Eiabc orthodox Christan network

Eiabc orthodox Christan network Well come to EiABC and joined student info!!!!

15/08/2018
Pleas read this heart breaking poem to our lady st virgn mery
03/11/2017

Pleas read this heart breaking poem to our lady st virgn mery

አዶናይ ቅርብሽ ነው
♥♥♥♥♥
በሊቃናቱ አፍ__ የምትወደሽ
በቅዱሳኑ ዘንድ__ ከፍ ያለው ክብርሽ
የመላእክት እህት__እያልን የምንጠራሽ
የንፀኋን አክሊል__ሶልያና አንቺ ነሽ።
የቃለ እግዚአብሔር __ ማደሪያ አትሮንሱ
ከፍጥረት ለይቶ__ መረጠሽ ንጉሡ
ድንግልም እናትም __ሆነሻል ማርያም
አክብሮሻል አምላክ__ እስከ ዘለአለም።

ነቀፋ የራቀሽ__ የሌለብሽ ነውር
የመቅደሱ እንግዳ__የሕግ ደቀ መዝሙር
የመለኮትን ጸጋ__የለበስሽ በፍቅር
የነቢያት ዜና__የእውነት መነጽር።

ጌታ ካንቺ ጋር ነው__ ይድረስሽ ውዳሴ
ፀጋን የተሞላሽ__ ታመስግንሽ ነፍሴ
ጽኑ ቃል ኪዳንሽ__የነጻነት ልብሴ
አማላጅነትሽን__ ያውጃል ምላሴ።

ሰውነትሽ ንጹሕ__የምድር መቅደስ ነው
ዘር ያልተዘራበት __እርግማን የራቀው
በኃጢአት ምክንያት __ ሞት ቢሰለጥንብን
እንዳንጠፋ ፈቅዶ__ አንቺን አስቀረልን
ኢሳይያስ እንዳለው__ ከገሞራው ዳንን።

ፍጹም ንጽሕናን__ከላይ የተጎናጸፍሽ
እውነተኛው መና__ ሲሳይን የታቀፍሽ
አንቺን ከማን ጋራ__ ከቶ ላነጻጽርሽ?
በቃል ኪዳን ከሁሉ በላይ ነሽ።

የእግዚአብሔር መልእክተኛ__ አብሳሪው ገብርኤል
ሠላምታን ሲዘራ__ተልኮ ከልዑል
ባንቺ ያድራልና__ ቅዱስ አማኑኤል
በሎ ጀመረልሽ __ ተፈስሒ ድንግል።

በምድርም ተሰማ __ ሰማያዊው ደስታ
ቅድስት ኤልሳቤጥም __ ጮኽች አሰምታ
የጌታዬ እናት__ ወደ እኔ እንዴት መጣሽ?
ደንግል እናቴ ሆይ__ ከሴቶች ልዩ ነሽ።

ነውሬ ተወግዶ__ ጌታዬ ጎብኝቶኝ
ስላደረገልኝ __ለምስጋና ቆምኩኝ
የሰላምታ ድምጽሽን __ አንደሰማሁኝ
በመንፈስ ቅዱስ ኃይል__ሐሴት ለበስኩኝ።

በሆዴ ውስጥ ያለው__ የስድስት ወሩ ጽንስ
ሠገደ ለአምላኩ__ወልደ ዘካርያስ
ክብርና ምስጋና__ ለሥላሴ ይድረስ።

ሠማይና ምድር__ የማይሸከሙት
የዓለም ፈጣሪ__አምላከ አማልእክት
በዚች ብላቴና__ተወስኖ ስናይ
እጅግ ያስደንቃል__ጥበቡ የአዶናይ።

እንመሰክራለን__ አውጀን እውነት
እንናገራለን__ በምንሔድበት
የጌታን ማደሪያ__ ክብር እንዳላት
ልክ እንደ ትላንቱ __እንደተመረጡት።

ጥንት የነበረው__መድኃኒዓለም
ዘመን ሳይቆጠር__አለ በማርያም
ከፍጥረታት በፊት__በእግዚአብሔር ሕሊና
ወለተ ኢያቄም__ ታስባለችና።

