21/09/2026
"ሀገር ማለት ሰው ነው እያሉ በትውልድህ እንቅልፍ ላይ ብርድ ልብስ ይደርባሉ። ሀገር ማለት አፈር ነው፤ ሰውም ማለት አፈር ነው። ኢትዮጵያ ከተፈጠረች ጀምሮ የሞቱት ሰዎቻችን ስጋና አጥንት አፈር ሆኖ ይሄው" አሉና መሬቱን በጎረዴው ጫፍ ጫር አደረጉት።
"አየህ አሁን አፈር አይደለም የሚረክሰው፤ የሰው ስጋ ነው፤ ሲቆረጥ የሚያመመው፤ ሲወጋ የሚያቃስተው ሰው ነው አፈሩ!! ይህንን ነው ቆርሰው የሚወስዱት። ሀገር ማለት ሰው ከሆነ ሰው አፈር ነውና አፈርህን ሲነኩ እንቢ ልትል ይገባል ! ልጄ፤ ሕንፃ እና መንገድ አይግረምህ ፤ የሰው እጅ የሚሰራው የእጅ ጥበብ ሁሉ አይድነቅህ ፤ ነገም ልጆችህ ከአንተ በተሻለ ይሠሩታልና ! ልጆችህ መቼም ለማያገኙት ስንዝር መሬት ግን ያለህን ሁሉ ክፈል..."
📖 ዙቤይዳ ፥ ✍🏾 በአሌክስ አብርሃም
----------------------------------
ይህን ምርጥ መጽሐፍ ሀሁ መፃሕፍት/HaHu Books ቤት ታገኙታላችሁ።
አድራሻ 📍
ሜክሲኮ - ደብረወርቅ ህንጻ Ground floor 🏢
አራት ኪሎ - አብርሆት ቤተ - መጻሕፍት ጎን
ስልክ ቁጥር 📞 0911006705 | 0924408461
የፈለጋችሁትን መጽሀፍ እዘዙን፣ ጠይቁን። በቅልጥፍና እናደርስላን። መጻሕፍትን ከ20-50% በሚደርስ ተመጣጣኝ ቅናሽ በደስታ እናቀርብላችኋለን።
በመደብራችን 10 መጻህፍት ለሚገዛ 1 መጽሀፍ በነጻ በስጦታ መልክ እንሰጣለን።📚🙏🏾