Yom Belay

Yom
 Belay አሐተ ሰአልክዎ ለእግዚአብሔር ወኪያሃ አኀሥሥ ከመ እኅድር ቤቶ ለእግዚአብሔር በኩሉ መዋዕለ ሕይወትየመዝ ፳፮÷፬

20/03/2025
18/03/2025

💠💠 ሆድ አምላክ ይሆናልን ? 💠💠

የሰው ልጅ ወደድኳቸው በሚላቸው ነገሮች ሕይወቱ ይወሰናል ። ሰይጣንም በምንወዳቸው ነገሮች ቀዳዳ በኩል ገብቶ ነው በውንብድና የጸጋችንን መዝገብ የሚበረብር ። ለእግዚአብሔርም ያለንን ፍቅር የምንገልጠው በምንወዳቸው ነገሮች ነው ። እርሱ አንድ ልጁን በመስጠት ፍቅሩን እንደገለጠልን እኛም የምንወዳቸውን ለእግዚአብሔር ብለን ይቅርብን ብለን በመተው በዚህ ፍቅራችንን እንገልጣለን ። የምንወዳቸው ሁሉ በእግዚአብሔር ፍቅር ፋንታ ከገቡብን ፥ እነዚያ በእርግጥ የምንወዳቸው ነገር ግን በፍቅረ እግዚአብሔር የተካናቸው የወዳጅ ጠላት የሆኑበትን ጠዖታት ናቸው ። ከእነዚህም ሳይገባን ጣዖታት አደርገን ከምናመልካቸው መካከል አንዱ ሆድ ነው ። እግዚአብሔር አትብሉ ብሎ የከለከለንን ነገርና አትብሉ ባለን ሰአት የምንበላ ከሆነ በእርግጥ ከእግዚአብሔር ይልቅ ሆዳችንን እየወደድን ስለሆነ ሆዳችንን አመለክን ማለት ነው ። ይህ ብቻ አይደለም! እግዚአብሔር እውነት ነው እቸገራለሁ ብሎ አስቦ መዋሸትም ጣዖት ማምለክ ነው ። ለሆዱ ብሎ የሚዋሽ ሰው ከእግዚአብሔር ባሕርይ ጋር ይቃረናልና ። የእግዚአብሔር ባሕርይው እውነት ነው ስለሆነ ። ድኻ እየተቸገረ እያዩ ለነገ በማሰብ የማይመጸውቱ ሰዎችም በሁለት መንገድ ጣዖት አምልከዋል ። አንደኛ ከስቀድመን እንደ ገለጥነው ከፍቅር ይልቅ ገንዘብን በማስቀደም ፤ ሁለተኛ ደግሞ እግዚአብሔር ያኖረኛል ከማለት ይልቅ ራሳቸውን ለራሳቸው ጠባቂ መጋቢ አድርጎ በመሾም መግቦተ እግዚአብሔርን በመካድ ነው ።

እንግዲህ እናስተውል ! ሆድ በሦስት መሠረታዊ ምክንያቶች ጣዖት ሊሆንብን እንደሚችል ። መጀመሪያ እግዚአብሔር የከለከለንን በመመገብ ጊዜ ከእግዚአብሔር ይልቅ መብልን በመውደድ ፤ ሁለተኛ ለቅዳሴ መላእክት የተፈጠርን ክቡራን አገልጋዮቹ ስንሆን መላ ዘመናችን ሆዳችንን በማገልገል ራሳችንን የራሳችን ባርያዎች በማድረግ ፤ እግዚአብሔር እንደፈጠረኝ ያኖረኛል ከማለት ይልቅ ለነገ በመስገብገብ ለድኾች አለመራራት ናቸው ። ጾም ፍቅር እንጅ ቀመር አይደለም ። የምንጾመው ከምንወደው መብል መጠጥ በመከልከል ለእግዚአብሔር ያለንን ፍቅር ለመግለጥ እንጅ ሰባት ጾም የጾምን ሰዎች ነን የሚል መስፈርት ለማሟላት አይደለም ። የሰው ልጆች ሁሉ እናትና አባት የመጀመሪያዎቹ ሰዎች አንዲት የእንጨት ፍሬ የተከለከሉት ያችንን በመተው ፍቅረ እግዚአብሔርን እንዲገልጡ እንጅ ለአንዲት እንጨት ፍሬ ነፍጓቸው አይደለም። እርሱማ እንኳን የበለስ ፍሬ ሊነፍገን ሥጋውን ደሙን በለጋሥነት የሰጠ የባሕርይ ቸር አይደለምን ?

