Guramayle online book store

Guramayle online book store Telegram : t.me/guramaylebooks
Twitter : twitter.com/guramaylebooks
Instagram : Instagram.com/gurama

ሮበርት ግሪንን በሀገራችን አንባብያን ዘንድ በስፋት "The 48 laws of power" እና "The law of human nature" በተሰኙ መጽሐፍቱ እናውቀዋለን። አሁን ደግሞ ከሱ ስራዎች...
16/10/2023

ሮበርት ግሪንን በሀገራችን አንባብያን ዘንድ በስፋት "The 48 laws of power" እና "The law of human nature" በተሰኙ መጽሐፍቱ እናውቀዋለን። አሁን ደግሞ ከሱ ስራዎች አምስተኛውን መጽሐፉን (MASTERY) በኦሪጅናሉ የህትመት ጥራት ደረጃ አሳትመን ለገበያ አቅርበንላችኋል። እጅግ በጣም ምርጥ መጽሐፍ ነው ያንብቡት ያተርፉበታል።

Robert Greene is the author of the New York Times bestsellers The 48 Laws of Power, The Art of Seduction, The 33 Strategies of War, and The 50th Law. His highly anticipated fifth book, Mastery, examines the lives of great historical figures such as Charles Darwin, Mozart, Paul Graham and Henry Ford and distills the traits and universal ingredients that made them masters. In addition to having a strong following within the business world and a deep following in Washington, DC, Greene’s books are hailed by everyone from war historians to the biggest musicians in the industry (including Jay-Z and 50 Cent).

Greene attended U.C. Berkeley and the University of Wisconsin at Madison, where he received a degree in classical studies. He currently lives in Los Angeles.

Each one of us has within us the potential to be a Master. Learn the secrets of the field you have chosen, submit to a rigorous apprenticeship, absorb the hidden knowledge possessed by those with years of experience, surge past competitors to surpass them in brilliance, and explode established patterns from within. Study the behaviors of Albert Einstein, Charles Darwin, Leonardo da Vinci and the nine contemporary Masters interviewed for this book.

The bestseller author Robert Greene has spent a lifetime studying the laws of power. Now, he shares the secret path to greatness. With this seminal text as a guide, readers will learn how to unlock the passion within and become masters.

ሀገርን ከነድንበሩ፣ ታሪክን ከነባህሉ፣ ቋንቋን ከነፊደሉ ያቆዩልን፣ ለዛሬው ማንነታችን የአካል እና የህይወት መስዋዕትነት የከፈሉልን የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖችን እና አርበኞቻችንን እናመሰግ...
01/03/2023

ሀገርን ከነድንበሩ፣ ታሪክን ከነባህሉ፣ ቋንቋን ከነፊደሉ ያቆዩልን፣ ለዛሬው ማንነታችን የአካል እና የህይወት መስዋዕትነት የከፈሉልን የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖችን እና አርበኞቻችንን እናመሰግናለን!

💚💛❤️ ምኒልክ ዛሬም ንጉስ ነው!!!💚💛❤️

የመዝጊያ መልዕክት ከእረኛየ!!!ይገርማል ሁሌም ድክም ብሎኝ ስቀር ምርኩዝ ይልክልኛል፤ አንቺም የበቃልዬ ምርቃት ይድረስሽ ሲል ምርኩዝ አርጎ አመጣሽ። በቃልዬ አብነትን የመረቃትን ሰምተሻል? ...
19/08/2022

የመዝጊያ መልዕክት ከእረኛየ!!!

ይገርማል ሁሌም ድክም ብሎኝ ስቀር ምርኩዝ ይልክልኛል፤ አንቺም የበቃልዬ ምርቃት ይድረስሽ ሲል ምርኩዝ አርጎ አመጣሽ። በቃልዬ አብነትን የመረቃትን ሰምተሻል? "እውቀት እንደ ምንጭ ይፍለቅብሽ፣ እንደጅረት ወርዶ ለዓለም ሁሉ ይድረስ ብሎ ነው የመረቃት" ። ለአንቺም ከምርቃቱ ይድረስሽ። አሜን፤ ጎሽ ልጄ አዎ፤

እማማ እንመለስ? ደከመዎት?
አየ ልጄ መመለስማ የለም፤ ወደኋላ ዞሬ መመልከቴ ከመነሻየ ምን ያህል ርቀት ተጉዤ እንደመጣሁ ለማወቅ፣ ወደፊት ለመጓዝ ተስፋ እንዲሆነኝ ነው፤ መመለስማ የለም።

