Elias official

Elias official ይህ የግል አስተያይቴ የሚቀርብበት ፔጅ ነው

15/07/2022
15/07/2022

እመቤቴ የጌታዬ እናት ሆይ የአንቺን ‛ይሁንልኝ’ የሚል ቃል ተከትሎ እግዚአብሔር ሰው ሆነ ። ሰው ሆኜ ተፈጥሬ ሰው መሆን ያቃተኝን እኔንስ ሰው የምታደርጊኝ መቼ ይሆን ? አምላክ ሰው እንዲሆን ይሁን ያልሺዋ ቅድስት ሆይ ስለ እኔ ሰው መሆን ‛ይሁን’ የምትዪው መች ይሆን ? ‛ በርታ ሰውም ሁን ’ የሚለውን ቃል መጠበቅ አቅቶኝ ኃጢአት ሠልጥኖብኝ ' ሰው ክቡር ሆኖ ሳለ አላወቀም እንደሚጠፋ እንስሳት መሰለ' የሚያሰኝ ሕይወት ለምኖረው ለእኔ ፣ እንደ ቃሉ መሆን ላቃተኝ ለኔ ወደ መሐሪው ልጅሽ ’ ይህ ኃጢአተኛው ባሪያህ እንደ ቃልህ ይሁንልኝ ’ ብለሽ እኔንም እንደ ቃሉ የምታደርጊኝ መች ይሆን ?
🤲

♣ከረፈደ      ✍በ ኪዲ ጥሊ ከረፈደ             ሰዉ ሲደነግጥ በየትኛዉ የአእምሮ ክፍል እንደሚያስብ አይገባኝም ብቻ በፍጥነት መሪዉን ወደ ቀኝ ጠምዝዤ መኪናዉን  ከአንድ ትልቅ ግቢ...
15/07/2022

♣ከረፈደ

✍በ ኪዲ ጥሊ



ከረፈደ


ሰዉ ሲደነግጥ በየትኛዉ የአእምሮ ክፍል እንደሚያስብ አይገባኝም ብቻ በፍጥነት መሪዉን ወደ ቀኝ ጠምዝዤ መኪናዉን ከአንድ ትልቅ ግቢ አጥር ጋር አላተምኩት። ሁሉም ነገር በፍጥነት የተከናወነ ስለነበር ምን እንደተፈጠረ የተረዳሁት እራሴን ከድንገተኛ ክፍል አልጋ ላይ ሳገኘዉ ነበር። ማን እንደደወለላቸዉ ባላዉቅም አከራዬ ወ/ሮ ሙሉ አቶ እንዳለና ከመገጨት ያዳንኳት ቆንጆ ሴት በታላቅ ድንጋጤና መጨነቅ ከአጠገቤ ቆመዉ ነበር። ዶክተሩ ለጤናዬ አሳሳቢ ነገር አለመኖሩንና እራሴን የሳትኩትም ከድንጋጤ የተነሳ መሆኑን እንዲሁም እረፍት እንደሚያስፈልገኝ ነግሮ አንዳንድ ቁስሎቼ ላይ ፕላስተር ካደረገልኝ በሗላ ወደ ቤት መሄድ እንደምችል ነገረኝ። ለማንኛዉም እባላለሁ ብላ እጇን ዘረጋችልኝ መናገር የቻልኩት ይሄን ብቻ ነበር። ከፍተኛ ድንጋጤ ላይ ስለነበርኩ ስሜን ከመናገር ዉጪ ቃል ሊወጣኝ አልቻለም።>>
እንዲህ ባለ እራስን ሰዉቶ የሰዉን ህይወት በማዳን አጋጣሚ ከ ሔርሜላ ጋር ፍቅር ከጀመርን ሁለት አመታትን አስቆጠርን። ያለፈዉን ትዝታና የጠዋቱን ዱካክ ወደ ሗላ ጥዬ ያለችኝ ፍቅሬን ለመቀበል ከአልጋዬ ላይ ወረድኩ...

