ourheart.com

ourheart.com alhamdulilah

04/05/2025

ለVAR በየአመቱ 1.5 ሚሊዮን ዶላር ያስፈልጋል ።

በተለይ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ላይ የዳኞች አጋዥ ሆኖ የሚያገለግለው VAR ን ስናስብ ፡ ለአብዛኛዎቻችን የሚመስለን ፡ ዳኛው ሄዶ የተቀረፀውን ቪዲዮ አይቶ የሚመጣ ብቻ እንጂ ፡ VAR ን ለመጠቀም ከፍተኛ ወጭና ፡ ቴክኖሎጂ የሚያስፈልግ ነገር አይመስለንም ።.

ሆኖም VAR ን ( Video Assistant Referee ) በተግባር ላይ ለማዋል ፡ በሰውና በራሳቸው የሚቀርፁ ከ33 በላይ እስከ 4 K የምስል ጥራት ያላቸው ካሜራዎች ያስፈልጋሉ ።..
ከነዚህ መሀከልም የአንዱ ዋጋ ከ84 ሺህ ዶላር በላይ የሚያወጣው Sony HDC-F5500 ካሜራና ፡ በሰከንድ 120 ፍሬም የሚያነሳ ፡ አልትራ slow motion ካሜራዎች ይገኙበታል ።...
የሰው ሀይልን በተመለከተም ይህንን ምስል ተቀብለው የሚቆጣጠሩና ፡ ከዳኛው ጋር በራዲዮ የሚገኛኑ ሰወችንና ካሜራ ማኖችን ጨምሮ አንድን VAR ለማሰራት ፡ እስከ 15 ሰወች የሚያስፈልጉ ሲሆን ፡ በአጠቃላይ VAR የካሜራዎቹንና ሌሎች እቃዎችን ዋጋ ሳይጨምር. . በየአመቱ ከ1.5 ሚሊየን ዶላር በላይ ወይም ከ200 ሚሊየን ብር በላይ በየአመቱ ወጭ የሚጠይቅ ነገር ነው ።

24/02/2025

አንድ የአረብ ጭዌ አግኝቼ ወደኛ አመጣሁት፦

አንድ ሰይድ የተባለ "በመርሳት ችግር" አልዛይመር በሽታ የሚሠቃየው ሰው ነበር። ታድያ ሰይዶ እንደሱ በአልዛይመር በሽታ የሚሰቃዩ ሁለት ጀለሶች ነበሩት። እና እቤቱ ጋብዞ እያስተናገዳቸው ነው። ቤት ውስጥ ከጓደኞችሁ ጋር ማውራትና መሳቅ ተያያዙት። ሰይድም በመሃል “ሻይ ላምጣላችሁ” በማለት ይዞላቸው መጣና ጠጡ።

ከትንሽ ቆይታ በኋላ ሰይድ “እኔ ምለው ሻይ ትጠጣላችሁ እንዴ?” አላቸው። ሁለቱም ጓደኞቹ “አዎ አምጣልን” በማለት መለሱ። እናም ሰኢድ እንደገና ተነሳና ሻይ አመጣላቸው።

ትንሽ ከተነጋገሩ በኋላ ሰይድ በድንጋጤ፡- “አምላኬ ሆይ! ሻይ አመጣላችዋለው እያልኩ ዘነጋው” በማለት ድጌ ለሦስተኛ ጊዜ ተነስቶ አመጣና ጠጡ።

ምሽቱ ካለቀ በኋላ ሁለቱ ጓደኛሞች ከቤቱ ወጡ። ከመካከላቸው አንዱ ከቤቱ በር ሳይርቅ ሌላኛው ጓደኛውን “ይገርማል ሰይድ እንዲህ የተረገመ ቋጣሪ ነው ለካ። ምሽቱን ሙሉ በቤቱ አሳልፈን አንድ ኩባያ ሻይ እንኳን አላቀረበልንም!” አለው።

ሌላውኛው በመገረም ጠየቀ “እንዴ ዛሬ ሰይድ ቤት ሄደን ነበር እንዴ?!”

በዚህ ንግግር መሃል ሰይድ በመስኮት ሁለቱ ጓደኞችሁን ተመለከታቸውና “በአሏህ ይዣችኋለሁ በቤቴ በኩል አልፋችሁ ሻይ ሳትጠጡማ አለቃችሁም!” አላቸው። ስለዚህ ሁለቱ ጓደኛሞች ለአራተኛ ግዜ ሻይ ሊጠጡ ወደ ሰይድ ቤት ገቡ።

