Dabat City Communication

Dabat City Communication Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Dabat City Communication, Shopping & retail, Dabat.

በዳባት ከተማ “በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ "በሚል በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የተገነቡ የአቅመ ደካማ መኖርያ ቤቶች ተጠናቆ  ርክክብ ተካሄደ ። ነሀሴ 07/2018 ዓ.ም ዳባት ከተማ ኮሙኒ...
13/08/2026

በዳባት ከተማ “በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ "በሚል በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የተገነቡ የአቅመ ደካማ መኖርያ ቤቶች ተጠናቆ ርክክብ ተካሄደ ።

ነሀሴ 07/2018 ዓ.ም ዳባት ከተማ ኮሙኒኬሽን

የዳባት ከተማ አስተዳደር በክረምት በጎ ፍቃድ አግልግሎትና በመንግሥት ድጋፍ የተገነቡ አስራ ሁለት ቤቶችን ቤት ለሌላቸው አቀመ ደካሞች አስረከበ ።

የአልማ ዩኒሴፍ  ቻይልድ ፕሮቴክሽን ፕሮጀክት በዳባት ከተማና ወረዳ በግጭትና በወቅታዊ ችግር ምክንያት ለ56 ህፃናቶች 897,535ብር ወጭ በማድረግ የቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል። ነሀሴ 05/20...
11/08/2026

የአልማ ዩኒሴፍ ቻይልድ ፕሮቴክሽን ፕሮጀክት በዳባት ከተማና ወረዳ በግጭትና በወቅታዊ ችግር ምክንያት ለ56 ህፃናቶች 897,535ብር ወጭ በማድረግ የቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል።

ነሀሴ 05/2018 ዓ.ም የዳባት ከተማ ኮሙኒኬሽን

በድጋፍ ተገኝተው ንግግር ያደረጉትየሴቶች ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ምርኩዝ ወንዴ በዛሬው እለትየአልማ ዩኒሴፍ ቻይልድ ፕሮቴክሽን ፕሮጀክት ለ56ህፃናቶች 897,535ብር ወጭ በማድረግ ብርድ ልብስ፣ ፍራሽ ከነ ትራሱ፣ አንሶላ, ሳሙና (የገላ እና የልብስ)፣ የመማሪያ ደብተር፣ እስክብሪቶ፣ እርሳስ፣ ፖርሳ እና የመሳሰሉ ቁሳቁሶች ድጋፍ አድርገዋል ብለዋል ።

አልማ ዩኒሴፍ ቻይልድ ፕሮቴክሽን ፕሮጀክት በዳበት ወረዳ እና በዳባት ከተማ አስተዳደር በ10 (አስር) የገጠር ቀበሌዎች የኢኮኖሚ አቅማቸው ዝቅተኛ ለሆኑ ህጻናት፣ በጦርነት ምክንያት ወላጆቻቸውን ላጡ እና ከትምህርት ገበታቸው ለተፈናቀሉ 262 ህፃናትን 3,026,886ጨብር በጥሬ ገንዘብ ድጋፍ ያደረገ ሲሆን በዛሬው እለት ደግሞ በግጭትና በወቅታዊ ችግር ምክንያት ለ56 ህፃናቶች 897,535ብር ወጭ በማድረግ የቁሳቁስ/የአይነት ድጋፍ ማድረጉንየዳባት ከተማ የአልማ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት አቶ ታደሰ ገልጸዋል ።

የአልማ ዩኒሴፍ ቻይልድ ፕሮቴክሽን ኦፊሰር አቶ አበባው ሽታሁን ከድጋፉ በተጨማሪ የማሕበረሰቡን ግንዛቤ ለማሳደግ የተለያዩ የግንዛቤ ማስበጫ ውይይቶች እና ስልጠናወችን እየሠራ ይገኛል።ስልጠናውም ስለወሲባዊ ብዝበዛ፣ ወሲባዊ ጥቃት፣ የተሻለ የልጅ አስተዳደግ፣ ማሕበራዊ ስሜታዊ ኩነቶችን መረዳት፣ አእምሮ ጤና ፣ስለ ማሕበራዊ ስነልቦናዊ ድጋፍ ፣ስለ ስርአተ ጾታ ጥቃት፣ እና ጾታዊ ጥቃት ላይ ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጫ እና ስልጠና ፕሮጀክቱ በሚሰራባቸው በአስሩ ቀበሌወች ስልጠናው እንደተሰጠ ገልፀዋል።

