21/05/2026
እንኳን ደህና መጣህ ዲላን
ገብቷል ዲላን
የዲጂታል ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪው ዲላን ፔጅ አዲስ አበባ ገባ፤
አዶናይ የገባውን ቃል ፈጽሟል
ዛሬ ሐሙስ ጠዋት በአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ለየት ያለ ደማቅ ድባብ ተስተውሏል።
በፈጣን የዓለም ዜና አቀራረቡ የሚታወቀውና ከ19 ሚሊዮን በላይ የቲክቶክ ተከታዮችን ማፍራት የቻለው ዝነኛው የይዘት ፈጣሪ ዲላን ፔጅ (Dylan Page) ከሀገር ውስጥ ተጽዕኖ ፈጣሪው አዶናይ ጋር በመሆን በሰላም አዲስ አበባ ገብቷል።
ይህንን ታላቅ ዓለም አቀፍ ጉብኝት እውን በማድረግ ረገድ የ2025 የኢትዮጵያ የዓመቱ ምርጥ ቲክቶከር አዶናይ ቀዳሚውን ሚና ተጫውቷል።
ለተከታዮቹ የገባውን ቃል በተግባር ለማሳየት ወደ ለንደን የተጓዘው አዶናይ፣ ከዲላን ፔጅ ጋር የነበረውን ቅድመ-ዝግጅት በከፍተኛ ስኬት በማጠናቀቅ ይህንን ታዋቂ የዲጂታል ሚዲያ ኮከብ ወደ እናት ሀገሩ ይዞ ለመምጣት በቅቷል።
ይህ ስኬት የአዶናይን ጠንካራ የሥራ ቁርጠኝነት ከመግለጹ ባለፈ፣ ለሀገራዊ ገጽታ ግንባታ ያለውን ትልቅ አበርክቶ ያሳየ በመሆኑ ከፍተኛ አድናቆት እየተቸረው ይገኛል።
የዲላን ፔጅ ወደ ኢትዮጵያ መምጣት ተራ ጉብኝት ከመሆን ባለፈ፣ ለአገር ውስጥ ቱሪዝም ማስተዋወቂያ፣ ለዲጂታል ዲፕሎማሲው ስኬት እንዲሁም የኢትዮጵያን ሰላማዊ እውነታ ለዓለም ማህበረሰብ ለማሳየት እጅግ ግዙፍ ፋይዳ እንዳለው የዘርፉ ባለሙያዎች ይገምታሉ።
በዚህ ታሪካዊ ክስተት ምክንያት በአስር ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የዓለም ዜጎች ትኩረት በአሁኑ ሰዓት በአዲስ አበባ ላይ አርፏል።
የጉርሻ ፔጅ የዚህን ታላቅ ጉብኝት ቀጣይ ሁነቶች፣ የአቀባበል ሥነ-ሥርዓት እና ልዩ ልዩ መረጃዎችን በቅርበት እየተከታተለች ለውድ ቤተሰቦቿ የምናደርስ ይሆናል።
ለወጣቱ ተጽዕኖ ፈጣሪ አዶናይ ላቅ ያለ አክብሮትና ምስጋና ይገባዋል!
እንኳን ደህና መጣህ ዲላን!
Welcome to Ethiopia, Dylan Page!
📷Solen