Jafer books

Jafer books ጃዕፈር መጻሕፍት

የንባብ ባህል እንዲዳብር እንተጋለን !!

ለቴሌግራም https://t.me/Jafbok

ለዌብሳይት www.jaferbooks.com

 #ታዳጊዎች መጻሕፍትን እንዴት ያንብቡ? ታዳጊዎች መጽሐፍ ሲያነቡ ዋናው ነገር ብዙ ገጽ ማንበብ ብቻ ሳይሆን፣ ያነበቡትን መረዳትና ከእሱም አዲስ ነገር መማር ነው ። ስለዚህ ታዳጊዎች በየቀኑ...
20/08/2026

#ታዳጊዎች መጻሕፍትን እንዴት ያንብቡ?

ታዳጊዎች መጽሐፍ ሲያነቡ ዋናው ነገር ብዙ ገጽ ማንበብ ብቻ ሳይሆን፣ ያነበቡትን መረዳትና ከእሱም አዲስ ነገር መማር ነው ። ስለዚህ ታዳጊዎች በየቀኑ ቢያንስ 15–30 ደቂቃ ለንባብ ጊዜ መመደብ ይጠቅማቸዋል። በመጀመሪያም የሚወዱትንና የሚስባቸውን መጽሐፍ መምረጥ አለባቸው።

በማንበብ ጊዜ የማይገባቸውን ቃላት በመፈለግ ትርጉማቸውን መረዳት፣ የሚያስደንቃቸውን ወይም ጠቃሚ የሆኑ ሐሳቦችን ማስታወሻ መያዝ በጣም አሪፍ ናው ። ከዚያ ደግሞ “ደራሲው ምን ሊያስተምረኝ ፈለገ?” ወይም “እኔ ከዚህ ታሪክ ምን ተማርኩ?” ብለው ራሳቸውን መጠየቅ ንባባቸውን የበለጠ ውጤታማ ያደርገዋል።

ከመጽሐፍ ያነበቡትን ከጓደኞቻቸው፣ ከወላጆቻቸው ወይም ከመምህራኖቻቸው ጋር መወያየትም ጥሩ የንባብ ልምድ ነው። ምክንያቱም ሐሳባቸውን ለሌሎች ሲያብራሩ ያነበቡትን በበለጠ ይገነዘባሉ።

መጽሐፍ አንብቦ መጨረስ ብቻ አይደለም፤ ማንበብ፣ መረዳት፣ ማሰብና የተማሩትን በሕይወት መተግበር ነው። ይህንን ልምድ ከልጅነት ጀምሮ የሚያዳብር ታዳጊ በትምህርቱም ሆነ በሕይወቱ የተሻለ አስተሳሰብና ሰፊ እውቀት ሊያዳብር ይችላል።

አዲስ መጽሃፍ ...ትናንት ባህር ተሻግረው ንጉሱን አጅበው ሀገር ሊያቀኑ  ወንድማማችነትን ሊያጠናክሩ ሲሄዱ የታጠቁት ጥሩር በጊዜ ብዛት ዝ ጓል አንደበታቸው ጎልድፏል አይናቸው ሞጭሙጯል። እና...
19/08/2026

አዲስ መጽሃፍ ...ትናንት ባህር ተሻግረው ንጉሱን አጅበው ሀገር ሊያቀኑ ወንድማማችነትን ሊያጠናክሩ ሲሄዱ የታጠቁት ጥሩር በጊዜ ብዛት ዝ ጓል አንደበታቸው ጎልድፏል አይናቸው ሞጭሙጯል። እናም ይምጡና የሞጨሞጨው አይናቸው እንዲጠራ አርፈው ይነሱ ጡሩራቸውን የወረረው ድር ይጠረግ የጎደለው አንደበታቸው ይሳል! የዘመኑን ትምህርት ከአባቶቻችን ጥበብ ጋር ያዋህዱትና የተራራውን ንፋስ ተመልሰው ይቆጣጠሩት! ቀስታቸውንም በዛ ይትከሉ!
ከመጽሃፉ የተወሰደ
መጽሃፉንበ መደብሮቻችን ያገኙታል

