Directions

Mule Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Mule, Shopping & retail, Adis ababa, Addis Ababa.

Match day🇬🇧 የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ 19ኛ ሳምንት ጨዋታ        🇬🇧 ብሬንትፎርድ ከ አርሰናል 🇬🇧⏰ የጨዋታ ሰዓት፦ ማታ 02:30🏟️ ስታድየም ፦ ጂ ቴክ ኮሚኒቲ⛳️የመሀል ዳኛ ፦...
01/01/2025

Match day

🇬🇧 የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ 19ኛ ሳምንት ጨዋታ

🇬🇧 ብሬንትፎርድ ከ አርሰናል 🇬🇧
⏰ የጨዋታ ሰዓት፦ ማታ 02:30
🏟️ ስታድየም ፦ ጂ ቴክ ኮሚኒቲ
⛳️የመሀል ዳኛ ፦ ፒተር ባንክስ
ድል ለእንግሊዙ ኩራት አርሰናል 🔴

የ17ኛው ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አርሰናል Vs ክሪስታል ፓላስ በፍጹም የጨዋታ ብልጫ 5 - 1 ተጠናቀቀ ።ጣፋጭ 3 ነጥብ እንኳን ደስ አለን ቤተሰብ 👏👏👏የ17ኛው ሳምንት የእንግሊዝ...
21/12/2024

የ17ኛው ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አርሰናል Vs ክሪስታል ፓላስ በፍጹም የጨዋታ ብልጫ 5 - 1 ተጠናቀቀ ።

ጣፋጭ 3 ነጥብ

እንኳን ደስ አለን ቤተሰብ 👏👏👏የ17ኛው ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አርሰናል Vs ክሪስታል ፓላስ በፍጹም የጨዋታ ብልጫ 5 - 1 ተጠናቀቀ ።

ጣፋጭ 3 ነጥብ

እንኳን ደስ አለን ቤተሰብ 👏👏👏

Abatachin atan 😭😭😭😢
17/09/2024

Abatachin atan 😭😭😭😢

10/08/2024

Shout out to my newest followers! Excited to have you onboard! Marde Best, Adinew Alibene

King
05/07/2024

King

05/07/2024

Shout out to my newest followers! Excited to have you onboard! Mathiwos Mehamed, Teme Ye Johon Liji, Shola Gamo Bayaa, Abdulfata Badri

ዛሬ ስቅለት ነው!!   | ተስፋ የጨለመ በሚመስልበትና ጨለማ በነገሠበት ዘመን፣ ስለ ፍቅርና ርኅራኄ የሚናገር አንድ ሰው ተከሰተ፡፡  ንግግሩ በተስፋ መቁረጥ በደነደነ ልብ ውስጥ የለውጥ ነበ...
03/05/2024

ዛሬ ስቅለት ነው!!

| ተስፋ የጨለመ በሚመስልበትና ጨለማ በነገሠበት ዘመን፣ ስለ ፍቅርና ርኅራኄ የሚናገር አንድ ሰው ተከሰተ፡፡ ንግግሩ በተስፋ መቁረጥ በደነደነ ልብ ውስጥ የለውጥ ነበልባል አቀጣጠለ። ነገር ግን መልእክቱ ኃያላንን በመገዳደር፣ ሁሌም መቆጣጠርን የሙጥኝ በሚሉት ዘንድ ፍርሃትና ቁጣን ቀሰቀሰ፡፡

ወዳጄ እያለ በሚጠራው ሰው ክህደት ተፈጽሞበት፣ በውሸትና ፍትህ በማጣት ለፍርድ ውሳኔ ቀረበ፡፡ ምንም እንኳን አንዳችም ያላጠፋ ንፁህ ሰው ቢሆንም ቅሉ፣ እጅግ እኩያን ለሆኑ ወንጀለኞች የሚጣለውን ቅጣት እንዲቀበል ተፈረደበት - ስቅላት!!

