Zeraf Books - ዘራፍ ቡክስ

Zeraf Books - ዘራፍ ቡክስ Your #1 Source For Ethiopian Books
Shipping Worlwide 🇺🇸🇨🇦🇩🇪🇬🇧🇮🇹~🌎 & Delivering Locally. T.me/Zerraffbooks

 ? :(📖 ''መጽሐፈ ትዝታ'' ከተሰኘው የአለቃ ለማ ኃይሉ ግለታሪክ የተወሰደ) 😊~ታሪክ፣ ባህል፣ ሃይማኖት፣ በድሮ ዘዬ ያለው አማርኛ አንደበት የተሸመኑበት ፥ በታሪክ ፈረስ ወደኋላ ተጉዘው...
12/08/2026

?
:

(📖 ''መጽሐፈ ትዝታ'' ከተሰኘው የአለቃ ለማ ኃይሉ ግለታሪክ የተወሰደ)



😊

~
ታሪክ፣ ባህል፣ ሃይማኖት፣ በድሮ ዘዬ ያለው አማርኛ አንደበት የተሸመኑበት ፥ በታሪክ ፈረስ ወደኋላ ተጉዘው በኢትዮጵያ የተፈጠሩ አስደሳች፣ አሰቃቂ፣ አስቂኝና ታላቅ ክስተቶችን : ከአፄ ቴዎድሮስ ዘመን እስከ አፄ ኃይለሥላሴ ያለውን በኖሩ ታላቅ አዛውንት ምስክርነት የሚማሩበት ወሳኝ መጽሐፍ...

~~
Inbox To Order. Shipping Worldwide 🇺🇸🇨🇦🇩🇪🇫🇷🇷🇺🇮🇹 & Delivering Locally.

T.me/Zerraffbooks

አቶ መኮንን ኃብተወልድ እና አባቴ ዘወትር ይጣሉ ነበር። የአቶ መኮንን ፍላጎት የእኛን ግቢ ከአገር ፍቅር ጋር አጠቃልሎ ማስፋፋት ሲሆን ፥ የአባቴ ደግሞ ከጀርባው የሩቅ አለቃውን የግቢ ሚኒስ...
10/08/2026

አቶ መኮንን ኃብተወልድ እና አባቴ ዘወትር ይጣሉ ነበር። የአቶ መኮንን ፍላጎት የእኛን ግቢ ከአገር ፍቅር ጋር አጠቃልሎ ማስፋፋት ሲሆን ፥ የአባቴ ደግሞ ከጀርባው የሩቅ አለቃውን የግቢ ሚኒስትሩን ፊታውራሪ አስፋው ከበደን መከታ በማድረግ የአቶ መኮንን ኃብተወልድ ምኞት እውን መሆን እንዳይችል መጋፈጥ ነበር። ሁለቱም ባለስልጣኖች በየራሳቸው ለንጉሠ- ነገሥቱ የቅርብ ሰዎችና ተደማጭ ነን ባዮች ነበሩ። ፊታውራሪ አስፋው የታወቁ ተደባዳቢ ናቸው ይባላል፤ አባቴንም አይዞህ ይሉታል። አቶ መኮንን ደግሞ የሆነ ያልሆነውን ምክንያት እየፈለጉ እዚህ ግቢ ውስጥ በሰላም እንዳንኖር ያደርጉናል። በአሁኑ ጊዜ የሌለች ጣሊያኖች የቆፈሯት አንዲት የውሃ ጉድጓድ በእኛና በአገር ፍቅር ግቢ መካከል ነበረች። ከሷም እየቀዳን እንዳንጠቀም አንዳንዴ ያጥሩብናል፤ ይከለክሉናል። አባቴም ለአለቃው ሲያመለክት ወታደሮች ተልከው መጥተው የታጠረውን ያፈርሱታል። ከማይረሱኝ ነገሮች አንዱ ከዕለታት አንድ ቀን የእኛ ከብቶች ከአገር ፍቅር ቲአትር ጓሮ ሲግጡ ተይዘው ምድር ቤት ታሠሩ። ማታ አባታችን