ዩኒቲ መጻሕፍት-Unity Books

ዩኒቲ መጻሕፍት-Unity Books የአንባቢያን እና የደራሲያን ቤት ነው። ይግቡ።

24/09/2026

የ6ኛ ክፍል የሚኒስትሪ ፈተናን በተሻለ ዝግጅት ለመፈተን ዝግጁ ነዎት?
እነሆ! ማርቭል የመግቢያ ፈተናዎች(ሚኒስትሪ) ፈተና ስብስብ ለ6ኛ ክፍል ተማሪዎች በልዩ ሁኔታ ተዘጋጅቶ ለገበያ ቀረበ።
ማርቭል የ6ኛ ክፍል የሚኒስትሪ ፈተና መጽሐፉ በውስጡ፡-
+ ከ2015 እስከ 2018 የሚኒስትሪ ፈተናዎችን ያጠቃለለ
የፈተና ጥያቄዎችን በቀላሉ ለመረዳት የሚረዱ ማብራሪዎች
+ ለተማሪዎች የፈተና ልምምድ ያግዛል
+ ጥያቄዎችን በጥልቀት ያብራራል
+ ፈጣን የክለሳ አቀራረብ
+ ራስን ለመገምገም የሚረዳ
+ ስድስቱን የመመዘኛ የትምህርት ዓይነቶች የተካተቱበት
@ ሌላው መጽሐፉን ልዩ የሚያደርገው በ2018 የተካተተውን የአፋን ኦሮሞ የሚኒስትሪ ፈተናን በማካተት በተጨማሪም 2 የአፋን ኦሮሞ ሞዴል ፈተናዎችን እንደ ቦነስ የተካተቱበት መሆኑ።
ለ6ኛ ክፍል የሚኒስትሪ ፈተና ዝግጅት ዛሬውኑ ይጀምሩ!
ማርቭል ይልቃል!

24/09/2026

ማርቭል
አካባቢ ሳይንስ
ለ5ኛ እና ለ6ኛ ክፍል
በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት መሠረት የተዘጋጀ
ማርቭል አካባቢ ሳይንስ ለ5ኛ እና ለ6ኛ ክፍል አጋዥ መጽሐፍ በውስጡ፡-
+ ስምንት ምዕራፎች ከሰፊ ማብራሪያዎች ጋር እንዲሁም ገላጭ ከሆኑ ካርታዎች ፣ ሥዕሎችና ፎቶግራፎች ያካተተ።
+ በእያንዳንዱ እርዕሶች ላይ በጣም በርካታ የመልመጃ ጥያቄዎች ከበቂ ማብራሪያና መልሶቻቸው ጋር የተካተቱበት።
+ በየምዕራፎቹ መጨረሻ በርካታ የማጠቃለያ ጥያቄዎች ከመልስና ማብራሪያ ጋር
+ከ አምስት በላይ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ እንዲሁም በተለያዩ ክፍለ ከተሞች የተዘጋጁ ለ6ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ሞዴል ጥያቄዎች ከነመልሶቻቸው የቀረቡበት።
ማርቭል አካባቢ ሳይንስ ለ5ኛ እና ለ6ኛ ክፍል አጋዥ መጽሐፍ በውስጡ፡-
+ አዲሱን ሥርዓተ ትምህርት መሠረት በማድረግ ለ5ኛ እና ለ6ኛ ክፍል ተማሪዎች በሳይንስ፣በጂኦግራፊ፣በታሪክ እንዲሁም በወቅታዊና አካባቢአዊ ጉዳዮችህ ላይ ያላቸውን ዕውቀት ከፍ እንዲያደርግ ታስቦ የተዘጋጀ ነው።
*** በተጨማሪም በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት መሠረት በማድረግ ለ5ኛ እና ለ6ኛ ክፍል ተማሪዎች ጥልቅ ግንዛቤ እዲኖራቸሁ የኢትዮጵያና የአፍሪካ ጂኦግራፊ፣ የኢትዮጵያና የአፍሪካ ታሪክ፣ የባዮሎጂ፣ የኬሚስትሪ፣ የፊዚክስና የአፍሪካና የኢትዮጵያ ወቅታዊ ና አካባቢያአዊ ጉዳዮች ላይ ያላቸውን ዕውቀት ከፍ እንዲያደርግ ታስቦ የተዘጋጀ ነው።
በተለይም ደግሞ ለ6ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ተፈታኞች ተማሪዎች በቂ ማስታወሻ ( Note) እንዲሁም መለማመጃ ጥያቄዎችን በማካተት የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግቡ ያስችላቸዋል።
ማርቭል ይልቃል!