ነውና ክርስትና የፍቅር ሃይማኖት ነው እግዚአብሔር ፍቅር ነውና። ስለ ፍቅር ትጾማለህ ፤ ስለ ፍቅር ትጸልያለህ ፤ ሰለ ፍቅር ትሰደዳለህ ፤ ስለ ፍቅር ትታሰራለህ ፤ ስለ ፍቅር ትናቃለህ ፤ ስለ ፍቅር ግፍን ሁሉ ተቀብለህ ትሞታለህ ፤ በፍቅር ብሮሃን ደምቀህ ትነሣለህ ። ፍቅር ደግሞ ስለ ፍቅር በመማር የምታውቃት አይደለችም ስለ ፍቅር በመኖር ። ፍቅር በልቡናህ ዛፍ ሆኖ የተተከለ እንደሆነ ሥሩ እስከ ተረከዝህ ይወርዳል ፤ ቅርንጫፎቹ ወደ ራስህ ያድጋሉ ፤ አበባቸው በአንደበትህ ይፈነድቃሉ ፤ የፍቅር ፍሬዎችም እነ ጾምና ጸሎት ምጽዋት ከአንተ በመላእክት እጅ እየተለቀሙ በሰማይ ጎተራ ይከማቻሉ ፤ የፍቅርን ፍሬ እየበላህ ለዘለዓለም ትኖራለህ ።
እግዚአብሔርን የምትወደው ከሆነ እንኳን ሰባቱን አጽዋማትን ሁሉንም ቀን ትጾማለህ ። ፍቅረ እግዚአብሔር ያነሰህ ፍቅረ መብልዕ የበዛልህ ስትሆን ደግሞ ጾም ይቀነስልኝ ብለህ ክተት ሠራዊት ትወጣለህ

ርዕሰ አድባራት ወገዳማት ተድባበ ማርያም         ********✍️ርዕሰ አድባራት ወገዳማት ተድባበ ማርያም ገዳም በደቡብ ወሎ ዞን አማራ ሣይንት ወረዳ ከዞኑ ከተማ ደሴ 228 ኪ.ሜ፣ ከወ...
12/03/2025

ርዕሰ አድባራት ወገዳማት ተድባበ ማርያም
********
✍️ርዕሰ አድባራት ወገዳማት ተድባበ ማርያም ገዳም በደቡብ ወሎ ዞን አማራ ሣይንት ወረዳ ከዞኑ ከተማ ደሴ 228 ኪ.ሜ፣ ከወረዳው ከተማ አጅባር 25 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ትገኛለች፡፡

✍️ተድባበ እና በስሯ የሚተዳደሩ ስምንት አብያተ ክርስቲያናት “ቅጥር” በተባለ 2500 ሜትር ርዝመት ባለው አምባ ላይ ተመስርተው ይገኛሉ፡፡

✍️ርዕሰ አድባራት ወገዳማት ተድባበ ማርያም መጀመሪያ “ተድባበ ጽዮን” ተብላ ትጠራ እንደነበርና ከክርስቶስ ልደት በፊት በ928 ዓመተ ዓለም እንደተመሰረተች የታሪክ ሰነዶች ያስረዳሉ፡፡

✍️ተድባበ የሚለው ቃል ከግዕዝ የተወረሰ ሲሆን ትርጓሜውም ድባብ ወይም ጫፍ ማለት ነው፡፡ ከአመሰራረቷ ጋር በተገናኘ የነገደ እስራኤላውያን እና የሕገ-ኦሪት ሥርዓት አሻራ በስፋት የሚስተዋልባት እንደሆነም በሃይማኖት አባቶች ይገለጻል፡፡

