Ethio dave

Ethio dave ethio dave

02/03/2025

የእናንተን ድጋፍ የፈለግኩት የሶስት ልጆች አባት ነኝ ስራ አጥቼ በማፈላለግ ሳለሁ መንጃ ፍቃዴ expired ሆነብኝ ግብርም የምከፍለው አጣሁ ልጆቼንም ስራ እስካገኝ የማጎርሳቸው አጣሁ ለዚያም ነወይ ሰው ፊት የቀረብኩት አመሰግናለሁ ቀድሜ ለምታደርጉልኝ ነገር ሁሉ 1000008804827 CBE

Sunlight used good condition Price 3500Call@ # 0912657007
22/11/2024

Sunlight used good condition
Price 3500
Call@ # 0912657007

አስፍዬ እግዚአብሔር በቸርነቱ ይማርህ
22/10/2023

አስፍዬ እግዚአብሔር በቸርነቱ ይማርህ

በድል ተመለስ በሉት ለታላቁ መሪ!
23/11/2021

በድል ተመለስ በሉት ለታላቁ መሪ!

27 ከተሞችን የናጠው ዓለም አቀፍ  የኢትዮጵያዊያን ተቃውሞ ከደቡብ አፍሪካ እስከ ዋሽንግተን ዲሲ ኋይት ሃውስ   | ኢትዮጵያዊያን ፣ኤርትራዊን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች አሜሪካ የኢትዮጵያን እ...
22/11/2021

27 ከተሞችን የናጠው ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያዊያን ተቃውሞ ከደቡብ አፍሪካ እስከ ዋሽንግተን ዲሲ ኋይት ሃውስ

| ኢትዮጵያዊያን ፣ኤርትራዊን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች አሜሪካ የኢትዮጵያን እጅ ጠምዝዛ ህልውናዋን የሚፈታተን ፖሊሲ ለማጫን እያደረገች ያለውን ጥረት የሚያወግዝ የተቃውሞ ሰልፍ በኋይት ሃውስ ቤተመንግስት ፊት ለፊት አድርገዋል።

ሰልፈኞቹ አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ በተለይም የአፍሪካ ቀንድ ህዝቦችን በመከፋፈል ላይ የተመሰረተ ፖሊሲዋን እንድታርም ጠይቀዋል።

የኢትዮጵያን እጅ ለመጠመዘዝ የሚደረግ ሙከራ የአፍሪካን ነጻነት መግፈፊያ ዳግም የቅኝ አገዛዝ ፖሊሲ አካል በመሆኑ “ ” በሚለው መሪ መፈክራቸው ተቀባይነት እንደሌለው አስገንዝበዋል።

በዋሽንግተን ዲሲ አደባባይ በርካቶች በተካፈሉበት የተቃውሞ ሰልፍ ላይ የኢትዮጵያን የአፍሪካ የነጻነት አርማነቷን፣ወራሪዎችን አሳፍራ የመለሰች የጀግኖች አገር መሆኗን ፣ከጥቁር ህዝቦች በብቸኝነት በቅኝ አገዛዝ ጥላ ስር ያልወደቀች አገር መሆኗን በማስታወስ አሜሪካ የተሳሳተ ፖሊሲዋን ከማራመድ እንድትቆጠብ ጠይቀዋል።

የህወሓት የሽብር ቡድንን መደገፍ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን የአፍሪካ ቀንድን እና መላ አህጉሪቱን አደጋ ላይ የሚጥል አካሄድ መሆኑን የፕሬዝዳንት ባይደን አስተዳደር እንዲገነዘብ ሰልፈኞቹ ጠይቀዋል

በዛሬው ዕለት ብቻ በአምስቱ አለማችን ክፍለ አህጉሮ በሚገኙ 27 የዓለማችን ከተሞች ከደቡብ አፍሪካ እስከ ዋሽንግተን ዲሲ ኋይት ሃውስ በርካቶች የተሳተፉበት ትዕይንተ ህዝብ መካሄዱ ትኩረትን የሳበ አጀንዳ ሆኗል።

