Mele sebona offiijantube

Mele sebona offiijantube You can get YouTube videos

22/09/2022
09/09/2022

🌻🌻🌻🌻🌻አበባየሆሽ ፣ እንቁጣጣሽ ፣ 🌻🌻🌻🌻አዲስ ዓመት🌻🌻🌻🌻 ፣ ዘመን መለወጫ🌻🌻🌻🌻፣ 2014 ፣🌻🌻🌻🌻 አውዳመት ፣ አመትባል🌻🌻🌻🌻🌻

09/09/2022

🌻🌻🌻🌻🌻የኢትዮጵያ - አዲስ አመት - እንቁጣጣሽ - አመትባል - አውዳመት - 2015 ETHIOPIAN New year ❤❤❤❤❤🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹 ምርጥ ምርጥ🌻🌻🌻🌻🌻 የአዲስ አመት ዘፈኖች🌻🌻🌻🌻....

" አልሸባብ ዳግም ከፍተኛ ኪሳራ ተከናንቦ ወደ መጣበት ተመልሷል " ሜጀር ጀኔራል ተስፋዬ አያሌውየሀገር መከላከያ ኃይል ስምሪት ኃላፊና ጊዜያዊ የፀጥታ ኮማንድፖስት አስተባባሪ ሜጀር ጄኔራል ...
30/07/2022

" አልሸባብ ዳግም ከፍተኛ ኪሳራ ተከናንቦ ወደ መጣበት ተመልሷል "

ሜጀር ጀኔራል ተስፋዬ አያሌው

የሀገር መከላከያ ኃይል ስምሪት ኃላፊና ጊዜያዊ የፀጥታ ኮማንድፖስት አስተባባሪ ሜጀር ጄኔራል ተስፋዬ አያሌው ወደ ኢትዮጵያ ሰርጎ ለመግባት የሞከረው የአልሸባብ የሽብር ቡድን በጸጥታ ኃይሉ በተወሰደበት እርምጃ ዳግም ከፍተኛ ኪሳራ ተከናንቦ ወደ መጣበት መመለሱን ተናግረዋል።

ከቀናት በፊት የአልሸባብ አሸባሪ ቡድን በሶማሌ ክልል በ5 ትናንሽ የጠረፍ አካባቢዎች ወደ አገር ውስጥ ሰርጎ በመግባት ጥቃት ለመፈጸም ያደረገው ሙከራ በጸጥታ ሃይሉ ሙሉ በሙሉ መክሸፉን ይታወሳል።

ይህን ተከትሎም የጸጥታ ኃይሉ ተቆርጠው የቀሩትን የሽብር ቡድኑ አባላትን የማጽዳት ዘመቻ ሲያከናውን መቆየቱን ገልፀዋል።

ባለፉት ቀን ከኢፌዴሪ አየር ኃይል ጋር በመቀናጀት በተወሰደው ርምጃ የሽብር ቡድኑ ኢትዮጵያን ለማጥቃት ያዘጋጃቸውን የትጥቅና ስንቅ ዴፖዎች ማውደም ተችሏል፡፡ በዚህም በሽብር ቡድኑ ላይ ከፍተኛ ኪሳራ እንደደረሰበት ጠቁመዋል፡፡

ነገር ግን የሽብር ቡድኑ ላይ የተበታተነ ኃይሉን በማሰባሰብ ኢትዮጵያና ሶማሊያ በሚዋሰኑበት አካባቢ ወደ አገር ውስጥ ሰርጎ በመግባት ጥቃት ለመፈጸም መሞከሮ ነበር።

ሆኖም የጸጥታ ኃይሉ በወሰደው እርምጃ የሽብር ቡድኑ ዳግም ከፍተኛ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራዎችን ተከናንቦ ወደ መጣበት መመለሱን ነው ያብራሩት፡፡

እስካሁን ባለው መረጃም ከ150 በላይ የሽብር ቡድኑ አባላት መደምሰሳቸውንና የሽብር ቡድኑ ለአጥፍቶ መጥፋት ያዘጋጃቸው ተሽከርካሪዎች መውደማቸውን ፣ የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች እንደተማረኩ አመልክተዋል።

