ትንቢተ ሼህ ሁሴን ጅብሪል

Directions Website

ትንቢተ ሼህ ሁሴን ጅብሪል ትክክለኛው የሸህ ሁሴን ጅብሪል ትንቢታዊ ግጥሞች እዚህ ያገኛ

የሸህ ሁሴን ጅብሪል ሚስጥራዊ ትንቢቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን JOIN ይበሉ።👉 https://t.me/ShehHusenJibrilTinbit
07/07/2024

የሸህ ሁሴን ጅብሪል ሚስጥራዊ ትንቢቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን JOIN ይበሉ።
👉 https://t.me/ShehHusenJibrilTinbit

23/06/2024

ትንቢተ ሸህ ሁሴን ጅብሪል ስለ አማራ (ከባለፈው የቀጠለ...)

ህዝቡን ኩፍኝ ይዞት ያመጥፎ አንከሊስ
የማያነቃንቅ የማያላውስ
ባለፉት ሲገርመን መጣ የሚብስ
በምላሱ ቆርጦ ባፉ የሚጠብስ
ለጥፋት የላከው የልቡ የማይደርስ
ተመክሮ የማይሰማ የማይመለስ
አገር እንደዳቦ የሚቆራርስ
መቆፈሪያ ይዞ ሌት ተቀን ሲምስ
ቴድሮስ የካበውን እየሁት ሲያፈርስ
መናገር ቀላልነው ማውራት በምላስ
ሳይናገር አይቀር ሰው ሳይተነፍስ
አማራን አግልሎ ወያኔ ሲነግስ።

ኦሮሞ የራሱን መንገድ ሳይቀይስ
ወያኔን አጂቦ አማራን ሲውቅስ
አማራው ሲበደል እያየው ሲያለቅስ
በየደረሰበት ሲባል ኪሳኪስ
በሰራው ባልሰራው ወንጀል ሲከሰስ
ስድብ ታንገቱ ላይ እንደጌጥ ሲለብስ
ባገር ፍቅር ነዶ ልቡ ሲጠበስ
አብረው እንዳልበሉ እራትና ቁርስ
ልክ እንደማያውቀው ሆነበት አድስ
ወዳጅ ይከዳል ወይ ክፉቀን ሲደርስ
ለመጣ ወያኔ ከትግራይ መለስ
ፍቅራቸው አረጀ እንዳሮጌ ልብስ።

ይቀጥላል.....

የሸህ ሁሴን ጅብሪል ሚስጥራዊ ትንቢቶችን ለመከታተል
የቴሌግራም ቻናላችንን JOIN ይበሉ።
👉 https://t.me/ShehHusenJibrilTinbit

ትትንቢተ ሸህ ሁሴን ጅብሪልሸትንቢተ ሸህ ሁሴን ጅብሪልሁትንቢተ ሸህ ሁሴን ጅብሪልጅትንቢተ ሸህ ሁሴን ጅብሪል@

23/06/2024

ትንቢተ ሸህ ሁሴን ጅብሪል (የቀጠለ...)
https://t.me/ShehHusenJibrilTinbit
የወያኔን ጂራፍ ኦሮሞው ቲቀምስ
እንቅፋት ሲመታው ጫማው ሲበጠስ
ግብዣ ጠራ ሕዝቡን እንዲንቀሳቀስ
የወያኔን ትዛዝ ሕጉን እንድጥስ
መንግስቱን ሊፋለም እልህ ሊያስጨርስ
የወገኑን ጥቃት ደሙን ሊመልስ
በሰው አጥር ዘሎ ደንበር ለሚጥስ
ለኔ ብቻ ብሎ ጠቅሎ ለሚጎርስ
አጥብቀህ ታገለው እንዳትመለስ
ተፈለግከው ቦታ ስፍራ እስተምደርስ
ባለስልጣን ቢሾም ሕጉን ቢያሳድስ
ቡዙም አያራምድ የትም አያደርስ
አገር አያሻሽል ችግር አይቀንስ
ይሂንን እያለ ያዘ መገስገስ።