እድሜ ለሔርሜላ ቤቴን የቤት ቅርፅ አስይዛልኛለች። እርሷ ወደ ቤቴ መምጣት ከጀመረች ግዜ አንስቶ ቤቴ በየእለቱ በአዳዲሰ ሀሳቦችና እቃዎች ተሟልታለች!
የተኛሁበትን አልጋ አነጣጥፌ እንደጨረስኩ ቤቴ በሀይል ተንኳኳ
ወ/ሮ ሙሉ ነበሩ!
አልኳቸዉ በሩን በሀይል ሲያንኳኩ ስለነበር በድንጋጤ አሉና የጠዋት ፈገግታቸዉን ቸሩኝ። ወ/ሮ ሙሉ ቀላ ብለዉ ወፈር ያሉ የእናትነት ገፅታቸዉ ከፊታቸዉ ላይ የሚነበብ በሀዘንና በለቅሶ ብዛት ፊታቸዉ ላይ የተወሰነ ማድያት ጣል ጣል ያደረገባቸዉ የ 45 አመት ጎልማሳ ናቸዉ። በስደት ከሀገር ለመዉጣት ሲሞክር ህይወቱ ያለፈ ብቸኛ ወንድ ልጅ ስለነበራቸዉ እሱን እንደምመስል ይነግሩኛል! የልጃቸዉ የ40 ቀን መታሰቢያ ሰሞን ቤቱን ስለተከራየሁ የልጄ ምትክ እያሉ ይጠሩኛል።
መርካቶ ላይ የልብስና የህንፃ መሳሪያ መደብር የሆነ ግዙፍ ሱቅ አላቸዉ። ከሚኖሩበት ባለ አንድ ፎቅ ህንፃ በተጨማሪ ሶስት የሰርቪስ ክፍሎች ሲኖሩ ከሶስቱ አንዱ ሟች ልጃቸዉ ይኖርበት የነበረና አሁን በእኔ ተከራይነት የተያዘ ነዉ። በእርግጥ ቤት የማከራየት ፍላጎት እልነበራቸዉም በስህተት የእሳቸዉን ግቢ አንኳኩቼ ፊቴ ከሟች ልጃቸዉ ጋር ይመሳሰልባቸዉና ያለምንም ማንገራገር ልጃቸዉ ይኖርበት የነበረዉ ባለ አንድ መኝታ ክፍል አከራዩኝ። የቤት ኪራይ ገንዘብ አልቀበልህም ማለት ከጀመሩ 5 ወር ያህል ሊሞላቸዉ ነዉ ከእናትነት ፍቅራቸዉ በላይ ዉለታቸዉ ስለከበደኝ አልቀበልም በሚሉኝ ገንዘብ የሆነ ስጦታ እየገዛሁ አመጣላቸዋለሁ እሷቸዉ ባይፈልጉትም። ያልገባኝ ነገር ቢኖር ጥሩ እናትና የገንዘብ ችግር የሌለባቸዉ ሆነዉ ሳለ ብቸኛ ወራሽ ልጃቸዉ ለምን ስደትን እንደመረጠ ነዉ?
አሉና እጄን አየጎተቱ የለሊት ልብሴን እንኳን ለመቀየር እድል ሳይሰጡኝ ወደ ሳሎናቸዉ ይዘዉኝ ገቡ...


💛💛💛💛ክፍል 3 ቶሎ እዲቀጥላል❤❤❤❤
Like
ሼር

♥እጅግ ጠቃሚ♥በሥነ-ልቦናው ዘርፍ የተገኙ ስኬቶች በሥራ አካባቢ ውጤታማ ያደርጋሉ የሚለውን ግኝት ከግምት ውስጥ በማስገባት የለንደን ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎቹ ኢየን መክሪ እና ኤድሪየን ፈርሃም...
15/07/2022

♥እጅግ ጠቃሚ♥
በሥነ-ልቦናው ዘርፍ የተገኙ ስኬቶች በሥራ አካባቢ ውጤታማ ያደርጋሉ የሚለውን ግኝት ከግምት ውስጥ በማስገባት የለንደን ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎቹ ኢየን መክሪ እና ኤድሪየን ፈርሃም በተሰማሩበት ሙያ ስኬታማ የሚያደርጉ ስድስት የስብዕና መገለጫዎችን አስቀምጠዋል።

መክሪ እንደሚለው እያንዳንዱ መገለጫዎች የራሳቸው የሆነ ውስንነት እና ጠንካራ ጎን አላቸው። ስለዚህ የእያንዳንዱ መገለጫ ጥቅም የሚወሰነው ግለሰቦች በሚሰሩት ሥራ ላይ ስለሆነ መለኪያው ከእያንዳንዱ ሁኔታ ጋር ይቀያየራል።

ይህንን ከግምት ውስጥ በማስገባት እነዚህ ስድስት የስብዕና መገለጫዎች እንዴት ወደ ስኬት እንደሚወስዱ አመላእተዋል።

1. ጠንቃቃነት

ጠንቃቃ ሰዎች ሁሌም እቅዳቸውን በትክክል ይተገብራሉ።
የእያንዳንዱ ውሳኔያቸው የወደፊት ውጤት ተጽዕኖን ያውቃሉ። ስሜታቸውንም መቆጣጠር ይችላሉ። ይህ የጠንቃቃነት ባህሪ በህይወትዎ ስኬታማ ለመሆን ወሳኝ ነው።