23/09/2026

ማርቭል
የግብረ ገብ ትምህርት
ለ5ኛ እና ለ6ኛ ክፍል አጋዥ መጽሐፍ
በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት መሠረት የተዘጋጀ
ማርቭል የግብረ-ገብ ትምህርት ዋና ዋና ገጽታዎች:-
+ በእያንዳንዱ ንዑስ ርዕስ ላይ አጭር እና ትክክለኛ ማብራሪያ ይሰጣል።
+ 2015 ዓ.ም እና የ2018 ዓ.ም ሞዴል ጥያቄዎችን የያዘ ነው።
+ ወቅታዊ እና ሳይንሳዊ መረጃዎች፡
+ እሴት ላይ የተመሰረቱ ጥያቄዎች
+ ዝርዝር ፅንሰ-ሃሳብ በሥዕሎች እና ቻርቶች የተደገፈ።
+ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ እንዲሁም በተለያዩ ክፍለ ከተሞች የተዘጋጁ የ6ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና እና ሞዴል ጥያቄዎች ከመልሶቻቸው ጋር ያካተተ ነው፡፡
+ በቂ ማስታወሻ እንዲሁም መለማመጃ ጥያቄዎችን በማካተት የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግቡ ያስችላቸዋል።
መጽሐፉ የተዘጋጀው ከ15 ዓመት በላይ የማስተማር ልምድ ባላቸው መምህራን ነው።
ማርቭል ይልቃል!

በቅርቡ ይጠብቁን!                                ማርቭል ይልቃል!                                  ማርቭል        የመግቢያ ፈተናዎች (Ministry...
17/09/2026

በቅርቡ ይጠብቁን!

ማርቭል ይልቃል!
ማርቭል
የመግቢያ ፈተናዎች (Ministry) ስብስብ
ለ5ኛ እና ለ6ኛ ክፍል
በ2015 - 2018 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ተዘጋጅቶ የቀረቡትን ለ6ኛ ክፍል አገር አቀፍ የተማሪዎች መመዘኛ ፈተን ከነመልሱ ጭምር በጥልቀት ተብራርቶ የቀረበበት መጽሐፍ።
(2015፣2016 ፣ 2017 እና 2018 የተካሄዱ የመግቢያ ፈተና ወረቀቶችን ያካተተ)
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ተዘጋጅቶ የቀረቡትን ለ6ኛ ክፍል አገር አቀፍ የተማሪዎች መመዘኛ ፈተናን ከነመልሱ ጭምር በጥልቀት ተብራርቶ የቀረበበት መጽሐፍ
በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት መሠረት የተዘጋጀ
+ ግልፅ የሆኑና የተደራጁ አጫጫር ማስታወሻዎች
+ ሥልታዊ እና የተሻሻለ አቀራረብ
+ ራስን ለመገምገም የሚረዳ
+ ፈጣን የክለሳ አቀራረብ
+ ልዩ ጥናት እና ተግባራዊ ይዘት
2015፣2016 ፣2017 እና 2018 የተካሄዱ የመግቢያ ፈተና ወረቀቶችን ያካተተ

ስድስቱን የመመዘኛ የትምህርት ዓይነቶች የተካተቱበት፡-
1. አማርኛ 4. አካባቢ ሳይንስ
2. እንግሊዘኛ 5. የግብረ ገብ ትምህርት
3. ሒሳብ
6. አፋን ኦሮሞ

“ሰማያዊ ጽጌረዳዬስ” በMeaza Girma [በሚስቴ አካሌ ]ምንጭ:- ቴዎድሮስ አጥላው የፌስቡክ ቤት የተወሰደ ።ጊዜ እንደ ቀጥታ መስመር ባለ ፍሰት ከጅማሬው ወደፊት የሚነዳን ቢመስለንም፣ አ...
17/09/2026