እንዳትረሳው ቃሌን እንድታስታውስ
ውነቱን እናውራ ወሬ አናድበስብስ
ሕዝቡ ተሰልፎ ድምጡን ሲለግስ
ሲሯሯጥ አየነው ሁሉም ለመንገስ
ስልጣን የጠማችው የያዛቸው ሱስ
በምርጫ መስሏቸው ደም የሚመለስ
ጉልበቱን ተመትቶ ሸዋ ቢያነክስ
ቀን እስቲያልፍ በሎ ትንሽ ቢታገስ
ባፉ አያላመጠ ከንፈሩን ቢነክስ
አልገመተም ነበር አጥሩ እንዴሚጣስ
ለሰው ይመስለዋል ደግና ለጋስ
ሸዋ አንዳይገርማችሁ ቃልኪዳን ቢያፈርስ።

ይቀጥላል.....

የሸህ ሁሴን ጅብሪል ሚስጥራዊ ትንቢቶችን ለመከታተል
የቴሌግራም ቻናላችንን JOIN ይበሉ።
👉 https://t.me/ShehHusenJibrilTinbit

03/05/2024

Ethiopia - ሸህ ሁሴን ጅብሪል | Sheh Husen Jibril Tinbit | Jibril Tube | Eritrean News | Ethiopian News ...

17/04/2023

በአንድ ቃል ብቻ ግለፁት !

17/04/2023

ማስታወቂያ
ከስር በፎቶ የምትመለከቷቸው ሽማግሌ ከቀናት በፊት ወደ ሸገር ስራ ላፈላልግ ብለው ከቤታቸው እንደወጡ እስካሁን አልተመለሱም። ወዳጅ ዘመዶቻቸው ተጨንቀዋል። ያሉበትን ያወቀ ወይም የተመለከተ 10K ሽልማት..........ቤተሰቦቻቸው

ሸህ ሁሴን ጅብሪል ስለ ጌታቸው ረዳ እጣፈንታ ስለ ህወሃት መገ*ደል የተነበዩት ! Sheh Husen Jibril Tinbit |
09/04/2023

ሸህ ሁሴን ጅብሪል ስለ ጌታቸው ረዳ እጣፈንታ ስለ ህወሃት መገ*ደል የተነበዩት ! Sheh Husen Jibril Tinbit |

ትንቢተ ሸህ ሁሴን ጅብሪል || Sheh Husen Jibril Tinbit | Prophecy sheh husen jibril (tinbit),sheh husen jibril tinbitsheh...

09/04/2023
ሸህ ሁሴን ጅብሪል ዶ/ር አቢይ ስልጣናቸውን መቼ እንደሚለቁና ቀጥሎ ማን እንደምሾም የተነበዩት | Sheh Husen Jibril Tinbit |
26/03/2023

ሸህ ሁሴን ጅብሪል ዶ/ር አቢይ ስልጣናቸውን መቼ እንደሚለቁና ቀጥሎ ማን እንደምሾም የተነበዩት | Sheh Husen Jibril Tinbit |

ትንቢተ ሸህ ሁሴን ጅብሪል || Sheh Husen Jibril Tinbit | Prophecy husen jibril (tinbit),sheh husen jibril tinbit...

14/03/2023

የሀገሬ ሙስሊሞች በትግራይ ክልል ከዉቅሮ ከተማ አጠገብ ነጃሽ በምትባል ቀዬ ዉስጥ ለሚገኘዉ የቀብር ስፍራ የተለየ ክብር እንዳላቸዉ ይታወቃል፡፡ ይህ መካነ መቃብር በተለይም ጥንት በሀጅ ጉዞ ወቅት በብዛት ይዘየር ነበር፡፡ ዚያራዉ አሁንም ድረስ በተለያዩ አጋጣሚዎች ይከናወናል፡፡ በየዓመቱ የዐሹራ ቀን ደግሞ መዉሊድ ይደረግበታል፡፡ ከመዉሊድ ለመታደም ሙስሊሞች ከአራቱም አቅጣጫ ወደርሱ ይጎርፋሉ፡፡ ይህ ከጥንት ጀምሮ ለትዉልድ የተላለፈ ልምድ ነዉ፡፡ ‹‹ሪህለተል ሀበሻ›› ከተሰኘ የጉዞ ማስታወሻ ዉስጥ የሚከተለዉ መልዕክት ሰፍሮ እናገኛለን፡-

وينـعـقد فيه أي في محل دفنه كل سنة سوق كبير يأتي إليه ألوف من المسلمين والمسيحيين لزيارة قبر النجاشي.