ሲመጣ ነገሩ አስቆጣው። ከብቶቹን እንድነዳ ዱላ ይዤ እንድከተለው ካደረገኝ በኋላ፤ ከምድር ቤቱ መግቢያ ከብቶች እንዳይወጡ የተጋደሙትን እንጨቶች እያነሳ ወደጎን ሲወረውር እነዚያ የሚያከብሩት የቲአትር ቤቱ የግቢ ዘበኞች ''እባክር ተው ክቡር ሚኒስትሩ ናቸው እንደዚህ ያደረጉት'' ቢሉት አሻፈረኝ ብሎ ከብቶቹን እንዳስወጣ አዘዘኝ። እኔም በደስታ ከዚያ ጨለማ ጉረኖ ውስጥ ገብቼ ከብቶቹን እየነዳሁ ሳስወጣ አቶ መኮንን ኃብተወልድ በመኪናቸው ሳይታሰብ ከቸች አሉ። ተቆጡ! አበዱ! ...አባቴም የሆኑ ቃላትን መለሰላቸው። እነዚያን ሁለት ዘበኞች ''ያዙልኝ'' አሉ። ዘበኞቹም እየፈሩ፣ እየተቡ አባቴን ያዙት። አቶ መኮንንም በጥፊ ሊማቱ ቀርብ ሲሉ አባቴ አንቆ ያዛቸው። እኔም አባቴ ከነዚህ በምወዳቸው ሦስት ሰዎች ሊደበደብ ሲደፈር ማየቱ ስላስቆጣኝ ለከብቶቹ ጠመኔጃ በያዝኩት ዱላ እየፈራሁ እየተባሁ የአቶ መኮንን ኃብተወልድን እንዝርት መሳይ እግር ሁለት ጊዜ መታሁት። እሳቸውም ከአባቴ ድርጊት ይልቅ የኔ ድርጊት እና ተግባር ስላሳመማቸው ''ይቺ ቁጫጭ እንዲህ ስወዳት ለአባቷ አግዛ ትምታኝ?'' ብለው ደጋግመው ተናገሩና ሁለተኛ ከብቶቹ ሥፍራ ቢገኙ የሚያደርጉትን እሳቸው እንደሚያውቁ ተናግረው አባቴንም ዘበኞቹ ለቀውት ፀቡም በረድ ብሎ ከብቶቻችንን ይዘን ወደቤታችን ገባን።

ከጥቂት ጊዜ በኋላ አባቴ እንደዛ የሚመካባቸው ፊታውራሪ አስፋው ከበደ ከሥልጣናቸው እንደወረዱና በቁም እስር ላይ እንደሆኑና በምትካቸው ሊጋባ ጣሰው ዋለሉ እንደተሾሙ ተነገረ።''
:
[ 📖 ''ኩርፊያ የሸፈነው ፈገግታ'' በስዩም ወልደራምሴ ]

በአማርኛ ከተፃፉ ምርጥ ግለታሪኮች ውስጥ ከፊት የሚሰለፍ መጽሐፍ።
~~~

Inbox To Order. Shipping Worldwide 🇺🇸🇨🇦🇫🇷🇮🇹 & Delivering Locally

T.me/Zerraffbooks

የታሪክ፣ የግለታሪክ፣ የልቦለድ፣ የፖለቲካ፣ የግጥም እንዲሁም ሌላ ዘውግ ያላቸውን መጻሕፍት ከእኛ ዘንድ ያገኛሉ። ካሉበት ቦታ ሆነው ይዘዙን።T.Me/Zerraffbooks
10/08/2026

የታሪክ፣ የግለታሪክ፣ የልቦለድ፣ የፖለቲካ፣ የግጥም እንዲሁም ሌላ ዘውግ ያላቸውን መጻሕፍት ከእኛ ዘንድ ያገኛሉ።

ካሉበት ቦታ ሆነው ይዘዙን።

T.Me/Zerraffbooks

ውድ የክፍለሀገር ደንበኞቻችን፤ ያዘዙን መጻሕፍት ወዳሉበት የኢትዮጵያ ክፍል በፈጣን ፖስታ አገልግሎት ስንልክልዎ፣   በዚህ መልኩፐየማረጋገጫ መልዕክት ወደ ስልክዎ እንደሚደርሶት ማሳወቅ እንወ...