ብዙ መከራ አይቻለሁ፣ ብዙ መከራና ስቃይ ፈትኖኛል ልጄ፤ ያኔ ከአበባየ መርገፍ በኋላ ጉልበት ተስኖኝ እቤት ቀርቼ ነበር።

ሰው የጭረት ጠባሳውን እየገለጠ፣ የሌላውን ቁስል እየወጋ፣ በቂም መከፋፈሉን አይታ፣ መቁሰሌ ሌላውን ሰው ወደ ሞት የሚወስድ አይሁን፣ ለእርቅና ለይቅርታ ይሁን ብላ የመንደሩን ሰው በአደራ መራችው። ወደኋላ መመለስ የለም ብላ ሁሉን በአንድነት አስተሳስራ የኔ ልጅ ወደፊት መራችው። ለወደደችው፣ ላመነችበት ዋጋ ከፈለች፤ ዋጋ ከፈለች እኔ ግን እሷ የከፈለችውን ዋጋ ከንቱ ለማስቀረት እቤቴ ቁጭ አልኩ፣ እቤት ቀረሁ፤ ግን ትውልድ አይጥፋ፣ ተስፋ አይጥፋ ይሄው አንቺ መጣሽልኝ እና ምርኩዝ ሆነሽ ይዘሽኝ ወጣሽ።

ዛሬ እግሬ እንዲቀጥልና እንድበረታ ያጸናኝ ተስፋ ነው።

የኔ ልጅ በዚህ እድሜሽ የደረሰብሽን እናትሽን ማጣትሽን ሰምቻለሁ ልጄ ግን ወደኋላ መመልከቱ ምን ያህል ትተሽው እንደመጣሽ ለማወቅ እንጂ ወደኋላ ለመመለስ አይሁን፤ አይሁን ልጄ።

ከመጣንበት ይልቅ ገና የምንሄድበት ብዙ ነው።

አሁን ምንድን ነው የሚመረቀው?
ዛሬ ሸክላ በመስራት ነው የሚያስመርቁት ብለዋል።
ጎሽ ጥሩ አድርገዋል የሰው ልጅስ ከመነሻው እንዲሁ አይደል እንደሸክላ ከአፈር፤ ሁሉም የሰው ልጅ እኮ ከአፈር ተነስቶ ወደ አፈር ነው።

ከአፈር እስከ አፈር!!!

መቼም_ተስፋ_አትቁረጥ! እውነተኛ ታሪክ  አዲስ መጽሐፍ በገበያ ላይሴልቨስተር ስታሎን ከታዋቂ አሜሪካውያን የፊልም ተዋንያን መካከል አንዱ ነው። አብዛኞቻችን "ራምቦ" እና "ሮኪ" በሚሉ የትወ...
14/08/2022

መቼም_ተስፋ_አትቁረጥ!
እውነተኛ ታሪክ


አዲስ መጽሐፍ በገበያ ላይ

ሴልቨስተር ስታሎን ከታዋቂ አሜሪካውያን የፊልም ተዋንያን መካከል አንዱ ነው። አብዛኞቻችን "ራምቦ" እና "ሮኪ" በሚሉ የትወና ስሞቹ እናውቀዋለን። የትወና ብቃቱም በብዙሃን ልብ ውስጥ ተቀርጾ ቀርቷል።

በወሊድ ወቅት በደረሰ የህክምና ስህተት ምክንያት ስታሎን ግማሽ ፊቱ ፓራላይዝ እንዲሆን ሆኗል። በትምህርት ቤት ሳለም ድህነቱ እና የገጹ ሁናቴ መሳቂያ ነበሩ።

እሱን የሚሰድቡ እና የሚያንቋሽሹ ሰዎችን ማስፈራሪያ እንዲሆነው፤ የተለያዩ የሰውነት መገንቢያ እንቅስቃሴዎችን መስራት ጀመረ።

ቀስ በቀስም ወደ ፊልም ስራ ተሳበ። ሆኖም የፊልም ተዋናይ መሆን እንዲህ ቀላል አልነበረም። በ1974 አካባቢ የሚወደው ውሻ፣ እርጉዝ ሚስት፣ ያልተሳካ የተዋናይነት ሙከራና ያልተከፈሉ ብዙ እዳዎች ነበሩበት።

እንዲያውም እዳው ከመብዛቱ የተነሳ እረፍት አጣ፤ ጭንቀት በዛበት፤ ቢሆንም ግን አሁንም ትልቅ የመሆን ተስፋ ነበረው።

ነገሮች እየባሱ ሲመጡ የሚስቱን ጌጣጌጦች ሸጠ፤ ቤት አልባ ሆነው ጎዳና ወጡ። ለሶስት ቀናት ያህልም የኒውዮርክ የባስ ማቆሚያ ፌርማታዎች ላይ ተኝተው አደሩ።

የክረምት ወራት ሲመጣም ለማሞቂያ የሚጠቀሙበትን ኤሌክትሪክ አልያም ውሻውን መምረጥ ነበረበት። እናም ከአንድ መጠጥ ቤት ፊት ለፊት ውሻውን በሃያ አምስት ዶላር ሸጠው።

ከሁለት ሳምንታት በኋላም በቴሌቪዥን የቦክስ ውድድር እየተመለከተ ሳለ፣ ድንገትም አንድ ሃሳብ ብልጭ አለለት። ለቀጣዮቹ ሃያ ሰዓታት ያህልም ቁጭ ብሎ ዛሬ ላይ ROCKY ብለን የምንጠራውን ፊልም ስክሪፕት ጻፈ።