‹‹ነጃሺ ከተቀበሩበት ሥፍራ በየዓመቱ ሰፊ የገበያ ማዕድ ይዘረጋል፡፡ በሺዎች የሚቆጠሩ ሙስሊሞችም ክርስቲያኖችም የነጃሽን ቀብር ለመዘየር ወደርሱ ይመጣሉ፤›› (ኢዕላመል አግቢያ ገጽ 150)

የማስታወሻዉ ባለቤት ሷዲቅ ባሻ የተባለ የኦቶማን ኤምፓየር የጦር ጄኔራልና ዲፕሎማት ሲሆን የጉዞዉ ዓላማ ከሱልጣን ዐብዱል ሀሚድ የተላከ መልዕክት ለዳግማዊ ምኒልክ ማድረስ ነበር፡፡ ጉዞዉ የተከናወነዉ እንደፈረንጆች የዘመን ቀመር በ1896 ነበር፤ከአድዋ ድል ማግስት፡፡ 127 ዓመት ሆኖታል፡፡ ከዚያ ዘመን በፊት በየዓመቱ የነጃሽን ቀብር ለመዘየር ሰዎች ወደቦታዉ ይጎርፉ እንደነበር ያረጋግጣል፡፡

የቀብር ዚያራን ከ‹ሽርክ›› የሚያገናኝንና መዉሊድን እንደ ክፉ ‹‹ቢድዐ› የሚቆጥርን ወገን ይህ ለምዕተ ዓመታት የቆየ ልምድ ማስከፋቱ አልቀረም፡፡ ህዝቡን ከ‹‹ሽርክ›› እና ከ‹‹ቢድዐ›› ‹‹ለመታደግም›› ልምዱ ይቋረጥ ዘንድ ይህ ወገን ቢመኝና ቢተጋ የሚጠበቅ ነዉ፡፡ ለዚህ ደግሞ አሪፉ ዘዴ ይህን ሥፍራ ልዩ የሚያደርገዉን ነገር መንጠቅ ነዉ፡፡ ያ ልዩ ነገር የነጃሺ መካነ መቃብር መሆኑ ነዉ፡፡ ‹‹እንቲሻረል ኢስላም…›› ኪታብ ውስጥ ዉቅሮ አጠገብ፣ በነጃሺ ቀዬ የሚገኘዉን ይህን መካነ መቃብር በተመለከተ"لاتوجد أدلة تؤكدها" (የነጃሺ ትክክለኛ ቀብር ስለመሆኑ ማረጋገጫ አይገኝለትም- ቅጽ 2 -ገጽ 114) የሚል አወዛጋቢ ሀሳብ የመንጸበረቁ አንደኛዉ መግፍኤ ይህ አይዲዮሎጂያዊ ስሌትና ሥነ ልቦናዊ ስሜት ይሆን?

አሁን አሁን የሀገራችንን በጎ ቅርሶችና ትዉፊቶች፣ ድሎችና ስኬቶች የሚያጥላላ ወይም የሚያጠይም፣በሀገር ታሪክና ጥቅም ላይ የሚሳለቅ፣በጎ ነገሮችን ሁሉ ከኢትዮጵያ የሚያርቅ አተያይ የዘዉግ ፖለቲካን ተደግፎ ድምጹ እየተሰማ ከመሆኑ አኳያ ይህ ድምዳሜ የዚህ አተያይ እንፅብራቂ እንዳይሆን የሚሰጋ ወገን ሊፈረድበት ይገባልን?