10/08/2026

ውድ የክፍለሀገር ደንበኞቻችን፤

ያዘዙን መጻሕፍት ወዳሉበት የኢትዮጵያ ክፍል በፈጣን ፖስታ አገልግሎት ስንልክልዎ፣ በዚህ መልኩፐየማረጋገጫ መልዕክት ወደ ስልክዎ እንደሚደርሶት ማሳወቅ እንወዳለን። ካሉበት የኢትዮጵያ ጥግ እንዲሁም የዓለም ክፍል ሆነው ይዘዙን። ፖስታ ያለበት ሁሉ በታማኝነት እናደርሳለን ✉️ 🇪🇹 🇺🇸🇰🇪 🇨🇦😊

መልካም ቀን!

T.me/Zerraffbooks

ብዙ ጸሐፊያን (በተለይ ወጣት) አዳዲስ መጻሕፍቶቻቸውን ጀባ እያሉን ነው። የትኞቹን እያነበቡ ነው...የትኛውንስ ለማንበብስ አስበዋል?~Available to order Via Inbox. Shipp...
09/08/2026

ብዙ ጸሐፊያን (በተለይ ወጣት) አዳዲስ መጻሕፍቶቻቸውን ጀባ እያሉን ነው። የትኞቹን እያነበቡ ነው...የትኛውንስ ለማንበብስ አስበዋል?

~
Available to order Via Inbox. Shipping Worldwide 🇺🇸🇨🇦🇫🇷🇮🇹 & Delivering Locally.

T.me/Zerraffbooks

📖 The Ethiopian Cross A Book By : Dr KorabiewiczPublisher: Holy Trinity Cathedral, Addis AbabaPublication Date: 1973*Inb...
09/08/2026

📖 The Ethiopian Cross

A Book By : Dr Korabiewicz

Publisher: Holy Trinity Cathedral, Addis Ababa

Publication Date: 1973

*
Inbox To Order. Shipping Worldwide 🇺🇸🇨🇦🇫🇷🇮🇹 & Delivering Locally.

T.me/Zerraffbooks

''...ዶ/ር ደጃዝማች ዘውዴ የዶሮ አለቃዬ ፣ ወዳጄ አማቼም ስለሆኑ ተሳስመን ስናበቃ ወደቤቴ እንዲገቡ ጋብዣቸው ነበር። ወደ ከተማ ሄደን አገር ማየትን ስለመረጡ ፣ አንድ ባር ውስጥ ገብተን...
08/08/2026

''...ዶ/ር ደጃዝማች ዘውዴ የዶሮ አለቃዬ ፣ ወዳጄ አማቼም ስለሆኑ ተሳስመን ስናበቃ ወደቤቴ እንዲገቡ ጋብዣቸው ነበር። ወደ ከተማ ሄደን አገር ማየትን ስለመረጡ ፣ አንድ ባር ውስጥ ገብተን ቡና ያዝንና ወሬአችንን ዘረጋን...