ስታሎን እንደሚለው "ከአንድ ሺ አምስት መቶ አለመቀበሎች" በኋላ ስክሪፕቱን ለመግዛት የ125,000 ዶላር ክፍያ ቀረበለት። ድህነቱ፣ እርጉዟ ሚስቱ እና ውሻውን ማጣቱ ቢደራረብበትም - የእርሱ ፍላጎት ግን ታዋቂ የፊልም ተዋናይ መሆን ነበር።

ያኔ ጀግና ተብለው በፊልም ውስጥ የሚሳሉ ሰዎች - ንግግራቸው ያማረ እና ስርዓትን የተሞሉ ነበሩ። ስታሎን እንደዱርዬ ደረቱን አሳብጦ እና ከአፉ የሚወጡትን ቃላት እየጨፈለቀ (ግማሽ ፊቱ ፓራላይዝ በመሆኑ ንግግሩን ያንሻፍፈው ነበር) እርሱ የጻፈው ድርሰት ላይ ያለውን ዋና ተዋናይ ድርሻ መጫወት እንደሚፈልግ ገለጸላቸው።

ፊልሙን ሊገዛው የሚፈልገው ስቱዲዮ ይሄ እንደማይሆን ነግሮ አሰናበተው። እናም ስታሎን እድሉን እያማረረ ወጣ።

ከጥቂት ሳምታት በኋላ በድጋሜ ደወሉለት፤ እናም ለፊልም ጽሁፉ ብቻ 250,000 ዶላር አቀረቡለት። እርሱን ዋና ተዋናይ አድርገው መቅጠር አልፈለጉም። አሁንም አይሆንም አላቸው።

ብዙም ሳይቆይ የ350,000 ዶላር ክፍያ ለፊልም ጽሁፉ ብቻ አቀረቡለት።

በአጠገቡ ያሉ ሁሉም ሰዎች እየገፉት ነበር። "እንዴት አልቀበልም ትላለህ? ያምሃል!" እያሉ ይጎተጉቱታል። የቀረበለት ገንዘብ እጅግ በጣም ብዙ ነው። ሆኖም ስታሎን አላማ ነበረው።

ስቱዲዮ ውስጥ ከነበሩ ሰዎች አንዱ ጽሁፉን በጣም ወዶት ነበርና፣ ባልደረቦቹን አሳምኖ የፊልም ጽሁፍን እና ስታሎንን ተቀበሉት። ሆኖም የከፈሉት ገንዘብ 35 ሺ ዶላር ነበር።

ቀጥሎ ያለው ታሪክ ነው!

ፊልሙ በአንድ ሚልዮን ዶላር ወጪ ተሰርቶ በአለም ዙሪያ 200 ሚልዮን ዶላር ገቢ አስገብቷል፡፡

የኦስካርን ሽልማትን በሶስት ዘርፎች ወስዷል፡፡

ስታሎን ለቀጣዮቹ አመታት ታዋቂ የፊልም ተዋናይ ሆነ፤ የእርሱም ፊልሞች ብዙ ቢልዮን ዶላሮችን ሰሩ።

እና ስታሎን የመጀመሪያ 35 ሺ ዶላሩን ምን አደረገው?

ውሻውን የሸጠበት መጠጥ ቤት ለሶስት ቀናት ያህል ውሻውን የሸጠለትን ሰው ጠበቀው። ውሻውንም መልሶ በ15 ሺ ዶላር ገዛው።
🥇🥇🥇

መቼም ተስፋ አትቁረጥ። ማለምህን መቼም እንዳታቆም። እንደምትችል እወቅ … ህልምህንም እመን። ህልምህን አፍቅረው። ምናልባትም አሁን ላይ ቀን ጨልሞብሃል፤ ብድሮች ተደራርበውብሃል፤ ከሚስትህ ጋር ልትፋታ፣ ወዳጆችህ ሊርቁህ ይችላሉ። ሰዎች ህልምህን ስትነግራቸው ሊስቁብህ ይችላሉ...

ሁሉንም ነገሮችህን መልሰህ ማግኘት ትችላለህ … ስራህን፣ ቤተሰቦችህን፣ ወዳጆችህን፣ ክብርህን፣ ሁሉንም … መጀመሪያ ግን በራስህ አቅም ተማመን። ነገህንም በተስፋ ገንባ።
🥇🥇🥇

መጽሐፍ
በዘፈቀደ መኖር አቁመን በተግባር በተፈተኑ የስኬት መርሆዎች አማካይነት የምንሻገርበት መጽሐፍ ነው፡፡

 ምንም እንኳ ሰውነቱ በጉዞ ብዛት ቢደክምም አዕምሮው ግን ማረፍን አልመረጠም።  ሻወር ከወሰደ በኋላ የብራናውን ካርታ አወጣና በትኩረት መመልከት ጀመረ። ካርታው ሙሉ የኢትዮጵያን ምስል የማያ...
16/06/2022