ቀደም ብሎ በእስራኤል እና እንግሊዝ በተካሄዱ የተቃውሞ ሰልፎችም በተመሳሳይ ብዛት ያለው ህዝብ በመሳተፍ የዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙሃን የሀሰት ዘገባ እና መንግስታት በምርጫ ወደ ስልጣን የመጣ መንግስትን ለመጣል የሚያደርጉትን ጥረት ክፉኛ ኮንነዋል ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድም በውጭ የሚኖረው አገር ወዳዱ ህዝብ ለአገሩ አንድነት መጠበቅ እያሳየ ላለው አጋርነት በማህብራዊ ትስስር ገፃቸው ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ከፋና የተወሠደ                                                                             አዲስ አበባ፣ ህዳር 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) “ኢት...
22/11/2021

ከፋና የተወሠደ
አዲስ አበባ፣ ህዳር 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) “ኢትዮጵያ” የሚለውን የነጻነት ስም የማስጠበቅ የታሪክ አደራ አለብን - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ

ውድ የሀገሬ ልጆች፣
የተከበራችሁ የኢትዮጵያ ወዳጆች፣

ኢትዮጵያ በልጆቿ ጀግንነትና መሥዋዕትነት ክብሯንና ነጻነቷን አስጠብቃ የኖረች ሀገር ናት። ይሄን ወዳጅም ጠላትም ያውቀዋል። ድንበሯን ሊደፍሩ የሞከሩ አይበገሬ ክንዷን አይተዋል። ሊያስገብሯት የቋመጡ አቀርቅረው ተመልሰዋል። ክህደት ለፈጸሙባት ተገቢውን ትምህርት መስጠት፣ ከጀርባ የወጓትን አይቀጡ ቅጣት መቅጣትን ታውቃለች። ለሺህ ዘመናት የተጎናጸፈችው ነጻነትና ሉዓላዊ ክብር በችሮታ የተገኘ አይደለም። ያለ ዋጋ ነጻነትን አጽንቶ መጠበቅ አይቻልምና፤ ኢትዮጵያ የሚለው የነጻነት ስም የደም ዋጋ ተከፍሎበታል፣ ብርቱ ጀግኖች ሞተውለታል።

በታሪክ የምናውቃቸው አባቶቻቸው በአስተዳደርና በርእዮተ ዓለም ይለያያሉ፤ ለመብት፣ ለፍትሕና ለእኩልነት በነበራቸው አመለካከት ይለያያሉ። ለኢትዮጵያ የግዛት አንድነት፣ ነጻነትና ሉዓላዊነት ባላቸው ቦታ ግን ልዩነት አልነበራቸውም። በቋንቋ፣ በብሔርና በጎሳ ብዝኃነት ቢኖራቸውም የአልደፈርም-ባይ ቆራጥነታቸው አንድ ያደርጋቸዋል። የግል ፍላጎታቸው የቱንም ያህል የተራራቀ ቢሆን፣ የጋራ ጠላት ሲመጣ ኢትዮጵያዊነት ከግላዊነታቸው በላይ ይቀመጣል።

ድሮም ሆነ ዛሬ የእያንዳንዳችን ፍላጎት፣ የሁላችንም ሕይወት ከኢትዮጵያ በታች ነው። እኛ ኖረን ኢትዮጵያ ከምትሞት እኛ ሞተን ኢትዮጵያ እንድትኖር እንፈልጋለን። የሁላችንም የሆነች፣ ነጻነትና ፍትሕ የሰፈነባት፣ በገናናነቷና በነጻነቷ በዓለም አደባባይ የምትጠራ ሀገር እንድትኖረን ምኞታችን ነው። ለኢትዮጵያ ትልቅ በመመኘት፤ ሀገራችን አንገቷ ቀና እንዲል በመፈለግ፤ ባለፉት ሦስት ዓመታት ዐቅማችን የፈቀደውን ሁሉ አድርገናል። ፖለቲካችን ከመገዳደል ወደ መተጋገል እንዲቀየር ታግለናል። ኢትዮጵያ የሁላችን ናት ብለን በሰው ሀገር የሚንከራተቱት ሁሉ እንዲገቡ ለማድረግ ሞክረናል። ካለፈው በጎውን ወስደን ጥፋቱን በይቅርታ ለማረም ተንቀሳቅሰናል። “በፍቅር እንደመር፣ በይቅርታ እንሻገር” ብለን አዲስ ምዕራፍ ከፍተናል። የመለያየትና የጥላቻን ግንብ አፍርሰን የመደመርና ኅብረ ብሔራዊ ወንድማማችነት ድልድይን ልንገነባ ቃል የገባነውን ወደ ተግባር ለመተርጎም ዐቅማችን የፈቀደውን አድርገናል።

