12/01/2021
ከፖለቲካው አረፍ ስንል...
ዳንኤል ተፈራ..
የአገራችን ረጅሙን ግጥም እናገኛለን። ገጣሚው ረዘምዛሜ ይለዋል።
ለም ሆቴል አካባቢ አብርሆት መጽሐፍት ቤት ዘው ስል ነው የተፋጠጥነው። አነበብኩትም።
የሶሻል ሚዲያው ማኅበረሰብ በአጭሬ ይደመማል። ፕ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ የረዘምዛሜ ግጥምም ጌታ ናቸው።
እስከማውቀው "ይቺ ናት የእኔ ምድር" በኢትዮጵያ ረጅሙ ግጥም ነው። ግጥሙ የአገር ናፍቆትን፣ የተፈጥሮ ጸጋን፣ በቁጭት መንገብገብን እየተረከ ነጮችን እየሞገተ 76 ገጽ ድረስ ዘልቆ ይቋጫል።
እኔ የማስታውሰው ረጅም ግጥም የታላቁ ገጣሚና ባለቅኔ ፀጋዬ ገ/መድህን "እሳት ወይ አበባ" ነው። ካልተሳሳትኩ 7 ገጽ መሰለኝ።
የፕሮፌሰር ፍቅሬ ረዘምዛሜ በመጽሐፍ ብቻ ሳይሆን በድምጹ አንብቦት በሲዲ አለ። ይሄ የኢትዮጵያችን ረጅም ግጥም ሲነበብ 1 ሰዓት ይፈጃል።
እና ምን ለማለት ነው? ፕሮፌሰሩ የረጅሙ ግጥም ባለቤት ብቻ ሳይሆኑ ባለሪከርድም ናቸው ለማለት ነው።