Ahadu Radio & Tv አሀዱ ራድዮ እና ቲቪ

Directions

Ahadu Radio & Tv አሀዱ ራድዮ እና ቲቪ Selling online products

Online shopping and selling channel with good quality product with reasonable  price.
21/04/2021

Online shopping and selling channel with good quality product with reasonable price.

Online shopping and selling channel with good quality product with reasonable price.

21/01/2021

በሱዳን ዳርፉር ግዛት በተቀሰቀሰው ግጭት ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር 155 ደረሰ

በዳርፉር የተቀሰቀሰውን ደም አፍሳሽ ግጭት ተከትሎ የሱዳን ጦር በአካባቢው የተሰማራ ሲሆን ከተገደሉት 156 ሰዎች በተጨማሪ በርካቶች ክፉኛ ቆስለዋል።

ባሳለፍነው ቅዳሜ በአረብ ዘላኖች እና አረብ አይደለንም በሚሉት የማሳሊት ጎሳ አባላት መካከል በምዕራባዊ ዳርፉር ግዛት መዲና ኢል ገኒና ግጭት መቀስቀሱን የግዛቲቱ ገዢ ሞሃመድ አል ዶዩማ ተናግረዋል።

50 ሺ ያህል ዜጎች ግጭቱ ለስደት መዳረጉን ዓለም አቀፋዊው የረድኤት ድርጅት የልጆች አድን(Save The Children) አስታውቋል ።

ከካርቱም እና ከሌሎች ግዛት የተውጣጡ የፀጥታ አካላት ወደ ምዕራባዊ ዳርፉር ግዛት ያቀኑ ሲሆን በግዛቲቱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታውጇል።

21/01/2021

ጆ ባይደን 46ኛው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ሆነው በዋሽንግተን ዩኤስ ካፒቶል ተሰየሙ።

ከእርሳቸው ጋር ምክትል ፕሬዚዳንት ካሚላ ሀሪስ የተገኙ ሲሆን፣ የመጀመሪያዋ ሴት ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነው ቃለ መሀላ ፈጽመዋል።በበዓለ ሲመቱ ላይ የቀድሞዎቹ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ እና ባለቤታቸው ሚሼል ኦባማ፣ ጆርጅ ዎከር ቡሽ እና ባለቤታቸው ላውራ ቡሽ እንዲሁም ቢል እና ሂላሪ ክሊንተን ተገኝተዋል፡፡የትራምፕ ምክትል ፕሬዚዳንት የነበሩት ማይክ ፔንስም በበዓለ ሲመቱ ተገኝተዋል፡፡አዲሱ ተመራጭ ጆ ባይደን ቃለ መሀላ እስኪፈጽሙ ድረስ ወደ ዋሽንግተን ዲሲ የሚደረገው ማንኛውም በረራ እንደሚቋረጥ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ዘግበዋል።

11/01/2021

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በትግራይ ክልል የተወሰደውን የሕግ ማስከበር ርምጃ አስመልክቶ ለፓርላማ የሰጧቸውን ምላሾች የያዘ ኤሌክትሮኒክ መጽሐፍ ይፋ ተደረገ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ኅዳር 21 ቀን 2013 ዓ.ም በትግራይ ክልል የተወሰደውን የሕግ ማስከበር ርምጃ አስመልክቶ ለፓርላማ የሰጧቸውን ምላሾች የያዘ ኤሌክትሮኒክ መጽሐፍ በጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ይፋ ተደርጓል።

መጽሐፉ 142 ገፆች ያሉት ሲሆን "ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በትግራይ ክልል የተወሰደውን የሕግ ማስከበር ርምጃ አስመልክቶ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች የሰጡት ምላሽ" የሚል ርእስ ተሰጥቶታል።https://lm.facebook.com/l.php?u=https%3A%2F%2Fbit.ly%2F2K3D4RD%3Ffbclid%3DIwAR3-rsTLHbqBtvWje-4zPvmfgyXhH4XxrCs4Ywma5e0SVzbnXnu3NHsXZ6Q&h=AT2mV5V0d3Leim75KExg3aMTzTA7VvMHhKonC-8CLf7whNjbCyedGZqD1xTrzfNIMAfkiQ7TKf4LumxwcjoSHoDC7Ee4xhJrw3ja9KsoJfgjmCe4DE4cCjoQh9m6Mjf-5G5s7xYQdvskHhTvraw

