Chosen Generation Ministry

Chosen Generation Ministry መፅሀፍ ቅዱስን የምንማማርበት Page። Like Share ያድርጉና አብረን

  ተከታታይ ትምህርት በጂጆላ ከተማ ቃ/ሕ/ቤ/ንዘውትር ረቡዕ 12:00በአቤነዘር ያዕቆብሁላችሁም ተጋብዛችኋል።
04/11/2025


ተከታታይ ትምህርት በጂጆላ ከተማ ቃ/ሕ/ቤ/ን

ዘውትር ረቡዕ 12:00
በአቤነዘር ያዕቆብ
ሁላችሁም ተጋብዛችኋል።

23/08/2025

አንድ አንድ ሰዎች አካላቸው ሳያረጅ በአዕምሯቸው ያረጃሉ፡፡
አንዳንዶቹ ደግሞ በአካላቸው ደክመውም አዕምሯቸው የልጅ ነው፡፡

25/11/2024
25/11/2024

ያውቁ ኖሯል!!!!

እግዝአብሔር ለሰው ልጅ ያዘጋጀውን ዕቅድ የሰው ልጅ ብዙውን
ጊዜ አይረዱትም አይጠቀሙትምም

በመንፈሳው ዓለም ያሉ እናም መታወቅ ያለባቸው ነገሮች

እግዝአብሔር ይወደኛል ስለዝህም ለሕይወቴ አስደናቅ ዕቅድ
አዘጋችቶልኛል፡፡

# የእግዝ/ር ፍቅር

በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ
እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ
ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና። ዮሃ 3፡16

# የእግዝ/ር ዕቅድ

ክርስቶስ እንድህ አለ…. እኔ ሕይወት እንዲሆንላቸው
እንዲበዛላቸውም መጣሁ። ዮሓ 10፡10
ነገር ግን ሰዎች ይህንን ሙሉና አርኪ ሕይወት አልተለ ማመዱም
ምክንያቱም ……..
ሰው ኃጢአተኛ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት ከእግዝአብሔር
ተለይቷል፡፡ ስለዝህም የእግዝ/ር ፍቅርና ዕቅድ ማወቅና
በሕይወቱ መለማመድ አይችልም፡፡

# ሰው ኃትኣተኛ ነው…

ሁሉ ኃጢአትን ሠርተዋልና የእግዚአብሔርም ክብር
ጎድሎአቸዋል፤ ሮሜ 3፡23
እግዝ/ር ሰውን ስፈጥር ከእርሱ ጋር የቀረበ ግንኙነት
በመመስረት በደስታ እንድኖር ነው፡፡ ነገር ግን ሰው በራሱ
መንገድ ለመጓዝ በመምረጡ ግንኙነታቸው ተቋረጠ፡፡ በራሳቸን
መንገድ ስንጓዝ ለእግዝ/ር የማንታዘዝና ለእርሱም ግድ የለለን
እንሆናለን፡፡ መፅሃፍ ቅዱስ ይህንን ዐይነቱን አስተሳሰብን ነው
ኃጥኣት ብሎ የሚጠራው፡፡
እኛ ሁላችን እንደ በጎች ተቅበዝብዘን ጠፋን ከእኛ እያንዳንዱ
ወደ ገዛ መንገዱ አዘነበለ እግዚአብሔርም የሁላችንን በደል
በእርሱ ላይ አኖረ። ኢሳ 536
በዝህም ምክንያት ሰው ከእግዝአብሔር ተለይቷል
የኃጥኣት ደመወዝ ሞት ነው፡፡ ሮሜ6፡23 ይህም ሞት በመንፈስ
ከእግዝአብሔር መለየት ነው፡፡
የሰው ልጅ አምላክን ከመፈለግ ማንነት ጋር ስለተፈጠረ ሁል ጊዜ
አምላክን ስፈልግ ይኖራል፡፡ የምያሳዝነው ነገር ግን አምላክን
የምፈልግበት መንገድ ትክክለኛውን አምላክ የምያገኝበት
አለመሆኑ ነው፡፡ ይህ ማለት የሀይማኖት ስርዓቶችን በመፈፀም፣
በቴክርስትያን ወይም ወደ ተለያዩ በቴ ዕምነቶች ሳያቋርጡ
በመመላለስ ፣ መልካም ስራን በመስራት ፣ ሰውን ባለመጉዳት
ወ.ዘ.ተ እነዝህን በትክክል በመፈፀም አምላክን የምያገኙ
የምመስላቸው ብዙዎች ናቸው፡፡ ነገር ይህን ሁሉ መፈፀም
መልካም ብሆንም ይህ ጥረት ብቻውን ወደ እግዝአብሔር
ሊያደርስ አይችልም፡፡ ይሁን እንጅ ሰው ወደ እግዝ/ር
የምደርስበት ብቸኛ መንገድ አለ፡፡ ይህም መንገድ ኢየሱስ
ክርስቶስ ነው፡፡ እርሱ ስለ እኛ ሞቷል፡፡ ስለዝህም
ሰው በእርሱ በኩል የእግዝ/ርን ፍቅርና ዕቅድ ሊያውቅና
ሊለማመድ ይችላል፡፡

