GoGebeya

GoGebeya Online Shopping site in Ethiopia.

ካነበብነው እናካፍሎ......|ጎገበያየቆዳ ላይ ሽፍታውድ የዶክተር ቤዛ ቤተሰቦች እንደምን አላችሁ? ሰውነታችን ላይ በተለያዩ የቆዳ ችግሮች እንዲሁም ሌላ ምክንያቶች ሽፍታዎች ይታዩብናል ዛሬ ...
12/03/2020

ካነበብነው እናካፍሎ......|ጎገበያ
የቆዳ ላይ ሽፍታ

ውድ የዶክተር ቤዛ ቤተሰቦች እንደምን አላችሁ? ሰውነታችን ላይ በተለያዩ የቆዳ ችግሮች እንዲሁም ሌላ ምክንያቶች ሽፍታዎች ይታዩብናል ዛሬ ስለ ለነዚህ ሽፍታዎች ትንሽ ልንላችው ወደናል መልካም ቆይታ ከዶክተር ቤዛ ባለሙያዎች ጋር !!!

ሽፍታ ምንድን ነው?

👉👉 የቆዳ ላይ ሽፍታ በአጭሩ ቆዳ በተለያዩ ምክንያቶች በሚቆጣበት ግዜ የሚ ከሰት ሁኔታ ነው እንደ ምክንያቱና ባህሪያቸው የሚለያዩ ቢሆንም የሚጋሯቸው ምልክቶች የመቅላት፣ የማሳከክ፣ የመላጥ ባህሪያት ሲሆኑ ደረጃቸው ከፍ ሲል ደግሞ ውሃ መሳይ ፈሳሽ መያዝ እንዲሁም በተቃራኒው ከፍተኛ ድርቀትና መጥቆር ያሳያሉ አንዲሁም ስያሜያቸው ከምክንያትና ከታዩበት የአካል ክፍል እና ከሚኖራቸው ቅርፅ የሚለያ ቢሆንም ህክምናቸው በአብዛኛው ተመሳሳይ ነው፡፡

👉 የቆዳ ሽፍታን ከዚህ በታች በተቀመጡት መልኩ ልንከፍላቸው እንችላለን፡፡

• አለርጂክ፡-መንስኤዎቹ ታሽገው የሚመጡ ምግቦች እና መጠጦች ፣ከምግቦች ደግሞ እንቁላልና ያልተፈተገ ስንዴን እና መድሃኒቶች ተጠቃሽ ናቸው፡፡

• ኮንታክት(የንክኪ)፡- መንስኤ የሚሆኑ ነገሮች በአብዛኛው የፀጉር ቀለም፣ ሜክአፕ፣ የቁልፍ ብረት፣ የቀበቶ ብረት፣ የአንገት ሃብሎች እና አሮጌ ጫማዎች ተጠቃሽ ናቸው፡፡

• ክብ ቅርፅ የሚይዙ፡-መንስኤዎቹ የሚባለው ብዙ ጊዜ ያልተለመደ አይነት የአየር መቀያየር ሲኖር በጣም ትንንሽ የሚያሳክክ ፍሬ የሚያካክሉ ቀያይ ሽፍታዎች በአብዛኛው እግር እና እጅ ላይ በመቀጠልም በመላው የአካል ክፍል ላይ ይወጣሉ፡፡

• አቶፒክ(ኢኬዜማ) ፡-በአብዛኛው በህፃናት ላይ የሚከሰት ሲሆን ከአስምና ሌሎች የአለርጂ በሽታዎች ጋር የተያያዘ ነው መንስኤዎቹ ጸደይ፣የአበባ ብናኝ እና የአየር ለውጥ የመሳሰሉትን መጥቀስ ይቻላል፡፡

• ኢሪታንት (በሚለበልብ ንጥረ ነገር የሚከሰት)፡-እንደ ዋናው ምክንያት የሚገለፀው በባህሪያቸው የመለብለብ ወይንም የማቃጠል ስሜት ከሚያስከትሉ ኬሚካሎች( ንጥረ ነገሮች ጋር ያልተሸፈነ) ቆዳ ንክኪ ሲኖር ነው፡፡

• ኒውሮ ደርማታይቲስ (ከጭንቀት ጋር የሚያያዝ)፡-• ይሄኛው አይነት ከላይ ከተጠቀሱት 5ቱ የሽፍታ አይቶች የሚለይበት ይህ ነው / በዚህ ይመጣል ተብሎ የተለየ ምክንያት ያለመኖሩ ሲሆን እስካሁን ሳይንሱ የተስማማበት ነገር ቢኖር የበዛ የዓይምሮ ጭንቀት ሲኖርና ሽፍታው በሚወጣበት አከባቢ ተደጋጋሚ መፈጋገፈግ በሚኖር ጊዜ እንደሆነ ነው፡፡
ዶክተር ቤዛ
https://gogebeya.com/

የሚያምሩ የልጆች አሻንጉሊቶችን.....|ከጎገበያhttps://bit.ly/38F48gd
10/03/2020

የሚያምሩ የልጆች አሻንጉሊቶችን.....|ከጎገበያ
https://bit.ly/38F48gd

09/03/2020
ውብ የጆሮ ጌጦችን ለማግኘት ሊንኩን ይጫኑ......|ጎገበያ https://bit.ly/2ToYdY7
06/03/2020

ውብ የጆሮ ጌጦችን ለማግኘት ሊንኩን ይጫኑ......|ጎገበያ
https://bit.ly/2ToYdY7

ካነበብነው እናካፍሎ......| ጎገበያበየቀኑ የምናደርጋቸው እና ለካንሰር የሚያጋልጡን ነገሮችውድ የዶክተር ቤዛ ተከታታዮች ዛሬ ይዘንላቹ የቀረብነው በየቀኑ የምናደርጋቸው ግን ሳናስተዉል ለጤ...
06/03/2020