በሥራ አካባቢ ለትንሽ ነገሮች ትኩረት መስጠት ስልታዊ በሆነ መልኩ እያንዳንዱን ሥራ ለማቀድ ይጠቅማል።

2. ከነገሮች ቶሎ መላመድ

ሁሉም ሰው የሚያስጨንቀው ነገር ያጋጥመዋል፤ ዋናው ጥያቄ ግን እንዴት ያልፈዋል የሚለው ነው። ይህ ማለት ሥራዎት እና ሌላ ህይወትዎ ላይ ጫና እንዳሳያሳድር ለመላመድ መሞከር ማለት ነው።

ይህ ባህሪ የሌላቸው ሰዎች የሥራ አካባቢ አፈጻጸማቸው ደካማ ነው። ነገር ግን ተገቢውን የሥነ-ልቦና እርምጃ ከወሰዱ ውጤታማ መሆን ችላሉ።

ብዙ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ውጤታማ ለመሆን ሲባል አስጨናቂ ጉዳዮች ላይ በደንብ ትኩረትን መስጠት ከተቻለ፤ በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ያለ ሰው ያሰበውን ነገር ማሳካት ይችላል።

3. ግራ መጋባትን አምኖ መቀበል

የማያውቁትን ነገር የማይፈሩ እና ግራ መጋባትን አምነው የሚቀበሉ ሰዎች የተሻለ ውሳኔ ለመወሰን ይችላሉ። ብዙ ነገሮችንም ከግምት ውስጥ ያስገባሉ።
እንደዚህ አይነት ሰዎች ትንሽ የምትባለው ነገር ትርጉም እስከምትሰጣቸው ድረስ ስለሚጨነቁ የራሳቸውን ውሳኔ የመጨረሻ አድርገው ሊወስዱ ይችላሉ።
ግራ መጋባትን አምኖ መቀበል የሚችል ሰው ለማንኛውም አይነት ለውጥ ሁሌም ዝግጁ ነው።

4. ጉጉ መሆን

ጥናቶች እንደሚያሳዩት የማናውቀውን ነገር ለማወቅ ያለን ጉጉት ሁሌም አዲስ ነገር ለመፍጠር ይረዳናል። ይህ ማለት ለአዳዲስ ነገሮች ክፍት የሆነ ጭንቅላት አለን ማለት ሲሆን፤ በምንሰራው ሥራ ደስተኞች እንድንሆን ይረዳናል።

5. አስቸጋሪ ሁኔታዎችን መቋቋም

ደስ የማይል ነገር ሲያጋጥምዎት ለጊዜው ስለቀለልዎት ብቻ ዝም ብለው ያልፋሉ ወይስ ምቾት ባይሰጦትም ጉዳዩን ተጋፍጠው ዘላቂ መፍትሄ ለማምጣት ይሞክራሉ?
ከአስቸጋሪ ሁኔታዎች ጋር እራስን ማላመድ መቻል ወደፊት ወደ አመራር ቦታ እንድንመጣ እና ለብዙ ነገሮች ውሳኔ መስጠት እንድንችል ይረዳናል።

6. ተፎካካሪ መሆን

ለስኬት ሲባል የሚደረግ ትንቅንቅ እና ጤናማ ያልሆነ ፉክክር ወይም ቅናት ትልቅ ልዩነት አላቸው።
ፉክክር ሁሌም ለበለጠ ሥራ የሚያነሳሳ ሲሆን፤ ተጨማሪ ጥረት እንድናሳይና እቅዳችንን እንድናሳካ ሊረዳን ይችላል። ሲበዛ ግን የቡድን ሥራዎችን ያስተጓጉላል።

እነዚህ ስድስቱ ባህሪያት በአንድነት በሥራ ገበታችን ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ አላቸው። በተለይ ደግሞ ወደ አመራር ቦታ መምጣት ለሚፈልጉ ሰዎች።

ከላይ የተዘረዘሩት የሰዎች ባህሪያት በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ የሥራችንን ፍሬ እና ውጤታማነታችንን ለመለካት ይረዱናል።
በመጨረሻም ተፎካካሪነት እና ግራ መጋባትን አምኖ መቀበል ከሁሉም በተሻለ ተቀባይነትን ያገኙ ሲሆን፤ የተሻለ ገቢ እንደሚያስገኙም ተጠቁሟል።