ኢኮኖሚው እንዲያገግምና መዋቅራዊ ለውጥ እንዲያመጣ፤ የዳኝነት ሥርዓታችን እንዲሻሻል፣ የሰብአዊ መብት አያያዛችን እንዲስተካከል፤ የውጭ ግንኙነት መርሐችን ጎረቤት ተኮር እንዲሆን ታግለናል። በዚህ መካከል እንደ ሰው በርትተናል። እንደ ሰውም ደክመናል። እንደሰው አልምተናል፣ እንደ ሰውም አጥፍተናል። በኢትዮጵያ ኅብረ ብሔራዊ አንድነት፣ በኢትዮጵያ ክብርና በኢትዮጵያ ታላቅነት ግን ለአፍታም አዘንብለን አናውቅም።

ኢትዮጵያ የምታጓጓ ሀገር ናት። ከትናንትናዋ ይልቅ ነገዋ ታላቅ ነው። መከራ ማለፍ ነባር ችሎታዋ ነው። ይሄንን የገጠመንን መከራም እናልፈዋለን። ኢትዮጵያ ማሸነፏ አይቀርም። አሁን ኢትዮጵያን ለመታደግ የመጨረሻውን ፍልሚያ የምናደርግበት ጊዜ ላይ ነን። ጠላቶቻችን በውጭና በውስጥ ተቀናጅተው ዘምተውብናል። በአንድ በኩል ታሪካዊ ጠላቶቻችን በራሷ ፈቃድና በራሷ መንገድ ብቻ የምታድግ ኢትዮጵያ ላለማየት የጥፋት በትር ሰንዝረዋል። ኢትዮጵያ አፍሪካዊ በሆነ መንገድ ከተነሣች፣ ተነሥታም ካሸነፈች፣ ከዚህ በኋላ ለማንም የማትመለስ ትሆናለች። ይሄን አፍሪካዊ መንገድ ለማደናቀፍ ሁሉንም ዓይነት የክፋት መሣሪያዎች አሰልፈዋል። የውጭና የውስጥ ጠላቶቻችን የእነርሱን ብርታት በኢትዮጵያ ድካም ላይ ለመገንባት ተነሥተዋል። የኢትዮጵያ ፍላጎት ይዞ ማለፍ እንጂ ጥሎ ማለፍ አልነበረም፤ ለዚህ ነው የውጭ ግንኙነት ፖሊሲያችን በዋናነት ጎረቤት ተኮር እንዲሆን ያደረግነው፤ ይህ ትግል የመላ ጥቁር ሕዝቦች ትግል ነው። ኢትዮጵያ አንበርክኮ ጥቁር ሕዝብን ለማሳፈርና አዲሱን የቅኝ ግዛት ቀንበር ለመጫን የሚደረግ ሤራ ነው።
ጥቁር ሕዝቦች የራሳችን ታሪክ፣ ባህል፣ ማንነትና ክብር እንዳይኖረን ሆን ተብሎ የሚደረግ አንገት የማስደፋት ትግል ነው። ይህ በኢትዮጵያ ላይ የተከፈተ ዘመቻ፣ ኢትዮጵያን በማንበርከክ ጥቁር ሕዝቦች የነጻነትና የአሸናፊነት አርአያ እንዳያገኙ የተከፈተ ዘመቻ መሆኑን ላስታውሳችሁ እወዳለሁ። ለጥቁር ሕዝብ ክብርና ልዕልና ስትሉ፣ በፓን አፍሪካ መንፈስ፣ ሁላችሁም ጥቁር ሕዝቦች፣ ከኢትዮጵያ ጋር እንድትቆሙ ጥሪ አቀርብላችኋለሁ።