የአማራ ሴቶች ማህበር በዳባት ከተማ ለችግር ተጋላጭ ለሆኑ ሴቶች ከ2 ሚሊዮን 640ሽ ብር  ግምት ያላቸው የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል ። ነሀሴ 01/2018 ዓ.ም የዳባት ከተማ...
08/08/2026

የአማራ ሴቶች ማህበር በዳባት ከተማ ለችግር ተጋላጭ ለሆኑ ሴቶች ከ2 ሚሊዮን 640ሽ ብር ግምት ያላቸው የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል ።

ነሀሴ 01/2018 ዓ.ም የዳባት ከተማ ኮሙኒኬሽን
የአማራ ሴቶች ማህበር ከዩኒሴፍ ጋር በመተባባር በከተማው ለሚገኙ ለ420 ሴቶች የቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጉን የሴቶችወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት አስታውቀዋል።

በመርሃ ግብሩ ተገኝተው ንግግር ያደረጉትየሴቶች ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ምርኩዝ ወንዴ ለተደረገው ድጋፍም ለአማራ ሴቶች ማህበር እና ለዩኒሴፍ ላቅ ያለ ምስጋና አቅርበዋል ፡፡

የዳባት ወረዳ የአማራ ሴቶች ማህበር የምክር አገልግሎት ባለሙያ እና የፕሮጀክት አስተባበሪ አቶ መግብ አንዷለም ማህበሩ ከዩኒሴፍ ጋር በመተባባር ለዳባት ከተማ ለችግር ተጋላጭ ለሆኑ ሴቶች በ3ዙር ከ3ሚሊየን ብር በላይ የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጋቸውን ገልፀዋል፡፡

ድጋፉ የኢኮኖሚያዊ ጫና ያለባቸውን ሴቶች እና ልጃገረዶችን እንዲሁም ተማሪዎች በንጽህና መጠበቂያ ጉድለት ምክንያት ከትምህርት ገበታ ውጭ እንዳይሆኑ ያግዛል ብለዋል፡፡

የአማራ ሴቶች ማህበር በስርዓተ ጾታ፣ ጾታዊ ጥቃትን በመከላከልና ምላሽ በመስጠት ማህበረሰቡን የማስተማር ስራዎችን፣የሴቶችን የህይወት ክህሎት ስልጠና ጾታዊ ጥቃት እንዳይደርስባቸው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሲሰጡ መቆየታቸውን አቶ ምግበ አንስተዋል፡፡

የከተማና የገጠር መሬት ይዞታ ማረጋገጥ እና  ምዝገባ (ካዳስተር) አስመልክቶ ከባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ ተካሄደ ። ነሀሴ 01/2018 ዓ.ም ዳባት ከተማ ኮሙዩኒኬሽን በዳባት  ...
07/08/2026

የከተማና የገጠር መሬት ይዞታ ማረጋገጥ እና ምዝገባ (ካዳስተር) አስመልክቶ ከባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ ተካሄደ ።

ነሀሴ 01/2018 ዓ.ም ዳባት ከተማ ኮሙዩኒኬሽን

በዳባት ከተማ አስተዳደር መሬት ጽ/ቤት በከተማ መሬት ይዞታ እና መሬት ነክ ንብረት ምዝገባን በተመለከተ ከባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ በዳባት ከተማ ተካሂዷል።