ሸር ሸር ሸር

🚺🚺  !   #ይነበብ 🚹🚹አንድ ቀን ነው ፤ ዶሮ ፣ ፍየል ፣ በሬና ሰው በአንድ ቤት ውስጥ አብረው ነበሩ። ከዛ እባብ ቀስ እያለ ወደ ቤቱ ሲገባ መጀመርያ ዶሮዋ ነበር ያየችው "እኔ ምን አገ...
15/07/2022

🚺🚺 ! #ይነበብ 🚹🚹

አንድ ቀን ነው ፤ ዶሮ ፣ ፍየል ፣ በሬና ሰው በአንድ ቤት ውስጥ አብረው ነበሩ። ከዛ እባብ ቀስ እያለ ወደ ቤቱ ሲገባ መጀመርያ ዶሮዋ ነበር ያየችው "እኔ ምን አገባኝ ጣራ ላይ ስለወጣሁ አይደርሰኝም" በማለት እባብ እየመጣ እንደሆነ ሳትነግራቸው ዝም አለች። እባቡ እየተቃረበ መጣ።

በመቀጠል ፍየሏ ነበር ያየችው ። "መቼም ቤትን የምያኽል ትልቅ በሬ እያለ እኔን ይበላኛል ብሎ ማሰብ ሞኝነት ነው ። ስለዚህ ምን አገባኝ መምጣቱን ይሁን መግባቱን የሚያስጨንቀኝ" ብላ ዝምታን መረጠች ።

አሁንም እባቡ እየቀረበ መጣ መጨረሻ ላይ ትልቁ በሬ እባቡን መግባቱ ተመለከተ ። እሱም እባብ ቤቱን እንደገባ ከማሳወቅ ይልቅ በጉልበቱ የሚተማመን ስለነበረ "ቢገባስ ምን አገባኝ ፤ እኔን ምን እንዳይጎድለኝ ፤ ቢነድፍ ሰውዬው እንጂ እኔን ዞር ብሎ አያየኝም ትልቅ መሆኔ እያየ አይደፍረኝም" ብሎ እንደሌሎቹ ሳያሳውቃቸው ቀረ ።

በሚያሳዝን ሁኔታ ግን እባቡ ያሁሉ ክፍተት ስላገኘ ተኝቶ ዓለሙን በእንቅልፍ ልቡ ሲዋኛት ለነበረ ሰውዬው እግሩን ነደፈው ።

በሁኔታው በጣም የተደናገጠ፤ሰውየው ከእንቅልፉ በሰከንዶች ተነስቶ"ኡ ኡ ኡ..." በማለት ጩኸት ማሰማት ጀመረ ። እንዳለ ጎረቤቶቹ ምን አገኘው በማለት ግልብጥ ብለው መጡ ። ታላቆች ተጠርተው እባብ እንደነደፈው ሲነግራቸው ፤ ሰውዬው እንዴት መፈወስ እንዳለባቸው መመካከር ጀመሩ ።

ከዛ አንድ ታላቅ አባት ተነስተው ዶሮዋ በተነደፈው እግሩ እንዲያስቀምጧትና መርዙን በአፏ ስባ እንድታወጣው መከሩ ። ትልቁ አባት ያሉትን ሰምተው ነገሩን ሞኮሩት ፤ ሰውዬው ግን ተጨማሪ መድኃኒት ሳያስፈልገው አልቀረም ጨርሶ አልዳነም። ዶሮዋም መርዙን ስለሳበችው ሞተች እንጂ "ምን አገባኝ" ማለቱ አልጠቀማትም።

ቀጥሎውም የፍየል መረቅ እባብን የተነደፈ ሰው ከጠጣው ፍቱን መድኃኒት መሆኑ ከመኸል በመነሳት አንድ አባት ተናገሩ ። ድጋሜም እንሞክረው በማለት ፍየሏ ታረደችና በመረቅ መልኩ ለታመመ ሰውዬ አቀረቡለት ። ፍየሏም "ምን አገባኝ" ማለቱ ለራሷ ጥሩ አልገጠማትም ።
ታማሚው ባሉት መሠረት መረቁ አንድ ሳያስቀር ጠጣው ። ጭራሽ ግን ለውጥ አልነበረውም ፤ ልያገግም ባለመቻሉ እንዲሁም ሕመሙን
እየበረታው ስለመጣ መቋቋም አቃተውና ወደ የዘላለሙ ቤታችን በሰላም ሄደ። መላ ቤተሰቦቹና ወዳጆቹ አልቅሰው አለቃቅሰው # RIP ብለው ሸኙት ዓለም ምን ዋጋ አላትና ።