ታላቅ የመጽሐፍ ፊርማ ፕሮግራምቅዳሜ ነሐሴ 16 ከ 8 ሰዐት እስከ10 ሰዐትበ እለቱም ደራሲና ተርጓሚ ሂወት ተፈራ እና ዮርዳኖስ አልማዝ ሰይፉ የሚገኙ ይሆናል📚✨ የመጽሐፍ ፊርማ ! ✨📚🎻 የቫ...
19/08/2026

ታላቅ የመጽሐፍ ፊርማ ፕሮግራም
ቅዳሜ ነሐሴ 16 ከ 8 ሰዐት እስከ10 ሰዐት
በ እለቱም
ደራሲና ተርጓሚ ሂወት ተፈራ እና ዮርዳኖስ አልማዝ ሰይፉ
የሚገኙ ይሆናል
📚✨ የመጽሐፍ ፊርማ ! ✨📚
🎻 የቫዮሊን ዜማ…
☕ የቡና ጣዕም…
📚 የመጽሐፍ ዓለም…
በዕለቱም የፎቶና የመጽሐፍ ፊርማ ፕሮግራም ይኖረናል።

📍 ቦታ፦ ጃዕፈር መጻሕፍት – ለገሃር፣ ተወልደ ሕንጻ ስር የሚገኘው አዲሱ፣ ሰፊና ዘመናዊ መደብራችን

📖 ደራሲውን ከአንባቢው፣ መጽሐፉን ከአንባቢው ጋር ይገናኛሉ ::

ከዚህ በፊት ያካሄድናቸውን የመጽሐፍ ፊርማ ዝግጅቶች በቀጣይም አስፋፍተን እንቀጥላለን !

የመጽሐፍ ፊርማ ዝግጅት ደራሲውን ከተደራሲው፣ መጽሐፉን ከአንባቢው ጋር በትክክለኛው ቦታ፣ በክብርና በሞገስ የሚያገናኝ ድንቅ ፍኖት ነው።

ይህም አንባቢን የማፍራት፣ ደራሲን የማበረታታትና የንባብ ባህልን የማጠናከር የጃዕፈር መጻሕፍት ተልዕኮ አንዱ አካል ነው።

ጃዕፈር መጻሕፍት
የንባብ ባህል እንዲዳብር እንተጋለን!

" እቴጌ ጣይቱ እና ዳግማዊ ምኒልክ (ኢትዮጵያ 1883 - 1910 እ.ኤ.አ.) " የተሰኘው አዲስ የታሪክ መጽሐፍ ለንባብ ። ይህ መጽሐፍ ታዋቂዋ የታሪክ ተመራማሪ ክሪስ ፕራውቲ (Chris P...
18/08/2026

" እቴጌ ጣይቱ እና ዳግማዊ ምኒልክ (ኢትዮጵያ 1883 - 1910 እ.ኤ.አ.) " የተሰኘው አዲስ የታሪክ መጽሐፍ ለንባብ ።

ይህ መጽሐፍ ታዋቂዋ የታሪክ ተመራማሪ ክሪስ ፕራውቲ (Chris Prouty) በእንግሊዝኛ የጻፈችው ሲሆን፣ በሕይወት ተፈራ እና በዮርዳኖስ አልማዝ ሰይፉ ተተርጉሞ ለንባብ የበቃ ድንቅ የኢትዮጵያ ታሪክ ምስክር ነው።

