የኢማሙ አህመድ ልጅ

Cómo llegar

የኢማሙ አህመድ ልጅ Información de contacto, mapa y direcciones, formulario de contacto, horario de apertura, servicios, puntuaciones, fotos, videos y anuncios de የኢማሙ አህመድ ልጅ, Madrid.

08/03/2021

ቤተሰብ❤️አላህ ይጠብቃችሁ እህቶቼ

08/03/2021

ኢናሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጅኦን

02/01/2021
የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት በአህመድ አን-ነጃሺይ መስጂድ ላይ የደረሰውን ጥቃት በጥብቅ ያወገዘ ሲሆን መንግሥትም ማብራሪያ እንዲሰጥ ጠይቋል። ◈ ◈ ◈ ◈ ◈ ◈ ◈ ◈ ◈ ...
02/01/2021

የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት በአህመድ አን-ነጃሺይ መስጂድ ላይ የደረሰውን ጥቃት በጥብቅ ያወገዘ ሲሆን መንግሥትም ማብራሪያ እንዲሰጥ ጠይቋል።

◈ ◈ ◈ ◈ ◈ ◈ ◈ ◈ ◈ ◈ ◈ ◈ ◈ ◈◈ ◈ ◈ ◈
©Mujib Amino
◈ ◈ ◈ ◈ ◈ ◈ ◈ ◈ ◈ ◈ ◈ ◈ ◈ ◈◈ ◈ ◈ ◈

የዓለም ሙስሊሞች ቅርስ የሆነውና እስልምናን ተቀብለው ባስተናገዱት ታላቅ ንጉስ አል-ነጃሺ የተሰየመው መስጂድና የመቃብር ስፍራ በጦርነቱ ወቅት ጉዳት እንደደረሰበትና ቅርሶችም እንደተዘረፉ በማሕበራዊ ሚዲያዎች በሰፊው ተሰራጭቷል።

የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት በትግራይ ክልል በሚገኘው በታሪካዊው በአህመድ አንነጃሺይ መስጂድ ላይ የደረሰውን ጥቃት በጥብቅ ማውገዙን የገለጸ ሲሆን የሚመለከተው የመንግስት አካል ይህን ጉዳይ አስመልክቶ ከህዝበ ሙስሊሙ እየተነሱ ላሉ ጥያቄዎች አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጥ ጠይቋል።

አህመድ አን-ነጃሺይ መስጂድ አስመልክቶ በጦርነቱ ስለደረሱ ውድመቶች በማን እንደተፈፀመ መንግሥ ትበማስረጃ በተደገፈ መልኩ ለህዝብ ይፋ ማድረግ እንዳለበትም ይታመናል።

◈ ◈ ◈ ◈ ◈ ◈ ◈ ◈ ◈ ◈ ◈ ◈ ◈ ◈◈ ◈ ◈ ◈
ስለፍትህ እንጮሀለን፣ ሠላምን እንሰብካለን፣ አንድነትንና መከባበርን እንሻለን!
የቴሌግራም ቻናል-https://t.me/MujibbinISLAM

ፍትህ ለውድ ወንድማችን ጀዋር ሙሀመድ
22/11/2020

ፍትህ ለውድ ወንድማችን ጀዋር ሙሀመድ

አሳዛኝ ዜና‼️==========«ይህን ግፍ ሼር በማድረግ ለሚመለከተው አካል እናድርስ!»✍murad tadesse በዚህ ጦርነት ወቅት ህዝብ እና ሀገር በተጨነቀበት ወቅት የአማራ ክልል ብልፅግና...
17/11/2020

አሳዛኝ ዜና‼️
==========
«ይህን ግፍ ሼር በማድረግ ለሚመለከተው አካል እናድርስ!»