✍️አመሰራረቷም ሕገ-ኦሪትን በኢትዮጵያ ለማስፋፋት ከአገረ-እስራኤል ከቀዳማዊ ምኒልክ ጋር ከመጡት ነገደ እስራኤላውያን አንዱ በነበሩት ሊቀ ካህን አዛሪያስ በተባሉት አማካኝነት መሆኑን የቤተ ክርስቲያኗ ታሪክ ያስረዳል፡፡

✍️ተድባበ በኢትዮጵያ መስዋዕተ-ኦሪት ሲሰዋባቸው ከነበሩት አራቱ ጥንታዊ አብያተ ክርስቲያናት ማለትም አክሱም ጽዮን፣ ተድባበ ማርያም፣ መርጡለ ማርያም እና ጣና ቂርቆስ ጋር ትመደባለች፡፡

✍️ ከቀዳማዊ ምኒልክ እስከ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ድረስ የነበሩ የኢትዮጵያ ነገሥታት በበዓለ ሲመታቸው የአክሱሙ ንቡረዕድ ለነጋሲው ዘውድ በመድፋት፣ የተድባበ ማርያሙ ፓትርያሪክ ሰይፍ በማስታጠቅ፣ የመርጡ ለማርያሙ ርዕሰ ርዑሳን ልብሰ መንግስት በማጎናፀፍ እንዲሁም የጣና ቂርቆሱ ሊቀ ካህን ቅብዓ መንግስት በመቀባት በትረ መንግስት በማስጨበጥ በፀሎትና ቡራኬ የማንገሥ ሥርዓት እንዲፈጽሙ በፍትሃ ነገሥት ተደንግጓል፡፡

✍️ተድባባ ማርያም በአገራችን ከፍተኛ የቅርስ ክምችት ከሚገኝባቸው ታሪካዊና ሃይማኖታዊ ቦታዎች መካከል አንዷ ናት፡፡ የብራና መጻሕፍት፣ የነገሥታት ዙፋን፣ በወርቅ የተጌጠ ዘውድ፣ መስቀሎች፣ ካባዎች፣ በወርቅና ብር የተጌጡ ጋሻዎች እና ሌሎች በገንዘብ የማይተመኑ ውድ ቅርሶች በቤተ ክርስቲያኗ ሙዚየም በሥርዓት ተቀምጠው ጎብኝዎችን ይጠባበቃሉ፡፡

✍️ተድባበ ማርያም በምትገኝበት አምባ ዙሪያ የሚገኙ ቀበሌዎችም ለነገደ እስራኤላውያን መታሰቢያ እንዲሆኑ ቢታንያ፣ ደብረ ዘይት፣ ኮሬብ፣ ደብረ ሲና፣ ቃዲስ፣ ኬብሮን፣ ኢያሪኮ፣ ኢየሩሳሌም፣ የኤለት፣ ደብረ ታቦር፣ ደብረ ፋጌህ፣ ደብረ ፋራህ፣ ጎለጎታ፣ ፍልስጤም፣ ሊባኖስ፣ አርሞኒየም እና ደማስቆ ተብለው ተሰይመዋል፡፡

✍️

“ለድሃው ልብሶቹ ቢያድፉበት በውሃ እጠብለት አዲስም ልብስ ገዝተህ አልብሰው፤ ደሃው ወደ ቤትህ የገባ እንደሆነ እግዚአብሔር ወደቤትህ ይገባል፤ በመኖሪያህም ያድራል፡፡ ከመከራ ከስቃይ ላላቀቅኅ...
10/03/2025

“ለድሃው ልብሶቹ ቢያድፉበት በውሃ እጠብለት አዲስም ልብስ ገዝተህ አልብሰው፤ ደሃው ወደ ቤትህ የገባ እንደሆነ እግዚአብሔር ወደቤትህ ይገባል፤ በመኖሪያህም ያድራል፡፡ ከመከራ ከስቃይ ላላቀቅኅው ለዚያ ድሃ እግዚአብሔርም አንተን ከሚመጣብህ መከራና ስቃይ ያላቅቅሃል፡፡

የእንግዳውን እግር አጠብክን? የበዛ ሃጢአትህን አጥበህ አስወገድከው፡፡ ለድሃው ይመገብ ዘንድ ማዕድን አቀረብክለትን? እነሆ እግዚአብሔር አብ ከማዕድህ በላ፤ ክርስቶስም ለደሃው ካቀረብክለት ውሃ ጠጥቶ ረካ፤ መንፈስ ቅዱስም ማደሪያ ቤቱ አደረገህ፡፡