በተወዳጅ ክንዷ__ ሕፃኑን ታቅፋ
በክብር ላይ ክብርን__ ማርያም ተጎናጽፋ
ትውልድን ስታስምር__በሞት እንዳይጠፋ
ኪዳነምሕረት__የአዳም ልጆች ተስፋ
አለች በሠማያት__ በወርቅ ተጽፋ።

ከዘመነ አዳም__ እስከ ምጽአት
በብሩካን ጻድቃን__በአበው አንደበት
የነቢያት ዜና__ የሐዋርያት ደስታ
ሰምሽ የሚጠራ__በቅዱሱ ቦታ
ሐረገ ወይን ድንግል__ የሰላም አንድምታ።

ቀድሞ የተጠሩት__በወንጌል ያመኑ
የተመረጡትም __ ከቅስፈት የዳኑ
ከብረው የጸደቁት__ በቃል የመነኑ
አንቺን ለማወደስ__ በቅኔ ተካኑ
የመስቀሉን ፍቅር__ እያመሰገኑ።

በደጀ ሰላምሽ__ በዝክርሽም ስፍራ
በዕንባ በጸሎት __ ስምሽን ስንጠራ
ፈጥነሽ ድረሽልን__ ከቦናል መከራ
ብልጣሶር ታብይዋል__ ልቦናችን ፈራ።

በከብቶቹ ግርግም__ በዚያ የታቀፍሽው
በግብጽ በረሃ__ በጀርባሽ ያዘልሽው
የምሕረት ባለቤት__እኛ የምናመልከው
ይማረን አሳስቢ__ ፊቱን ይመልሰው
ድንግል ማርያም ሆይ__አዶናይ ቅርብሽ ነው።

25/10/2017

መምህር ግርማ ወንድሙን ይዋጣልን ፊትለፊት እንገናኝ ደውሉልኝ ብሎ ስልኩን የተናገረው አነጋጋሪ ፓስተር | Pastor Message to Memihr Girma Wendmu | መምህር ግርማ ወንድሙንመምህር ግርማ ወንድሙን ይዋጣልን ፊትለፊት እንገናኝ ደውሉልኝ ብሎ ስልኩን የተናገረው አነጋጋሪ ፓስተር | Pastor Message to Memihr Girma Wendmu | መምህር ግርማ ወንድሙን