በመድረኩም 2017 ዓ.ም የወጣውን የከተማ መሬት ይዞታና መሬት ነክ ንብረት ምዝገባ አዋጅ ቁጥር 1381/2017 አስመልክቶ በጠቅላላ ድንጋጌው መሬት ነክ ንብረት ምዝገባ መሠረቱ ና አተገባበሩ፣ ህጋዊ ካዳስተር፣ ስለመሬት ይዞታ ማረጋገጥ መሠረቱና የአተገባበር ሥርዓት፣ የካዳስተር የገጸ ምድር መረጃ፣ስለምዝገባ ሥርዓት ውጤቱ እና ልዩልዩ ድንጋጌዎችና የመሬት አስተዳደር ዋና ዋና ስራዎችና የቀጣይ አቅጣጫዎችን አስመልክቶ የዳባት ከተማ አስተዳደር መሬት ጽ/ቤት የስመ-ንብረት ዝውውር ባለሙያ እና የመሬት ማስተላለፍ ተወካይ ቡድን መሪ በአቶ አገሬ እሸቴ በሰነድ የተደገፈ የግንዛቤ ፈጠራ ስልጠና ለተሳታፊዎች ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል።

በመድረኩም የዳባት ከተማ አስተዳደር መሬት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ብርሃን ቤዛ ህጋዊ ካዳስተር ማለት ለእያንዳንዱ ህጋዊ ወሰን ለተለየለት የይዞታ መብት ክልከላና ሃላፊነት የሚመለከት መረጃ እና የይዞታ ካርታ አጣምሮ የያዘ ወቅታዊ የመሬት ይዞታ መረጃ ስርዓት ነው ብለዋል ።

የዳባት ከተማ አስተዳደር ሲቪል ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ እና ተወካይ ከንቲባ የካዳስተር ሥርዓቶችን መገንባት በመንግስት በኩል አቋም መያዙን የገለጹ ሲሆን በከተሞች የመሬት አስተዳደር ሂደቱን ይበልጥ የተሳለጠና ውጤታማ ለማድረግ የመሬት መረጃን ማዘመን እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡
የሰሜን ጎንደር ዞን መሬት መምሪያ የከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ቡድን መሪ አቶ ይሁኔ ያዜ እንደገለጹት የካዳስተር ዋና አላማውም የባለ ይዞታውን የመሬት ይዞታ ተጠቃሚነት ዋስትና በማረጋገጥ እንዲሁም የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለቤትነት መብትን እውቅና በመስጠት የከተሞችን ኢኮኖሚያዊ፣ማህበራዊና እና አካባቢያዊ ልማትን ማፋጠን ነው ብለዋል።

የግንዛቤ ፈጠራ ስራውን በባለቤትነት የፖለቲካ አመራሩ ወስዶ ወደ ተግባር መግባት ይኖርበታል ያሉት የዳባት ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፖርቲ የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሞላ ምስጋናው ስራውን በውጤታማነት ለማጠናቀቅ በመናበብና በባለቤትነት ለመፈፀም በቁርጠኝነት መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።

06/08/2026
ዉጤታማ አፈጻጸም ላሳዩ ተቋማት የምስክር ወረቀት ሽልማት ተሰጣቸው። ሐምሌ 30/2018 ዓ.ም የዳባት ከተማ ኮሙኒኬሽን የዳባት ከተማ አስተዳደር ሲቪል ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ጽ/ቤት በበ...
06/08/2026

ዉጤታማ አፈጻጸም ላሳዩ ተቋማት የምስክር ወረቀት ሽልማት ተሰጣቸው።

ሐምሌ 30/2018 ዓ.ም የዳባት ከተማ ኮሙኒኬሽን

የዳባት ከተማ አስተዳደር ሲቪል ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ጽ/ቤት በበጀት አመቱ የተሻለ አፈጻጸም ላሳዩ ጽ/ቤቶችና ቀበሌዎች የምስክር ወረቀት ሽልማት ሰጥቷል።
የ2018 ዓ.ም አመታዊ የሪፎርም አፈፃፀም የተቋም ግብረ መልስ ከባለድርሻ አካላት ጋር ግምገማ አካሄዷል።
የዳባት ከተማ አስተዳደር የሲሰርቨስ የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መንግስቱ ውበት የ2018 ዓ.ም አመታዊ የሪፎርም አፈፃፀም እና የተቋም ግብረ መልስ ሪፖርት በዝርዝር አቅርበው በተሳታፊዎች ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል።