ደሃው ባቀረብክለት ማዕድ በልቶና ጠጥቶ ደስ አለውን? ጌታ ክርስቶስን ደስ አሰኘኅው፤ እርሱ ያደረክለትን መልካም ችሮታ የሚረሳ አይደለምና በመላእክትና በሰወች ፊት ያከብርሃል፡፡ ከረሃቡ እንዳሳረፍከው በመጨረሻው ቀን ይመሰክርልሃል፡ ለጥማቱ የሚጠጣ ስላቀረብክለት በመላእክቱ ፊት ያመሰግንሃል፡፡

ልጄ ሆይ መልካም ዘርን በደስታና እግዚአብሔርን ተስፋ በማድረግ ዝራ ልፋትህም ፍሬ ይስጥህ”

(ከስብከት ወተግሳፅ ዘቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ መጽሐፍ የተወሰደ)

አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜንየካቲት 29-ባሕርን በአጽፏ ተሻግራ ወደ ሀገረ ናግራን አገር ሄዳ ወንጌልን የሰበከችው ታላቋ ሐዋርያዊት እናታችን የእመ ምኡዟ ቅ...
07/03/2025

አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን
የካቲት 29-ባሕርን በአጽፏ ተሻግራ ወደ ሀገረ ናግራን አገር ሄዳ ወንጌልን የሰበከችው ታላቋ ሐዋርያዊት እናታችን የእመ ምኡዟ ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ ዕረፍቷ ነው፡፡ ለእርሷም እመቤታችን ተገልጣላት በጌታችን መከራ ሞት ምክንያት ስለደረሱባት ሀዘናት የነገረቻት፣ የፈለገችውንም ታደርግበት ዘንድ የእጇን መስቀል የሰጠቻት ሲሆን ሰውን ወደሚበሉ ሰዎች አገር ሄዳ ስንዴን በአንድ ቀን ብቻ ዘርታ፣ አብቅላ፣ አጭዳ፣ ፈጭታ ለምግብነት አብቅታ ከመገበቻቸው በኋላ እንደዚህ እያደረጉ እየሠሩ እንዲበሉ አስተምራ አስጠምቃቸው ስድስት አብያተ ክርስቲያናትን የሠራችላቸውና ቅዱስ ወንጌልን፣ ስንክሳርን፣ ሃይማኖተ አበውን፣ ግንዘትን፣ መዝሙረ ዳዊትን፣ አርጋኖንን ሁሉ በእጇ ጽፋ ያስቀመጠችላቸው ሐዋርያዊት እናታችን ስትሆን በሌላም በኩል ሙታንን እያስነሣች ለዐፄ ሱስንዮስ ስለእውነት እንዲመሰክሩለት ታደርግ የነበረችና እርሷም ራሷ አንገቷን ተሰይፋ ሰማዕትነትን የተቀበለችና ጌታችን ከሞት ያስነሣት ቅድስት ናት፡፡
+ ዳግመኛም በዚህች ዕለት የከበረ አባ ቢላካርዮስ በሰማዕትነት ዐረፈ፡፡ ይኸውም ቅዱስ ብዙ ድርሳናትንና ተግሣጻትን የደረሰ ሲሆን ፈጽሞ እስካረጀም ድረስ አርሞኒ በምትባል አገር ላይ በኤጲስቆጶስ ተሾሞ ያገለገለ ነው፡፡ ከደረሳቸው ብዙ ድርሳናትና ተግሣጻትም ውስጥ ስለከበረች የጌታችን ልደት በዓል፣ የብርሃን እናቱ ስለሆነች ስለ እመቤታችን፣ ስለሞትና ስለ መቃብር፣ በኃጥአን ላይ ስለሚደርስባቸው ሥቃይ፣ ስለ መድኃኒታችን የረቀቀ ጥበብ፣ ስለከበሩ በዓላትና ስለሌሎችም ብዙ ምሥጢራት ሕይወት በሆኑ ትምህርቶቹ ብዙ ድርሳናትን በመጻፍና በማስተማር ብዙ ነፍሳትን ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አድርጎ አቅርቧል፡፡