ምንም እንኳ ሰውነቱ በጉዞ ብዛት ቢደክምም አዕምሮው ግን ማረፍን አልመረጠም።

ሻወር ከወሰደ በኋላ የብራናውን ካርታ አወጣና በትኩረት መመልከት ጀመረ። ካርታው ሙሉ የኢትዮጵያን ምስል የማያሳይና በከፊል የሆነ ቦታ ላይ የተወሰደ መሆኑን ሲመለከት ፍለጋው ቀላል እንደማይሆን ተረዳ። የካርታው መካከለኛ ክፍል ውኃማ ቀለም የተቀባ ሲሆን ከዚሁ ውኃማ ቀለም ከተቀባው ክፍል በስተ-ምስራቅ፣ በስተ-ሰሜን ምስራቅ እና በስተ-ደቡብ (ወደ ምዕራብ የተወሰነ ጋደል ብሎ) የግዕዝ ቁጥር የተጻፈባችው ሦስት የመስቀል ምልክቶች ተቀምጠዋል።

ሰሎሞን በስተ-ምስራቅ በኩል ያለው ቁጥር ፲፭፻፲፮ ዓ.ም (1516 ዓ.ም)፤ በስተ-ሰሜን ምስራቅ በኩል ያለው ፲፫፻፴፭ ዓ.ም (1335 ዓ.ም) እንዲሁም በስተ-ደቡብ ምዕራብ ያለው ቁጥር ደግሞ ፲፪ (12) እንደሆነ ካርታው ላይ በግልፅ አነበበ። “አባ እንድንፈልግ ያዘዙን ሦስቱ ቦታዎች እነዚህ መሆናቸው ነው?” አለ ሰሎሞን ከራሱ ጋር በሀሳቡ።

አሁንም ትኩረቱን ወደ ካርታው ሲመልስ ከሦስቱ ውስጥ አንዱ ማለትም በስተ-ምስራቅ በኩል የተቀመጠው ምልክት ውኃማ ቀለም ከተቀባው ክፍል ተነስቶ የሚሄድ የተሰመረ ቀጥ ያለ ቀይ መስመር አለው።

ለመሆኑ ቁጥሮቹ ምንን ይሆን የሚያመላክቱት? ከየትስ ነው ተነስተን የምንፈልጋቸው? ካርታ ላይ ያለን ነጥብ ምድር ላይ መፈለግ እንዴትስ ይቻላል? በሚል ጥያቄ ሰሎሞን ውስጡ ተሞላ። ለማክዳም ካርታውን በሚታይ መልኩ ፎቶ አንስቶ ከላከላት በኋላ እጅግ ደክሞት ስለነበር እረፍት ለማድረግ ተኛ።

ለመሆኑ ይህ በካርታ ቁጥሮች የተደበቀው ታላቅ የሀገር ምሥጢር ምን ይሆን? #ሰርድዮን መጽሐፍ

 ? - ፕሌቶበመንገድህ ላይ አንዲት አሮጊት አጋጠመችህ፤ እናም ይህቺ ሴት ትንሽ፣ ግን እጅግ በጣም ጠቃሚ የሆነን ስጦታ ሰጠችህ - አስማተኛ ቀለበት! ይህም ቀለበት አንተን ለሌሎች እንዳትታይ...
23/05/2022

? - ፕሌቶ

በመንገድህ ላይ አንዲት አሮጊት አጋጠመችህ፤ እናም ይህቺ ሴት ትንሽ፣ ግን እጅግ በጣም ጠቃሚ የሆነን ስጦታ ሰጠችህ - አስማተኛ ቀለበት!

ይህም ቀለበት አንተን ለሌሎች እንዳትታይ አድርጎ ይሰውርሃል፤ ወደፈለግከው ስፍራ መጓዝ ትችላለህ፤ ማንም ሰው አንተን ማየት አይችልም።

ጥያቄውም ይህ ነው - በዚህ ቀለበት ምን ታደርጋለህ? ይህን አስማታዊ ሃይል እንዴት ትጠቀመዋለህ?

“የጋይጂ ቀለበት” ሪፐብሊክ በተሰኘው የፕሌቶ ዘመን አይሽሬ ስራ ውስጥ እናገኘዋለን። መጽሀፉ የፕሌቶ ታላቅ ወንድም ስለሆነውና ግላውኮን ጋይጂ ስለተባለ አንድ ተራ በግ ጠባቂ ታሪክ ይነግረናል።

ይህ እረኛ ከክርስቶስ መወለድ ሰባት መቶ አመታት በፊት የሊድያ ግዛት ተብላ በምትጠራው ስፍራ ይኖር ነበር። (ይህን ግዛት አሁን ላይ በቱርክ ውስጥ እናገኘዋለን።)
ፕሌቶ ታሪኩን እንዲህ ይተርከዋል፡-

