25/08/2026
የአንድ ድምፅ 27፡ ተልዕኮ ለሁሉም
@(One_Voice27_Mission_for_All)
የመላው ዓለም የሰባተኛው ቀን አድቬንቲስት ቤተሰብ ኢየሱስ በተጠመቀበት፣ በመንፈስ ቅዱስ የመሲሕነት ቅባቱን በተቀበለበት እና የሕዝብ አገልግሎቱን በጀመረበት በ2,000 ዓመቱ አካባቢ ወደሚውለው ወደ መስከረም 2027 (እ.ኤ.አ) በጋራ እንዲጓዝ ይጋብዛል።
ኢየሱስ ከዚያ ውሳኔ ሰጪ ቅጽበት ጀምሮ ወንጌልን በማብሰር፣ ሰዎችን በማገልገል እና እንዲከተሉት በመጥራት ወደ ሕዝብ አገልግሎቱ ገባ።
OneVoice27 የመላው ዓለም አድቬንቲስት ቤተሰብ የእሱን አርዓያ እንዲከተል
— በመንፈሳዊ ሁኔታ እንዲዘጋጅ፣ በጸሎት እንዲተባበር፣ እና ኢየሱስንና የዘላለም ወንጌልን በመሰጠት እንዲያካፍል ጥሪ ያቀርባል።
ራዕዩ በመላው ዓለም የሚገኙ አባላት፣ አብያተ ክርስቲያናት እና አገልግሎቶች በአንድ ድምፅ እና በአንድ ዓላማ ወደፊት እንዲገሰግሱ ነው፡ የኢየሱስን ተስፋ ለዓለም ማካፈል።
2,000 አመታት
ኢየሱስ ከተጠመቀ እና የሕዝብ አገልግሎቱን ከጀመረ ወዲህ የተቆጠሩ ዓመታት
12 ወራት
የጸሎት፣ የዝግጅት እና የተልዕኮ ወራት — ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ እስከ መስከረም 2027 የቀጥላል።
ዓለም አቀፍ ማስጀመሪያው ቀን
ቅዳሜ (ሰንበት)፣ መስከረም 5፣ 2026 (እ.ኤ.አ)፣ የዓለም ቤተ ክርስቲያን «OneVoice27» የተሰኘውን እንቅስቃሴ በይፋ የምታስጀምር ሲሆን፣ ይህም እስከ መስከረም 2027 (እ.ኤ.አ) የሚዘልቀውንና ለወንጌል ስርጭት ትኩረት የሚሰጠውን የ12 ወራት ጉዞ ያስጀምራል።
አብያተ ክርስቲያናት ይህንን ቀን አባላትን በአዲስ የተልዕኮ ቁርጠኝነት ዙሪያ በማሰባሰብ ለልዩ ጸሎት፣ ለቁርጠኝነት እና ለአገልግሎት ለመላክ እንደ መልካም አጋጣሚ እንዲጠቀሙበት ይበረታታሉ።
ከዚያ ማስጀመሪያ ጀምሮእያንዳንዱ አባል
☞በግል ግንኙነቶች፣
☞በመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች፣
☞በትንንሽ ቡድኖች፣
☞በማህበረሰብ አገልግሎት፣
☞በወንጌል ስርጭት ስብሰባዎች፣
☞በህትመት፣
☞በሜዲያ እና በዲጂታል ወንጌል ስርጭት አማካይነት
ወንጌልን በማካፈል እንዲሳተፍ ለሁሉም እድሉ ቀርቧል።
ዓላማው አባላትን ማስታጠቅ እና እውነትን ለሁሉ ማድረስ ነው፤ ይህም እያንዳንዱ አማኝ በኢየሱስ ተልዕኮ ውስጥ ንቁ ተሳታፊ እንዲሆን መርዳት ነው።