"ማን አባቱ ቀና ብሎ ያየኛል"እያለ ሲፎክር የነበረ ታላቁ በሬም ከሞት ልያመልጥ አልቻለም ። ቀኑ መሮጡን አላቆመምና ሟቹ
80(ሰማንያ)ቀኑ ደረሰ። ለተዝካሩ ይሆን ዘንድ እንደባህላችን መሠረት እህልና ውኋ ማጥፋት የግድ ነበረና በሬ መታረድ ስለነበረበት ታላቁ በሬ "ምን አገባኝ ማለት"ቄራ ሳያገባው አልቀረምና ነው።
ለማለት የፈለግሁት ሁላችን ኢትዮጵያውያን እርስ በርሳችን ተግባብተን "አንዱ ሲጎዳ ስናይ" ጉዳቱ የሁላችን መሆኑ እናስብ። ዛሬ አንዱን ሲጨንቀው ሲቸገር አይተን እንዳላየን ሰምተን እንዳልሰማን ችላ ብለን ካለፍነው ፤ ጊዜው ጠብቆ ችግሩ ወደ'ኛም እንደሚመጣ አንዳንረሳ። እንተጋገዝ እንተዛዘን እንተባበር እንመካከር ልዪነታችን ውበታችን ነው።

ምርጥ መጣጥፎች
ሼርርርር

ቆንጆልጅ  አግብቶ  ሆዴን ከማለት    ፉንጋዎን አግብቶ  ጠግቦ  መተኛት......
15/07/2022

ቆንጆልጅ አግብቶ ሆዴን ከማለት
ፉንጋዎን አግብቶ ጠግቦ መተኛት......

ፍቅርና እምነትክፍል ሁለት(2)   በስልክ ለወራት የቆየው ግንኙነት በአካል ለመገናኘት ስአታት ቀርተውታል .... ብሌን ውስጣ ቢፍራባትም ለወራት በስልክ ካላገኝሁሽ እያለ ሲያስጨንቃት የነበር...
15/07/2022

ፍቅርና እምነት

ክፍል ሁለት(2)