በኢሳት ቴሌቪዥን ላይ የቀረቡት የኢትዮጵያ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄነራል ብርሃኑ ጁላ ኢትዮጵያ ሱዳንን አላጠቃችም ብለዋል‼️ጄነራል ብርሃኑ ኢትዮጵያ እና ሱዳን ያላቸው ትስስር ጥ...
28/11/2021

በኢሳት ቴሌቪዥን ላይ የቀረቡት የኢትዮጵያ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄነራል ብርሃኑ ጁላ ኢትዮጵያ ሱዳንን አላጠቃችም ብለዋል‼️

ጄነራል ብርሃኑ ኢትዮጵያ እና ሱዳን ያላቸው ትስስር ጥብቅ መሆኑን በመግለፅ ጎረቤት ሀገሯን ሱዳንን የምታጠቃበት ምንም ምክንያት የለም ሲሉ ገልፀዋል።

የድንበር ጭቅጭቅ አለ ይሄ የድንበር ጭቅጭቅ ኢትዮጵያ በሰላማዊ መንገድ ነው መፈታት ያለበት የሚል ፅኑ አቋም አላት ኢትዮጵያ አሁን ከጁንታው ጋር ጦርነት ላይ እያለች በጣም ብዙ ትርፍ ኃይል ኖሯት ሱዳንን የምታጠቃበት አይነት ቁመና ላይ አይደለችም ያለችው ሲሉ ተናግረዋል። መሬትን በተመለከተ በሰላምና በድርድር በህግ ይመለሳል ብለዋል።

ብዙ ጊዜ የመሬት ጭቅጭቅ መጨረሻ ፍርድ ቤት ነው የሚሄደው ይሄን ስለምናውቅ እኛ ሱዳንን የመተናኮል ፍላጎት የለንም ነገር ግን ሱዳን የመተናኮል ምልክቶች እያሳየች ነው፤ ጁንታውን በብዛት አስገብታለች እንደገና የታላቁ የህዳሴ ግድብን ለማደናቀፍ እየሰራች ነው እናውቃለን፤ እነሱ የላኳቸው ኃይሎች እየመጡ እየደመሰስናቸው ነው።

የራሳችንን ተላላኪ መደምሰስ እንጂ ለምን ትልካላችሁ ብለን ከሱዳን ጋር ወደአታካራ መግባት አንፈልግም ፤ ከሱዳን ጋር ግጭትም ጦርነትም አንፈልግም፤ ከሱዳን ጋር ያለን ግንኙነት እንዲሻሻል ነው የምንፈልገው በጣም ይሻሻላል ብለንም እናስባለን።

እንዳንድ የሱዳንን ህዝብ እና መንግስት የማይወክሉ ግን በሌላ ሶስተኛ ወገን የተገዙ የኢትዮጵያ እና ሱዳንን ግንኙነት ለማበላሸት የሚሰሩ አሉ ፤ እነማን እንደሆኑም ለይተን እናውቃቸዋለን፤ ታሪክ ይፈርዳል፤ የኢትዮጵያ እና የሱዳን ህዝብ ችግሩን በህዳሴ ግድብም ይሁን በመሬት ይገባኛል ጥያቄ ይፈታል ብለን ተስፋ እናደርጋለን ብለዋል።

የአሸባሪው ሕወሓት ድርጊት በአሜሪካ የተቀነባበረ ነው ሲል እንግሊዛዊው ጸሐፊ ግርሃም ፒብልስ ገለጸየአሸባሪው ሕወሓት ድርጊት በተባበሩት መንግሥታት ኤጀንሲዎች ውስጥ ያሉ አካላትን ጨምሮ በአሜ...
28/11/2021

የአሸባሪው ሕወሓት ድርጊት በአሜሪካ የተቀነባበረ ነው ሲል እንግሊዛዊው ጸሐፊ ግርሃም ፒብልስ ገለጸ

የአሸባሪው ሕወሓት ድርጊት በተባበሩት መንግሥታት ኤጀንሲዎች ውስጥ ያሉ አካላትን ጨምሮ በአሜሪካ እና በሌሎች የውጭ ኃይሎች የተደገፈ መሆኑን እንግሊዛዊው ጸሐፊ ግርሃም ፒብልስ ገለጸ፡፡