የሰማይ ስባሪ የሚያህለውን መስቀል በትከሻው ሲሸከም ሰውነቱ ቢደክምም፣ መንፈሱ ግን አልተሰበረም፡፡ ወደ ቀራንዮ በሚደረገው ስቃይ የተሞላበት ጉዞ ወቅት በንቀት የተጠማዘዙ ፊቶች፣ በጥርጣሬ የተመረጉ ልቦች አጋጥመውታል። ቢሆንም፣ በዓይኖቹ ውስጥ፣ የይቅርታ ጭላንጭል፣ የማይናወጥ የፍቅር ብርሃን ፈነጠቀ።

በጎልጎታ ኮረብታ ላይ ችንካሮች ሥጋውን ቸነከሩት፤ ጭንቅላቱም ላይ የእሾህ አክሊል አደረጉበት፡፡ በመከራው ጩኸት መሃል፣ የሚያደርጉትን ለማያውቁት እየጸለየ፣ የምሕረት ቃል ተናገረ። በዚያ ታላቅ የመስዋዕትነት ጊዜ፣ ህይወቱን ብቻ ሳይሆን፣ ለሚያምኑ ሁሉ የመቤዠትን ቃል ኪዳን ሰጥቷል።

ሰማዩ ሲጨልም እና ምድር ስትንቀጠቀጥ፣ የመጨረሻ እስትንፋሱ ወደ ዘላለማዊ ንፋስ ሹክ አለ። በመከራም ውስጥ እንኳን ፍቅር ጥላቻን እንደሚያሸንፍ፣ ተስፋም ከተስፋ መቁረጥ አመድ ውስጥ እንደሚወጣ፣ በዚያ ዝምታ ውስጥ ጥልቅ እውነት በየዘመናቱ አስተጋብቷል፡፡

***
ዛሬም ብርሃነ ስቅለቱን እያሰብን በስግደት እየወደቅንና እየተነሣን ስለ እኛ ሲል የተቀበለውን መከራ እናስባለን። ለብርሃነ ትንሣኤው በሰላም ያድርሰን። ..........𝗙𝗼𝗹𝗹𝗼𝘄 𝗮𝗻𝗱 𝗠𝗼𝗻𝗲𝘆𝗼𝗙𝗼𝗹𝗹𝗼𝘄 𝗮𝗻𝗱 𝗠𝗼𝗻𝗲𝘆.𝗙𝗼𝗹𝗹𝗼𝘄 𝗮𝗻𝗱 𝗠𝗼𝗻𝗲𝘆Chrome
Google ChromehGoogle Chromen CentChristian Center Church PA Christian Center Church PA.Christian Center Church PAoChristian Center Church PAa ChrisEthiopia Christ for the Nations Bible collegeeEthiopia Christ for the Nations Bible collegenEthiopia Christ for the Nations Bible collegeBEthiopia Christ for the Nations Bible collegeeEthiopia Christ for the Nations Bible collegeeEthiopia Christ for the Nations Bible collegeEthiopia Christ for the Nations Bible college

ያብባል ያብባል ቡናችን ይፈካልይደምቃል ይደምቃል ቡና ያሸበርቃል×2  አማረመት ሜዳው አማረበት   አማረበት ሜዳው አማረበት×2  ኢትዮጵያ ቡና ሲጫወትበት   ድል ነው ዛሬ ድል ነው ዛሬ   ድ...
26/04/2024

ያብባል ያብባል ቡናችን ይፈካል
ይደምቃል ይደምቃል ቡና ያሸበርቃል×2

አማረመት ሜዳው አማረበት
አማረበት ሜዳው አማረበት×2
ኢትዮጵያ ቡና ሲጫወትበት

ድል ነው ዛሬ ድል ነው ዛሬ
ድል ነው ዛሬ ዛሬ ነው ×2

ስንገባ ከሜዳው ቡኒ ቢጫ ለብሰን
የማሸነፍ ወኔን ሁልጊዜም ተላብሰን
ማንም የለም እኛን ችሎ የሚያቆመን
ከማሸነፍ ማማ ደርሶ የሚያወርደን
ከማሸነፍ ማማ ደርሶ የሚያወርደን

አማረበት ሜዳው አማረበት
አማረበት ሜዳው አማረበት ×2
ኢትዮጵያ ቡና ሲጫወትበት

ድል ነው ዛሬ ድል ነው ዛሬ
ድል ነው ዛሬ ዛሬ ነው ዛሬ ×2

እንደ ንስር ከንፈን እርቀን በረናል
ከቡና ጫፍ ሚደርስ ከወዴት ይገኛል
ሁልጊዜም ወደፊት ይጓዛል ቡናችን
ዘላለም ታላቅ ነው ውዱ ክለባችን
ዘላለም ታላቅ ነው ውዱ ክለባችን

