Kibru BookStore

Kibru BookStore በኢትዮጵያ በየጊዜው የሚታተሙ ታሪካዊ ፣ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚ?

ኢትዮጵያ እና ግብፅናፖሊዮን ግብፅን ከወረረበት እ.ኤ.አ ከ1798 አንስቶ አገሪቱ ለምዕራባዊያን ቁልፍ የንግድና የስትራቴጂ በር ሆና ብትቆይም፤ ኢትዮጵያም ከግብፅ ያልተናነሰ ጠቀሜታ ያበረከተ...
15/03/2024

ኢትዮጵያ እና ግብፅ

ናፖሊዮን ግብፅን ከወረረበት እ.ኤ.አ ከ1798 አንስቶ አገሪቱ ለምዕራባዊያን ቁልፍ የንግድና የስትራቴጂ በር ሆና ብትቆይም፤ ኢትዮጵያም ከግብፅ ያልተናነሰ ጠቀሜታ ያበረከተችባቸው ጊዜያት እንደነበሩ ሊዘነጋ አይገባም። ለዚህ ከ1950ቹ መባቻ እስከ 1960 ቹ አጋማሽ ያሉት ጊዜያት ዋቢ ይሆናሉ። ኢትዮጵያ ከአሜሪካ አስተዳድሮች ጋር በፈጠረችው ግብብ አስመራ የሚገኘው የቃኘው የሬዲዮ መገናኛ ጣቢያ የቀይ ባህር ቀጠናን እና የመካከለኛው ምስራቅን የመቆጣጠሪያ ዋነኛውም ነጥብ ሆኖ አገልግሏል። ኢትዮጵያም በተባበሩት መንግስታት ጥላ ስር በኮሪያና በኮንጎ የሰላም ማስከበር ዘመቻዎች ከአሜሪካ መራሹ የምዕራብ ጥምረት ጎን መሰለፏ ተሰሚነቷን በእጅጉ አጉልቶት ቆይቷል ። ይህ መቀየር እስከጀመረበት እስከ 1960ቹ መጀመሪያ ድረስም ኢትዮጵያ የወታደራዊ ፣ የስትራቴጂክ ፣ የሳይንስና የትምህርት ልማት ድጋፎችን ከአሜሪካና ከምዕራባዊያን ስታገኝ ቆይታለች። ግብፆቹ የኃይል አሰላለፋቸውን ወደ ምዕራቡ ጎራ ሲቀይሩ ግን የተሻለ ምርጫ ሆነው ቀረቡ። በአንፃሩ ኢትዮጵያ ራሷን ከሶሻሊስት ጎራ ውስጥ አገኘች ፤ የጂኦስትራቴጂ ፋይዳዋም ተቀዛቀዘ። የዚህና የመጪው ትውልድ እሳቤ ይህንን መቀልበስ በሚቻልበት መንገድ ላይ እና የአገሪቱን ተቀባይነት እና ተሰሚነት ከማጉላቱ ላይ ሊሆን ይገባል።

ኢትዮጵያ እና ጎረቤቶቿ
በበለጠ በላቸው ይሁን
ገፅ 209

07/02/2024
ጌታቸው ኩምሳየመኢሶን አባል የነበሩም ጥቂት ሰዎች የኢሕአፓ አባል የነበሩ ግለሰቦችን ሕይወት ታድገዋል። ከነዚህ መኻከል አንዱ ዘአማኑዔል ኃይሌ ነበር። በአንድ ምሽት ጌታቸው ኩምሳ አንድ ፀረ...
02/02/2023

