08/01/2026
አንድ ማንነቱ ያልታወቀ የክሪፕቶ ቁማርተኛ የቬንዙዌላ ፕሬዝዳንት ማዱሮ በአሜሪካን በቁጥጥር ስር ይውላል በማለት ተወራርዶ 436,000 ዶላር አግኝቷል።
ቁማርተኛው የቬንዙዌላው ፕሬዝዳንት በይፋ መያዛቸው ከመታወጁ በፊት በቁማር ተወራርዶ ግማሽ ሚሊዮን ዶላር የሚያክል ገንዘብ አግኝቷል።
ሰውየው ስለ አሜሪካ የቬንዙዌላ ዘመቻ ውስጣዊ እውቀት ካለው ሰው መረጃውን በማግኘት ለቁማር ጨዋታ ተጠቅሟል የሚለውን ጥያቄ አስነስቷል።
በቅርብ ዓመታት በአሜሪካ ውስጥ የትንበያ የቁማር ጨዋታ ተወዳጅነት በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል፣ እንደ 'ፖሊማርኬት' እና 'ካልሺ' ያሉ ኩባንያዎች ከስፖርት እስከ ፖለቲካ ድረስ የቁማር ጨዋታን ያጫውታሉ ።
------------