በዚህ ዘመን የብዙዎቻችን ሁኔታ ይህንን ይመስላል።

ለ አዳዲስ እና ወቅታዊ መረጃዎች
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ

https://t.me/Hulumereja123

06/02/2025
26/12/2024

ወደን ፈቅደን በፍቅር ስሜት የምናደርጋቸው ነገሮች ሁሉ ለራሳችን ስንል እንጂ ለምንወደው ሰው ስንል እንዳልሆነ እስኪገባን ድረስ ብዙ አላስፈላጊ የስሜት ውጣ ውረድ ውስጥ እናልፋለን። ፍቅርን ብለው የፍቅር አጋራቸውን ተከትለው ቦታ የቀየሩ ሰዎች ጥቂት ክርክር ሲነሳ "ላንተ ብዬ እዚህ ድረስ መጥቼ። ቤተሰቤን ትቼ" ብዙ ነገር ይባላል። በዋናነት እሱን ብለሽ አይደለም። ከእሱ ጋር መሆን እና ፍቅሩን ማግኘት የሚሰጠውን ደስታ መርጠሽ ነው። መስሎሽ ተሸውደሽ ይሆናል።

በሆነው ባልሆነው መነዛነዝ እና ያደረጉትን ገድል በየማዕዘኑ መቁጠር በሌላኛው ሰው ስሜት ላይ ከባድ ጫና እና ፍርሀት ይፈጥርና፣ ተራ የሚባሉ ጉዳዮች ላይ ሳይቀር መነጋገርን ተራራ እንደመውጣት ያከብደዋል። ሰው ለመነጋገር ከተቸገረ እና ያንን ችግር ካልተገነዘበና ለማስተከከል ካልሞከረ፣ ስሜት ቀስ እያለ ይሸረሸራል። ልብ ይሻክራል። በድን ለበድን ይሆናል ኑሮው።

ደግሞ የታይታ ዘመን ነው። ሰው ካልታየ የኖረ ስለማይመስለው፣ ካልሰማ ስለሚረበሽ፣ ጉድ ጉድ ካላለ ስለሚጨነቅ፣ ነገሩ ጸሐይ ሲመታው መልኩን ይቀይራል። መደበኛ ሰላምታ እንኳን "ጉድ ጉድ ሰላም ተባባሉ እኮ" ሲባልለት፣ "ሙዚየም አስገቡኝ" እንዳይል ነው የምፈራው። ተራ ደግነቶችን በማህበራዊ ሚዲያ ጩኸት የተነሳ ሩቅ ሰቅለናቸዋል። የዐይነ ስውር አባት ማዳበሪያ አግዞ መንገድ ማሻገር ካሜራ የሚያስፈልገው እና፣ ኋላ ገንዘብ ተዋጥቶ ሽልማት የሚያሰጥ ከሆነ ዓመታት አለፉ።

ንፍገት እና ጭካኔ ሲበዛ፣ ንፉጉን እና ጨካኙን ከመገሰጽ ይልቅ የመደበኛ ኗሪውን ጥቂት ደግነት መዘን፣ ክንፋም ደግ ነህ በማለት እናንቆለጳጵሳለን። ለሚወዱት ሰው የሚሰጥ ስጦታ በሰሚው ዘንድ መደነቅን ሲፈጥር፣ ምን ያህል ንፍገትና ገብጋባነት ሥር እንደሰደደ ማሳያ ነው። መወቃቀስ ካለ በስሜትና በመከዳዳት ዙሪያ እንጂ በቁስ ዙሪያ መሆን የለበትም። ቁስና ገድል ቆጠራው ጨርሰው የተለያዩ ቀን ይደርሳል።

ሙሉውን ቤት ለማፍረስ እየለፉ ስለ ስጦታዎች ማውራት ከመጣ፣ ያበቃ ቀን ዐይኑም ጥርሱም የጋራ ነው፤ አይከፋፈሉት ነገር ቸግሮ እንጂ። ከዚያ ሰው ጋር የሳቁትን ከሌላው አይስቁትም። ከዚያ ሰው ጋር ያዩትን ከሌላ ጋር አያዩትም። መሳቁ ማየቱ ይኖራል፤ ግን ኣንድ አይደለም። ከወደዱ ስሜትን ነው መንከባከብ።

ደግሞ ከስሜት ባሻገር እመር ብለው ዙሪያን፣ ማገር እና ምሰሶን መቃኛት። የላላ ቀን እናጥብቀው ቢባል የውለታን መዝገብ እዚያ ጋር አርቀው... ቆጡ ላይ ሰቅለው በነጻ መጨቃጨቅ ነው። እንጂ ገድል አበላልጦ የሹም ዶሮ ነኝ፣ ይህን ይህን ስለሰጠሁ፣ እንዲህ አትናገሩኝ ማለት ሲመጣ፣ ፍቅሩም ፍቅር ቤቱም ቤት አይሆኑ።

እኔ ይህን ይህን ስለሰጠሁ ብዬ ብታበይ፣ የሚቀበል እና ስጦታው ይገባዋል ብዬ ያመንኩበት ቢኖር ነው! ተቀባይ እምቢ ቢል ቢለግም ሰጪነት መች ዋጋ ይኖረዋል? It's mutual.

"ፍቅርን በውለታ መውደድን በገንዘብ
ልግዛሽ ትለኝና እንዳንተዛዘብ" ~ Tsedenia

Best.Friend
02/12/2024

Best.Friend

Address

Butajira

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ourheart.com posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to ourheart.com:

Share