07/01/2021

የደም መጣጩ ህውሀት አባላት በቁጥጥር ስር ዋሉ ። እርምጃም ተወሰደባቸው ።
የመከላከያ ሀይል ሰምሪት መምሪያ ኃላፊ ብ/ጄኔራል ተስፋዬ አያሌው እንዳረጋገጡት ፣ አቶ ተክወይኒ አሰፋ ፣ ዶክተር ሰለሞን ኪዳኔ ፣ አቶ ገ/መድህን ተወልደ ፣ አቶ ወ/ጊዮርጊስ ደስታ ፤ አምባሳደር አባዲ ዘሞ ፣ ወ/ሮ ቅዱሳን ነጋ ፣ አቶ ቴድሮስ ሃጎስ ፣ ወ/ሮ ምህረት ተክላይ ፣ አቶ አብርሃም አደም መሃመድ በቁጥጥር ስር ውለዋል ።
አቶ ሴኮ ቱሬ ጌታቸው ፣ አቶ ዘርአይ አስገዶም ፣ አቶ አበበ ገ/መድህን ፣ አቶ ዳንኤል አሰፋ ደግሞ እርምጃ የተወሰደባቸው ናቸው ።

07/01/2021

ሰበር ዜና
መከላክያ ሰራዊት ላይ መብረቃዊ ጥቃት ፈፅመናል ያሉት አቶ ሴኩ ቱሬ በትግራይ ክልል ህግን የማስከበር ዘመቻ እጅ አልሰጥም በማለታቸው እርምጃ ተወስዶባቸዋል::

07/01/2021

እርምጃ የተወሰደባቸውና የተያዙ የህወሓት ከፍተኛ አመራሮች ስም ዝርዝር ዛሬ ይፋ ይደረጋል የሚል ወሬ ደርሶናል

29/12/2020

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፖሊስ ም/ኮሚሽነር ኢንስፔክተር ምስጋና እንጂፈታ በመተከል ዞን የጸጥታ ችግር እጃቸው እንዳለበት በመጠርጠራቸው ዛሬ በቁጥጥር ስር እንደዋሉ ተገለፀ። ይህን የገለፁት የክልሉ ሰላም ግንባታና ፀጥታ ቢሮ ም/ኃላፊ አቶ ሙሳ ሃሚድ ናቸው።

አቶ ሙሳ ፥ ሌሎችም ከፀጥታ ችግር ጋር እጃቸው ያለባቸውን አመራሮች እና ግለሰቦች የማደኑ ስራ መቀጠሉን ለኢዜአ ተናግረዋል። ዛሬ ረፋድ የመተከል ዞን ዋና አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ አትንኩት ሽቱ በቁጥጥር ስር እንደዋሉ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን መገለፁ ይታወሳል::

23/12/2020

እንግሊዝ ተቸግራበታለች የተባለው አዲሱ የኮሮና ዝርያ ቫይረሱ ራሱን የመቀያየር ተፈጥሮ ያለው ሲሆን እስከ 70 በመቶ የመዛመት ፍጥነት አለው ተብሏል::

ቫይረሱ እንዴት ሊፈጠር እንደቻለ የታወቀ ነገር ባይኖርም የመከላከል አቅም ካነሰው የኮሮና ቫይረስ ተጠቂ እንደመጣ እየተነገረነው::

በእንግሊዝ ሀገር ያጋጠመው አዲሱ የኮሮና ባይረስ ዝርያ በቤልጄምና በሌሎች ሀገሮችም እየታየ እንደሆነም ታውቋል::

22/12/2020

ኢትዮጵያ ሁለተኛዋን ሳታላይት አመጠቀች፡፡

ሳተላይቷ የሪሞት ሴንሲንግ ሳተላይቷ ET-SMART-RSS በስኬት መምጠቋንም የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በማህበራዊ ገጹ አስታውቋል፡፡

Address

Addis Ababa

Opening Hours

Monday 09:00 - 17:00
Tuesday 09:00 - 17:00
Wednesday 09:00 - 17:00
Thursday 09:00 - 17:00
Friday 09:00 - 17:00
Saturday 09:00 - 17:00
Sunday 09:00 - 17:00

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ahadu Radio & Tv አሀዱ ራድዮ እና ቲቪ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share