ከእለታት በአንዱ ቀን በእጅጉ ሃይለኛ የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ በሊድያ ግዛት ውስጥ ተከሰተ። በምድር ገጽ ላይም ትልቅ መሰንጠቅ ተፈጠረ። በስንጥቁ መሃልም እረኛው ጋይጂ አንድ የተደበቀ ዋሻ ተመለከተ። በዋሻው ውስጥም ጋይጂ ከነሐስ የተሰራ የፈረስ ሐውልት አገኘ። በዚህ ሐውልት ውስጥ በከፊል የበሰበሰ የአንድ ግዙፍ ሰው ሙት አካል ይገኝበት ነበር። በአስክሬኑ የቀኝ እጅ አንደኛው ጣት ላይም ወርቃማ ቀለበት ያብረቀርቅ ነበር። እናም ጋይጂ ይህንን ቀለበት ለራሱ ወሰደው።

እረኛው ይህ ቀለበት ተራ ቀለበት እንዳልነበረ ለመረዳት ጊዜ አልወሰደበትም። በቀለበቱ አናት ላይ ያለችውን ጌጥ ሲያሽከረክራት፣ ጋይጂ ሰው እንዳያየው ሆኖ ተሰወረ። ቀለበቱ ለጋይጂ የመሰወርን ሃይል ሰጠው።

አስደናቂ የመሰወር ሃይልን እንዳገኘም፣ ይህ ተራ የበጎች እረኛ ወደ ቤተ መንግስት ቅጥር ዘለቀ። በዚያን ዕለት ምሽትም ከንግስቲቷ ጋር ተኛ። ንጉሱንም ገደለው። ንግስናንም ተቀበለ። እናም ራሱን የሊድያ ግዛት ገዢ አድርጎ ሾመ። ታሪኩ ይቀጥላል… እስቲ ልጠይቅህ…

አንተስ የመሰወር ሃይል ቢኖርህ ምን ታደርጋለህ?

በአጠገብህ ያለ ጓደኛህን ጠይቀው፤ ራስህንም ጠይቅ።
የሚያስገርም፣ የሚያስቅ አልያም የሚያሳቅቅ ምላሽን ታገኛለህ። እናስ የመሰውር ሃይል ቢሰጥህ … ባንክ ቤት አትዘርፍም? ልክ እንደ ጋይጂ ወደ ቤተመንግስት ለመግባት አትሞክርም? ከዚህም ሲከፋ ለመናገር የሚከብዱ ወንጀሎችንስ አትፈጽምም?

እረኛው ራሱን ንጉስ ካደረገ በኋላ የገጠመውን ሁሉ ፕሌቶ ያጫውተናል፡፡ ጨዋታው ደግሞ
በ የተሰኘው መጽሐፍ ውስጥ ተተርኳል፡፡

*
ቤተሰብ ይሁኑ

Facebook- https://www.facebook.com/guramaylebooks/

Telegram-
https://t.me/guramaylebooks

 #ሉባር መጽሐፍ“ሉባር መጽሐፍ የተፃፈበት ማራኪና ልዩ የአፃፃፍ ስልት ለወደፊቱ የኢትዮጵያ ሥነ-ፅሑፍ ራሱን የቻለ ጉልህ አስተዋፅኦ ያደርጋል። ድርሰቱ የተፃፈበት ቅኝት እጅግ ተወዳጅ ከመሆኑ...
12/04/2022

#ሉባር መጽሐፍ

“ሉባር መጽሐፍ የተፃፈበት ማራኪና ልዩ የአፃፃፍ ስልት ለወደፊቱ የኢትዮጵያ ሥነ-ፅሑፍ ራሱን የቻለ ጉልህ አስተዋፅኦ ያደርጋል። ድርሰቱ የተፃፈበት ቅኝት እጅግ ተወዳጅ ከመሆኑ የተነሳ በአንባቢያን ልብ ውስጥ በርካታ ዘመናትን እንዲሻገር ያደርጋል። ደራሲው መምህር በረደድ ገዳሙ በብዙ ደራሲዎች ዘንድ ያልተለመደውን እና ያልተደፈረውን በርካታ ዘውጎችን በአንድ ቅኝት አግባብቶና አጣጥሞ አንድ ወጥ የሆነ ድርሰት በመክተብ አንባቢያን የተሟላ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ማድረግ ችሏል።

በሉባር መጽሐፍ ውስጥ ታሪክ፣ እውቀት፣ ባህል፣ ፍልስፍና፣ ማህበራዊ ሕይወት፣ እምነት፣ ጥበብና ምስጢር በሚጣፍጥ ለዛና ውበት ፍሰታቸውን ጠብቀው፣ ስሜት በሚሰጠው ንፁህ መለኮታዊ ፍቅር ታሽተውና ተለውሰው ዘምረውበታል።

በዚህ ልብ አንጠልጣይ ድርሰት ውስጥ የተሳሉት በታሪክና ገጠመኝ የተካኑት፣ በድንቅ የሕይወት ፍልስፍና የታጀቡት፣ ኢትዮጵያዊ ለዛና ውበትን የተጎናፀፉት ጥንዶች (ማክዳና ሰሎሞን) እጅግ አስተማሪና ጣፋጭ ገፀ ባህሪን ከመላበሳቸው የተነሳ ለትውልድ የምንጊዜም ተምሳሌት ሆነው እንዲኖሩ ያስችላል። በሉባር ውስጥ ያለው የሀገር ፍቅር፣ የሀሳብ ፍሰት፣ የቋንቋ አጠቃቀም፣ የቃላት ሀብት ክምችት፣ ኢትዮጵያዊ ለዛና ውበት ተደማምሮ ድርሰቱን በማንኛውም ኢትዮጵያዊ ልብ ውስጥ ልዩ ቦታ እንዲኖረው ያስችሉታል።