ባለ 457 ገጾች ድንቅ የታሪክ ድርሳን፦

🔍 ከ1883 እስከ 1910 እ.ኤ.አ. የነበረውን የቤተመንግሥት ፖለቲካ በዝርዝር ይተነትናል።

⚔️ የውጭ ኃይሎች በኢትዮጵያ ላይ የነበራቸውን ተፅዕኖ እና የተመከቱበትን ምስጢር ያጋልጣል።

🇪🇹 የዓድዋን ዓለም አቀፋዊ ድልነት እና የአባቶቻችንን ጥበብ ለትውልድ ያሳያል።

የኢትዮጵያ ታሪክ የነጻነት፣ የሉዓላዊነትና የጽናት ተምሳሌት ነው ። ከ1883 እስከ 1910 እ.ኤ.አ. የነበረው ዘመን ደግሞ የኢትዮጵያ ዘመናዊ የመንግሥት መዋቅር የተዘረጋበትና የሀገሪቱ ታላቅነት በዓለም አደባባይ የተመሰከረበት ወቅት ነው።

ይህንን ወሳኝ የታሪክ ምዕራፍ በሰነድና በማስረጃ አስደግፎ የሚያቀርበው የክሪስ ፕራውቲ መጽሐፍ በአማርኛ ትርጉም ቀርቦላችኋል።

ይህ መጽሐፍ በተለይ እቴጌ ጣይቱ በአመራር ብቃታቸው፣ በጽናታቸውና በዓድዋ ጦርነት ወቅት የነበራቸውን ስልታዊ ሚና በስፋት ይዳስሳል።

ለአንባቢያን አዲስ እይታን የሚሰጥ፣ የትናንቱን የአባቶች ጥበብ ዛሬ ላይ ቆመን እንድንመረምር የሚያስችል የትውልድ ስጦታ ነው። የታሪክ ፍቅረኞችና ማንነታቸውን ማወቅ የሚሹ ሁሉ ሊያነቡት የሚገባ ድንቅ የታሪክ ሰነድ ነው።

መጽሐፉን በመደብቻችን ሁሉ ያገኙታል !
ጃዕፈር መጻሕፍት

አዲስ መጽሐፍ ! በታምሬ ተካ ደልኬሮ የተዘጋጀው " የኤርትራ ነጻነትና የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ "  መጽሐፍ ለንባብ በቃ !
17/08/2026

አዲስ መጽሐፍ !

በታምሬ ተካ ደልኬሮ የተዘጋጀው " የኤርትራ ነጻነትና የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ " መጽሐፍ ለንባብ በቃ !

17/08/2026

ለአዲሱ የትምህርት ዘመን




#ከነሐሴ 19 - ነሐሴ 24 የሚቆይ

📚 ልጆቻችን ወደ ትምህርት ቤት
ሊመለሱ ነው !

ልዩ ቅናሽ .... ልዩ ዕድል ... ይዘን መጥተናል !!

በትምህርት አጋዥ መጻሕፍት ላይ የ 30% ቅናሽ አድርገናል !

ጃዕፈር መጻሕፍት የ 2019 ኝን የትምህርት ዘመን መጀመር አስመልክቶ ለተማሪዎች አጋዥ የሆኑ የተለያዩ መጻሕፍትን እስከ 30% ቅናሽ አዘጋጅቷል።

የ 2019 ን አዲሱ የትምህርት ዘመን በአዲስ ተስፋ ፣ በአዲስ ጉጉት እና ከሁሉም በላይ አዲስ ዕውቀት የሚገበይበት ጊዜ ነው ::

ተማሪዎች ለትምህርት ሲዘጋጁ ደብተር ፣ ስክሪብቶ ፣ ቦርሳ ፣ ዩኒፎርም .... ብቻ አይበቃም .. ያለ Physics ፣ Maths ፣ Biology ፣ Chemistry አጋዥ መጻሕፍት ዓመቱ እንዴት ይገፋሉ ?

History , Geography , Citzen ... የትምህርት ዓይነቶች በአጋዥ መጽሐፍ ካልታገዙ ፈተናው እንዴት ይታለፋል ?

