AI-Ftawa/አል-ፈታዋ

AI-Ftawa/አል-ፈታዋ ይህ ቻናል የተለያዩ ኡስታዞች እና ዑለማወች በተለያዩ ረዕሰ ?

ፈጅር መውጣቱን የተጠራጠረ=================➫ #ጥያቄ፡- (አንድ ሰው) ፈጅሩ መውጣቱን ቢጠራጠርመብላትት መጠጣት ይችላል? #መልስ፡-ፈጅሩ ለእርሱ ግልጽ ስስኪሆንለት ድረስ መብላት እ...
13/04/2022

ፈጅር መውጣቱን የተጠራጠረ
=================➫
#ጥያቄ፡-
(አንድ ሰው) ፈጅሩ መውጣቱን ቢጠራጠር
መብላትት መጠጣት ይችላል?

#መልስ፡-
ፈጅሩ ለእርሱ ግልጽ ስስኪሆንለት ድረስ መብላት እና መጠጣት ይችላል። አላህ እንዲህ ብሏል፡-
{فالآن باشروهن وابتغوا ما كتب الله لكم وكلوا واشربوا حتى يتبين لكم الخيط الأبيض من الخيط الأسود من الفجر ثم أتموا الصيام إلى الليل}
البقرة: ۱۸۷
“(ሚስቶቻችሁን) አሁን ተገናኙዋቸው፡፡ አላህም ለናንተ የጻፈላችሁን ነገር (ልጅን) ፈልጉ፡፡ ከጎህ የሆነው ነጩ ክርም ከጥቁሩ ክር (ከሌሊት ጨለማ)
ለእናንተ አስከሚገለጽላችሁ ድረስ ብሉ፤”
(አል በቀራህ፡ 187)
በጸሐይ መጥለቅ በተጠራጠረ ሰው ተቃራኒ ፈጅሩ መውጣቱን የተጠራጠረ ሰው እርግጠኛ አስከሚሆን ድረስ መብላት ይችላል። የጸሐይን
መጥለቅ የተጠራጠረ ሰው ግን መጥለቋን አስከሚያረጋግጥ ወይም ጥርጣሬው አመዛኝ አስከሚሆን ድረስ እንዳይበላ።

مجموع الفتاوى ورسائل لفضيلة الشيخ محمد بن صالح العثيمين

ሌሎች ፈታዋወች እንዲደርስወ ፔጃችንን ያድርጉ

የቴሌግራም ቻናላችንን ያድርጉ👇👇👇👇
https://t.me/Ftawa_Tube

እየፆመ ብልቱን በመነካካት መንይ ያስወጣ ከፋራ አለበት?=============================➫ #ጥያቄ፡-ጾመኛ ብልቱን በመነካካት መንይ (የፍትወትጠብታ) ቢያስወጣ ከፋራ ግዴታ አለበ...
05/04/2022

እየፆመ ብልቱን በመነካካት መንይ ያስወጣ ከፋራ አለበት?
=============================➫

#ጥያቄ፡-
ጾመኛ ብልቱን በመነካካት መንይ (የፍትወት
ጠብታ) ቢያስወጣ ከፋራ ግዴታ አለበት?

#መልስ፡-
ጾመኛ ብልቱን በመነካካት መንይ (የፍትወት
ጠብታ) ቢያስወጣ ጾሙ ይፈርሳል። ብልቱን ነካክቶ መንይ (ፍትወት ጠብታ) ያስወጣበትን ቀን ቀዷ ማውጣት እንጅ ከፋራ የለበትም። ከፋራ ግዴታ የሚሆነው ግብረ ስጋ ግንኙነት ከፈጸመ ብቻ ነው፡፡

مجموع الفتاوى ورسائل لفضيلة الشيخ محمد بن صالح العثيمين

ሌሎች ፈታዋወች እንዲደርስወ ፔጃችንን ያድርጉ

የቴሌግራም ቻናላችን ያድርጉ
https://t.me/Ftawa_Tub

በፆም ላይ ያለች ሴት ምግብ መቅመስ ትችላለች?==============================➫ #ጥያቄ፡- የረመዳንን ወር የምትፆም ሴት የምታበስለውን ምግብ መቅመስ ይፈቀድላታልን? #መልስ፡...
04/04/2022

በፆም ላይ ያለች ሴት ምግብ መቅመስ ትችላለች?
==============================➫
#ጥያቄ፡-
የረመዳንን ወር የምትፆም ሴት የምታበስለውን ምግብ መቅመስ ይፈቀድላታልን?