በጥቅሉ ሉባር ታሪክን ከወቅታዊ ክስተት፣ ፍልስፍናን ከነባራዊ ሁነት፣ ስልጣኔን ከባህልና ወግ ጋር አግባብቶና አጣጥሞ በፍቅር ቅኝት ሞሽሮና ገምዶ የያዘ፤ ትውልድና ሀገርን ለመታደግ ታልሞ የተፃፈ፤ እንደ ስሙ ቅዱስና ከፍ ያለ የሀሳብ ልዕልናን የተጎናፀፈ ድንቅ መጽሐፍ ነው። በአጠቃላይ ሉባር በእጅጉ የተዋጣለትና ሁሉም ኢትዮጵያዊ ቢያነበው ብዙ ያተርፍበታል ብዬ ከልብ ከምጋብዛቸው መጻሕፍት መካከል ግምባር ቀደም ነው።”
#ዶ/ር መስፍን ወጋየሁ
ከባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ

“ሉባር የባለራእይ ወጣት ድርሰት ነው፡፡ ደራሲው በቁጭት የሀገራችንን የከፍታ ዘመን እያነሳ ወደ ኃላቀርነትና ድኅነት የተንደረደርንባቸውን ምክንያቶች እየጠቀሰ ከችግሮች የምንላቀቅባቸውን መንገዶች በዝርዝር ያስረዳል፡፡ ያለትግል ድል ስለማይገኝ ጨለማን በብርሃን፣ መከራን በፍስሐ፣ ችጋርን በድሎት፣ ጥላቻን በፍቅር፣ መበታተንን በኅብረት ለመቀየር በሚታትሩ የድርሰቱ ዋና ገጸ ባህርያት (በድሉ/ሰሎሞን/ እና ማክዳ) የሕይወት ውጣ ውረዶች አማካይነት ይገልፅልናል፡፡ ቢያነቡት አስተማሪ ተሞክሮዎችንና በርካታ ጭብጦችን ያገኙበታል።”
#ዶ/ር ሞገስ ሚካኤል
በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ፣ የዐባይ የቋንቋና የባህል ጥናት ተቋም ኃላፊ

ስለ ሉባር መጽሐፍ ከተሰጡ የምሁራን ሀሳቦች በጥቂቱ።

መጽሐፍት ቤትዎ ድረስ ያለተጨማሪ የማድረሻ ክፍያ (free delivery) እንዲሁም ከ10-50% በሆነ ቅናሽ እንዲመጣልዎ ሲፈልጉ ከታች ያለውን የቴሌግራም ሊንክ ይጠቀሙ።

Telegram- https://t.me/guramaylebooks

ቴዎድሮስ እንዲህ ሲል ጀማነሽን ይጠይቃል ፦ ህይወት እና ሞትን እንዴት ነው በንፅፅር የምታያቸው? ስለየቱ (ከሞትና ከሕይወት) ማወቅ ነው የበለጠ የሚያረካሽ?ጀማነሽም ስትመልስ እንዲህ ባማረ ...
09/04/2022

ቴዎድሮስ እንዲህ ሲል ጀማነሽን ይጠይቃል ፦ ህይወት እና ሞትን እንዴት ነው በንፅፅር የምታያቸው? ስለየቱ (ከሞትና ከሕይወት) ማወቅ ነው የበለጠ የሚያረካሽ?

ጀማነሽም ስትመልስ እንዲህ ባማረ አገላለጽ ነበር ፦

ለእኔ በሰው ልጅ የኑሮ ዘመን ውስጥ ሕይወትና ሞት እኩል መሳ ለመሳ አብረው የሚሔዱ ነገሮች ናቸው። የሰው ልጅ ብዙ የሚቸገረውና የማይሆን ጉዳይ ውስጥ የሚገባው ሞቱን እየረሳ ነው የሚመስለኝ። ሞታችንን ብናውቅ ነገ ጥለነው ለምንሔደው አለም መተናነቅና መዋጋት ውስጥ አንገባም ነበር። የጀርመን ተረት ይመስለኛል "ልጄ ሆይ እንደምትኖር ሆነህ ስራ እንደምትሞት ሆነህ ኑር" ይላል። ሞትና ሕይወት እኩል አንድ ቀን ነው የተሰጡን፣ ሁለት ገጽታዎቻችን ሆነው።

ጀማነሽ የሰጠችው መልስ ሁላችንም ሕይወት ላይ የሚሰራ ነውና እንደምንሞት ሆነን እንኑር።

ቴዎድሮስ ተክለአረጋይ በዚህ መጽሐፉ የሀገራችንን ታላላቅ ሰዎች ጥሩ ጥሩ ጥያቄዎች እያነሳ ያፈላስፋቸዋል የተጠያቂዎቹ መልሶችም ማለፊያ የሆኑ የፍልስፍና ሃሳቦ አሏቸው ያንብቡት ይወዱታል።

