15/10/2022
ላፕቶፕ ስንገዛ ማወቅ እና ማየት ያለብን ወሳኝ ነጥቦች
ላፕቶፕ ሲገዙ ማገናዘብ ያለብዎ አስፈላጊ ነገሮች⤵
1.➡ምን ሊሰሩበት አስበዋል?
✔ ብዙ ሚፅፉ ከሆነ ኪቦርዱን ማየት ይገባል
✔ ጌም ሚያበዙ ከሆነ ግራፊክስ ካርዱንና ስፒከሩን
ይመልከቱ
✔ለቪዲዮ ቅንብር (editing or software Engineering) ከሆነ ከፍተኛ የፕሮሰሰር አቅም ፣ ትልቅ ሳይዝ ራም high definition (HD) ስክሪን
መኖሩን ያረጋግጡ
2 ➡አዲስ ከካምፓኒው እንደመጣ ( brand new ) ነው
ወይም በብልሽት ምክንያት ተመልሶ ካምፓኒው
ገብቶ የተሰራ (Refurbished ) መሆኑን ያረጋግጡ
3.➡የስክሪን ወይም የዲስፕለይ መጠን: ለርሶ ትክክለኛዉን የስክሪን መጠን ይምረጡ
(13.3” ,15.6”,17.3”)
4.➡የላፕቶፑን ስፔሲፊኬሽን በጥልቀት ይመርምሩ
✔ፕሮሰሰር (intel core 2 dou, core i3, core i5,
core i7 or AMD and others)
✔ራም (ስንት እንደሆነ 1GB,2GB,3GB,4GB , 8G and above)
✔ ሀርድ ዲስክ (160 GB, 250GB, 320GB,500GB, 750GB and above)
✔ዲቪዲ ወይም ብሉሬይ ድራይቭ ( re-writable )
5.➡ባትሪ ይህ በጣም ወሳኝ ነው ። ሊደራደሩበት
አይገባም! ቢያንስ 3 ሰአት እና ከዛ በላይ ቢሆን አሪፍ ነው
6.➡የሚፈልጉት ኦፕሬቲንግ ሲስተም ይምረጡ:
ማክሮሶት ዊንዶውስ (windows 7, windows
8,windows10, windows11) , mac, Ubuntu,Linux ወዘተ
ዊንዶውስ 10 ወይም windows 11 ቢመርጡ ይመከራል!
1 የመሳሪያ ስርዓት (Operating system)
2 የስክሪን መጠን (Screen Size)
3 ሲፒዩ(CPU)
4 ራም(RAM)
5 የሃርድ ድራይቭ አይነት (Hard Drive Type)
6 የምስል ጥራት (Image Quality)
7 የባትሪ ቆይታ (Battery Life)
8 ብራንድ (Brand)
ኮርi3 ኮርi5 ኮርi7 ምንድናቸው?
በሃገራችን ገበያ አሁን አሁን በርከት ያሉ የላፕቶፕ እና
የኮምፒውተር ሱቆች እየታዩ ይገኛሉ፡፡ለገቢያም የተለያዩ
የላፕቶፕ አይነቶች.በተለያየ ይዘት ይገኛሉ፡፡ እንዚህን
የተለያየ ይዘት ያላቸውን የላፕቶፕ አይነቶች ለመግዛት በዋናነት
መታየት ያለበትን ከዚህ በታች በዝርዝር ተቀምጠዋል፡፡
1. የመሳሪያ ስርዓት (platform) Windows, Mac and Linux
ለአጠቃቀም ምቹ እንደሆነ የሚነገርለት Windows የብዙ ሰዎች
ምርጫ ነው፡፡ቀላል፣ ምቹ እና ተለዋዋጭ ነው፤ በዋጋም ደረጃ
ጥሩ የሚባል ነው፡፡ ማክ( Mac) የአፕል ድርጅት ምርት ሲሆን ለዲዛይን
ተመራጭ የሆነ ፕላትፎረም ነው፡፡ለደህንነትም ከWindows እንደሚሻል ይነገርለታል፡፡
2. የስክሪን መጠን ወደ ግዢ ከመግባታችን በፊት የምንገዛው ላፕቶፕ ከቦታ
ወደ ቦታ ይዘን ለመንቀሳቀስ (portable) ምቹ መሆኑን ማረጋገጥ
ያስፈልጋል፡፡ ላፕቶፖች እንደየስክሪን መጠናቸው የተከፋፈሉ ናቸው፡፡
☑️ 11 to 12 inches(27.94cm-30.48cm) ፡በጣም
ቀጭን እና ቀላሉ የስክሪን ሳይዝ ነው፡፡ ከ1.1ኪሎ እስከ1.5ኪሎ
ይመዝናል፡፡
☑️ 13 to 14 inches (33.02cm- 35.56cm) ፡ይህ የስክርን
ሳይዝ ያለቸው ላፕቶፖች በጣም ተመጣጣኝ portability
ያላቸው እና በላፕቶፕ ተጠቃሚዎች ተመራጭ ናቸው፡፡
☑️ 15 inches(38.1cm): እውቁ የላፕቶፕ የስክሪን
ሳይዝ ሲሆን፤ተለቅ ያለ የስክሪን ሳይዝ ከፈለጉ ይህንን እንዲገዙ
እንመክራለን ፡፡
☑️ 17 to 18 inches (43.18cm- 45.72cm)፡
ላፕቶፖን ይዘው የማይንቀሳቀሱ ከሆነ