25/10/2017


====================================
ጣና ሃይቅ ከኢትዮጱያ ትልቁ ሃይቅ ነው፡፡ ጣና ሃይቅ ስያሜውን ያገኘው ቅድስት ድንግል ማርያም በስደት ዘመኗ በጣና ቂርቆስ ገዳም የ3 ወር ከ10 ቀን ቆይታዋን አጠናቃ ወደ ገሊላ ናዝሬት ይመለሱ ዘንድ ይመራቸው የነበረው መልዓክ እግዚአብሔር ለአረጋዊ ዮሴፍ በህልም ተገለጦ "ህፃናኑን እና እናቱን ይዘህ ወደ አገራችሁ ሂዱ" ብሎ ስለነገረው ቅዱስ ዩሴፍም ወደ ህፃኑ በመቅረብ "ፀአና በደመና" (በደመና ጫናት) ባለው ጊዜ የገዳሙና የሃይቁ ስም ጣና ተባለ ተብሎ ይተረካል፡፡
የጣና ሃይቅ የባህር ዳር ከተማ በከፊል አካል ሲሆን ሰሜናዊ አቅጣጫ ላይ ይገኛል የምዕ/ጐጃም፣ ሰሜንና ደቡብ ጐንደር አስተዳደር ዞኖችን ያዋስናል፣
የጣና ሃይቅ ከባህር ጠለል በላይ 1830 ሜትር ከፍታ ላይ ሲገኝ 3600 እስኩየር ኪሎ ሜትር የቆዳ ስፋት ሲኖረው ከ9-14 ሜትር ጥልቀት አለው፡፡ ከሰሜን ወደ ደቡብ 75 ኪ.ሜትርና ከምስራቅ ወደ ምዕራብ 60 ኪ.ሜትር ተንጣሎ ይገኛል፡፡ በሃይቁ ውስጥ ከ37 በላይ ደሴቶች ሲኖሩ ከ13ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ጀምሮ የተሰሩ 21 ገዳማትና አብያተ ክርስቲያናት ይገኙበታል፡፡
በሃይቁ መሃልና ዳርቻ ከ30 በላይ የሚሆኑ የኢትዩጱያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያት በብዙ ቢሊዮን ከሚገመቱ ክቡር ቅርሶቹ ጋር የሚገኘበት አስደናቂና ሃይማኖታዊ ሃይቅ ነው፡፡
የመምህር ዘመድኩን ፅሁፍ እንደሚያስረዳው በኢትዩጱያ የክርስትና ሀይማኖትን የሰብከው የመጀመሪያው የኢትዩጱያ ጰጰስ የሆነው አባ ሰለማ ከሳቴ ብርሃን ወይም ፍሬምናጦስ መቃብር የሚገኘው በጣና ሃይቅ ላይ ነው፡፡ የአፄ ዳዊት የአፄ ዘርአያቆብ፣ የአፄ ሱስንዬስ እና የአፄ ፋሲል አስከሬናቸው ሳይፈርስ በክብር ተቀምጠው የሚገኘትም በጣና ሃይቅ ከሚገኘ ገዳማት አንዱ በሆነው በደጋ እስጢፋኖስ ገዳም ነው፡፡
ኢትዩጱያዊ የቅኔ ሊቅ ማህሌታ የቅዱስ ያሬድም ሁለት ዓመት ከስድስት ወር ያህል በዚህ በጣና ሃይቅ በቅዱስ ቂርቆስ ገዳም በመቀመጥ ከተለያዩ የዕዋት ቀለም በመጭመቅና በመቀመም በራሱ እጅ በብራና ላይ የፅፈው ምልክት አለባው የድጉ መጽሐፍ፣ የእጅ መስቀሉና ከሃር የተሠራው ካባው በቅዱስ ቂርቆስ ገዳም ውስጥ ይገኛል፣
በጣና ሃይቅ ላይ የትራስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ትላላቅና ትንንሽ ጀልባዎች ይገኛሉ፡፡
አሁን ባለው ይዞታ የጣና ሃይቅ 1454 ቶን አሳ በዓመት ይመረትበታል ተብሎ ይገመታል፡፡
በአጠቃላይ የጣና ሃይቅ ጉብኝዎችን የማማለል ድንቅ ውብት ያለውና በውስጡ በያዛቸው ጥንታዊ አድባራት፣ ገዳማና ደሴቶች ምክንያት በ2008 ዓ.ም ላይ ተግባሩት መንግስታት የድንቃድንቅ መዝገብ ላይ ሊመዘገብ የቻለ ሃይቅ ነው፡፡