ታዲያ መጽሐፉን ሲፈልጉ ከስራ መልስ ያለዎትን የእረፍት ጊዜ በየመጽሐፍ መደብሩ መጽሐፍ በመፈለግ አያባክኑት ቤትዎ ሁነው ይደውሉልን ያለምንም ተጨማሪ ክፍያ ቤትዎ በር ድረስ እናመጣልዎታለን ኸረ እንደውም ከመጽሐፉ ዋጋ ላይም ቅናሽ እናደርግልዎታለን።

የመጽሐፍት የዋጋ ዝርዝር ማየት ሲፈልጉ ቴሌግራም ገጻችንን ይጎብኙ።

t.me/guramaylebooks

Guramayle online book store Tewodros Teklearegay

 ?!ይህ መርህ የሚያመለክተው ከተከፈላችሁ ወይም ከሚጠበቅባችሁ አለፍ ያለ ሥራ መሥራት ወይም ጥረት ማድረግ እንደሚገባችሁ ነው፡፡ ያንን ስታደርጉም ደስ እያላችሁ ይሁን፡፡ ነገር ግን በርካታ ...
06/04/2022

?!

ይህ መርህ የሚያመለክተው ከተከፈላችሁ ወይም ከሚጠበቅባችሁ አለፍ ያለ ሥራ መሥራት ወይም ጥረት ማድረግ እንደሚገባችሁ ነው፡፡ ያንን ስታደርጉም ደስ እያላችሁ ይሁን፡፡

ነገር ግን በርካታ ሰዎች ለምን ብዬ ነው ከተከፈለኝ ውጪ አንድ ደቂቃስ ቢሆን የምጨምረው? ሲሉ ኖረዋል፡፡ አሁንም ይላሉ፡፡ ከሚጠበቅብን አለፍ ያለ ጥረት ማድረግ ግን በራሳችን ላይ መተማመንን፣ በሌሎች ዘንድ ደግሞ መከበርና መታመንን የሚያስገኝልን ቁልፍ ነው፡፡

ብዙ ሰዎች እንኳን ሁለተኛውን ተጨማሪ ኪሎሜትር ሊራመዱ ይቅርና የመጀመሪያውን ከተራመዱ በኋላ በጉራና ማልጎምጎም የተሞሉ ይሆናሉ፡፡ ነገር ግን በወጣትነት እድሜያችሁ የምትፈልጉትን ማግኘትና ማሟላት የምትፈልጉ ከሆነ፣ ይሰራሉ ተብሎ ከሚጠበቅባችሁ አለፍ ያለ እርምጃ መራመድ ይገባችኋል፡፡ ይህንንም ስታደርጉ ደስ እያላችሁ መሆን አለበት፡፡

የምነግራችሁ የተፈጥሮ ሕግ ነው፡፡ ተፈጥሮ ሕጓን ያከበረን ሁሉ ትሸልማለች፡፡ ሕጓን የሚቃረንን ደግሞ ትቀጣለች፡፡ የዚህን ሕግ ባለቤት ማንም ብላችሁ ብትጠሩት፣ ዞሮ ዞሮ ይህ ሕግ መኖሩን ተገንዝቦ በሕይወት ውስጥ ተግባራዊ ማድረግና መጠቀም የሰው ልጅ ድርሻ ነው፡፡

ተጨማሪ ጥረት ስታደርጉ ቀጣሪያችሁ ወይም የሥራው ባለቤት የሆነው አካል እንዲያውቀው ማድረግ ይገባል፡፡

ከሚለው የናፖሊዮን ሂል መጽሐፍ የተወሰደ።

 !!እውነተኛ ታሪክአባቱ በጣም በዝቅተኛ ደሞዝ ለረጅም ሰዓታት ይሰራ ነበር፡፡ በልጅነቱ አባቱ ጫማ ሊገዛለት ባለመቻሉ የቀዶ ጥገና ሐኪሙ በባዶ እግሩ ወደ ትምህርት ቤት መሄድ ነበረበት። የቤ...
23/03/2022

!!
እውነተኛ ታሪክ

አባቱ በጣም በዝቅተኛ ደሞዝ ለረጅም ሰዓታት ይሰራ ነበር፡፡ በልጅነቱ አባቱ ጫማ ሊገዛለት ባለመቻሉ የቀዶ ጥገና ሐኪሙ በባዶ እግሩ ወደ ትምህርት ቤት መሄድ ነበረበት። የቤተሰቡ ዋነኛ ምግብ አሬራ፣ ድንች እና ሻይ ሲሆን ፍራፍሬ እና ስጋ የሚመገቡት በአመት ሁለት ጊዜ ለገና እና ፋሲካ በአላት ብቻ ነበር፡፡