:
ወደ 1966 ሁኔታ መለስኳቸውና የጸሐፌ ትእዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ መንግሥት ወድቆ ልጅ እንዳልካቸው መኮንን መንግሥት ባቋቋሙ ጊዜ የመንግሥቱ አባል ስለነበሩ እንዴት ከደርግ ጡንቻ እንዳመለጡ ጠየቅኳቸው።

ዶ/ር ዘውዴ እንደመሣቅ አሉና "'እንደምታውቀው የአክሊሉ መንግሥት ወድቆ እንዳልካቸው መንግሥት እንዲቋቋም ጃንሆይ በሾሙት ጊዜ ኒውዮርክ ነበር ያለሁት። እንዳልካቸው ስልክ ደውሎ ይለኛል። ለምንድነው የማስፈልግህ ባልኩት ጊዜ በሚቋቋመው መንግሥት ውስጥ አንድ ካቢኔ ለምሳሌ የእርሻ የመገናኛ የፍርድ የሕዝባዊ ኖሮ ከእነዚህ ውስጥ አንዱን የፈለግከውን ትይዛለህ ብሎ መለሰልኝ። በቅድሚያ የማሰላስለው ከካቢኔውስጥ መገኘት አለመገኘቴን ነው እንጂ የሥራ ቦታዎችን ምርጫ አይደለም አልኩት። እንግዲያው የምትጠራህ አገርህ ስለሆነች እንጠብቅሃለን ስላለኝ ወደ አገሬ የምገባ መሆኔን አረጋገጥኩለት። ይህ በዚህ እንዳለ ተሰናድቼ አገሬ ከመግባቴ በፊት ያገር ግዛት ሚኒስትር መሆኔን በሬድዮና ቴሌብዥን ተነግሮ አገኘሁት። ከእንዳልካቸው ጋር ስንገናኝ ሳላስፈቅድህ የአገር የአገር ግዛት ምኒስቴርን እንድትይዝ ያደረግሁት ለቦታው በጣም አስፈላጊ መሆንህ ታይቶኝ ነው ብሎ ይቅርታ ከጠየቀኝ በኋላ ካልተስማማህበት መለወጥ እንችላለን ይለኛል። ትላንት የተሠራውን በማግሥቱ መለወጥ የልጅጨሥራ መሆኑን ተገንዝቤ ሥራውን ቀጥዬ ሳለ፥ በአክሊሉ መንግሥቱ ጊዜ በሥልጣን ላይ በነበሩት ሰዎች የተነሣ በእኔና በልጅ እንዳልካቸው መካከል አለመግባባት ተፈጥሮ ነበር። ይህ በዚህ እንዳለ ከእለታት አንድ ቀን ኢዮቤልዩ ቤተመንግሥት ለሥራ ሄጄ እነዚሁ የድሮ ባለሠልጣኖት አንዱ ከሌላው በኋላ እየተዥጎደጎዱ ሲገቡ ተመለከትኩና ብዬ እራሴን እየጠየቅኩ ሳሰላስል እንዳልካቸውን ባጠገቤ አገኘሁትና ለምንድነው እነዚህ ባለሥልጣኖች የተሰበረቡት ብዬ እጠይቀዋለሁ። ብሎ ሲያበቃ... ብለው ወታደሮቹ አመልክተው በአንድ በተወሰነ ቦታ ልናስቀምጣቸው ነው ይለኛል። ነገሩ አስገርሞኝ ሰማህ እንዳልካቸው ካልኩት በኋላ ፤ አልኩት። ''እውነትህን ነው። በሥራ ላይ ስለነበረክ እንዳናቋርጥህ ብለን ነው እንጂ" ይለኛል። እንግዲያውስ ይህ እርምጃ መወሰዱን የካቢኔ አባሎች ማወቅ ስለሚገባቸው በራዲዮና በቴሌቭዥን ከመስማት ይልቅ አስቸኳይ ሰብሰባ አድርጎ ማስረዳት ይሻላል። አልኩትና ስብሰባ ተደረገ። ለሚኒስትሮች ጉዳዩ ከቀረበ በኋላ አከራከሪ ሆኖ ስለተገኘ ብዙ ውዝግብ ፈጠረ። የመናገሪያዬ ተራ ደረሰና ''እነዚህ ባለሥልጣናትን የምታስሩት ስራውን የለቀቀው መንግስት አባል በመሆናቸው ከሆነ ይህንን ካቢኔ የምንመራው ሰዎች ከጠቅላይ ሚኒስቴሩ ጀምሮ ከእነርሱ ቦታ የማንገኝበት ምክንያት የለም። ባጠቃላይ መርማሪ ኮሚሽኑ ተቋቁሞ ሥራውን በማካሄድ ላይ ስለሆነ ታሰርም መፈታት ቢኖር ሊመጣ የሚችለው በእነርሱ ውሳኔ ላይ ይሆናል። ከዚህ ውጪ የመንግሥቱ ካቢኔ አባሎች ሳናውቀው ማንኛውም ዓይነት ትእዛዝ የሚሰጥ ከሆነ ሥራ እለቃለሁ'' ብዬ አስታወቅሁ። እንዳልካቸው ተቃወመኝ...