ጌታቸው ኩምሳ

የመኢሶን አባል የነበሩም ጥቂት ሰዎች የኢሕአፓ አባል የነበሩ ግለሰቦችን ሕይወት ታድገዋል። ከነዚህ መኻከል አንዱ ዘአማኑዔል ኃይሌ ነበር። በአንድ ምሽት ጌታቸው ኩምሳ አንድ ፀረ “ ኢሕአፓ ” በነበረ ቀበሌ አካባቢ፣ መጠጥ ቤት ውስጥ ሆኖ ከአንድ ጓደኛው ጋር ቢራ ሲጠጣ ነበር፡፡ ከዚያም የድሮ ጓደኛውን እና “የመኢሶን” አባል የነበረውን ዘአማኑዔል ኃይሌን አየው። በዚያን ሰዓት የቀበሌ ታጣቂዎች ጌታቸው ኩምሳ እዚያ መሆኑን ተረድተው ለማሰር ወደ መጠጥ ቤቱ ገቡ። ጌታቸው ኩምሳ የነበረበት ቀበሌ ዘአማኑዔል ኃይሌ ከሚመራው ቀበሌ ራቅ ያለ አካባቢ ነበር። ሆኖም ዘአማኑዔል ጌታቸው የእኔ አስረኛ ነው በማለት ከቀበሌ ታጣቂዎች ጋር ተጨቃጭቆ ጌታቸውን ወደ ራሱ ቀበሌ በመወሰድ በዚያች ዕለት ከመገደል አተረፈው።
ጌታቸው ኩምሳ በጊዚያዊ የሕዝብ ድርጅት ጽ/ቤት የሚፈለግ ግለሰብ ነበር። ስለሆነም ጌታቸው ኩምሳን በነፃ ከቀበሌ እስር ቤት ለመልቀቅ ለዘአማነዔል አስቸጋሪ ነበር። ስለሆነም ዘአማኑዔል ጌታቸው ኩምሳን ወደ ከርቸሌ ( ዋናው እስር ቤት ) እንዲዛወር አደረገ። ምክንያቱም ከቀበሌ ወደ ከርቸሌ የሚዘዋወር ሁሉ ከመረሸን የመዳን እና በሕይወት የመቆየት ዕድሉ ከፍተኛ ነበር።
ጌታቸው ኩምሳ በከርቸሌ ከብዙ የኢሕአፓ አባላት ጋር የእስረኝነት ኑሮውን ቀጠለ እዚያም ሆኖ እስረኞች ባቋቋሙት የከርቸሌው ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ በታሪክ አስተማሪነት ተሰማርቶ ነበር፡፡ ጌታቸው ኩምሳን ዘአማኑዔል ወህኒ ቤት (ከርቸሌ) እየሄደ ይጎበኘው ነበር። አልፎ አልፎ ዘአማኑዔል ጌታቸው ኩምሳ ፈቃድ እንዲሰጠው እያደረገ፣ ወደ አካባቢ መጠጥ ቤት እየወሰደ ይጋብዘውም ነበር። ዘአማንዔል እና ሌሎች ጓደኞቹ ፣ ጌታቸው ኩምሳ ከከርቸሌ በፈቃድ በሚወጣበት ጊዜ አምልጦ ወደ ውጭ እንዲሰደድ ይመክሩት ነበር። ጌታቸው ኩምሳ ግን እምቢ ብሎ ከርቸሌ ከረመ።
ከርቸሌ በነበረበት ዘመን ጌታቸው በነበረው አብዮታዊ እምነቱ የማያወላውልና የፀና ነበር። በ1977 ዓ.ም ደርግ ከጥቂት የፓለቲካ አስረኞች በስተቀር ብዙዎችን ፈታ። ጌታቸው ኩምሳ ካልተፈቱት ጣም ጥቂት እስረኞች መኻል ነበር። ጌታቸው ኩምሳ እስከ 1979 ዓም ድረስ በከርቸሌ ታስሮ ከርሞ፣ ምንም በከተማ አካባቢ ከኢሕአፓ የሚሰነር ጥቃትም ሆነ ዛቻ ባከተመበትና የሱ መለቀቅ ለውጥ በማያመጣበት ዘመን፤ ካለምንም ምክንያት፣ ደርግ ጌታቸው ኩምሳን እና ሌሎችን ረሸነ። ያኔ ነበር የመጨረሻው ግድያ። ያኔም ነበር የቀሩት የመጨረሻዎቹ የከርቸሌ እስረኞች ሁሉ የተፈቱት።
ጌታቸው ኩምሳ ክብረ መንግሥት ( ሲዳሞ ) ያደገ ኦሮሞ ወጣት ነበር። ጌታቸው ኩምሳ አድዋ ውስጥ ተወዳጅ አስተማሪ ሆኖ ብዙ ተማሪዎችን ከግራ ዘመም ፓለቲካ ጋር ያስተዋወቃቸው እሱ ነበር። በነገራችን ላይ ጌታቸው ኩምሳ አድዋ በሚያስተምርበት ጊዜ ቀደም ሲል ዩኒቨርሲቲ ከሚያውቃቸው ህወሓትን ከመሠረቱት ጥቂት አባላት ጋር የቅርብ ግንኙነት ነበረው። ገና ሜዳ ሳይወጡ "የትግራይ ብሔራዊ ድርጅት" (TNO) የህቡዕ ቡድን ባቋቋሙ ጊዜ ጌታቸው ኩምሳ ድጋፍ አድርጎላቸው ነበር። ይህ የትግራይ ብሔራዊ ድርጅት ( TNO ) ነው በኋላ ወደ ህወሓት የተቀየረው።
ህውሓት ከተመሰረተ በኋላም ጌታቸው ኩምሳ ከተማ ከነበሩ የህውሓት አባላት ጋር ግንኙነት ነበረው። በየካቲት 1968 ዓ.ም የህውሓትን "ማኒፌስቶ" ለማግኘት ችሎ ነበር። "ማኒፌስቶው" ስለትግራይ በጣም ጠበብ ያለ አስተያየት የያዘ እና በትግራይ ትግል ላይ ያተኮረ ብቻ ነበር። ጌታቸው ኩምሳ ምንም ብሄራዊ ንቅናቄዎችን ቢደግፍም፣ እነሱ ጠበብ አድርገው ያቀረቡትን ፕሮግራም ግን አልተስማማውም ነበር።

