድምፃችን ይሰማ ሕዝባዊ ትግል ዋነኛ አጀንዳ አልነበረም። ስለዚህ የጥቅል ትግላችንን ስኬት «ዕርቅ» በሚል የትርክት ቅርጫት ውስጥ መክተት ግልጽ ያለ ስህተት ነው። መታረም አለበት።
———
እውነታ ❹
መንግሥት ላለማው ይመሠገናል... የተሳሳተ ትርክቱ ግን አይጸድቅለትም!
———
በአገሪቱ የተለያዩ ቦታዎች እየተፈጸሙ ያሉ ጥቃቶች እና የመብት ጥሰቶች እንዳሉ ሆነው የዶ/ር ዐቢይ አሕመድ መንግሥት የሕዝበ-ሙስሊሙን ተቋማዊ የመብት ጥያቄዎች ለመመለስ መልካም እርምጃዎችን እየወሰደ ነው። እስካሁን የተጓዘው ሂደት የሚያስመሠግነው ነው። ልክ እንደሌላው ማኅበረሰባችን ሁሉ የሕዝበ-ሙስሊሙ ጥቅም የአገር ጥቅም፣ የሕዝበ-ሙስሊሙ ጉዳት የአገር ጉዳት መሆኑን በመረዳት የሚወሰዱ አገር ገንቢ እርምጃዎች ሁሉ የሚያስመሠግኑ ናቸው። ይህ ሲባል ግን «አስታራቂ» ሆኖ ለመቅረብ የሚያደርገውን ጥረት እናጸድቃለን ማለት አይደለም።
ዶ/ር ዐቢይ ለግላዊም አሥተዳደራዊም ቅንነታቸው ሊመሠገኑ ይገባል። ምናልባትም በእኔ ዕድሜ የእሳቸውን ያክል በሚወስዳቸው ቆራጥ እርምጃዎች አርክቶኝ የሚያውቅ እና «መሪዬ» የምለው ፖለቲከኛ ያለ አልመሰለኝም። ግና የሕወሓት አሥተዳደር ሲፈጥር የቆየውን ቀውስ የሙስሊሙ የእርስ በእርስ ጸብ እንደሆነ አድርገው መቅረጻቸው እና «አስታራቂ» ሆነው መቅረባቸው ትክክል ሊሆን አይችልም።
እርግጥ ዶ/ር ዐቢይ ባለፉት 10 ወራት ለተፈጠሩት «መጅሊስ-መር» ልዩነቶች አስታራቂ ሚና ተጫውተዋል። ድንበር አላፊዎችንም ተቆጥተው አስታግሠዋል። ይህ በእጅጉ ያስወድሳቸዋል። የ7 ዓመት ትግላችን ግን የእርስ በእርስ ጸብ ሳይሆን ያለፈው መንግሥት ግልጽ ሃይማኖታዊ ጣልቃ-ገብነት የፈጠረው ቀውስ መሆኑን ለማመን አለመፈለግ በእርሳቸው ተክለ‐ስብዕና ካለ መሪ የሚጠበቅ አይደለም። የመንግሥት ኃላፊዎች የመጅሊሱን ሕገ-ወጥ አመራር በመጠቀም በግድ «ካላጣላናችሁ» አሉን። እኛ ደግሞ «ከነጭራሹ መጅሊሱ ላይ የምናውቃቸውና የምናምናቸው አባቶቻችን ካልተቀመጡ መስሚያ የለንም! የካድሬ ተንኮላችሁን ተዉን!» ብለን ታገልናቸው። የሆነው ይህ ነው!
———
እርማት ለማድረግ አልረፈደም!
———
በሚሌኒየም አዳራሽ የተከተልነው ትርክት የመንግሥትን ስሁት ትርክት በራሳችን አንደበት የማጽደቅ ነበር። በትልቅ አገራዊ መድረክ ይህንን ዓይነት ስህተት መሥራት የዝግጅት ማነስን እና የታሰበበት ትርክት ያለመቅረጽን ችግር ይጠቁም ይመስለኛል። መስተካከል ይችላል፤ አለበትም። ይህን መሰል ጽሑፎችን መጻፉም የማስተካከሉ አንድ አካል ነው። ሰዎቻችን በቀጥታም በጥቁምታም፣ በግልጽም በለሆሳስም የተሳሳተውን ትርክት መጠገንና ማስተካከል አለባቸው። አሊያ ግን ታሪክ ይታዘበናል!
ዶ/ር ዐቢይ በአንድ መድረክ ጋዜጠኞችን ሲመክሩ ቃል በቃል ባይሆንም «ዛሬ የሚጻፍ ዜና ነገ ታሪክ ይሆናል» ማለታቸውን አስታውሳለሁ። ትክክል ናቸው። አል-ጀዚራም በመድረኩ ያቀበልነውን የተሳሳተ ትርክት መከተሉ ጉዳዩ ችላ ሊባል እንደማይገባው የሚጠቁም ነው። በአጭር ቃል ጉዳዩ ለታሪክ የሚኖር ታማኝነት ጉዳይ ነውና በወጉ ተስተካክሎ ይጻፍ። መሪዎቻችን ይህንን የማስተካከል ኃላፊነት አለባችሁና በተለመደው አስተዋይነታችሁ እንደሚሆን እንደሚሆን አድርጉት! ሕዝባችሁ ከእናንተ ጋር ነው!
Tags: #መጅሊስ #9ኙኮሚቴ #ተቋማዊለውጥ #ዕርቅ #ሚሌኒየምኢፍጣር #አገራዊኢፍጣር
Original Picture Credit © Bright Production