አማረበት ሜዳው አማረበት
አማረበት ሜዳው አማረበት ×2
ኢትዮጵያ ቡና ሲጫወትበት

ድል ነው ዛሬ ድል ነው ዛሬ
ድል ነው ዛሬ ዛሬ ነው ዛሬ ×2

ስንተሳሰር ቡና
ባንድላይ ሆነን ቡና
ከመንገዳችን ቡና
የለም ሚያቆመን ቡና
ለክለባችን ቡና
ቃልኪዳን ያለን ቡና
የኢትዮጵያ እግርኳስ ቡና
እስትንፋሶች ነን ቡና
የኢትዮጵያ እግርኳስ ቡና
እስትንፋሶች ነን ቡና
ኢትዮጵያ ቡና ህዝባዊ ክለብ
🎧 💪

የልጅነት የኳስ ጨዋታ ህጎች!  ትዉስታ በድጋሚ 1 ምንጊዜም ሰፈር ውስጥ ወፍራሙ ልጅ ጎል ጠባቂ ነው።2 ሁልጊዜ ጨዋታ የሚያልቀው ሁሉም ተጫዋች ከደከመው  ብቻ ነው።3 አስር ጊዜ ጎል ስታስገ...
26/04/2024

የልጅነት የኳስ ጨዋታ ህጎች! ትዉስታ በድጋሚ

1 ምንጊዜም ሰፈር ውስጥ ወፍራሙ ልጅ ጎል ጠባቂ ነው።

2 ሁልጊዜ ጨዋታ የሚያልቀው ሁሉም ተጫዋች ከደከመው ብቻ ነው።

3 አስር ጊዜ ጎል ስታስገባ ብትውልም የሚያሸንፈው መጨረሻ ላይ ጎል ያስገባው ቡድን ነው።

4 ዳኛ ቢኖርም በጩህትና በጭቅጭቅ ያሳመነው ያሸንፋል።

5 ምንጊዜም የኳሱ ባለቤት ካኮረፈና ከተበሳጨ ጨዋታው ያልቃል።

6 ሁለት ጎበዝ ተጨዋች አንድ ቡድን ውስጥ መጫወት በልጅነት ህግ የተከለከለ ነው።

7 ድንገት ተቃራኒ ቡድኑ ፔናሊቲ ካገኘ የኳሱ ባለቤት ከመቅፅበት ጎል"ጠባቂውን አባርሮ ራሱ ጎል ጠባቂ ይሆናል።

8 ኳሱ ፎሪ ወጥቶ የሰው ግቢ ውስጥ ከገባ ያስገባው ልጅ ሙሉቀንና ሙሉ ለሊት ሸፋፋ እየተባለ ሲሰደብና ሲረገም ይውላል።

9 ምንጊዜም በጣም ጎበዙ ተጫዋች የኳሱ ባለቤት ጋር አንድ ቡድን ናቸው።

10 ጨዋታው አንዱን ቲም ከተቃራኒው ለመለየት አንዱ ቲም ከወገብ በላይ ራቁቱን ይጫወታል።

11 ምንጊዜም ጨዋታ የሚጀመረው ኳሷን ወደ ሰማይ በመጠለዝ ነው።

12 አጥቂ ተከላካይ የሚባል የለም ሁሉም ያጠቃል ሁሉም ይከላከላል የደከመው ወገቡን ይዞ በረኛውን ያወራዋል።

13 ምንጊዜም የኳሱ ባለቤት FIFA በለው።

14 ኦፍ ሳይድ የለም ግር ብለህ ታጠቃለህ ግር ብለህ ትከላከላለህ ግሪሳ ሁላ።

15 ድንገት በጨዋታ መሃል እናትህ ከጠሩህ ሰው ተክተህ ትሄድና ስትመለስ የተካህውን ሰው አባርረህ ጨዋታውን ከቆምክበት መቀጠል ትችላለህ።😂

ጨምሩበት! ትዝታ ካለባችሁ ሼር አድርጉ

Address

Adis Ababa
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Mule posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share