መልካም በሆነው አገልግሎቱ እግዚአብሔርን እያገለገለ ሳለ ከሃድያን ተነሥተው አምልኮተ ጣዖትን ሲያስፋፉ በክርቲያኖችም ላይ ስደትና ዕልቂት በሆነ ጊዜ አባ ቢላካርዮስ በክብር ባለቤት በጌታችን ስም ደሙን አፍስሶ ሰማዕትነትን ይቀበል ዘንድ ተመኘ፡፡ ሕዝቡንም ሰብስቦ እስከመጨረሻው ድረስ በቀናች ሃይማኖት እንዲጸኑ መከራቸው፡፡ ነገር ግን እርሱ ለሰማዕትነት የተዘጋጀ ነውና ካሁን በኋላ በሥጋ እንደማያገኙት በመንገር ተሰናበታቸው፡፡ ሕዝቡም ሁሉ ይህንን በሰሙ ጊዜ እጅግ እያዘኑና እያለቀሱ ‹‹የሙት ልጆች እንሆን ዘንድ ለምን ትተወናለህ?›› እያሉ በመለመን ወደ ሰማዕትነት እንዳይሄድ ለማስቀረት ብዙ ለፉ፡፡ ነገር ግን ማስቀረት አልተቻላቸውምና አባ ቢላካርዮስ ከእነርሱ ዘንድ ወጥቶ ወደ ከሃዲው መኮንን ዘንድ በመሄድ በፊቱ ቆሞ በጌታችን ስም ታመነ፡፡ የረከሱ የንጉሡን አማልክት በመርገም የጌታችንን ዕውነተኛ አምላክነት ጮኾ መሰከረ፡፡ መኮንኑም ይዞ ብዙ አሠቃየው፡፡ ሕዝቡም ብዙ ልመናን አብዝተው በመለመን ራሱን እንዲያድንና ከከተማው እንዲወጣ ግድ አሉት፡፡ እርሱም ልባቸውን ደስ ለማሰኘት እሺ አላቸው፡፡ ነገር ግን በዚያች ሌሊት መልአክ ተገለጠለትና የተመኘውን ሰማዕትነት በድል እንዲፈጽም ነገረው፡፡
ከዚህም በኋላ አባ ቢላካርዮስ በመኮንኑ ፊት ቆሞ አሁንም የረከሱ የንጉሡን አማልክት በመርገም የጌታችንን ዕውነተኛ አምላክነት መሰከረ፡፡ በዚህም ጊዜ መኮንኑ እጅግ ተቆጥቶ የአባ ቢላካርዮስን አንገት በሰይፍ እንዲቆርጡ ጨፍሮቹን አዘዛቸው፡፡ አባ ቢላካርዮስም ሰማዕትነቱን በድል ፈጽሞ በመንግሥተ ሰማያት የሰማዕትነት አክሊልን ተቀዳጀ፡፡ ሥጋውንም ምእመናን ወስደው ለኤጲስቆጶሳት በሚገባ ክብር አክብረው ቀበሩት፡፡ ረድኤት በረከቱ ይደርብን በጸሎቱ ይማረን!
+ + +
እናታችን ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ፡-

አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜንየካቲት 28-ሮማዊ ቅዱስ ቴዎድሮስ ከስድስት ሺህ ሦስት መቶ አራት ማኅበርተኞቹ ጋር በሰማዕትነት ዐረፈ፡፡ በቴዎድሮስ ስም የሚጠሩ...
06/03/2025

አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን
የካቲት 28-ሮማዊ ቅዱስ ቴዎድሮስ ከስድስት ሺህ ሦስት መቶ አራት ማኅበርተኞቹ ጋር በሰማዕትነት ዐረፈ፡፡ በቴዎድሮስ ስም የሚጠሩ ከዘጠኝ በላይ ቅዱሳን ሰማዕታት አሉ፡፡ በተለይም ታላላቆቹ ሰማዕታት ማለትም ቅዱስ ቴዎድሮስ ሊቀ ሠራዊት፣ ሮማዊ ቅዱስ ቴዎድሮስ፣ ቅዱስ ቴዎድሮስ በናድልዮስ የእነዚህን የሦስቱን ታሪክ የመደባለቅ ችግር አልፎ አልፎ ይታያል፡፡ ዛሬ በዓመታዊ የዕረፍቱ በዓል አስበነው የምንውለው ሮማዊ ቅዱስ ቴዎድሮስ ነው፡፡ ይኽም ሮማዊው ቴዎድሮስ በዘመነ ሰማዕታት በነገሥታቱ መክሲሞስና መክሲምያኖስ ዘመን የነበረ ከእስያ አውራጃ አስጢር ከሚባል አገር የተገኘ ከታላላቅ ሰማዕታት ውስጥ አንዱ ነው፡፡ በነገሥታቱ ዘንድ ‹‹የእናንተን አማልክትን አያመልክም›› ብለው ወነጀሉት፡፡ በግልጽ ወደ አደባባይ ወጥቶ በዐላዊያን ነገሥታት ፊት ስለ እምነቱ መስክሮና አስተምሮ ብዙዎችን ወደ እምነት መልሷል፡፡

ነገሥታቱም አስጠርተው ለጣዖታቸው ለምን እንደማይሰግድ ሲጠይቁት ‹‹እኔ ክርስቲያን ነኝ፣ ከሕያው የእግዚአብሔር ልጅ ከጌታዬና ከፈጣሪዬ ከኢየሱስ ክርስቶስ በቀር ሌላ አላመልክም›› አላቸው፡፡ ከዚህም በኋላ ነገሥታቱ በእሳት እያቃጠሉና ሌሎችንም እጅግ አሠቃቂ መከራዎችን አደረሱበት፡፡ የበርብዮስጦስ ልጅ ንጉሥ ‹‹ለአማልክቶቼ ብትገዛ በወታደሮቼና በመኳንንቶቼ ሁሉ ላይ አዛዥ አለቃ አድርጌ እሾምሃለሁ፣ ብዙ ወርቅና ብር የከበሩ ልብሶችም እሰጥሃለሁ…›› አለው፡፡ ቅዱስ ቴዎድሮስም ንጉሡን ‹‹ወርቅህና ብርህ ለጥፋት ይሁኑህ፣ እኔስ በሕያው እግዚአብሔር ልጅ በፈጣሪዬ በኢየሱስ ክርስቶስ ባለጸጋና አለቃ ነኝ›› አለው፡፡ ንጉሡም ‹‹ለአምላክ ልጅ አለውን?› ብሎ ጠየቀው፡፡ ቅዱሱም ‹‹አዎን ከመለኮቱ ባሕርይ የተገኘ ከእርሱ ጋራ ዓለምን የፈጠረ በእውነት ልጅ አለው›› ብሎ መለሰለት፡፡ ንጉሡም ‹‹አምላህን ብናውቀው ልናገኘው እንችላለን?›› ሲለው ቅዱስ ቴዎድሮስም ‹‹ወደ እርሱ ከተመለስክ እንደእኔ አገልጋዩ ትሆናለህ፣ የተወደደ መሥዋዕትም ያደርግሃል›› አለው፡፡ ከዚህም በኋላ ንጉሡ ‹‹ነገር አታብዛ ብዙ ገንዘብ እሰጥህ ዘንድ ለአማልክቶቼ መሥዋዕትን አቅርብ›› ብሎ ብዙ በተከራከረው ጊዜ ቅዱስ ቴዎድሮስ አማልክቶቹን ሰደበበት፣ ንጉሡንም ረገመው፡፡ ንጉሡም ተቆጥቶ ራቁቱን ካስገረፈው በኋላ በትምህርቱ ካመኑት ክርስቲያኖች ጋር በጨለማ ቤት አሠረው፡፡ ቅዱስ ቴዎድሮስም ከጸለየ በኋላ ሌሊት ወጥቶ እንጨት ከሰበሰበ በኋላ ጣዖታቱን ሁሉ አመድ እስኪሆኑ ድረስ በእሳት አቃጠላቸው፡፡ እንዳይሰሙም እግዚአብሔር በጣዖታት አገልጋዮቹ ላይ ከባድ እንቅልፍ ጥሎባቸው ነበር፡፡ ንጉሡም በኋላ ይህን በሰማ ጊዜ ቅዱስ ቴዎድሮስን በጽኑ ሥቃይ አሠቃይቶ ይገድለው ዘንድ ለመኮንኑ አሳልፎ ሰጠው፡፡