አንድ ቀን ይህ ወጣት አባቱን “አባዬ፣ የቀዶ ጥገና ሐኪም መሆን እፈልጋለሁ፤ የቀዶ ጥገና ሀኪም ለመሆን የምፈልገው ለምን እንደሆነም እነግርሀለሁ። ወደ ትምህርት ቤት አብሮኝ የሚሄደው ልጅ የዓይን ሞራ ግርዶሽ ነበረበት፡፡ የዓይን ቀዶ ሐኪሙ ቀዶ ጥገና አደረገለት እና አሁን በትክክል ያያል። እኔም እንደዚያ ሐኪም ጥሩ መሥራት እፈልጋለሁ።” አለው፡፡

አባቱም፤ “ልጄ፣ ባንክ ውስጥ በሃያ አምስት ዓመታት ጊዜ ውስጥ ያጠራቀምኩትን ሦስት ሺህ ፓውንድ (8,000 ዶላር ገደማ) አለ። ይህ ገንዘብ ለትምህርትህ የተቀመጠ ቢሆንም የህክምና ትምህርትህን እስክትጨርስ ድረስ ባትነካው እመርጣለሁ፡፡ ትምህርትህን ስትጨርስ በሃርሊ ጎዳና በሁሉም የስራ መሳሪያዎች የተሟላ እና የሚያምር የህክምና ማእከል ትከፍትበታለህ፡፡ እስከዛው ድረስ ግን ገንዘቡ ወለድ ያስገኝልሀል፤ መተማመኛም ይሆንሀል፡፡ በህክምና ትምህርትህ ላይ እያለህ ገንዘብ የግድ ሲያስፈልግህ ከላዩ ላይ መውሰድ ትችላለህ፤ ገንዘቡ ያንተ ነው፡፡ ነገር ግን ወለድ እየወለደልህ እስክትመረቅ ድረስ ቢጠራቀምልህ እመርጣለሁ፡፡” ሲል መለሰለት፡፡

ይህ ነገር ወጣቱን እጅግ ስላስደሰተው ከህክምና ትምህርት ቤት እስከሚመረቅ ድረስ ገንዘቡን በጭራሽ ላለመንካት ቃል ገባ። በበአላት እና በምሽት ፋርማሲ ውስጥ በመስራት በሚያገኘው ገንዘብ እንዲሁም በአንድ ኮሌጅ ውስጥ ኬሚስትሪ እና ፋርማኮሎጂ ኮርሶችን እያስተማረ በሚያገኘው ገንዘብ የህክምና ትምህርቱን ወጪ ሸፈነ፡፡

ሃሳቡ በሙሉ ለአባቱ የገባውን ቃል እስኪያጠናቅቅ ድረስ በባንኩ ውስጥ ያለውን ገንዘብ ላለመንካት ሆነ።

የሚመረቅበት ቀን ደረሰ፤ እናም አባቱ በዚያ እለት “ልጄ፣ ዕድሜዬን በሙሉ የድንጋይ ከሰል እየቆፈርኩ የትም አልደረስኩም። በባንክ ውስጥ አንድ ሺሊንግ ወይም ሳንቲም የለኝም፤ በጭራሽም አልነበረኝም። በጥልቀት እንድትቆፍር እና በውስጥህ ያለውን ገደብ አልባ፣ የማያልቅ እና ዘላለማዊ የወርቅ ማእድን እንድታገኝ እፈልግ ስለነበረ ነው፡፡” አለው፡፡

የቀዶ ጥገና ሀኪሙ፡- “ይህንን ስሰማ ማመን አልቻልኩም፤ እጅግ ከመደነቄ የተነሳ ቃል ማውጣት እንኳን አልቻልኩም፡፡ ድንጋጤና መደነቄ ለጥቂት ደቂቃዎች ካለፉ በኋላ ሁለታችንም በሳቅ ፈረስን፡፡ ያኔ አባቴ ሊያስተምረኝ የፈለገው በፈለግኩት ሰአት ከባንክ ላወጣው በምችለው ገንዘብ የተደገፈ የብልጽግና ስሜት እንዳዳብር ነበር፡፡ ይህም ድፍረት፣ እምነት እና በራስ መተማመን ሰጠኝ፤ እናም በራሴ እንዳምን አደረገኝ። በባንክ የተቀመጠ ሶስት ሺህ ፓውንድ አለኝ የሚለው እምነቴ እውነተኛ በባንክ የተቀመጠ ፓውንድ ቢኖረኝ ኖሮ እንዳሳካው የሚያስችለኝን አላማ ለማሳካት እረድቶኛል፡፡” አለኝ፡፡

ከሚለው መጽሐፍ የተወሰደ።

መጽሐፍት ቤትዎ ድረስ ያለተጨማሪ የማድረሻ ክፍያ (free delivery) እንዲሁም ከ10-50% በሆነ ቅናሽ እንዲመጣልዎ ሲፈልጉ ከታች ያለውን የቴሌግራም ሊንክ ይጠቀሙ።

Telegram- https://t.me/guramaylebooks

Address

Addis Ababa

Telephone

+251912319263

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Guramayle online book store posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Guramayle online book store:

Shortcuts

Share

Category