በመጨረሻም ይህ ትግል የሁሉም ኢትዮጵያዊ ትግል ነው። ልጆቻችን ሀገር እንዲኖራቸው የሚደረግ ትግል ነው። ልጆቻችን ክብርና ነጻነትን ለብሰው፣ በዓለም አደባባይ በኩራት ቀና ብለው እንዲሄዱ የሚደረግ ትግል ነው። በዓለም ላይ በክብር የምንጠራበት ስም እንዲኖረን የሚደረግ ትግል ነው። መኖር ወይም አለመኖራችንን የሚወስን ትግል ነው። ያለ ጥርጥር ግን እናሸንፋለን። ኢትዮጵያን ጠርቶ መሸነፍ ፈጽሞ የማይታሰብ ነው።

ጊዜው ሀገርን በመሥዋዕትነት መምራት የሚያስፈልግበት ጊዜ ነው። ከእንግዲህ እኔ መከላከያን በግንባር ሆኜ ለመምራት ከነገ ጅምሮ ወደ ትግሉ ሜዳ እዘምታለሁ። ታሪክ ከሚያደንቃቸው የኢትዮጵያ ልጆች አንዱ ለመሆን የምታስቡ ሁሉ ለሀገራችሁ ስትሉ ዛሬውኑ ተነሡ፤ ግንባር ላይ እንገናኝ፡፡ የእኛ መዝመት የሚፈጥረውን ክፍተት ከግንባር የቀሩት በሙሉ ዐቅማቸው ሸፍነው ይሠራሉ፡፡ በግንባር ያልተሰለፉ የክልልና የፌደራል አመራሮች ከመቼውም ጊዜ በላይ የልማትና አስተዳደር ሥራዎችን በሙሉ ዐቅማቸው ይከውናሉ።

ጎልማሶች በዘዴና በብልሃት አካባቢያቸውን እየጠበቁ፣ አረጋውያን እናትና አባቶች በጸሎት እየተጉ፣ ሁሉም ሰው ተባብሮ የኢትዮጵያን አሸናፊነት ያረጋግጣል። ከዚህ በኋላ በሩቁ ተቀምጠን ተቺና አራሚ የምንሆንበት ጊዜ አይደለም። መደረግ ያለበትን እኛው ራሳችን እናድርገው። ለኢትዮጵያ ከእኛ በላይ ከየትም አይመጣም። ኢትዮጵያ የሚለው ስም የአሸናፊዎች ስም ነው፤ የነጻነት ምልክት ነው። አልጠራጠርም፣ የእኔ ትውልድ ለአሸናፊ ስሙና ለነጻነት ምልክቱ የሚጠበቅበትን ዋጋ ከፍሎ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን በክብር መዝገብ ላይ በወርቅ ብዕር ያትማል።

አመሰግናለሁ!!

ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትሩር!!
ፈጣሪ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ኅዳር 13፣ 2014 ዓ.ም

1 GB የ ኢንተርኔት ጥቅል ይሸለሙ! 🎁ጥያቄ?በአፍሪካ ብቸኛዋ ቅኝ ያልተገዛች ሃገር ማን ትባላላች?ለማሸነፍ 🤩1፣ ቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiodave ይቀላቀሉ2፣ ጥያቄ...
22/11/2021

1 GB የ ኢንተርኔት ጥቅል ይሸለሙ! 🎁

ጥያቄ?

በአፍሪካ ብቸኛዋ ቅኝ ያልተገዛች ሃገር ማን ትባላላች?

ለማሸነፍ 🤩
1፣ ቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiodave ይቀላቀሉ
2፣ ጥያቄውን በቴሌግራም ቻናላችን ብቻ ይመልሱ!

በየእለቱ ሽልማት ያላቸውን ጥያቄዎች ስለምንለቅ ቴሌግራም ቻናላችንን ተቀላቅለው ይጠብቁን!

https://t.me/ethiodavd

ማሳሰቢያ ⚠️
ጥያቄውን በትክክል የመለሱ በልዩ ሁኔታ 5 ተወዳዳሪዎች ተመርጠው ይሸለማሉ::

የሳይኮሎጂ መምህሩ ወደ ክፍል ገባና "ዛሬ አንድ Game እንጫወታለን" አለ፡፡ ተማሪዎቹም "ምን አይነት Game?" በማለት በህብረት ጠየቁ፡፡ መምህሩ ቀጥሎ "ፈቃደኛ የሆነ አንድ ሰው?" አለ...
04/08/2021