የሀገራችንን የተሰነዱ ታሪኮች ለመሰረዝና መነሻ በሌላቸዉ አፈታሪኮች ለመተካት እየባዘኑ ላሉ ‹‹የታሪክ ሌቦች›› "ኢንቲሻር.." ውስጥ የሰፈረ ይህ እይታ ‹‹ሰርግና ምላሽ›› እንደሚሆን ጥርጥር አለዉን?

ዉቅሮ አጠገብ የሚገኘዉ ቀብር የነጃሽ ስለመሆኑ ከትዉልድ ትዉልድ ለምዕተ ዓመታት ሲተላለፍ የኖረ ነዉ። ቀየዉም የቀብሩን ባለቤት ስም ወርሶ ለዘመናት ኖሯል፡፡ ይህን የተጠራጠረም ያስተባበለም አሊም ወይም ሙስሊም የታሪክ አዋቂ በበኩሌ አልገጠመኝም።

እንዲህም ስለሆነ ዕዉቁ የሀበሻ ታሪክ ጸሀፊ ሸህ ሰይድ ሙሀመድ ሳዲቅ ‹‹መንሀሉል ዐጥሻን ፊታሪኺል ሁብሻን›› ከተሰኘ ኪታባቸዉ ዉስጥ (ገፅ 134) ይህ ቀብር የነጃሺ መሆኑን አፅንተዋል ብቻ ሳይሆን የአላህ በረከት የሚዘንብበት ስለመሆኑ በአቡዳዉድ የተዘገበዉን ተከታዩን የእናታችን ዐኢሻን ዘገባ ዘክረዋል፡-

كنا نتحدث أنه لايزال على قبر النجاشي نور

‹‹ከነጃሺ ቀብር ላይ ‹‹ኑር›› ያለ ስለመሆኑ እናወጋ ነበር፤››

እዉቁ አሊምና የታሪክ አዋቂ አበልቃሲም ሸህ ሙሀመድ ታጁዲንም “ኢእላሙል አግቢያእ” በተሰኘ ስራቸዉ (ገጽ 149) ስለነጃሽ ሲተርኩ መካነ መቃብሩ ከዉቅሮ አጠገብ ነጃሽ በምትባል ቦታ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

وأصحمة النجاشي مدفون في محل يسمى اليوم بنجاش من أعمال مقاطعة تغراي

‹‹አስሀመተ ነጃሺ የተቀበሩት በትግራይ ክፍለሀገር በአሁኑ ሰአት ነጃሺ እየተባለ በሚጠራ ሥፍራ ነዉ፡፡››

የኢማም አህመድ አልጋዚ (አህመድ ግራኝ) ዜና መዋዕል ጸሀፊ ዐረብ ፈቂህ ‹‹ፉቱሀል ሀበሽ›› ከተሰኘ ኪታባቸዉ ዉስጥ ስለአንድ ክስተት ሲዘግቡ የሚከተለዉን ማስፈራቸዉን አበልቃሲም ጠቅሰዋል (ኢዕላም ገጽ 150)፡-

وسار الإمام وأصحابه من التـنبـيـن وهم مجدون كالماء الجاري ووصل في اليوم الثاني عند قبر أحمد النجاشي الذي كان زمن النبيّ -صلى الله عليه وسلم-، فقال المسلمون نزور اليومَ أحمد النجاشي، ونروح غدا للقتال الخ

‹‹ኢማሙና ባልደረቦቹ ከተንቤን ተነስተዉ እንደወራጅ ዉሀ ገሰገሱ፡፡ በሁለተኛዉ ቀን በነብዩ ዘመን ይኖር ከነበረዉ ከአህመደነጃሽ ቀብር ደረሱ፡፡ ሙስሊሞችም ‹ዛሬ አህመደነጃሽን እንዘይርና ነገ ወደዉጊያ እንሂድ› አሉ…፤››