“ሰማያዊ ጽጌረዳዬስ”
በMeaza Girma [በሚስቴ አካሌ ]
ምንጭ:- ቴዎድሮስ አጥላው የፌስቡክ ቤት የተወሰደ ።
ጊዜ እንደ ቀጥታ መስመር ባለ ፍሰት ከጅማሬው ወደፊት የሚነዳን ቢመስለንም፣ አንዳንዴ ትዝታ እና ተስፋ እንደ ቱባ ይጠቀልሉታል። ለሕይወት መያዣዋ አንቀልባስ ከጊዜ ውጪ ሌላ ምን አለ? ከጊዜ መስመር ላይ ሳት ብለን የተደለዝን ዕለት ያው እንደ የ HEnock Bekele መጽሐፍ መክፈቻ ርእስ “ሕይወት ይቀጥላል።”

ምናልባት አንድ ቀን መጽሐፍ በ207 ገጽ፣ በአራት የተለያዩ ግን በሚጠራሩ ከፍሎች፡- “ሕይወት ይቀጥላል”፣ “እኔ በልቤ ለሰው ልጆች”፣ “የመርሳት ታሪካዊ አመጣጥ”፣ “ገል አፈር መሆኑን” በተሰኙ እና በአንድ አንድ ገጽ ምርቃቶቹ እነ “ተረፈ ቦታ፣ትዝታ እና ጊዜ” ቀርባለች።

ጠቅላላ የመጽሐፉ አተራረክ አነፋርቆ ባያስለቅሰኝም፤ የሆዴን እህህህ ቀስቅሶ፣ የረጋ እንባዬን አደፍርሶ፤ ዕጣ ፈንታዬን (ዕጣ ፈንታሽን፣ ዕጣ ፈንታህን፣ ዕጣ ፈንታችንን) የጨከነ ሳይመስል በሚያረዳ (የመርዶ ነጋሪ) ድምጽ ቀርቦ ያልጠላሁት ትካዜ ውስጥ ከቶኛል። ሔኖክ! በዚህ ፉት ብሎ ባለቀብኝ 2018 ዓ.ም. ውስጥ ስላደረግሁት ደስ ከሚለኝ መሐል ይሄን የአንተን መጽሐፍ ማንበቤ ነው፤ አመሰግናለሁ።

ሰሞኑን ባየሁት Paterson የሚባል ሙቪ ላይ በየመሐሉ ከሚደመጡት ግጥሞች መካከል “Time the fourth dimension…” የምትሰኝ ሐረግ ክመላ ግጥሙ ተነጥላ ብቻዋን ትዝ ትለኛለች (ደግሞስ እንግሊዘኛ ግጥም ትዝ ሊለኝ ነው)። ብቻ እንደው የሄኖክን መጽሐፍ እያሰላሰልኩ በትይዩ ስለሰማኋት ነው ውስጤ መቅረቷ። ጊዜ ለሄኖክ በ መጽሐፉ ከዚህኛውም ይልቅ የጽሑፉ ዋና ጉዳይ ስለነበረና አሁንም እኛ ያው ከጊዜ ክንዶች በታች መሆናችን ግዱ ሆኖ መቀጠሉን ሳይ ተያይዞብኝ ነው። አባትና ልጅነት ውስጥ በትውልድ መተካካት ሂደት የአንዱ የአንድ ጊዜ እውነት የቀጣዩም መሆኑን በቃላት መሳልን የሚጠበብት ሄኖክ እንዴት ቅልብጭ አድርጎ እንደሚገልፀው፣ በሁለት ተተካኪ አባቶች ገለጻው እዩልኝማ፤ [ደግሞ “እንዴት?” እንኳን እንዳንል አድርጎን፤ የምርም ከቅርብ ስናየውም እኮ ይኸው ነው ያስብለናል።]

ማሳያዬን በ“የፈሩት ይደርሳል” አባባል ሸክፉልኝ፡-

“ኩልኩልቱ ከዓይኑ በታች ተንጠልጥሏል። ጥላው በእኩለ ቀን ኮስሷል። የአንገቱ ሽብሻቦት የሺህ ዥረቶችን መንገድ ይመስላል። የግንባሩ ላይ መሥመሮች ተቆራርጠው አያልቁም። እልፍ አእላፍ የታሪክ ክሮች ናቸው። እያንዳንዱ መሥመር የራሱ ታሪክ አለው።” (ገጽ 63)