# እርሱ በእኛ ምትክ ሞቷልና

ነገር ግን ገና ኃጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞቶአልና
እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያስረዳል። ሮሜ 5፡8

# ከሞት ተነስቷል

እኔ ደግሞ የተቀበልሁትን ከሁሉ በፊት አሳልፌ ሰጠኋችሁ
እንዲህ ብዬ። መጽሐፍ እንደሚል ክርስቶስ ስለ ኃጢአታችን
ሞተ፥ ተቀበረም፥
መጽሐፍም እንደሚል በሦስተኛው ቀን ተነሣ፥ 1ቆሮ 15፡3-5

#እርሱ ብቸኛ መንገድ ነው

ኢየሱስም፦ እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር
ወደ አብ የሚመጣ የለም። ዮሐ 14፡6
እግዝ/ር ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ስለእኛ እንድሞት
በመላክ ፈፅሞታል ፡፡ከዚህም የተነሳ ሁላችንንም በእርሱ በኩል
ወደ እግዝ/ር መድረስ እንችላለን፡፡
ስለዝህ እያንዳዳችን ኢየሱስ ክርስቶስን እንደ ግል አዳኛችን
እንደ ጌታችን፣ ልንቀበለው ይሀባናል፡፡ ከዝያም የእግዝአብሐርን
ፍቅርና ዕቅድ በሕይወታችን ልናውቅና ልንለማመድ እንችላለን፡፡
# ክርስቶስን ልንቀበለው
ይገባናል፡፡ ዮሓ 1:12
Abenezer Yacob 0916929228

   እነዚህ ዓይነት መሪዎች አስመሳዮች ናቸው። ከዉጪ ስታዩ የለውጥ ባህርያትን የሚያንፀባርቁ ቢመስሉም ከውስጥ ግን የግል አጀንዳዎቻቸውን የሚያራምዱ ናቸው። የለውጥ መሣይ (Pseudo-Tran...
27/04/2024




እነዚህ ዓይነት መሪዎች አስመሳዮች ናቸው። ከዉጪ ስታዩ የለውጥ ባህርያትን የሚያንፀባርቁ ቢመስሉም ከውስጥ ግን የግል አጀንዳዎቻቸውን የሚያራምዱ ናቸው። የለውጥ መሣይ (Pseudo-Transformational) አመራሮች የተጣመመ ተግባር እና የተዛቡ የስነ-ምግባር መርሆች ላይ የተመሠረቱ ናቸው።
እነዚህ መሪዎች የለውጥ አላማዎችን እንድሽፋን በመጠቀም ራስ ወዳድ ምኞታቸውን ያካሂዳሉ።
የለውጥ መሳይ አመራር መካከል:-
✓ራስን ብቻ ማገለገል
✓ማታለል
✓መበዝበዝ
✓ስልጣን ተኮር መሆን
✓የለሎችን ፍላጎት ከሟሟላት የራስ ፍላጎት ላይ ትኩረት ማድረግ
✓ለራስ የተጋነነ የተጋነነ አመለካከት ፤ ችኩልነት ፤ ✓ስሜታዊ እና ሀይለኛ መሆን
✓የተጣመሙ ይህን ምግባር መርሆች
✓በተከታዮች ውስጥ የግል አመለካከቶች እንዳይኖሩ መከልከል
✓ለለሎች በቂ እንክብካቤ አለመስጠት
✓የጋራ ጥቅምን ወደ ጎን በመተው የተከታዮችን ደህንነት ስጋት ላይ መጣል
✓በአስገዳጅነት በተከታዮች ላይ መሠልጠን
✓ ሥልጣን በመጠቀም በራስ ፍቃድ ሌሎችን መሸለም እና መቅጣት (መሾም እና መሻር) ናቸው።
የለውጥ መሳይ አመራሮች በተለይ ሌሎችን ከማነሳሳት ጋር ተያይዞ የለውጥ አመራር ጋር የሚመሳሰሉ በርካታ ባህርያትን እንደ ሚያንፀባርቁ ሊታወቅ ይገባል። ይሁን እንጂ የራስ ወዳድነት፤ ሌሎችን የመበዝበዝ እና ራስን ክፍል የማድረግ አጀንዳዎችን በውስጣቸው ይዘዋሉ።
በዚህ ምክንያት የለውጥ አምጪ አመራሮች እንደዚህ ዓይነት መሪዎች ዘንድ ከሚመጣ የማታለል እና የማጭበርበር ድርጊቶች ራሳቸውን ሊጠብቁ ይገባቸዋል።

አቤኔዘር ያዕቆብ ነኝ

 #እንመሠክርማለን
21/08/2023

#እንመሠክርማለን

24/07/2023

በእርሱ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው።

አንተም(አንቺም ) ማግኘት ይቻላል። ኢየሱስ ለሁሉ ነው

Address

Arba Minch'

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Chosen Generation Ministry posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Chosen Generation Ministry:

Share

Category