23/05/2026
ብሩኖ ፈርናንዴዝ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች ተብሎ ተመረጠ
*****************************
ፖርቹጋላዊው የማንቸስተር ዩናይትድ አማካይ ብሩኖ ፈርናንዴዝ የ2025/26 የውድድር ዘመን ምርጥ ተጫዋች ሽልማትን አሸንፏል፡፡
ብሩኖ ፈርናንዴዝ በውድድር ዘመኑ 20 አሲስቶችን በማስመዝገብ ሪከርዱን የተጋራ ሲሆን 8 ግቦችንም በማስቆጠር ማንቸስተር ዩናይትድ ወደ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ እነዲመለስ የጎላ አስተዋጽኦ አበርክቷል፡፡
ብሩኖ ፈርናንዴዝ ከ ኒማኒያ ቪዲች የ2011 የፕሪሚየር ሊጉ ምርጥ ተጫዋችነት ሽልማት በኋላ ይህን ሽልማት ያሸነፈ የመጀመሪያው የማንችስተር ዩናይትድ ተጫዋች መሆን ችሏል፡፡
በሀብተሚካኤል ክፍሉ