“ትልቁ ፍርሃቴ ፊት ለፊቴ በድክመት የተቀመጠውን አባቴን መሆን ነው።” (ገጽ 64) የ“ምናልባት አንድ ቀኑ” ጎዳና የሚባል ገጸባሕርይ “ቀልድ አይደለም መንገድ” አለና የፍርሃቱን ሐውልት አፍርሶ ጉዞ……ከዚያ ተጉዞ ተጉዞ ቢመለስ በርግጥ መመለሻ ያለው መሆኑ እኔንና መሰሎቼን ያስቀናናል፣ ምን ይሆናል…. የፈራው ይደርሳል።

አባቱን ሲሄድ ተቀምጦ ባየበት በዚያው ቦታ እሱ ደግሞ በተራው ይቀመጥና የራሱን ምስል ይገልጣል፡-“ኩልኩልቴ ከዓይኔ በታች ተጋድሟል። ጥላዬ በእኩለ ቀን ኮስሷል የአንገቴ ሽብሽባት የሺህ ዥረቶች መንገድ ይመስላል። የግንባሬ ላይ መስመሮች ተቆራርጠው ተቆራርጠው አያልቁም። እልፍ አእላፍ የታሪክ ክሮች ናቸው። እያንዳንዱ መስመር የራሱ ታሪክ አለው” (ገጽ 83)። የተደገመው ከዚህ ቀደም እልፍ አእላፍ ጊዜ የተደጋገመ ነው፤ የታሪክ ክሮቹም በቀለም፣ በክረት፣ በርዝመት… ጥቂት ዝርዝሮች ላይ የተለያዩ ቢመስሉም መነሻና መድረሻቸው ያው ነው።

ዘልቄ ወደ ሁለተኛው ክፍል “እኔ በልቤ ለሰው ልጆች” ስደርስ፣ ሐዋዝን ከሄኖክ ቀዳሚ ሥራ መጽሐፍ ወደዚህኛው ፈልሶ አገኘሁት። ሀገር የቀየረው፣ መታወቂያ መሰንቆውን ግን ያንጠለጠለውን ሐዋዝ የተስፋ የመቁረጥ አፋፍ ድረስ ስሸኘው ማን ትዝ ይለኛል? - የነፍሰ ሔር ስብሐት ገብረእግዚአብሔር በርሱፍቃድ (ስሙ ራሱ የስቃዩ ክስ ማቅረቢያ አይመስልም?)። ውስጥ ያየሁት የበርሱ ፍቃድ ሲሳዬ (በሬው ወዳጁ) በማን ይተካብኛል? - በሐዋዝ መሰንቆ። ሁለቱም ወዳጃቸውን ለምን እና በምን ለወጡት- ለሥጋ፣ በሥጋ። ከሩቅም ከቅርብም ሀገርኛ የሥነ ጽሑፍ ሥራዎች ውስጥ ከስቃዮቻችን ሁሉ ፊተኛ ሆኖ ረሃብ ያለመታጣቱን ሰበብ ደርድሬ አልጨርስም። ደግሞ እንደምንወቃቀስበት በስንፍና እና ሀብትን በወጉ በመጠቀም ጉድለት ብቻ ሳይሆን፤ በአንዱ ጥጋብ ሌላው በረሃብ ሲገረፍ - ረሃብ ድምፅ አልባ ኑክሌር ቦምብ ሲሆን ሰርክ በፀጥታ የሚታዘቡ ትውልዶች አባላት ነን። የዚህ ትውልድ አባሉ ሄኖክ “የዱባ ወጥ እንደ ድንቅ ይታያል” (ገጽ 114) የሚለውን በመሳሰሉ ልብን በሚፍቁ ገለፃዎች ንጥፈትን ሲገልፃት ለብቻው ነው።