በመድረክ ተሳታፊዎችም የሪፎርሙን አፈፃፀም ውጤታማ ለማድረግ በየጊዜው ተቋማት እየተገመገመ በጥብቅ ድጋፍና ክትትል በትኩረት መሰራት እንደለበት እንዲሁም ከውጤት አፈፃፀም ጋር መተሳሰር እንዳለበት አስቀምጠዋል ።

አቶ ቻሌ ፀጋው የሪፎርም ድጋፍና ክትትል ቡድን መሪ ደግሞ መመሪያ መሰረት በማድረግ የሪፎርም ድጋፉን ውጤታማ ለማድረግ የሁላችን ርብርብ የሚጠይቅና ህዝብን ለመጥቀም ከይስሙላና ከልዩ ልዩ ምክኒያት ወጥተን ለመተጋገዝ ሙሉ ፈቃደኛ ልንሆን ይገባል በተጨማሪም ለሪፎርሙ አፈፃፀም ትልቅ ድርሻ ያለው አመራሩነው ብለዋል።

የዳባት ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ፖርቲ ፖለቲካ ዘርፍ አቶ ሞላ ምስጋናው በተቋማት ግንባታ ሂደት የተሻለ አፈጻጸም ላላቸዉ ተቋማት ደረጃ በማውጣት የምስጋና የምስክር ወረቀት መስጠት መለመድ አለበት ብለዋል።

በ2018 ዓ.ም የሪፎርም አፈፃፀም እና የተቋም ግብረ መልስ ፕሮግራም የተገኙት የዳባት ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ ማህሌት ብርሃኑ የህዝብ አገልጋይና የመንግስት አገልግሎት ሰጭ የሆነዉን ሲቪል ሰርቫንት ማብቃትና መለወጥ ከተቻለ ሃገርን መታደግና ማሳደግ ይቻላል ብለዋል።
በበጀት አመቱ የተሻለ አፈጻጸም ያሳዩ ጽ/ቤቶችእና ቀበሌዎች የደረጃ ፍረጃ :- 1ኛ ደረጃ የዳባት ከተማ ገንዘብ ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት
2ኛ ደረጃ የዳባት ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት
3ኛ ደረጃ የዳባት ከተማ አስተዳደር መሬት ጽ/ቤት
በቀበሌ ደረጃ ፦
1ኛ ደረጃ የዳባት ከተማ ቀበሌ 04 አስተዳደር ጽ/ቤት
2ኛ ደረጃ የዳባት ከተማ ቀበሌ 02 አስተዳደር ጽ/ቤት
3ኛ ደረጃ የዳባት ከተማ ቀበሌ 03 አስተዳደር ጽ/ቤት

በበጀት አመቱ የተሻለ አፈፃፀም ያላቸው መሆኑን በደረጃ ተፈርጀዋል ።በፍረጃውም ዉጤታማ አፈጻጸም ላሳዩ ተቋማት የምስክር ወረቀትና የገንዘብ የማበረታቻ ሽልማት ተሰጥቷቸዋል።

ተሸላሚዎች በበኩላቸዉ የተሰጣቸው እዉቅና ለቀጣይ ስራቸው ስንቅ እንደሚሆናቸው እና ለሌሎች ተቋማት አርዓያነት ያለዉ ተግባር ለመፈጸም እንደሚያስችላቸዉ ተናግረዋል።

06/08/2026
የዳባት ህፃናት እና አረጋዊያን መርጃ ማህበር የሐምሌን ወርሃዊ ክፍያ ለ120 አቅመ ደካማ አረጋዊያን 60,000 ( ስልሳ )ሽ ብር ወጭ በማድረግ ድጋፍ አደረገ። ሐምሌ 29/2018 ዓ.ም የዳ...
05/08/2026

የዳባት ህፃናት እና አረጋዊያን መርጃ ማህበር የሐምሌን ወርሃዊ ክፍያ ለ120 አቅመ ደካማ አረጋዊያን 60,000 ( ስልሳ )ሽ ብር ወጭ በማድረግ ድጋፍ አደረገ።

