03/05/2026
#በአማራ እና #በትግራይ ህዝቦች መካከል ያለውን #ግንኙነት ማጠናከር እጅግ አስፈላጊ እና ጠቃሚ ነው።
እነዚህ ሁለት ህዝቦች ረጅም የታሪክ፣ የባህል፣ የሃይማኖት እና የስነ-ልቦና ትስስር ያላቸው ህዝቦች ናቸው ።
በመካከላቸው የሚፈጠር #አለመግባባት ወይም #ግጭት ለሁለቱም ህዝቦች ብቻ ሳይሆን ለመላው ኢትዮጵያ እና ቀጠናውም ጎጂ ነው።
ለምንድነው የአማራ እና የትግራይ ግንኙነት #መጠንከር ያለበት ለሚለው በርካታ ምክንያቶች አሉ፡-
#ለዘላቂ #ሰላም እና #መረጋጋት፡ በክልሎቹ መካከል የሚፈጠር ውጥረት እና ግጭት የሰዎችን ህይወት ይቀጥፋል፣ ንብረት ያወድማል፣ እና ልማትን ያደናቅፋል።
በመሆኑም፣ ግንኙነቱን በማጠናከር እና ልዩነቶችን በውይይት በመፍታት ዘላቂ ሰላምን ማስፈን አማራጭ የሌለው ምርጫ ነው።
#ለኢኮኖሚ #እድገት፡ ሁለቱም ክልሎች የየራሳቸው የኢኮኖሚ አቅም እና ሀብት አላቸው።
በመሆኑም በመካከላቸው የንግድ ልውውጥን እና የኢኮኖሚ ትብብርን በማጠናከር የሁለቱንም ክልሎች ልማት ማፋጠን የማፋጠን ዓቅሙ ከፍተኛ ነው።
#ለማህበራዊ #ትስስር፡ በሁለቱ ህዝቦች መካከል ያለው የጋራ ባህል፣ ሃይማኖት፣ እና የስነ-ልቦና ትስስር እጅግ ጠንካራ ነው።
ይህንን ትስስር በማጠናከር በመካከላቸው ያለውን እምነት እና ወንድማማችነት ማሳደግ ይቻላል።
#ለሀገር #አንድነት፡ አማራ እና ትግራይ የኢትዮጵያ ዋና ዋና ብሄረሰቦች ናቸው። በመካከላቸው የሚፈጠር አንድነት ለሀገሪቱ አንድነት እና ጥንካሬ መሰረት ይሆናል( ኢትዮጵያ ከቆየች )።
ይህንን ለማሳካት ሁለቱም ህዝቦች፣ የፖለቲካ አመራሮች፣ኤሊቶች እና ማህበረሰቡ በቅንነት እና በትብብር መስራት አለባቸው።
#ያለፈውን #ጥለው( #ለህግ፣ #ለእርቅ ፣ #ለፍትህ ) ፣ ለጋራ የወደፊት ህይወታቸው ትኩረት በመስጠት፣ በመካከላቸው ያለውን እምነት እና ወንድማማችነት በማጠናከር ዘላቂ ሰላም መፍጠር ነው ያለባቸው ።
የፌዴራል መንግስት ሴራ መክሸፍ ነው ያለበት። ሁለቱም ህዝቦች ለማጣላት የወሰን ጥያቄዎች በፌደራል የተጠመዱ ቦምብ ናቸው ።
ሰለዚህ በአንዳንድ አካባቢዎች ያሉ የወሰን ጥያቄዎች በሁለቱ ክልሎች መካከል አለመግባባትን መፍጠራቸው አይቀሬ ነው።
እነዚህ ጥያቄዎች Genuine በሆነ ውይይት እና በህጋዊ መንገድ መፈታት አለባቸው ። ፌደራል በዘረጋው ወጥመድ መሄድ መሄድ የለብንም ።