ክርክራችን ተካረረና ካቢኔው ሥራ ይልቀቅ የሚል ሀሳብ ቀርቦ በድምፅ ብልጫ ተደገፈ በማግሥቱ ስንብት ለማቅረብ ኢዮቤልዩ ቤተመንግስት ሚኒስትሮች ተሰብስበን ሳሀ በአንድ ሻለቀ የሚመራ የወታደር ቡድን መጣና ቦታ ያዘ። ምንድነው እያልን ስንጠያየቅ ወታደሮቹ ተጠሩና ጃንሆይ ወደሚገኙበት አዳራሽ ገቡ። ቀጥሎ እኛ ሚኒስቴሮቹ ተጠሩና ጃንሆይ ወደሚገኙበት አዳራሽ ገቡ። ቀጥሎ እኛ ሚኒስቴሮች ተጠራንና ገባን። ሻለቃው እንዲናገር ተፈቀደለትና ብዙ የማታለያ ቃላቶችን ካሰማ በኋላ ''የተያዙትንና የሚያዙትን ሚኒስቴሮች ሊገድሏቸው ነው እየተባለ የሚወራው ሀሰት ነው። ማንንም ላለመግደል ቃል እንገባለን። እንዲያውም የእንዳልካቸው ካቢኔ በዚህ የተነሳ ሥራውን ሥራውን ሊለቅ መወሰኑን ሰምተን አዝነናል'' ብሎ ይናገራል።

እዚህ ላይ ጃንሆይ ሰማህ ካሉት በኋላ የምትናገሩትን ለምን አታስተውሉም ''አንገላቸውም የምትለው እናንተ ማን ሆናችሁ ነው። ለመግደልም ሆነ ላለመግደል ቃል የምትገቡት?'' ብለው የማልረሳውን ቃል ነገርዋቸው። ጃንሆይ በዙፋናቸው ላይ እስካሉ ድረስ ወታደሮች ይህንን ቃል የማሰሚት መብትና ሥልጣንም አልነበራቸውም ነገር ግን አደረጉት። የወታደሮቹ ቡዱን ከተሰናበተ በኋላ እንጠራለን ብለን ስንጠብቅ ደጃዝማች ከበደ ተሰማ 'ጃንሆይ ደክሟቸዋል። ለሌላ ጊዜ እናድርገው'' ብለው ወደየመጣንበት ተመለስን። ከዚህ በኋላ ዶ/ር ምናሴ ኃይሌ ሥራውን የማይቀጥል መሆኑን አስታወቀ። እንዳልካቸው ቢለምነውም ሀሳቡን ሳይለውጥ ቀረ። እንዳልካቸው ጠርቶኝ ባገር ግዛት ሚኒስትርነቱ ላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርነቱን ደርቤ እንድይዝ ይጠይቀኛል። ባገር ግዛት ሚኒስቴርነቴ ላይ ስንብት የሰጠሁ መሆኔን አስታወሼ የውጭ ጉዳዩንም እንደማልቀበለው ነግሬው ነበር። በዚህ ጊዜ በብዙ አገርን በሚመለከቱ ነጥቦች ስለያዘኝ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርነቱን ተቀበልኩት። በመጨረሻም ለሥራ ጉዳይ ኒውዮርክ በምገኝበት ደርግ በሚፈፅማቸው አፀያፊ ተግባሮች አንፃር እሱን መወከል ስላሳፈረኝ እንደወጣሁ ቀረሁ ብለው ሲደመድሙ'' እኩለ ሌሊት አልፎ ስለነበር ነገር ጠዋት 3:30 ልንገናኝ ተቃጠርና ተለያየን።

[ 📖 ''የስደት ዘመኔ'' ቅፅ 1 ፤ ፊታውራሪ ከበደ ኃብተማርያም]
~
Inbox to order. Shipping Worldwide 🇺🇸🇨🇦🇫🇷🇮🇹 & Delivering Locally.

