11/01/2026
"የንግግር ጥበብ"
Dale Carnegie
The art of public speaking
ትኩረት - ለራስ አንደበት
የፈረስ ኮቴ ጫማ ሠሪዎች ለፈረሱ ጫማ በሚሠሩ ጊዜ ፈረሱ ላይ ትንሽ
የህመም ስሜት ይፈጠራል። ፈረሱ እዚህ የህመም ስሜት ላይ ትኩረት እንዳይሰጥ ለማድረግ የፈረሱ አፍንጫ ላይ ገመድ ጠበቅ አድርገው ያስራሉ። ከብርጭቆ ውስጥ ያለውን አየር የማስወጪያ አንዱ መንገድ ብርጭቆው
ውስጥ ውኃ መቅዳት ነው። ንግግር በምታደርጉ ጊዜ የፈረስ ኮቴ ጫማ ሠሪውን መርህ ተከተሉ። በንግግራችሁ ጉዳይ ላይ በጥልቀት ትኩረትን
የምትሰጡ ከሆነ ሌላ ነገርን የማሰብ እድላችሁ ያነሰ ይሆናል። ትኩረት እርባና ከሌላቸው ወይም ከማይጠቅሙ ጉዳዮች የመገላገያ መንገድ
ነው። ንግግር ለማድረግ መድረክ ላይ ከወጣችሁ በኋላ ስለ ኮታችሁ እጥፋት ማሰብ የረፈደ ጉዳይ ነው። ስለዚህ ልትናገሩት ባለው ጉዳይ ላይ ብቻ
ትኩረት አድርጉ። ብርጭቆውን በውኃ እንደመሙላት ባለ ሁኔታ አእምሯችሁን በምትናገሩት ነጥብ ቃላት ብቻ ሙሉት። ይህም አላስፈላጊ ፍርሃቶችን ያስወግድላችኋል።
ዓይን-አፋርነት በራስ ዙሪያ ገባ ላይ የሚደረግ ከመጠን ያለፈ ትኩረት ነው። ለነጻነታችሁ ሲባል ዋናው ጉዳያችሁ ንግግራችሁ እንጂ እናንተ ስለ ራሳችሁ ወይም ታዳሚው ስለ እናንተ ያለው አስተያየት አይደለም። እዚህ ጋ “ራስ”
የሚባለው ነገር ተቀጥላ እንጂ ዋና ጉዳያችሁ ሊሆን አይገባም።
ብልህ ከሆናችሁ ውስጣችሁን ሁኑ። በንግግር ጊዜ ታላቁ ጉዳያችሁ ንግግራችሁ እያለ አእምሯችሁን በ “ምን ይሉኛል?” ሐሳቦች መሙላት ሙሉ በሙሉ የተሳሳተ ራስ ወዳድነት ነው። እውነት ለእናንተ ለራሳችሁ
ኮስተር ያለ ነገርን በመናገር ዓይን-አፋርነታችሁን እንዲወገድ ያደርገዋል። ትያትር ቤቱ በእሳት ቢያያዝ ወደ መድረኩ በጥድፊያ በመሄድ ያለ አንዳች ዓይን-አፋርነት እና ፍርሃት ለታዳሚው ከአዳራሹ የመውጫ አቅጣጫዎችን
በማሣየት ትጮኻላችሁ። የምትናገሩት ነገር ሁሉንም ፍርሃቶች ከአእምሯችሁ ጠራርጎ ያስወግዳቸዋል። አንድን ነገር በጥሩ ሁኔታ ልከውነው እችላለሁን የሚለው ግምት
ከሚያመጣው ዓይን-አፋርነት ይልቅ - በማይረባ ሁኔታ ላደርገው እችል ይሆን? በሚለው ፍርሃት ውስጥ ያለ ዓይን-አፋርነት የበለጠ መጥፎ ነው።
የታላቅነት የመጀመሪያው ምልክት ታላቅ መስሎ አለመተወን ነው።
ኪፕሊንግ ራሳችሁን ከናካቴው “ሰው” ብላችሁ መጥራት ከመቻላችሁ በፊት
“በጣም አምራችሁ አትታዩ፤ በጣም ብስለት በተሞላበት ሁኔታ አትናገሩ”
ሲል ያረጋግጥልናል። ማንም በመታበይ ራሱን ታዋቂ ማድረግ አይችልም። የምትናገሩት ይኑራችሁ በብዙ ተናጋሪዎች ላይ ያለው ችግር ባልተዘጋጀ አእምሯቸው በታዳሚው
ፊት መቆማቸው ነው። ተፈጥሮ ባዶ ነገርን መጥላቷ ደግሞ ምንም አያስደምም፤ ስለሆነም ተፈጥሮ እንደዚህ ዓይነት ሰዎችን በጣም
ቅርባቸው በሆኑ ትርኪ ምርኪ ነገሮች ትሞላቸዋለች። ይህ ደግሞ በአጠቃላይ ሁኔታ ይከሰታል። “ይህንን በትክክለኛው መንገድ ማድረጌን እጠራጠራለሁ! ጸጉሬ ምን ይመስል ይሆን? እንደምወድቅ አውቃለሁ”
ከባዶነት የተነሳ ነፍሳቸውም ትክክል እንደሆኑ እርግጠኞች ያደርገቸዋል። የሚያስቡትንም ልምዳቸው ያደርጉታል። በንግግራችሁ ጉዳይ ላይ ሙሉ በሙሉ ትኩረት ማድረግ ብቻ በቂ አይደለም። በራሳችሁ እንድትተማኑ የሚያደርጋችሁ ተጨባጭ እና አውነተኛ ነገር ሊኖር ይገባል። ያለ ምንም በቂ ዝግጅት ወይም ስለምትናገሩት ጉዳይ ዕውቀት ሳይኖራችሁ
በታዳሚዎቻችሁ ፊት ብትቀርቡ የታዳሚውን ጊዜ በማባከናችሁ ማፈር ይገባችኋል። ስለሆነም ራሳችሁን አዘጋጁ። ስለምታወሩት ነገር እወቁ።
ጠቅለል ባለ ሁኔታም እንዴት እንደምትናገሩት ማወቅ ይኖርባችኋል።
የንግግራችሁን ጥቂት ዓረፍተ-ነገሮችን ሙሉ በሙሉ ተለማመዷቸው። እንደዚያ ካደረጋችሁ በንግግራችሁ መጀመሪያ ላይ ስሜቶቻችሁን ሊሸከሙ የሚችሉ ቃላት ለመፈለግ ብላችሁ ችግር ውስጥ አትገቡም። የምታወሩበትን
ጉዳይ ከታዳሚው ይልቅ እናንተ የበለጠ እወቁት፤ ስለዚህም ምንም የሚያስፈራችሁ ነገር አይኖርም