ተማሪዎች ከ TextBook እና ከመምህራኖች ከሚቀስሟቸው ዕውቀት በተጨማሪ አጋዥ መጻሕፍት ያስፈልጓቸዋል ::

በአዲሱ የትምህርት ስርአት ትምህርት መሰረት ብቁ በሆኑ መምህራኖች በታማኝነት ፣ በጥራትና በጥናት የተዘጋጁ ፣ ከበቂ ማብራሪያና ከክለሳ ጥያቄዎች ጋር የተማሪዎች አጋዥ መጻሕፍት በመደብሮቻችን ከ 30% ቅናሽ ጀምሮ ያገኛሉ ::

ልጆቻችን በማንበብ ፣ በመመራመር እና ተጨማሪ እውቀት በማግኘት የትምህርታቸውን ውጤት የላቀ እና የአስተሳሰብ አቅማቸውን ወደ ተሻለ ደረጃ ከፍፍፍፍ ማድረግ ይችላሉ ።

📖 የትምህርት አጋዥ መጻሕፍት
📚 የንባብና የእውቀት መጻሕፍት
🧠 የአስተሳሰብና የክህሎት ማዳበሪያ መጻሕፍት
🎓 ለተማሪዎች የሚጠቅሙ የተለያዩ ይዘቶች

እንግዲህ የትምህርት ቤት ዝግጅትዎን በመጽሐፍ ያሟሉ ።

ልጆቻችን የትምህርት አጋዥ መጻሕፍት ያስፈልጋቸዋል ::

ዛሬ ለልጅዎ መጽሐፍ መምረጥ ማለት ለነገው ዕውቀቱ፣ አስተሳሰቡ እና ስኬቱ ላይ መዋዕለ ንዋይ ማፍሰስ ማለት ነው።

ጃዕፈር መጻሕፍት — የእዕቀት ጉዞዎ አጋር!

#ጃዕፈርመጻሕፍት #ወደትምህርትቤት #የመጽሐፍቅናሽ #እውቀት #ንባብ

አድራሻ :-

1- ለገሃር ተወልደ ህንጻ ስር
2 - አራት ኪሎ ብርሃና ሰላም ፊት ለፊት
3- አብርሆት ቤተመጻሕፍት ግቢ ውስጥ
4- መገናኛ መሰረት ደፋር ሞል ግራውንድ
5- ሜክሲኮ ደብረወርቅ ሕንጻ ስር
6 - ጀሞ ሚካኤል ትራፊክ መብራቱ አጠገብ ከሚና ሞል ፊትለፊት
7 ጥቁር አንበሳ ት/ቤትፊለፊት
8 ጀሞ የለቡ ታክሲ መያዣ ጋር
9 ሳሪስ አደይ አበባ
10 መሪ ጣዕም ዳቦ አጠገብ

የሶሻል ሚዲያ ገጾቻችን
---

ቴሌግራም:- https://t.me/Jafbok

ፌስቡክ:- https://www.facebook.com/jaferbookshop?mibextid=ZbWKwL

ዌብሳይት :- www.jaferbooks.com

"ይባስሊቆስ ዕንባ" በተሰኘው መጽሐፏ የምናውቃት ትግዕስት  ታፈረ ሞላ አሁን ደሞ "ጻማ" በተሰኘ መጽሐፍ መጥታልናለች መጽሐፉ በመደብሮቻችን ይገኛል።
17/08/2026

"ይባስሊቆስ ዕንባ" በተሰኘው መጽሐፏ የምናውቃት
ትግዕስት ታፈረ ሞላ አሁን ደሞ "ጻማ" በተሰኘ መጽሐፍ መጥታልናለች
መጽሐፉ በመደብሮቻችን ይገኛል።

መጽሐፍ — በዝምታ ውስጥ የሚናገር ዓለም ! መጽሐፍ የተጻፈ ወረቀት ብቻ አይደለም ፤ የሰው ልጅ አእምሮ ፣ ልብና ሕይወት በቃላት የተቀረጸበት የጊዜ ማስቀመጫ ነው ። ገጹን ስትገልጥ በእጅህ ...
17/08/2026

መጽሐፍ — በዝምታ ውስጥ የሚናገር ዓለም !