T.me/Zerraffbooks

ስብሃት:- ''የሚጥል በሽታ ነበረብኝ። የእኔ እንደ ዶስቶየቪሲኪ እያነሣ የሚያፈርጥ አይነት አይደለም። እኔ ላይ የደረሰብኝን ወንድሞቼ እንደነገሩኝ ሌሊት እነሳና በኃይል! በኃይል እጮሃለሁ። ...
07/08/2026

ስብሃት:-
''የሚጥል በሽታ ነበረብኝ። የእኔ እንደ ዶስቶየቪሲኪ እያነሣ የሚያፈርጥ አይነት አይደለም። እኔ ላይ የደረሰብኝን ወንድሞቼ እንደነገሩኝ ሌሊት እነሳና በኃይል! በኃይል እጮሃለሁ። ተነስቼ እሮጣለሁ። ይዘውኝ ያስተኙኛል።

ጡንቻዬ ደግሞ የዛን ጊዜ በጣም ጠንካራ ነው። ጠዋት ስነሣ በጣም ድክም ያደርገኛል። አንዳንዴም ጉንጬን እነክሳለሁ። አንዳንዴ ጧት ስነቃ ለመጀመሪያዎቹ ጥቂት ሰከንዶች ማን እንደሆንኩና የት እንደሆንኩ አላውቅም። በዚህ በሽታ ምክንያት ልጅ ላለመውለድ ወስኜ ነበር።

ዘነበ ወላ : ''ለምን?''

ስብሃት : በምወልደው ልጅ ይተላለፋል የሚል እምነት ነበረኝ።

ዘነበ ወላ : ባለቤትህ በዚህ ተስማማች?''

ስብሃት : ምን አማራጭ አላት? የሚቸልኮትስ ቼርማን እንደ አባቷ ነበር። ኤውሮፓ ውስጥ ከሚገኙት አራት ዋነኛ የንዲህ አይነት በሽታዎች እስፔሻሊስት አንዱ ከሆነው ሀኪም ጋር ሚስተር ዲክ ቀጠሮ ያዘልን።

''በሽታህ በዘር አይተላለፍም'' አለን ''ነገር ግን ማንኛውም ልጅ ሲወለድ ኤፕሌፕቲክ ለመሆን ሦስት ከመቶ እድል አለው። ስለዚህ ምናልባት ያንተ ልጅ ኤፕሌፕቲክ ቢሆን፣ ሎተሪው ሦስት ከመቶው ደርሶት ነው እንጂ ካንተ ወርሶት አይደለም'' አለኝ። መድኃኒት አዘዘልኝ በቀን አንዴ ጊዜ የሚዋጡ።

''ለብላታ ደሬሳ ያመኛል ሳልላቸው ላማክራቸው ወሰንኩ። ይህ በሽታ በእኛ ሀገር ይባላል። አነሣሁና ጠየቅኳቸው። ይህንን ጥያቄ ለመመለስ እንደ ማርኮ ፖሎ ጉዞ ከአንድ ሰአት በላይ በባርያ በሽታ ትንታኔ ይዘውኝ ተጓዙ። በመጨረሻ መልሣቸው እኔ ሠርቼበት አላውቅም ሆነ። እንደኔው የሀገራችንን መድሃኒት የሚያውቅ ጓደኛዬ እገሌ እንደነገረኝ ብለው አንድ መድሃኒት ጠሩ። ተጠቀምኩባት። ብዙም ሳልቆይ ከበሽታዬ ዳንኩኝ። ኬኒኑን መዋጥ አቆምኩ። ከሃና ጋርም የመጀመሪያ ልጃችንን ያለምንም ስጋት ለመውሰድ ተስማማንን።

ዘነበ : መድሃኒቱን ብትነግረኝ

ስብሃት : ታስሬበታለሁ

ዘነበ : ለምን?

ስብሃት : ፖሊስ ተወው ብሎ

ዘነበ : በሕግ የተከለከለ ነው?