✍murad tadesse
በዚህ ጦርነት ወቅት ህዝብ እና ሀገር በተጨነቀበት ወቅት የአማራ ክልል ብልፅግና ድምፁን አጥፍቶ በወሎ ውስጥ ሙስሊሞችን በገፍ እያፈነ፣ እያሰረ ፣ እያሳደደ እና እየጨፈጨፈ ነው።
የደሴ ከረሜላ ፋብሪካ እና የሰሜን ካፌ ባለቤት በፖሊስ ከፍተኛ ድብደባ ደረሰባቸው በአድስ አበባ ኮሪያ ሆስፒታል ደክመዋል።
በ ደሴ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ የ5ኛ ፖሊስ ጣቢያ አዛዥ የሆኑት ኮማንደር ዘሩ_ተገኝ በ30/02/2013 መናፈሻ ክፍለከተማ የአቶ ሙሀመድ አሊ ድርጅት በሆነው የደሴ ከረሜላ ፋብሪካ ለመግባት በሚጠይቁበት ወቅት አቶ ሙሀመድ አሊ እና የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ ፖሊስ ለምን እንደመጣ ዓላማው ምን እንደሆነ እንዲሁም የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ካለ ጠይቀዋል።
ኮማንደሩ እናተን ብሎ መብት ጠያቂ በማለት ከፍተኛ ድብደባ አድርገው ተጨማሪ ሀይል እንዲጨመርለት በመጠየቅ 18ፖሊስ በማስጨመር ከፍተኛ ድብደባ ፈፅመውባቸዋል።በዚህም የተነሳ አቶ ሙሀመድ አሊ የደሴ ከረሜላ ፋብሪካ ባለቤት ራሳቸውን የሳቱ በመሆኑና ከደሴ ሪፈራል ሆስፒታል አቅም በላይ በመሆኑ በአሁኑ ሰዓት አዲስ አበባ በሚገኘው ኮሪያ ሆስፒታል ለከፍተኛ ህክምና ገብተዋል በቦታው የነበሩት የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ አቶ ኤርሚያስ አብርሀና የአቶ ሙሀመድ አሊ ወንድምም ተደብድበው በደሴ ህክምና እየተከታተሉ ይገኛል።
በአሁኑ ሰዓት የተበዳይ ቤተሰቦች ፖሊስ ተልዕኮ ያለው በሚመስል መልኩ ስልጣኑን አላግባብ በመጠቀም ጉዳት አድርሰውብናል በሚል የሰውና የሰነድ ማስረጃ በማዘጋጀት ጉዳዩን ወደህግ ወስደውታል።
አቶ ሙሀመድ አሊ በአሁኑ ሰዓት በደረሰባቸው ጉዳት ምክንያት በሂወትና በሞት መካከል ይገኛሉ።
ሰሞኑን በተለያዩ የወሎ ከተሞች የሚገኙ ወጣቶች ለሞጣ ጥቃት ሰልፍ አስተባብራችሓል ብሎ ቂም የያዘባቸውን በማፈን ፣ በማሰር እና በመደብደብ ማሸበር ቀጥለውበታል። ሙስሊሙ ላይ ጦርነት ከፍተዋል።

ሳውዲ-ዓረቢያ የኢትዮጵያ አይደለችም!!!አክሱም ግን የሁሉም ኢትዮጵያዊ ነች። (Sisay agena- ሲሳይ አጌና) ትላንት ፍትህ ስላጡት የኢትዮጵያ ሙስሊሞች (በተለይ አክሱም ያሉ ሙስሊሞች) ...
15/11/2020

ሳውዲ-ዓረቢያ የኢትዮጵያ አይደለችም!!!

አክሱም ግን የሁሉም ኢትዮጵያዊ ነች።
(Sisay agena- ሲሳይ አጌና)
ትላንት ፍትህ ስላጡት የኢትዮጵያ ሙስሊሞች (በተለይ አክሱም ያሉ ሙስሊሞች) ላይ የራሴን ሃሳብ በማስተላለፌ ለቁጥር የሚያዳግቱ መልእክቶች እየደረሱኝ ነው። ከስድብ አንስቶ "ሃይማኖትህን ቀየርክ እንዴ??" እስከሚለው ብዙ ሰዎች ጠይቃቹኛል።
እኔ ሃይማኖቴን አልቀየርኩም!! አልቀይርም!! ሃይማኖቴን አልቀይርም ማለት ግን የማውቀውን እውነት በጨለምተኝነት አንጸባርቃለው ማለት አይደለም @ Ethiopian DJ. እና ZHABESHA..የሚባሉ የራሳችን አድርገን የተቀበልናቸው የፌስቡክ ገጾች ሳይቀሩ በአደባባይ ተችተውኛል። እንደ ማንኛውም ስለ ኢትዮጵያ ቁንጽል እውቀት እንዳለውም " አክሱም ላይ መስኪድ መስራት ማለት ፤ሳውዲ ላይ ቤተ-ክርስቲያን መስራት ማለት ነው!!" የሚል የዛገ አመለካከት አንጸባርቀዋል።