የሳይኮሎጂ መምህሩ ወደ ክፍል ገባና "ዛሬ አንድ Game እንጫወታለን" አለ፡፡ ተማሪዎቹም "ምን አይነት Game?" በማለት በህብረት ጠየቁ፡፡ መምህሩ ቀጥሎ "ፈቃደኛ የሆነ አንድ ሰው?" አለ፡፡አንድ ፈቃደኛ ወንድ ተማሪ እጁን አወጣ፡፡

መምህሩም ተማሪውን በህይወቱ ትልቅ ቦታ ያላቸውን 30 ሰዎች ስም ጥቁር ሰሌዳው ላይ እንዲፅፍ ጠየቀው፡፡
ተማሪውም ከቤተሰቦቹ ጀመሮ የጎረቤቶቹን፣ የዘመዶቹንና የጓደኞቹን ስም ፃፈ፡፡
መምህሩ በመቀጠል በጣም ጠቃሚ ያልሆኑ 3 ስሞችን እንዲሰርዝ አዘዘው፡፡ እሱም የጎረቤቶቹን ስም ሰረዘ፡፡
አሁንም ሌላ 5 ስሞችን እንዲሰርዝ ነገረው፡፡
ተማሪውም የሩቅ የምላቸውን ዘመዶቹን ስም ሰረዘ።
በዚህ መልኩ የአራት ሰዎች ስም ብቻ (የእናቱ፣ የአባቱ፣ የሚስቱና የብቸኛው ልጁ) እስኪቀር ብዙ ስሞችን ሰረዘ።
ሙሉ የክፍሉ ተማሪዎች Gamu ለዚህ ተማሪ ብቻ እንዳልሆነ ተረድተው በተመስጦ ይከታተላሉ፡፡
አሁንም መምሩ ከቀሩት አራት ስሞች 2 እንዲሰርዝ አዘዘው፡፡
ተማሪውም በጣም ከባድ ምርጫ ነበር፡፡
እያመነታና እንዳልተቀበለው በሚያስታውቅ መልኩ የወላጆቹን ስም ሰረዘ።
መምህሩ በስተመጨረሻ ከቀሩት ሁለት ስሞች 1 እንዲሰርዝ ነገረው፡፡
ተማሪውም ሙሉ በሙሉ አእምሮው ተረበሸ፡፡ በአይኖቹ እያነባ በሚንቀጠቀጡ ጣቶቹ የልጁን ስም ሰረዘ፡፡
መምህሩም ተማሪውን ወደ መቀመጫው እንዲመለስ ነገረው።
ከደቂቆች በኋላ መምህሩ "ለምን ሚስትህን አስቀረህ?
ቤተሰቦችህ ላንተ ብቸኞች ናቸው፤
ልጅህን የወለድከው ( ወደ ህይወት ያመጣኸው) አንተ ነህ፤ ሚስት ግን ሌላ ማግባት ትችላለህ፤
ለምን ከእነሱ እሷን አስቀደምክ?" በማለት ተማሪውን ጠየቀው፡፡ ሁሉም ተማሪውን ምላሽ ለመስማት ጓግቷል፡፡
ተማሪውም በተረጋጋ መንፈስ እንዲሁም በቀስታ እንዲህ ስል መለሰ፤
አንድ ቀን ቤተሰቦቼ ምናልባት ከእኔ ቀድመው ያልፋሉ፤
ልጄም ሲያድግ ለትምርት፣ ለስራ ወይም በማንኛውም ምክንያት ጥሎኝ ይሄዳል፡፡ሙሉ ህይወቴን ሁሉን አብራ የሚትጋራኝ ብቸኛ ሰው ቢኖር ባለቤቴ ናት፡፡" አለ።
ሁሉም ተማሪ ከመቀመጫቸው ተነስተው እውነተኛውን የህይወት ገፅታ
ስላካፈላቸው አጨበጨቡለት ይባላል።
#እናንብብ እንወያይ ነጻ እንውጣ
ንበብ ለንባብ

Address

Addis Ababa
ADDIS

Telephone

+251912657007

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethio dave posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Ethio dave:

Share