"ዘ ግሬት ትረስት"ን በማቋቋም በስሪላንካ፣ ኢትዮጵያ እና ህንድ የትምህርት ፕሮጀክቶች ላይ ትልቅ ስራ የሰራው በጎ አድራጊና ጸሐፊ ግርሃም ፒብልስ "በአሜሪካ የተቀነባበረው የኢትዮጵያ ግጭት" በሚል ርዕስ ካውንተር ፐንች በተሰኘ መጽሔት ላይ ሀተታ አስነብቧብ፡፡ አሸባሪው ሕወሓት በዲሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጠውን የኢትዮጵያ መንግሥት በኃይል ለመገልበጥ እና እንደገና ሥልጣን ለመያዝ እየሞከረ መሆኑን አንስቷል፡፡

ሙከራው በተባበሩት መንግሥታት ኤጀንሲዎች ውስጥ ያሉ አካላትን ጨምሮ በአሜሪካ እና በሌሎች የውጭ ኃይሎች የተደገፈ ነው የሚል እምነትም ያለው ሲሆን፤ ይህ ደግሞ ለአገርና ለአካባቢው ጥፋት ነው ሲል ድርጊቱን ኮንኗል፡፡ ግጭቱ የተጀመረው ሕወሓት ጥቅምት 24 በኢትዮጵያ በሰሜን እዛ ላይ በፈጸመው ክህደት መሆኑን ጸሐፊው ጠቅሷል፡፡

ይሁን እንጂ አሜሪካና፣ እንግሊዝ፣ የአውሮፓ ኅብረትና መሰል አገራት ከኢትዮጵያ መንግሥትና ሕዝብ ጎን መቆም ሲገባቸው ለአሸባሪው እየወገኑ ነው ብሏል፡፡ የኢትዮጵያን መንግሥት በሕገወጥ ለመተካት ከሚደረገው እንቅስቃሴ ጀርባ የባይ ደን አስተዳደር እንዳለ መረጃዎች በሰፊው እየወጡ እንደሚገኙም ገልጿል፡፡ የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ጄፍሪ ፌልትማን ይህን ሁሉ የተቀነባበረ ድርጊት ይክዳሉ ነው ያለው፡፡

ወደ ግንባር ለሚዘምቱ የኢዜማ አመራሮች ሽኝት ተደረገ  ‼️  ከአዲስ አበባ ከተማ ወደ ግንባር ለሚዘምቱ የኢዜማ አመራሮች በዛሬው ዕለት አሸኛኘት ተደርጓል።  የኢዜማ ሊቀመንበር አቶ የሽዋስ ...
26/11/2021

ወደ ግንባር ለሚዘምቱ የኢዜማ አመራሮች ሽኝት ተደረገ ‼️

ከአዲስ አበባ ከተማ ወደ ግንባር ለሚዘምቱ የኢዜማ አመራሮች በዛሬው ዕለት አሸኛኘት ተደርጓል።

የኢዜማ ሊቀመንበር አቶ የሽዋስ አሰፋ አመራሩ ወደ ግንባር በመሄድ ሰራዊቱን ያበረታታል አባላቱ ደግሞ ወደ ስልጠና በመግባት መከላከያውን ተቀላቅሎ ለአገሩ እንደሚቆም ገልጸዋል።

ኢዜማ የኢትዮጵያን ነጻነት ለማስጠበቅ ሁልጊዜም ከፊት ይሰለፋልም ነው ያሉት።

ወደ ግንባር የሚዘምቱ አመራሮችም ኢትዮጵያ ፈተና ውስጥ በምትሆንበት ጊዜ መስዋዕትነት መክፈል ከጥንት ጀምሮ በደማችን ያለ መሆኑን በመጥቀስ፥ በድል እንደምንመለስም እርግጠኞች ነን ብለዋል።

Address

Keble 04 Street
Woliso

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Mele sebona offiijantube posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Mele sebona offiijantube:

Shortcuts

Share