አሁን አሁን መከራ ላለመስማት (እንግዲህ ታዘቡኝ) ዐይኔንም ጆሮዬንም ለመዝጋት እየሞከርኩ፣ አየሩ ሁሉ እሱው ሆኖ በተባራሪ ሳልሰማው የቀረ ባይኖርም፤ ሄኖክ ግን የምኖርበትን ዘመን የመከራ መታወሻ እና ማስታወሻ በውብ ቋንቋና በሐሳብ ፍሰቱ፣ እንዲሁም ከዕድሜው በላይ በሆነው ሕይወትን የመረዳት ዐቅሙ ከመጽሐፉ መከደን በኋላ የምብሰለሰልባቸው ብዙ ጉዳዮች ትቶልኛል። ልሸሸው የምለፋለትን መከራችንን በፈቃዴ አንብቤ፣ ይኸው አተራረኩን መውደዴን እየመሰከለርኩለት ነው። ሄኖክ ይህቺ ሕይወት እንዲህም ብትሆን፣ ብዙ ብዙ ቢኖራትም፣ የመጻፉ ገፊ ምከንያት “ሕይወትን በመውደዴ ምከንያት” ብሎ በመጽሐፉ መክፈቻ “ምክንያተ ጽሕፈት” ሥር ይነግረናል። የውብ ሥነ ጽሑፍ ዐቅምም ይኼው ይመስለኛል - ወዶ መጻፍ የቸከውን፣ አንድም አዲስ ነገር የሌለውን ጉዳይ በአዲስ መንገድ ለመተረክ ዐቅም ሲሆናቸው፣ በምንወዳቸው ጸሐፊዎቻችን ስናይ ኖረናል።

ይህቺን ያህል ያካፈልኳችሁ መጽሐፏን እንድታነቧት ለመጋበዝ ብቻ ነው። ወደ ሦስተኛው ወደ አራተኛዋም እና አንድ አንድ ገፅ ስለተመረቁልን ተረፈዎችም ልናገር የምችለው ሽንፈታችንን ግቶ ሳይሆን ቀስ እያልን እንድናወራርደው አድርጎ መጻፉን ነው።

መጽሐፏን እንደወደድኳት የገባኝ አንብቤ ሳልጨርስ ስለመድገም ስለመደጋገም ሳስብ ነው። ሕይወት ላይ የሌለ ድራማም ሆነ አጉል ልብ ሰቀላ ሳይኖረው የታከተንን የከሰኞ እስከ ሰኞ ድግግሞሽ እና የሕይወትን ዘበትነት በአሰልቺነቱ ብቻ ሳይሆን ቸል ቸል የምንለውን አቅርብን እንድናይና ዕድል በመስጠት ተርኮልናል። ጸሐፊው እንደ ሕይወት ጨካኝ አይደለም፤ ሕይወት ያስጣለቻቸውን ደማቅ ሰማያዊ ጽጌረዳ ለገጸባሕሪው ከንቃቃት ውስጥ የሚያበቅል ነው። በስብሐት #አምስት፟_ስድስት_ሰባት ውስጥ የበርሱፈቃድ ሰማያዊ ጽጌረዳው የመሰለኝ ቅዠቱ ነው፤ ሕይወት አራቁታ ከመቃብር ድንጋይ ላይ በብቸኝነት ጥልቅ ጭርታ ውስጥ ከእብደት ድንጋጤና ፍርሃት ጋ ወደ ዳር ስታወጣ ቅዠት ይመጣና እንዲህ ያናግራል “ ኧረ ይግቡ……ፋናዬ ንሺ ውሃ ለእግር አምጪ….ወርቁ! በቃ ጫጫታ፣ ግቡ ጨልሟል” መደምደሚያው በእርሱ ፈቃድ አለፈለት፤ አረፈ።(አምስት ስድስት ሰባት፣ ገጽ 84) አንዳንዴ ሞትም እንዲህ ተስፋ ሆኖ ይመጣል።

ለጊዜው የእኔ ሰማያዊ ጽጌረዳ ምንድነው እያልኩ መጽሐፍህን ከድኛለሁ። ሰማያዊ ጽጌረዳ የማይቻለውን የመቻል ተምሳሌትነት የተሸከመ ነው። ለብቻ በመቃብር ጭርታ መሐል እየሞቱ “ለእግር ውሃ አምጡ” የሚያስብል፣ በደዌ ከማቀቁበት ፍራሽ ሥር አግኝተውት ለፈውስ ሆኖ፣ ደግሞ ሀገር ለሀገር ዞረው ዞረው አርጅተው ሲመለሱ እንደፈካ የሚቆይዎት ነው። [Blue Rose: a symbol of mystery and enigma; evoking a sense of Secret Wonder, the unknown, and deep imagination. ]