በስልክ ለወራት የቆየው ግንኙነት በአካል ለመገናኘት ስአታት ቀርተውታል .... ብሌን ውስጣ ቢፍራባትም ለወራት በስልክ ካላገኝሁሽ እያለ ሲያስጨንቃት የነበርውን ስው ለማየት ግን ጓጉታለች . አጋጣሚ ሆኖ እህቷ ሳራ መጣች ለወራት ያክል እራሳን ስትጠብቅና ለመውጣት ስትጣደፍ አይታት ስለማታውቅ ነገሩ አስገርሟት ..እህ ውዷ እህቴ ወዴት ነው እባክሽ ..አለቻት ፍገግ እያለች ብሌንና ሳራ በጣም ይወደዳሉ እህትማማችነታቸው በጣም ያስቀናል ያንዷ ደስታ አንዷን ያስደስታታል ..ብሌንም ለሳራ የሆነውንና ማንን ለማግኝት እንደምትሄድ ነገረቻት ሳራም እሽ ብላ ለአለባበሷ አስተያየት ስጥታት እራስሽን ጠብቂ እሽ ብላት ትታት ወጣች ,ብሌን ግን አሁንም ውስጧ ተርብሾባታል ምን አይነት ይሆን እያለች እራሷን በጥያቄ ታጨናንቀዋለች.
ቶማስ በበኩሉ እሷን ለማየት ካለው ጉጉት የተነሳ ከቀጠሮው ስአት ቀድሞ ለመገኝት ወደ ቦታው አመራ ድንገት የሆነ ነገር አስበ እሱም ሳያት እንዳውቃት ለምን ምን እንደምትለብስ ደውዬ አልጠይቃትም አለ ግን ፍራ የግዱን እንደምንም ብሎ ደወለላት ስላም ካላት በኃላ ስንገናኝ ምን ግራላለመጋባት ያክል ምን እንደምትለብሺ ልጠይቅሽ ብዬ ነበር ይቅርታ ግን አላት እሷም በመገርም የለበስችውን ነገርችው እሽ ብሎ ስልኩን ዘጋው። የቀጠሮው ስአት ሲደርስ ወደ ቦታው ሄደች ግራ በመጋባት ስሜት በረንዳው አንዱን ወንበር ስባ ቁጭ አለች ,ቶማስ ከውስጥ ሆኖ አይቷት ስለነበር ወደ እሷ ለመሄድ ተነሳ .
ብሌን የፀይም ቆንጆና እረዘም ያለች ፀጉሯን ፍሬዝ ማድርግ የምትወድ በፍገግታዋ ስው ገዳይ ያያት ሁሉ የሚመኛት አይነት ሴት ናት .
ቶማስ ወንዳወንድና ቀይ የሚባል ከለር ያለውና እርዘመ ያለ ቁመት ያለውና የሆነ ድንገት የሚስብ ነገር ያለው ወንድ ነው ።
ቶማስ ወደ ብሌን ወንበር አመራ ስታየው ግራ ገባት ከመቀመጫዋ ተነስታ ስላም ካለችው በኃላ አጠገቧ ተቀመጠ ባየው ነገር በጣም ተደስቷል ከጠበቃት በላይ ሆና ነው ያገኛት ምናለፍችሁ በቃ የተለየ የደስታ ስሜት ተስማው ይቼ ናት የኔ ብሎ ለራሱ ነገርው ።
ብሌን ነገር ስራው ሁሉ ነገሩ ቢስባትም ቆንጆ የሚባሉ ወንዶችን መቅርብ ትፍራለች ግን ስለተዋወቀችው ደስ አላት.
ሁለቱም ጁስ እዘዙ እሷ አብካዶ በ ማንጎ እሱ ደግሞ አቦካዶ በቪንቶ ነበር ያዘዙት 'ለደቂቃዎች ያክል በሁለቱም በኩል ዝምት ነገስ ሁለቱም አንገታቸውን አቀርቅረው ዝምታን መርጠዋል .
ቶማስ ዝምታው ለመግፍፍ ያክል ተጫወች አላት እሽ ብላ እንዳንድ ነገሮችን ስለሱም ስለሷም ስለ ስራ ስለ ቤተስብ ከተነጋገሩ በኃላ ሂሳባቸውን ከፍለው በስላማዊ መልኩ ለመለያየት ሲሉ ቶማስ መኪና ይዞ ስለነበር ወደ ቤት እንዲያደርሳት ጠየቃት እሷም እሽ ብላ ወደ ቤት ሲሄዱ ከዚህ በኃላ በጋደኝነት አብረው እንደሚሆኑና ስልክም እንደሚደዋወሉ ተነጋግርው ተለያዩ።
ብሌን እቤት ገብታ ለእህቷ የተፍጠረውን ሁሉ ነገረቻት በጣም የመደስት ስሜት ይታይባታል
ቶማስ ወደ ቤት እየሄደ በጣም ከመደስቱ የተነሳ "አበራሁኝ ሻማ ሞቅ አለ ጎጆዬ ...." የሚለውን ዘፈን በረዥሙ ከፍቶ ወደ ቤቱ አመራ......

ክፍል 3 ይቀጥላል...

ሀሳብ አስተያየታቹ አይለየን!

15/07/2022

በብዙ ነገር ተስፋ ልትቆርጥ ትችላለህ
በፈጣሪህ ግን ተስፋ አትቁረጥ
አልሰጠኝም ቆንጆ አላደረገኝም አልሰማኝም ....
ብለህ ፃሎትህን አትተው ምክንያቱም 10 ዓመት የጠየቅኽውን በ1 ደቂቃ ሊያሳካክህ ይችላልና
"ባለተስፋው የኔ ትውልድ"

🥀🥀    ከረፈደ   🥀🥀እነሆ ጀመርን መልካም ንባብ እንደምትወዱት ተስፋ እናደርጋለን like ና share አይለያችሁ''በእዉነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ''                       ...
14/07/2022

🥀🥀 ከረፈደ 🥀🥀

እነሆ ጀመርን መልካም ንባብ እንደምትወዱት ተስፋ እናደርጋለን like ና share አይለያችሁ

''በእዉነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ''

ከረፈደ ክፍል አንድ (1)

ያለ እረፍት የሚጮኸዉ የስልኬ ጥሪ ከተኛሁበት አነቃኝ ማልዶ የመነሳት ልምድ ስለሌለኝ የስልኬ ጥሪ አልያም ደግሞ አከራዬ ወይዘሮ ሙሉ ቤት የሚከፈተዉ መዝሙር ይቀሰቅሰኛል። እንደምንም ስልኬን አንስቼ አልኩኝ ሔርሜላ ነበረች