ሐምሌ 29/2018 ዓ.ም የዳባት ከተማ ኮሙኒኬሽን
የዳባት ህፃናት እና አረጋዊያን መርጃ ማህበር በከተማው ለሚኖሩ ምንም ገቢ ለሌላቸው ለ120 አቅማቸው ለደከሙ አረጋዊያን ለእያንዳንዳቸው 500 አምስት መቶ ብር በአጠቃላይ 60,000 ( ስልሳ )ሽ ብር ወጭ በማድረግ ድጋፍ አድርገዋል ።

የዳባት ህፃናት እና አረጋዊያን መርጃ ማህበር ሊቀመንበር ቻሌ አስፋው እንደገለጹት የዳባት ህፃናትና አረጋዊያን መርጃ ማህበር ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ የተለያዩ ድጋፍችን እያደረገ ለህፃናትና ለአረጋዊያን ብዙ ተግባራት እያከናወነ ቆይቷል። ከ2017 ዓ.ም ጀምሮ ለ120 አባል በማድረስ ለእያንዳንዳቸው በየወሩ 500 ብር በየወሩ ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ገልፀዋል።

በዳባት ከተማ ቀበሌ 04 አስተዳደር ጽ/ቤት በዝቅተኛ ደረጃ ለሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎች ማዕድ የማጋራት መርሐ ግብር ተካሄደ። ሐምሌ 28/2018 ዓ.ም የዳባት ከተማ ኮሙኒኬሽን በዳባት ከተማ...
04/08/2026

በዳባት ከተማ ቀበሌ 04 አስተዳደር ጽ/ቤት በዝቅተኛ ደረጃ ለሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎች ማዕድ የማጋራት መርሐ ግብር ተካሄደ።

ሐምሌ 28/2018 ዓ.ም የዳባት ከተማ ኮሙኒኬሽን
በዳባት ከተማ ቀበሌ 04 አስተዳደር ጽ/ቤት በዛሬው ዕለት በቀበሌው በጎአድራጊ ወጣቶች ከተቋማትና ግለሰቦች በተሰበሰበ ገንዘብ ለዝቅተኛ የኢኮኖሚ ደረጃ የሚገኙ ወገኖችን፣ አረጋውያንና ወላጆቻቸውን ያጡ ህፃናትን ማዕድ በማጋራት ፕሮግራም አዳሄዳል።

በማዕድ ማጋራት ስራው የዳባት ከተማ ብልጽግና ፓርቲ የፖለቲካ እና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሞላ ምስጋናው እና የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ ማህሌት ብርሃን፣የቀበሌው ባለሙያዎች ጨምሮ ሌሎች የከተማ አመራሮች ተገንተዋል ።

ከመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት የተሰጠ መግለጫ*********************ስንትባበር ምን ማድረግ እንደምንችል ደጋግመን ለዓለም ያሳየንበት የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር...
03/08/2026

ከመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት የተሰጠ መግለጫ
*********************

ስንትባበር ምን ማድረግ እንደምንችል ደጋግመን ለዓለም ያሳየንበት የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ዛሬም በድል ተጠናቋል።

ኢትዮጵያ የሚለው ስም በጋራ የመቻልና የጽኑ አቋም ተምሳሌት ነው። መንግሥት የሀገሪቱን ዘላቂ ጥቅም ለማረጋገጥ የሚያስፈልጉ ስትራቴጂካዊ አቅጣጫዎችን ሲያስቀምጥ፣ የኢትዮጵያ ሕዝብም ሀገራዊ ፍላጎቱን በጋራ ተነሣሽነት እውን የማድረግ የዘመናት ልምምድ አለው። በተለይም መንግሥት ለአረንጓዴ ልማትና ሀገራዊ ከፍታ ለሚያቀርበው ጥሪ ሕዝቡ በላቀ ተሳትፎ ምላሽ የመስጠት ቁርጠኝነቱ ለዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ አብነት የሚሆን ነው።