አንብቡት፤ አንብቡትና የሰማያዊ ጽጌረዳችሁን ምስጢር መርምሩ፣ ሌላም ሌላም ጠይቁ፣ ፈልጉ። ሔኖክ አሳቢ ጸሐፊ ነው! ደስ ትሰኙበታላችሁ። physically feel እያደረግሁ አንብቤሃለሁ። እንግዲህ እኛን እኛን ብለህ ምናልባት ሌላ ቀን እስክትጽፍ ቀጣይ ሥራህን ናፋቂ ነኝ።

ሄኖክ ከውብ ንኡስ ርእሶቹ ሥር ድንቅ ድንቅ ግጥሞች እንደ መክፈቻ (ምን ልላቸው እንደሚገባኝ ስላለወቅሁ ነው) ሰጥቶናል። በገጽ 193 የተጠቀመው እንዲህ ይላል፡-

ነፋሱ ነፈሰ፥ገላዬን ዳሰሰ
ምስጢሬን ሸክፎ፥ ሀገር አዳረሰ

እኔም የዚያ ቢጤ እንዳይሆንብኝ፣ ገና እየተነበበ ስላለው መጽሐፍ ከዚህ በላይ ከምዘከዝክ አንብቡት አንብቡት አንብቡት ብዬ ብጋብዛችሁ ይሻላል። ምስጢሩን ራሱ ይነግራችኋል።

15/09/2026

MARVEL TRULY EXCELLS!
ማርቭል ይልቃል!

📖📖 የመጽሐፍ ፊርማ ፕሮግራም 📚📚ቅዳሜ መስከረም 9 ከ 8 ሰዓት እስከ10 ሰዓትበ ዕለቱም እሸቴ አሰፋ እነሆ መቆያ ከተሰኘው መጽሐፉ ጋር የሚገኝ ይሆናልበሰዓቱ ... 📚✨ የመጽሐፍ ፊርማ ! ...
15/09/2026

📖📖 የመጽሐፍ ፊርማ ፕሮግራም 📚📚

ቅዳሜ መስከረም 9 ከ 8 ሰዓት እስከ10 ሰዓት
በ ዕለቱም እሸቴ አሰፋ እነሆ መቆያ ከተሰኘው መጽሐፉ ጋር የሚገኝ ይሆናል

በሰዓቱ ...

📚✨ የመጽሐፍ ፊርማ ! ✨📚
☕ የቡና ጣዕም…
📚 የመጽሐፍ ዓለም…
በዕለቱም የፎቶና የመጽሐፍ ፊርማ ፕሮግራም ይኖረናል።

📍 ቦታ፦ ጃዕፈር መጻሕፍት – ለገሃር፣ ተወልደ ሕንጻ ስር የሚገኘው አዲሱ፣ ሰፊና ዘመናዊ መደብራችን

📖 ደራሲውን ከአንባቢው፣ መጽሐፉን ከአንባቢው ጋር ይገናኛሉ ::

ከዚህ በፊት ያካሄድናቸውን የመጽሐፍ ፊርማ ዝግጅቶች በቀጣይም አስፋፍተን እንቀጥላለን !

የመጽሐፍ ፊርማ ዝግጅት ደራሲውን ከተደራሲው፣ መጽሐፉን ከአንባቢው ጋር በትክክለኛው ቦታ፣ በክብርና በሞገስ የሚያገናኝ ድንቅ ፍኖት ነው።

ይህም አንባቢን የማፍራት፣ ደራሲን የማበረታታትና የንባብ ባህልን የማጠናከር የጃዕፈር መጻሕፍት ተልዕኮ አንዱ አካል ነው።

ጃዕፈር መጻሕፍት
የንባብ ባህል እንዲዳብር እንተጋለን!

12/09/2026

Study Smarter, Not Harder

መልካም አዲስ ዓመት ለዩኒቲ መጻሕፍት ቤተሰቦች።
10/09/2026

መልካም አዲስ ዓመት ለዩኒቲ መጻሕፍት ቤተሰቦች።

Address

MEXICO Square
Addis Ababa
4143

Opening Hours

Monday 08:00 - 20:00
Tuesday 08:00 - 20:00
Wednesday 08:00 - 20:00
Thursday 08:00 - 20:00
Friday 08:00 - 20:00
Saturday 09:00 - 17:00

Telephone

+251912028794

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ዩኒቲ መጻሕፍት-Unity Books posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to ዩኒቲ መጻሕፍት-Unity Books:

Shortcuts

Share