አለችኝ! ድምጿ የተለየ መስህብ ነበረዉ! ሁልጊዜም ድምጿን ስሰማ የማላዉቀዉ የተስፋ ክምር በልቤ ላይ ይፈጠራል።

አልኳት ከእንቅልፌ ለመላቀቅ እየታገልኩ። መስከረም 1 2008 ዓ/ም የአዲሱ አመት የመጀመሪያዋ ቀን እጅግ በማፈቅራትና በማከብራት ሴት የመልካም ምኞት ብስራት ሀ ተብሎ ተጀመረ። ከ አንድ ሰዓት በሗላ እንደምትመጣና ተነስቼ እንድጠብቃት ቀጭን ትእዛዝ አስተላልፋልኝ ስልኩን ዘጋችዉ።
የወፎች ድምፅ ይሰማኛል ብሩህ ሰማያዊ ሰማይ ለስለስ ብሎ ሙዚቃዊ ስልቱን ጠብቆ ዛፎቹን ከግራ ወደ ቀኝ ከሚያስደንስ የጠዋት ንፋስ ጋር ለወራት ደምቃ ለመዉጣት ደመና ከጋረዳትና በቅርቡ ከደመና እስር ተላቃ ፍንጥቅ ብላ ከወጣች ፀሀይ ጋር ተዳምረዉ የአዲሱን ዓመት የመጀመሪያዋን ቀን ፀአዳ አልብሰዋታል...

በአንድ የግል መስሪያ ቤት ዉስጥ በሾፌርነት በወር 3500 ብር እየተከፈለኝ እሰራለሁ። የመስሪያ ቤቱን ሀላፊ አቶ እንዳለን ከቦታ ወደ ቦታ ማንቀሳቀስ ስለሆነ አብዛኛዉን ግዜ ስራ አይበዛብኝም መኪናዉም እኔ ጋር እንዲያድር ፈቃድ ተሰጥቶኛል። የመኪናዉ የሰርቪስ ቀን አልፎ ፍሬን ለመያዝ ያስቸግር ነበር ከዛሬ ነገ ሰርቪስ ይደረጋል እየተባለ ቀናቶች ሳምንቶች አልፈዉ የመኪናዉን ህመም ለማከም ችላ እንደተባለ አንድ ቀን ጠዋት አቶ እንዳለ ደዉለዉ በጠዋት ቢሮ መግባት እንዳለባቸዉና እቤት ድረስ መጥቼ እንድወስዳቸዉ ትዕዛዝ ሰጡኝ። የሚል አመለካከት ስላላቸዉ በመስሪያ ቤት ዉስጥ እንደ ሀላፊ ሳይሆን ሁሉም እንደ ወላጅ አባት ይቆጥራቸዋል። ወደ አቶ እንዳለ ቤት የሚወስደዉን ዋናዉን አሰፋልት ጨርሼ ወደ ቤታቸዉ የሚወስደዉን ቁልቁለታማ መንገድ ተያይዤዋለሁ ድንገት ከአንድ መታጠፊያ ዉብ የሆነች ጠይም ሴት እየሮጠች ከመኪናዉ ፊት ለፊት ድቅን አለች የመኪናዉን ፍሬን ለመያዝ ብሞክር መኪናዉ ሊቆም አልቻለም!! ህይወት እንዲህ ያሉ ክፉ ገጠመኞችን ለምን በማለዳ እንደምትሰጥ የማይፈታ እንቆቅልሽ ነዉ ለመጀመሪያ ጊዜ ከድንጋጤ ጋር ፊት ለፊት ተፋጠጥኩ....

💛💛💛💛ክፍል 2 ይቀጥላል....❤❤❤

🚹🚺 ጠቃሚ የህይወት መርሆች! 🚺🚹✴✅ ደግ ሁን የምትችል ከሆነ ከማንም የበለጠ ደግ ሁን፤ ቢሆንም ደግነትህን አትናገር!! ስለተረፈህ ሳይሆን ሰብአዊነት ኖሮህ ላንተ ከሚያስፈልግህ ሳትሰስት ለ...
14/07/2022

🚹🚺 ጠቃሚ የህይወት መርሆች! 🚺🚹

✴✅ ደግ ሁን

የምትችል ከሆነ ከማንም የበለጠ ደግ ሁን፤ ቢሆንም ደግነትህን አትናገር!! ስለተረፈህ ሳይሆን ሰብአዊነት ኖሮህ ላንተ ከሚያስፈልግህ ሳትሰስት ለሌሎች አካፍለህ ኑር! መስጠት የማያውቁ ሰዎች ሌሎች ሲሰጡ ይታመማሉ!!