መጽሐፍ የተጻፈ ወረቀት ብቻ አይደለም ፤ የሰው ልጅ አእምሮ ፣ ልብና ሕይወት በቃላት የተቀረጸበት የጊዜ ማስቀመጫ ነው ። ገጹን ስትገልጥ በእጅህ የምትይዘው ወረቀት ቢሆንም ፣ የምትገባበት ዓለም ግን ከወረቀቱ እጅግ የሰፋ ነው ። በጥቂት ገጾች ውስጥ ዘመናትን ትሻገራለህ ፤ ከማታውቃቸው ሰዎች ጋር ትወዳጃለህ ፣ ያልኖርከውን ሕይወት ትኖራለህ ፣ ያልተጓዝክባቸውን ሀገራት በምናብህ ትጎበኛለህ ።

መጽሐፍ አስገራሚው ነገር በዝምታ ውስጥ ብዙ መናገሩ ነው ። ድምፅ የለውም፤ ግን አእምሮህን ያነጋግራል። እግር የለውም፤ ግን ወደ ሩቅ ዓለማት ያደርስሃል ። ዕድሜ የለውም፤ ግን የትናንትን ጥበብ ለዛሬ እና ለነገ ያደርሳል።

አንድ ሰው ብቻውን ተቀምጦ የጻፈው ሀሳብ ከመቶዎች እና ከሺዎች ዓመታት በኋላ ከሌላ ሰው ጋር ውይይት ይጀምራል።

አንዳንድ መጽሐፍት እውቀትን ይሰጡሃል፤ ሌሎች ግን እራስህን እንድትጠይቅ ያደርጉሃል ። አንዳንዶቹ ያሳዝኑሃል፣ አንዳንዶቹ ያስቁሃል፣ አንዳንዶቹ ያስቆሙህና “ሕይወት በእርግጥ ምንድን ናት?” ብለህ እንድታስብ ያደርጉሃል።

የሚገርመው ደግሞ አንድ መጽሐፍ በሁለት ሰዎች እጅ ሲገባ ሁለት የተለያዩ ዓለማትን ሊፈጥር መቻሉ ነው።

መጽሐፍ በተዘጋ ጊዜ የሚያበቃ አይደለም፤ በአእምሮህ ውስጥ የሚቀጥል ጉዞ ነው። አንዳንድ ገጾች በእጅህ ውስጥ ቢቀሩም፣ ቃላቶቹ በልብህ ውስጥ ይቀራሉ።

አንድ መጽሐፍ አንብበህ በጨረስክ ቁጥር አንድ ሀሳብ የቀየረህ ፣ አንድ ቃል የነካህ፣ አንድ ታሪክ የተለወጠልህ ሰው ሆነህ ትወጣለህ ።

መጽሐፍ ማንበብ ገጾችን መቁጠር አይደለም፤ ከሌላ አእምሮ ጋር መነጋገር፣ ከሌላ ዘመን ጋር መገናኘትና በአንድ ሕይወት ውስጥ ብዙ ሕይወቶችን መኖር ነው። 📖✨

( ሐሳቡ ከተመቻችሁ ለወዳጆቻችሁ አጋሩልን )

15/08/2026

Address

Addis Ababa
0911932088

Opening Hours

Monday 01:00 - 15:00
Tuesday 01:00 - 15:00
Wednesday 01:00 - 15:00
Thursday 01:00 - 15:00
Friday 01:00 - 15:00
Saturday 01:00 - 15:00
Sunday 01:00 - 15:00

Telephone

+251919369844

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Jafer books posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category