መንግሥት በኢትዮጵያ የተራቆቱ አካባቢዎች በልጆቿ ብርቱ እጆች እንዲታከሙ፣ እየተስፋፋ የመጣው ድርቅና በረሃማነት በዘላቂነት እንዲገታ እና በአስተማማኝ መሠረት ላይ የተገነባ አረንጓዴ ኢኮኖሚ እውን እንዲሆን ግልጽና ጽኑ አቋም በመያዝ ጥሪ ሲያቀርብ ቆይቷል። በዚህም በላቀ የሕዝብ ተሳትፎና በመንግሥት መሪነት ታላቁን የሕዳሴ ግድብ እውን ማድረግ ተችሏል፤ ኢትዮጵያዊያን ዛሬ ላይ ምድራቸውን አረንጓዴ ማልበስ ባህላቸው አድረገውታል ፤ባለፉት ሰባት ዓመታት ብቻ በአረንጓዴ ዐሻራ ንቅናቄ ከ48 ቢሊዮን በላይ ችግኞች ተተክለው ኢትዮጵያ አረንጓዴ ሸማ ለብሳለች። ዘንድሮም በንቅናቄው 8ኛው ዓመት በአንድ ጀምበር 800 ሚሊዮን ችግኞችን፣ በክረምቱ ደግሞ በአጠቃላይ 8 ቢሊዮን ችግኞችን ለመትከል መንግሥት ቁርጠኛ አቋሙን በይፋ አሳውቋል።

ለመንግሥት ሀገራዊ ጥሪ ቀናኢ የሆኑ ውድ የኢትዮጵያ ልጆችም ይህንን ጥሪ በሙሉ ባለቤትነት ተቀብለው ለስኬቱ ከፍተኛ ርብርብ አድርገዋል። በዚህም በዛሬው ዕለት 26 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን በአንድ ጀምበር ከ805.3 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል የተቀመጠውን ግብ ከዕቅድ በላይ አሳክተውታል። ይህ መንግሥትና ሕዘብ ሲተባበሩ ምን ማድረግ አንደሚችሉ የሚያሳይ፣ ማንም በዓለም ላይ ያለ ሀገር በቀላሉ ሊያሳካው የማይችል ድንቅ ስኬት ነው።

ይህ ውጤት የኢትዮጵያ ሕዝብ ፍላጎትና የመንግሥት ስትራቴጂካዊ አቋም በአንድ አቅጣጫ ላይ እንደሚገኙ ማረጋገጫ ነው። በዛሬው የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር 26 ሚሊዮን ኢትዮያውያን ብርድ፣ ዝናብና ፀሐይ ሳይበግራቸው መሬት ሲያለምዱ ውለዋል፤ በዚሁ ጽኑ እንቅስቃሴም የዘንድሮው ክረምት ከገባ ጀምሮ 6 ነጥብ 5 ቢሊዮን ችግኞች ተተክለዋል። ኢትዮጵያ በልጆቿ ኮርታለች፤ መንግሥትም የሕዝቡን ከፍተኛ ቁርጠኝነትና ባለቤትነት ባየበት በዚህ ታሪካዊ ክስተት ከፍተኛ ኩራትና ክብር ተሰምቶታል። ይህም መንግሥት ይህንን ታላቅ ሕዝብ በበለጠ ኃላፊነትና ታማኝነት የማገልገል ጽኑ አቋሙን እንዲያጠናክር ተጨማሪ ብርታት ሆኖታል።

ክቡራን ኢትዮያውያን፣ ክቡራን የኢትዮጵያ ወዳጆችና የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ አካላት፤ ዛሬ ይኸንን አገራዊ ራዕይ በጋራ እውን ማድረግ እንድንችል ስላደረጋችሁት ከፍተኛ ርብርብ መንግሥት በኢትዮጵያ ስም ላቅ ያለ ምስጋና ያቀርባል። የክረምቱን አጠቃላይ የ8 ቢሊዮን ችግኞች ተከላ ዕቅድ ሙሉ በሙሉ ለማሳካት የተጀመረው አገራዊ ተሳትፎና ጽኑ አቋም ተጠናክሮ ይቀጠጥላል ።

ሐምሌ 27 ቀን 2018 ዓ.ም አዲስ አበባ

የኢፌዴሪ መንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

Address

Dabat

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dabat City Communication posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share