25/10/2017

የአርዮሳውያን የክህደትና የኑፋቄ ቅሪት በሲኖዶሱ ግብዓተ መሬቱ ተፈጸመ
ሐራ ጥቃ ተሐድሶን ና የአካባቢ ቆሻሻን በጋራ ማጽዳት ዘመቻው በመምህራን ዘንድ ቀደም ብሎ የተጀመረ ሲሆን አቶ በግ ዋሻው ጥቅምት 15 ቀን 2010 ዓ.ም በቅዱስ ተወግዞ ተለየ፤
የክርስቶስን አምላክነትን የሚቃወመው መናፍቃን ሐራ ጥቃ ተሐድሶውያን በየጊዜው ቢነሱም በሊቃውንት በቂ ትምህርት አከርካሪያቸው ተሰባብሮ ወደቀዋል፡፡የአርዮሳውያን የክህደትና የኑፋቄ ቅሪት ዛሬም ቢሆን በእነ በጋሻው እየተስፋፋ ትውልድ እየጨረሰ ያለው የክህደት ጎርፍ በሲኖዶሱ ተገታ፡፡ በጋሻው ከግራኝ አህመድና ከዩዲት ጉዲት የበሳ እሳት በቤተ ክርስቲያናችን ላይ የለኮሰ የፊደል ሽታ ነበር፡፡
አቶ በግ ዋሻው ስለ ክርስቶስ የሚያስምረው የተምታታና የተወናበደ ትምህርት ብዙዎችን ስለ አምላክነቱ እንዲጠራጠሩ ና ጨርሰውም እንዲክዱ በማድረግ ከሕይወት ጎዳና እንዳስወጣቸው ቅዱስ ሲኖዶስ በጉባኤው በአጽንዖት ተወያይቶበታል፡፡
ሐራ ጥቃ መናፍቃን በየስፍራው የሚያሰራጩአቸው የተለያዩ በራሪ ጹሑፎች ና የሚያሳትሟቸው የክህደደት መጻሕፍት የኑፋቄ ትምህርታቸውን ማሰፋፊያ መሣሪያዎቻቸው ምንም እንኳን ከአርዮስ ጀምሮ የመጣ ቢሆንም በሀገራችን ግን ደፋሩ በጋሻው ክህደትን በማለማመድ የሚቀድመው የለም ፡፡ ለብዙዎች ዘማርያን መጥፋት ተጠያቂ ነው፡፡
-ምእመናን ቅዱሳት መጻሕፍት በአንክሮ በማንበብ ከመናፍቃን የሐሰት ትምህርት ራሳቸውን እንዲጠብቁ ፤ የሊቃውንቱን የትርጓሜ መጻሕፍት እንዲመለከቱ ና አምላክነቱን ለሚክዱ ሰዎችም መልስ ለመስጠት በትምህርተ ሃይማኖት መዘጋጀት እንደሚገባ እንጂ በዕንቅልፍ የምንቀጥልበት ጊዜ እንዳልሆነ ቅዱስ ሲኖዶሱ በጥብቅ አሳሰበ፡፡ ምክንያቱም ተመሳስለው መጥተዋልና፡፡ቅዱሳን አባቶቻችን የሐራ ጥቃ ተሐድሶውያንን ስልታዊ ዘመቻ በጉባኤያት እንደ አንድ ልብ መካሪ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ በመሆን ከንቱ እያደረጉት ነው፡፡ የኑፈቄ መርዛቸውን በየጎዳናው በየቤታቸው በመርጨት ብዙ ሰዎችን በክህደት መርዛቸው እየጎዱ ያሉትን ተሐድሶውያን ሴራ በምስል ወድምጽ በተደገፈ መረጃ ሲቀርብ በራሳቸው አንደበት ምስጢረ ሥላሴንም በማፋለሳቸው የክህደት ንግግራቸውንም የሲኖዶሱ አባለት በጆሮአቸው በማሰማታቸውና በዐይናቸው በማየታቸው በጉባኤ አውግዘውታል፡፡

25/10/2017

Join us tomorrow for a discussion about urban entrepreneurship and sister city partnerships with Fabiola Vilchez, President and Executive Director of Sister Cities of Los Angeles, Inc. Sister City programs can foster increased trade, cultural exchanges, and more! Fabiola is American entrepreneur, urban planner, environmentalist and a former deputy director of International Trade at the office of Mayor of Los Angeles Eric Garcetti.
Where: Addis American Center in National Archive and Library Agency (Wemezekir)
When: Thursday, October 26, from 4:30 PM to 5:30 PM

25/10/2017

Education:- BSc Degree in civil engineering or other related field, Quantity:- Two , Related Work Experience:- 6 years and above work experience, Place Of Work :- Head Office /Project, salary:- Negotiable and Attractive, Road construction industry experience is advantageous. Interested

25/10/2017
25/10/2017

ከሁለት ሺሕ በላይ አዳዲስ አማንያን የሥላሴን ልጅነት አገኙ ኦክተውበር 25, 2017/in ዜና /by Mahibere Kidusanበካሣኹን ለምለሙ ጥቅምት ፲፭ ቀን ፳፻፲ ዓ.ም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በጋሞ ጎፋ ሀገረ ስብከት በዐርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ቤተ ክህነት በዝጊቲ ደብረ ሰላም አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም ከሁለት ሺሕ በላይ አዳዲስ አማንያን ጥቅምት ፬ ቀን ፳፻፲ ዓ.ም ተጠምቀው የሥላሴን ልጅነት አገኙ፡፡ ‹‹ይህን ያህል አዳዲስ ምእመናንን…

Address

Ledeta
Addis Ababa
0960812170

Telephone

0931572599

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Eiabc orthodox Christan network posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category