✴✅ ቀና ብለህ ተጓዝ

ዘወትር ቀና ብለህ ተጓዝ ምክንያቱም ራሱን ያጎበጠ ሰው መቼም ሌሎችን አቅንቶ አያውቅምና

✴✅ ችግሮችህን አስብ

የገጠሙህን ችግሮች ችላ አትበላቸው ምክንያቱም ችግርን በጥቅም ላይ እንደማዋል ጣፋጭ ነገር የለምና!!

✴✅ እውቀትን የምትሻ ሁን

ከሌሎች ሰዎች ለማወቅ የተዘጋጀህ ሁን ምክንያቱም የእብደት የመጀመሪያ ምልክት እራስን አዋቂ አድርጎ ማሰብ ነውና!

✴✅ መልካም አሳቢ ሁን

ሁሉም ሰው ራሱን የሚያገኘው በየእለቱ በሚፈጥረው አስተሳሰብ መሠረት ነው መጥፎ ቀን የምንለው መጥፎ ሃሳብ ያሰብንበት ቀን ነው ስለሆነም ሁሌም መልካም ነገር እንዲገጥምህ መልካም የሆነውን
ብቻ ተመልከት

✴✅ የቁሳዊ ድህነትን አትፈርበት

የቁሳዊ ድህነትን አትፈርበት ምክንያቱም ምድር ላይ እጅግ የሚያሳፍረው ነገር ቢኖር የአዕምሮ ድህነት ነውና!!

✴✅ ለገባኸው ቃል ታመን

ቃል ለመግባት የዘገየህ፤ ከገባህ ደግሞ የፈጠንክ ሁን!!

✴✅ ራስህን አሻሽል

የአንተን ውድቀት ለሚመኙ ስትል ራስህን አሻሽል!!

✴✅ መጀመሪያ ራስህን እወቅ

ጠንካራ ጎኖችህን ይበልጥ አጠንክርህ በድክመትህ ላይ ፈጥነህ ዝመትባቸው!!

✴✅ ህሊናህን አድምጥ

የተፃፈውን ሁሉ አንብበህ በህሊና መዝገብህ ከመፃፍህ በፊት በህሊናህ ሚዛንህ አብጠርጥር!! ሁሌም ለሕሊናህ እንጂ ለሰው አትገዛ ምክንያቱም የሰው ልጅ ዛሬ ወዳጅ መስሎ ቀርቦ ነገ ሊሸሽህ ይችላል ህሊናህ ግን በፀፀት እየወቀሰህ ዘወትር አብሮህ ይኖራልና!

✴✅ አንደበተ ርቱህ ሁን

ምላስህን ካልጠበካት እስዋ አትጠብቅህም!!"
ጨዋ አንደበት የተዘጉ በሮችን ይከፍታል!!

✴✅ ብልህ ሁን

መከራን እና የተወረወረ ድንጋይን ዝቅ ብሎ ማለፍ ብልህነት ነው
ምክንያቱም ምድር ላይ ስትኖር ለመኖር መፈተን ለማለፍ መታገስ ግድ ነውና!

✴✅ ሁልጊዜ ራስህን ሁን

ራሱን ያወቀ ሰው ሁልጊዜ በኑሮው ደስተኛ ነው!! ሌላውን ለመምሰል ስትሞክር ማንነትህን ታጣና ህይወት ጣእሟን ታጣለች

✴✅ ሞራል ይኑርህ

የማይዋዥቅ የህይወት ሞራል ይኑርህ ምክንያቱም ጠንካራ ሞራል የህይወት ተስፋ ነውና

✴✅ ባለህ ነገር ተደሰት

ዛሬን ስለነገ በመጨነቅ ካሳለፍከው ዛሬን በቅጡ መኖር ይሳንሃል!!
ስላለህ ነገር እንጂ ስለሌለህ ነገር አታስብ ምክንያቱም ነገ የፈጣሪህ ነውና!

✴✅ እውነታን ተቀበል

ተፈጥሮ የቸረችህን ማንነትህን አምነህ መቀበልን ትተህ ለማማረር ወይም ለመሸማቀቅ አትሞክር ምክንያቱም በተሰጠህ ተፈጥሮሯዊ ማንነትህ ላይ ያንተ ሚና የለበትምና! በማይለወጥ አንተነትህ ተደሰት ምክንያቱም ቁርጡን ያወቀ ሰው ምርጫ ይኖረዋልና!

#ሼርርርር
ምርጥ መጣጥፎች

♥    አስተማሪ ታሪክ   200ላይክ በኃላ
14/07/2022

♥ አስተማሪ ታሪክ
200ላይክ በኃላ

Address

Dubai

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Elias official posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share