ይህ የታሪክ መረጃ ስለ ነጃሺ የቀብር ስፍራ ጥቁምታ ይሰጣል፤ ነጃሺን ‹‹አህመደ ነጃሺ›› ብሎ የመጥራት ልምድ የቅርብ ጊዜ ሳይሆን ከ500 ዓመታት በፊት ጀምሮ እንደነበር ያጸናል፤ ኢማም አህመድና ሠራዊታቸዉ የነጃሽን ቀብር መዘየራቸዉንና ይህ የቀብር ዚያራ ከዚያ ዘመን በፊት ጀምሮ ሲወርድ ሲዋረድ እንደመጣ ይናገራል፡፡

‹‹ጀዋሂረል ሂሳን›› ከተባለ ኪታብ ዉስጥ ነጃሺ የተቀበሩባት ቀዬ ‹‹አህመደ ነጃሺ›› ተብላ ተጠርታለች፡-

إن قبره ببلدة (( أحمد نجاش )) بقرب (( حوزين)) بإقليم تغري

‹‹ቀብራቸዉ በትግራይ ክፍለሀገር ዉስጥ ከሀዉዜን አጠገብ አህመደነጃሺ በምትባል ሥፍራ ይገኛል፡፡›› (ኢዕላም ገጽ 150)

ስለዚህ ቦታዉ ከምዕተ ዓመታት በፊት ነጃሽ ወይም አህመደነጃሽ በመባል ይታወቃል፡፡ የርሳቸዉ ቀብር መሆኑም ከትዉልድ ትዉልድ ሲነገርና ሲጻፍ ኖሯል፡፡ ኢማም አህመድ አልጋዚ (ግራኝ) እና ከርሳቸዉ በፊት የነበሩ ዑለሞችና ሙስሊሞች ቦታዉን ሲዘይሩት ኖረዋል፡፡ በየዓመቱ የተለየ ዚያራና መዉሊድ ይደረግበታል፡፡ ይህ ልምድ እስካሁንም የቀጠለ ነዉ፡፡ የታወቀዉና የጸናዉ ዕዉነታ ይህ ሲሆን፣ المثبت مقدم على النافي በሚለዉ የሸሪዐ ‹‹ቃዒዳ›› መሠረት ከዚህ አስተሳሰብ የወጣ ወገን ከዘመናት ልምድና ለትዉልዶች ከተላለፈ መረጃ ያፈነገጠ ይሆናል፡፡

ይህችን አርቲክል በመጻፍ ላይ እያለሁ የባህል ሚኒስትሩ አቶ ቀጀላ መርዳሳ በዘንድሮዉ መዉሊድ ቀን በአንዋር መስጊድ የባዕል አከባበር ሥነ-ሥርዓት ላይ ዐረብኛውን ‹‹አስሀማ›› ከኦሮምኛው ‹‹አሸማ›› በማዛመድ ታሪክን ‹‹ለማወረም›› የተናገሯት ነገር ትዝ ብላኝ ብቻየን ፈገግ ብያለሁ፡፡ አባባላቸዉን እንደቀልድ ወስዶ ከመሳቅ በስተቀር ከቁም ነገር የሚጣፍ ባይሆንም ከፍተኛ የስነ ልቦና መዛነፍን ያሳያል፡፡ ለመረጃ ያህል ‹‹አስሀማ›› ትርጉሙ ‹‹ዐጥያህ›› (ስጦታ/ችሮታ) ማለት ነዉ፡፡

ይህ አጀንዳ የፖለቲካ፣የታሪክ፣የባህል፣ የቅርስና የሀይማኖት አንደምታ ስላለዉ እንዲህ በግርድፉ ብቻ የሚተዉ አይደለም፤ በወጉ መሰለቅ አለበት፤ ለማህበራዊ ሜዲያ አቅም ይህች መጣጥፍ በቂ ብትሆንም ወደፊት ዳግም ቅኝት ያስፈልገዉ ይሆናል፡፡

የቀሩኝን አንድ ሁለት ነጥቦች በቀጣይ ጽሁፍ፡፡

اللهم إنا نسألك علما نافعا ورزقا طيبا وعملا متقبلا

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ትንቢተ ሼህ ሁሴን ጅብሪል posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share