የንጉሡ መኰንንም ቅዱስ ቴዎድሮስን በመጀመሪያ የንጉሡ ትእዛዝ እንዲቀበልና ለጣዖታት እንዲሰግድ አግባባው፡፡ ቅዱሱም ‹‹እኔስ ለረከሱ አማልክት አልሠዋም፣ ለከሃዲ ንጉሥም አልታዘዝም›› አለው፡፡ መኮንኑም ቅዱስ ቴዎድሮስ በእምነቱ እንደጸና እና ትእዛዛቸውን ቸል እንዳለ ባየ ጊዜ እጅግ ተቆጥቶ ዘሎ በመነሣት አንገቱን አነቀው፡፡ ይዞም በጽኑ ሥቃይ ሲያሠቃየው ሊቀ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል መጥቶ መኰንኑን ገድሎ በአዘቅት ውስጥ ካሰጠመው በኋላ ለከበረ ቴዎድሮስ በእስያ ሀገር እየተዘዋወረ ወንጌልን እንዲያስተምር መንፈሳዊ ፀዓዳ ፈረስ ሰጠው፡፡ ንጉሡም ይህን ሲሰማ ከነፈረሱ እንዲይዙት በእርሱ ትምህርት ያመኑትንም እንዲይዙአቸው መቶ ፈረሰኞችን ላከ፡፡ መቶው ፈረሰኞችም ከሴቶችና ከልጆች በቀር ስድስት ሺህ አርባ ስምንት ያመኑ

05/03/2025

R
R
R
R
R

05/03/2025

አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን
የካቲት 27-ታላቁን ገዳም ማኅበረ ሥላሴን ያቀኑት ጻድቁ አቡነ ዓምደ ሥላሴ ዕረፍታቸው ነው፡፡
+ አባ አንስጣስዮስ ዕረፍቱ ነው፡፡ ይኽም ቅዱስ በትምህርቱ ዓለምን የመላ ሲሆን በታላቁ ንጉሥ በቆስጠንጢኖስ ዘመን የነበረ ነው፡፡ የከበሩ ቅዱሳን ሊቃውንት አባቶች በኒቅያ ከተማ የአንድነት ስብሰባ ባደረጉ ጊዜ በዚህ ጉባኤ ላይ ከተገኙት 318 ቅዱሳን ሊቃውንት ውስጥ የአንጾኪያ ሊቀ ጳጳሳት የሆነው አባ አንስጣስዮስ አንዱ ነው፡፡ በዚህም ጉባኤ ላይ ቅዱሳን ሊቃውንት ከሃዲ አርዮስን መክረው ዘክረው አስተምረው አልመለስ ቢላቸው ምእመናንን እንዳይበክል አውግዘው ለይተውታል፡፡

ቅዱሳን የከበሩ አባቶችም ሃይማኖትን አጽንተው ሥርዓትን ሠርተው ወደየሀገራቸው በተመለሱ ጊዜ ከኤጲስቆጶስነት ሹመት የተሻሩት ከሃድያኑ ወደ ኢየሩሳሌም የሚሄዱ መስለው ወጥተው ወደ አንጾኪያ ከተማ በአንዲት አመንዝራ ሴት ዘንድ ተሰበሰቡ፡፡ ለዚህችም አመንዝራ ሴት ብዙ ገንዘብ ለመስጠት ቃል ገብተው በአባ አንስጣስዮስ ላይ በሀሰት ነገር ሠሩበት፡፡ ሴቲቱ ወደ ቤተ ክርስቲያን ከገባች በኋላ አባ አንስጣስዮስ ከእርሷ ጋር እንዳመነዘረ የወለደችውም ልጅ የእርሱ እንደሆነ አስመስላ ለካህናቱና ለሕዝቡ ሁሉ እንድትናገር አግባብተው በገንዘብ ደለሏት፡፡ እርሷም ለሕዝቡ ይህን ስትናገር ሕዝቡ አላመናትም ነበርና ‹‹አንቺ ሀሰተኛ ነሽ በዚህ ቅዱስ አባት ላይም ሀሰት ተናግረሻል፣ በከበረ ወንጌል ምለሽ ተገዝተሽ ካልተናገርሽ በቀር ቃልሽን አንቀበልም›› አሏት፡፡ እርሷም ስለገንዘብ ፍቅር በሀሰት ማለች፡፡