ግን መልሰው "ኢትዮጵያ የሁላችንም ናት!" ሲሉ ይሰማል። እኔ እያወራሁ ያለሁት ወይም የኢትዮጵያ ሙስሊሞች እያወሩ ያሉት "በገዛ ሃገራችን ኢትዮጵያ ላይ መስኪድ መስራት ይፈቀድልን፤ የመቀበሪያ ቦታ አንከልከል፤ ሃይማኖታችንን በየቤታችን እንኳን እንዳናካሂድ ተጽእኖ አይፈጠርብን " ነው የተባለው። የሚሰጠው ምላሽ ደግሞ ስለ ሳውዲ ነው። አክሱም ላይ መስኪድ እንስራ ያሉት ኢትዮጵያውያን እንጂ ሳውዲ-ዓረቢያዎች አይደሉም!! ክርስቲያኖች ሳውዲ ላይ ቤተ-ክርስቲያን አትሰሩም ከተባሉ ተጠያቂዎቹ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ሳይሆኑ ሳውዲዎች ናቸው። ደግሞስ በሰው ሃገር እኛ ምን አገባን??? ሳውዲ ላይ ቤተ-ክርስቲያን አትሰሩም የተባሉ ሳውዲ-ዓረቢያዊ ክርስቲያኖች ካሉ (የሉም እንጂ) እነሱ ይጠይቁ። እኛ የምንጠይቀውም የሚያገባንም ስለሃገራችን ዜጎች ደማቸውን ለኢትዮጵያ ስላፈሰሱት አጥንታቸውን ለኢትዮጵያ ስለከሰከሱት ኢትዮጵያዊ ሙስሊሞች የመብት ጉዳይ ነው።
እዚህ ቦታ ቤተ-ክርስቲያን ካልተሰራ..እዚህ ቦታም መስኪድ አይሰራም የሚል ክርክር ከተነሳ ክርክሩ መሆን ያለበት ኢትዮጵያ ውስጥ ባሉ ክፍለ-ሃገራት ብቻ ነው። ግን ሙስሊሞች የሚበዙበት የኢትዮጵያ ከተማ ላይ ቤተ-ክርስቲያን አይሰራም አልተባለም።
እኔ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ የፈለገው ቦታ እምነቱን በነጻነት ማራመድ ይችላል ባይ ነኝ።

ካልሆነ ግን ማወዳደር ያለብን ሃረርን እና አክሱምን ነው እንጂ አክሱምን እና ሳውዲን አይደለም!! የሙስሊሞች መነሃሪያ ከተማ የሆነችው ሃረር (ድሬዳዋ) ላይ "ቁልቢ ገብርዔልን" የሚያክል ትልቅ ቤተ-ክርስቲያን ገንብቶ ፤ አክሱም ላይ "መስኪድ መስራትም ሆነ ፤ሲሞቱ መቀበር አይቻልም!!" ማለት ፤ አብሮ የሚያኗኑር አይደለም!!

ሁላቹም ስለፍትህ እና እኩልነት የምታምኑ ከሆነ በሃይማኖት እና በዘር ከረጢት ውስጥ ከመካተት ውጡ እና እንደ አንዲት ኢትዮጵያ ስለ ፍትህ እናስብ!!!

ኢትዮጵያ ሁሉም ሃይማኖት በእኩልነት የሚከበርባት ሃገር ትሁን!!!

#ፍትህለአክሱምሙስሊሞች።

ሙስሊም በድኑ ከመጣህበት እንድህ ነው  ለነብዩ  (ሶለላሁ አለይሂ ወሰለም.)  ዛሬ በባንግላዴሽ (ኢራን) የተደረገ ታላቅ ተቃውሞ
30/10/2020

ሙስሊም በድኑ ከመጣህበት እንድህ ነው ለነብዩ (ሶለላሁ አለይሂ ወሰለም.) ዛሬ በባንግላዴሽ (ኢራን) የተደረገ ታላቅ ተቃውሞ

በህንድ ውስጥ ከ10 ሺህ በላይ የሚበልጡ ሙስሊሞች ረሱልን በመደገፍ ትናንታ ታላቅ ተቃውሞ አድርገዋልHuge Rally In   In Defence Of Prophet ﷺTens of thousands ...
30/10/2020

በህንድ ውስጥ ከ10 ሺህ በላይ የሚበልጡ ሙስሊሞች ረሱልን በመደገፍ ትናንታ ታላቅ ተቃውሞ አድርገዋል
Huge Rally In In Defence Of Prophet ﷺ

Tens of thousands of Muslims attended a protest yesterday in in defence of Prophet Muhammad ﷺ.

Dirección

Madrid
28029

Página web

Notificaciones

Sea el primero en enterarse: le enviaremos un correo electrónico cuando የኢማሙ አህመድ ልጅ publique novedades y promociones. Su dirección de correo electrónico no se utilizará para ningún otro fin y puede darse de baja en cualquier momento.

Atajos

Compartir