24/08/2018

#ጁመዐ ሙባረክ
Mubarak
#جمعہ مبارک

Like if you agree!
21/08/2018

Like if you agree!

14/08/2018

( مَنْ عَمِلَ صَالِحًا فَلِنَفْسِهِ ۖ وَمَنْ أَسَاءَ فَعَلَيْهَا ۗ وَمَا رَبُّكَ بِظَلَّامٍ لِلْعَبِيدِ)

" መልካም የሠራ ሰው ለነፍሱ ነው ፡፡ ያጠፋም ሰው በእርሷ ላይ ነው ፡፡ ጌታህም ለባሮቹ በዳይ አይደለም ፡፡"
[ፉሲለት 46]

ይህ ኢስላማዊ የፌስቡክ ገጽ ቅዱስ ቁርአንን ለሙስሊሙ ማህበረ

🌙🌟عيد مبارك 🌴🌴🌴تقبل الله منا ومنكم صالح الأعمال 🌴🌴🌴كل عم وأنتم بخير🌙🌟
25/06/2017

🌙🌟عيد مبارك 🌴🌴🌴تقبل الله منا ومنكم صالح الأعمال 🌴🌴🌴كل عم وأنتم بخير🌙🌟

No Racisim in ISLAM!Like ☑ Comment ☑ Share ☑
25/04/2017

No Racisim in ISLAM!

Like ☑ Comment ☑ Share ☑

በሙስተቅበል የደም ልገሳ ፕሮግራም ላይ ተሳተፉ!
25/04/2017

በሙስተቅበል የደም ልገሳ ፕሮግራም ላይ ተሳተፉ!

በአላህ ላይ ተመካ!
25/04/2017

በአላህ ላይ ተመካ!

Eid Mubarek!Jaabir(RadiAllah Anhu) said: the Messenger of Allaah [ﷺ] said:❝Pilgrims for Hajj and Umrah are the delegates...
12/09/2016

Eid Mubarek!

Jaabir(RadiAllah Anhu) said: the Messenger of Allaah [ﷺ] said:
❝Pilgrims for Hajj and Umrah are the delegates of Allaah. He called them and they responded, they asked of Him and He gave them.❞
[Silsilah Ahadeeth As-Saheehah of Shaykh Al-Albaani, (No. 1820) | Translated By Abbas Abu Yahya Miraath al-Anbiyya]

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Holy Quran ቅዱስ ቁርአን posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share