ካነበብነው እናካፍሎ......| ጎገበያ
በየቀኑ የምናደርጋቸው እና ለካንሰር የሚያጋልጡን ነገሮች

ውድ የዶክተር ቤዛ ተከታታዮች ዛሬ ይዘንላቹ የቀረብነው በየቀኑ የምናደርጋቸው ግን ሳናስተዉል ለጤናችን ጠንቅ የሆኑ እና የካንሰር ህመም ሊያጋልጡን የሚችሉትን ነገሮች በማወቅ እንድትጠነቀቁ እና ጤንነትዎን እንዲጠብቁ የሚያስችል ተግባርዎ የከፋ የጤና ችግር ሊያስከትልብዎ እንደሚችሉ ልናስገነዝባቹ ወደድን ይከታተሉን።

1.በጨረር የሚደረጉ ምርመራዎች፡- ለምሳሌ ራጅ፣ ሲቲ ስካን፣ማሞግራፊ ፣ራዲዮቴራፒ…… ለምርመራው ሲባል ጨረር ስለሚለቀቅ በተደጋጋሚ ምርመራወን የምናደርግ ከሆነ ለካንሰር ተጋላጭ እንድንሆን ያደርገናል ስለዚህ 1 ሰው የጨረር ህክምና የሚያደርግ ከሆነ አስገዳጅ ካልሆነ በስተቀር የ6 ወር ልዩንት መኖር አለበት።

2.የላብ ማጥፊያ እና የጠረን መቀየሪያ(ዲዮድራንት)፡- ይህም የሚከሰተው በዲዮድራንት ውስጥ የሚገኘው አልሙኒየም አማካኝነት ሲሆን ይህንን በብብታችን ላይ በምንጠቀምበት ጊዜ ለጡት ካንሰር ተጋላጭ እንድንሆን ያደርጋል ስለዚህ በቀላሉ የሚዘጋጁ የጠረን መቀሪያ ስልቶችን መጠቀም ይቻላል ለምሳሌ ሎሚ

3.በምንመገበው ስጋ እና ወተት ውስጥ የሚጨመሩ ሆርሞኖች፦ ይህም ለከብቶች በሚሰጡ ሰው ሰራሽ ሆርሞኖች የሚከሰት ነው።

4.ሳሙናዎች፣ ሻምፑዎች እና ክሬሞች፦ ይህን በቆዳችን እና በፀጉራችን በምንጠቀምበት ወቅት ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል በተለይ በተሰነጠቀ ቆዳ ላይ በምንጠቀምበት ወቅት መጠንቀቅ ያስፈልጋል።

5.መርዛማነት ያላቸው የውብት መጠበቂያዎች፦ እነዚህ ምርቶች በፋብሪካ ውስጥ ያለፉ የውበት መጠበቂያ ምርቶች በምንጠቀምበት ወቅት በመጀመሪያ የቆዳችንን ባህሪ ማወቅ ያስፈልጋል እና በውስጣቸው ንጥረ ነገር የያዙ ስለሆኑ ቆዳን ዘልቆ የመግባት አቅም ስላላቸው ለካንሰር ተጠቂ እንድንሆን ያደርገናል እለዚህ ተፈጥሮአዊ የውበት መጠበቂያ ዘዴዎችን ቢጠቀሙ ጠቃሚ ነው።

6.ሰው ሰራሽ ማጣፈጫዎች፦ ማጣፈጫዎችን የሚያካትቱበት ነገሮች አብዝተን የምንጠቀም ከሆነ ለካንሰር ተጋላጭ እንድንሆን ያደርጉናል ለምሳሌ ከረሜላ፣ ለስላሳ መጠጦች…….

7.ከአኩሪ አተር የሚሰሩ ምርቶች፦ ለምሳሌ ሶያ ወተት ያለው ምግብ በውስጡ ሄማግሉቲኒን እና የደም መርጋትን የሚያስከትለውን ንጥረ ነገር ይዟል እና የኢስትሮጅን መጠንን ከፍ በማድረግ ለልብ ህመም ያጋልጠናል በተጨማሪም እነዚህን ምርቶች በብዛት መጠቀም ለካንሰር ተጋላጭ እንድንሆን ያደርገናል።

8.ፍሎራይድ የተጨመረበት ውሃ፦ በብዛት ፍሎሪድ በውስጡ የያዘ ውሃ በምንጠቀምበት ወቅት በሰውነታችን ውስጥ የሚገኙ ጠቃሚ ማእድናትን አጥቦ በማውትጣት ተፈጥሮአዊ በሽታ የመከላከል አቅማችንን ያዳክመዋል ስለዚህ ለካንሰር ተጋላጭ ያደርገናል።

9.መድሃኒቶች፦ በብዛት የምንወስዳቸው ለተለያየ ህመም የሚታዘዙ መድሃኒቶች

10.የታሸጉ ምግቦችን በብዛት መመገብ እና ሰው ሰራሽ ስኳር ማብዛት

11.ሲጋራ ማጨስ (ለሳንባ ካንሰር እንድንጋለጥ ያደርጋል
👌 ስለዚህ እነዚህን ነገሮች መጠቀም ለካንሰር ተጋላጭ ሁኔታዎች እንደሆኑ ተረድታቹ ከእነዚህ ጉዳቶች እራሳቹን እንድትጠብቁ ዶክተር ቤዛ መልእክቱን ያስተላልፋል።
https://gogebeya.com/

Address

Addis Ababa

Telephone

0911638452

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when GoGebeya posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to GoGebeya:

Share