ከዚህም በኋላ ከሃድያኑ ለንጉሡ ነግረውና በሀሰት ከስሰው አባ አንስጣስዮስን ከመንበረ ሢመቱ ወደ አጥራክያ ደሴት አሳደዱት፡፡ በስደትም ሳለ በዚያው ዐረፈ፡፡ ነገር ግን እነዚህ ከሃድያን የክብርን ባለቤት መድኃኔዓለም ክርስቶስን ከመለኮቱ ባሕርይ ለይተው ‹ፍጡር ነው› ብለውታልና ዳግመኛም ይህንን ንጹሕና ቅዱስ አባት አባ አንስጣስዮስን ከአምንዝራ ሴት ጋር አንድ ሆነው በሀሰት በዝሙት ከስሰው አሳደውታልና እግዚአብሔር ቸል አላላቸውም፡፡ አባ አንስጣስዮስን ካሳደዱት በኋላ ያች አመንዝራ ሴት ጭንቅ በሆነ ደዌ ተያዘች፡፡ ብዙ ዘመንም ተሠቃይታ ለሞት በደረሰች ጊዜ ይህ ሁሉ መከራ የደረሰባት በከበረ ወንጌል በአባ አንስጣስዮስ ላይ በሀሰት ስለመሰከረች እንደሆነ ተገነዘበች፡፡ በአንጾኪያም ሰዎች ሁሉ ፊት ኃጢአቷን ተናግራ በደሏን አመነች፡፡ እንዲህም አለቻቸው፡- ‹‹ይህ ቅዱስ አንስጣስዮስ ከዝሙት ንጹሕ ነው፣ እነዚያ ከሃድያን ብዙ ገንዘብ ሰጥተውኝ በእርሱ ላይ ሐሰት እንድድናገር በከበረ ወንጌልም በሐሰት እንድምል አድርገውኝ ነው፡፡››
የአንጾኪያ አገር ሰዎችም ኃጢአቷን ማመኗን በሰሙ ጊዜ እጅግ አዘኑ፡፡ ካህናቱም በጸሎትና በቅዳሴ ጊዜ የአባ አንስጣስዮስን ስሙን የሚጠሩ ሆኑ፡፡ ታላቁ የቤተ ክርስቲያን ሊቅ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅም አባ አንስጣስዮስን አመስግኖታል፡፡ በመታሰቢያውም ቀን ስለእርሱ ብዙ ቃላትን ደረሰ፡፡ ረድኤት በረከቱ ይደርብን በጸሎቱ ይማረን!
+ + +

አቡነ ዓምደ ሥላሴ:- አቡነ ዓምደ ሥላሴ የትውልድ ሀገራቸው ጎጃም ሲሆን በዐፄ ሱስንዮስ ዘመን የነበሩ ድንቅ ድንቅ ተአምራትን ያደርጉ የነበሩ ገዳማዊ መነኩሴ ናቸው፡፡ ጻድቁ ማኅበረ ሥላሴን ያቀኑ ታላቅ አባት ሲሆኑ በተለይም አንድ የሚታወቁበት ትልቅ ታሪክ አላቸው፡፡ እርሱም ዐፄ ሱስንዮስ ካቶሊካውያን ደግፈው 8ሺህ የሀገራችንን ሊቃውንት በአንድ ቀን ባሳረዱ ጊዜ ንጉሡ ወዲያው ‹‹ኦርቶዶክስ ይርከስ ካቶሊክ ይንገስ›› ብሎ ያወጀበት ምላሱ ተጎልጉሎ ወጣ፡፡ እንደ

Address

Dessie Town
Dese

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Yom Belay posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share