ፓርቲው
በወልደልዑል ካሣ
ገፅ 268-271

አዲስ መፅሐፍ በገበያ ላይለውጥ ናፋቂው ህይወቴ በአበራ የማነአብበ273 ገፆች ተቀንብቦ በ260ብር የጀርባ ዋጋ በገበያ ላይ ቀርቧል።በቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉንhttps://t.me/kibru...
15/08/2022

አዲስ መፅሐፍ በገበያ ላይ
ለውጥ ናፋቂው ህይወቴ
በአበራ የማነአብ
በ273 ገፆች ተቀንብቦ በ260ብር የጀርባ ዋጋ በገበያ ላይ ቀርቧል።

በቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉን
https://t.me/kibrubook

በኤግዚቢሽን ማዕከል ከነገ እስከሰኞ በሚቆየው አውደ ርእይ ላይ ያገኙናል።
03/08/2022

በኤግዚቢሽን ማዕከል ከነገ እስከሰኞ በሚቆየው አውደ ርእይ ላይ ያገኙናል።

ሁለተኛ እትም በገበያ ላይ ውሏል
29/07/2022

ሁለተኛ እትም በገበያ ላይ ውሏል

"የጥቁር እናት ነኝ።" የግጥም መፅሐፍ ምርቃት ካፒታል ሆቴል. ሐምሌ 1/2014አያምልጣችሁ
07/07/2022

"የጥቁር እናት ነኝ።" የግጥም መፅሐፍ ምርቃት
ካፒታል ሆቴል. ሐምሌ 1/2014
አያምልጣችሁ

አዝማች የጉራጌ ሕዝብ አጭር ታሪክበገበያ ላይ
02/07/2022

አዝማች
የጉራጌ ሕዝብ አጭር ታሪክ
በገበያ ላይ

ለሁለተኛ ጊዜ ታትሞ በገበያ ላይ ውሏል
23/06/2022

ለሁለተኛ ጊዜ ታትሞ በገበያ ላይ ውሏል

Address

Churchill Road
Addis Ababa

Telephone

+251911676457

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Kibru BookStore posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Kibru BookStore:

Share

Category