ስብሃት : ይላሉ

ዘነበ : ታዲያ አንተ በተፈጥሮህ ሕግ አክባሪ ሰው ነህ ለምን ሕገ ወጥነቱን መረጥከው?

ስብሃት : መድሐኒቴ ከሕመም ፈውሶኛል። ደስታንም ይፈጥርልኛል።

ዘነበ : መድሃኒቱን አልነገርኸኝም

ስብሃት : አንዳንዱ ሰው በሰው ሕይወት ውስጥ ገብቶ ይፈተፍታል።

ዘነበ : በምን?

ስብሃት : ደግሞ እኮ ከባለቤቱ ያወቀ ቡዳ ነው ሲል ትሰማዋለህ

ዘነበ : አልገባኝም?

ስብሃት : ግን የእኔም በባሕሪዬ አደባባይ መሆን የጎዳኝ መሰለኝ

ዘነበ : አዎን እንደሀበሻ በአደባባይ ተከናንበህ ጨለማን ተገን አርገህ የልብህን መከወን

ስብሃት : እንደዛ ነው የሚደረግ፣ ሰው ምን ይለኛል እያልክ

ዘነበ : መድሃኒቱን ግን አልነገርከኝም

ስብሃት : አልነግርህም

ዘነበ : ለምን?

ስብሃት : ዘነበ አምንሃለሁ። አንተም ሌላ የምታምንም ወዳጅ አለ። ስለዚህ ትነግረውና ሳይታወቅ መድሐኒቱን ታረክሱብኛላችሁ።

(ማስታወሻ - ዘነበ ወላ)

T.me/Zerraffbooks

ለክረምቶት መወጣጫ የሚሆኑ የተለያየ ዘውግ ያለቸው አዲስና የጠፉ መጻሕፍቶችን ከኛ ይሸምቱ።~Inbox to order. Shipping Worldwide 🇺🇸🇨🇦🇫🇷🇮🇹 & Delivering Local...
07/08/2026

ለክረምቶት መወጣጫ የሚሆኑ የተለያየ ዘውግ ያለቸው አዲስና የጠፉ መጻሕፍቶችን ከኛ ይሸምቱ።

~
Inbox to order. Shipping Worldwide 🇺🇸🇨🇦🇫🇷🇮🇹 & Delivering Locally.

T.me/Zerraffbooks

''አባቶቻችን በመሰላቸው ኖሩ።  ሀገር ገነቡ ፤ አፈረሱ። ሶሻሊዝምን አመጡ። ዲሞክራሲን ሞከሩ። ኮንፌድሬሽን አዋቀሩ። ፌደራሊዝምን አቆሙ። ደርቡሽን አሳደዱ ፥ እርስ በርስ ተጫረሱ። አሁን የ...
02/08/2026

''አባቶቻችን በመሰላቸው ኖሩ። ሀገር ገነቡ ፤ አፈረሱ። ሶሻሊዝምን አመጡ። ዲሞክራሲን ሞከሩ። ኮንፌድሬሽን አዋቀሩ። ፌደራሊዝምን አቆሙ። ደርቡሽን አሳደዱ ፥ እርስ በርስ ተጫረሱ። አሁን የእኛ ተራ ነው። ቀጣዩ ትውልድ ታሪክ ሲጽፍልን ያለፈውን ትውልድ ታሪክ ሲያጠኑ ነበር ብሎ ምሕረት አያደርግልንም። በታሪክ ላይ የሚተው ክፍት ቦታ ሁሉ አጸያፊ ወንጀል ነው።''

📖 ምናልባት አንድ ቀን

አዲስ መጽሐፍ በሄኖክ በቀለ ለማ

~~
Inbox to order. Shipping Worldwide 🇺🇸🇨🇦🇫🇷🇮🇹 & Delivering Locally.

T.me/Zerraffbooks

Address

Addis Ababa
46895

Telephone

+251985333153

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Zeraf Books - ዘራፍ ቡክስ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Zeraf Books - ዘራፍ ቡክስ:

Shortcuts

Share

Category