#መልስ፡-
ምግብ መቅመሷ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ይህን ማድረግ ችግር የለውም:: ሆኖም ግን ያን ስታደርግ የቀመሰችው ምግብ ወደ ሆዷ እንዳይገባ መከላከልና ወደ ውጭ መትፋት ይኖርባታል፡፡

ሸይኽ ሙሐመድ ኢብን ሷሊህ አል-ዑሰይሚን

ሌሎች ፈታዋወች እንዲደርስወ ፔጃችንን ያድርጉ

የቴሌግራም ቻናላችን ያድርጉ
https://t.me/Ftawa_Tube

የረመዳን የቀኑን ክፍል በእንቅልፍ የሚያሳልፉ ሰወች==================================➫ #ጥያቄ፡-(በረመዳን) ቀን ላይ ሰፊ ሰዓትን በመተኛት የሚያሳልፉ ሰዎች ሸረዐዊ ሁክ...
31/03/2022

የረመዳን የቀኑን ክፍል በእንቅልፍ የሚያሳልፉ ሰወች
==================================➫
#ጥያቄ፡-
(በረመዳን) ቀን ላይ ሰፊ ሰዓትን በመተኛት የሚያሳልፉ ሰዎች ሸረዐዊ ሁክማቸው ምንድን ነው? ሰፊ ሰዓት ተኝተው ለፈርድ ሰላት ብቻ የሚነሱ ሰዎችስ ሸረዓዊ ሁክም (ብይን) ምንድን ነው?

#መልስ፡-
ይህ ጥያቄ ሁለት ባህሪዎችን ያቀፈ ነው።
1- ቀን ላይ (ለፈርድ ሰላት) ምንም ሳይነቁ ሰፊ ሰዓትን የሚተኙ ሰዎች ናቸው። እነዚህ ሰዎች ያለምንም ጥርጥር በነፍሳቸው ላይ ድንበር ያለፋና ሶላታቸውን በመተው (ሁለት) ጥፋቶችን እየፈጸሙ እንደሆነ የሚታወቅ ጉዳይ ነው። አንደኛው ሶላታቸውን በመተው የአላህን ህግ ጥሰዋል።ሁለተኛው የሶላተል ጀማዓ ባለቤት(ሰላተል ጀመዐ ግዴታ የሚሆንባቸው) ከሆኑ ደግሞ ሶላትን በጀማዓ ባለመስገዳቸው ሀራም ተግባርን ፈጽመዋል። እንዲህ አይነት ተግባራቶችን መፈጸም ፆምን ያጓድላል። የዚህ አይነቱ ድርጊት ምሳሌ
ህንጻዎችን አየገነቡ ከተማዎችን እንደሚያፈርሱ ሰዎች አምሳያ ነው። እነዚህ ሰዎች ወደ አላህ ተውበት አድርገው ሊመለሱ ይገባል። ከእንቅልፋቸው ተነስተው ሶላታቸውን አላህ ባዘዘው መልኩ ወቅቱን ጠብቀው ሊሰግዱ ይገባል።
2- ሁለተኛው ባህሪ ቀን ላይ ሰፊ ሰአት ተኝተው ከቆዩ በኋላ ለፈርድ ሰላት ብቻ የሚነቁ ሰዎች ናቸው። እነዚህ ሰዎች ሀጢያተኛ ባይሆኑም በርካታ መልካም ነገሮች ግን አምልጧቸዋል። ጾመኛ የሆነ ሰው ዚክር በመዘከር፣ ቁርዓን በመቅራት እና ዱዓ በማድረግ ነፍሱን በመልካም ተግባራት ሊጠምዳት ይገባል። ማንኛውም ሰው በጾም ጊዜ ነፍሱን በዒባዳ ከጠመዳት መልካም ተግባራቶች ሁሉ ገር ይሆኑለታል። ነገር ግን ነፍሱን በስንፍና በድክመትና በእረፍት ካለማመዳት መልካም ተግባራት ሁሉ ይከብዱታል።
ስለዚህ በአሁኑ ሰዓት - ምስጋና ለአላህ ይገባው - ሙከየፍ (ቬንትሌተር) አና ሌሎችም ጾምን ቀላል የሚያደርጉ ነገሮች በተመቻቹበት ወቅት ማንኛውም ሙስሊም የጾም ወቅቱን በዒባዳ እንጅ በአንቅልፍ ሊያሳልፍ አይገባም።

مجموع الفتاوى ورسائل لفضيلة الشيخ محمد بن صالح العثيمين

ሌሎች ፈታዋወች እንዲደርስወ ፔጃችንን ያድርጉ

የቴሌግራም ቻናላችንን ያድርጉ👇👇👇👇
https://t.me/Ftawa_Tube

የቀዷ ፆማቸውን ሳይጨርሱ ረመዳን የደረሰባቸው=============================➫ #ጥያቄ፡-አንዳንድ ሴቶች በአንዱ የረመዳን ፆም ያልዖሟቸውን ቀናት ሳያካክሱ ሌላኛው ረመዳን መጥቶ...
26/03/2022

የቀዷ ፆማቸውን ሳይጨርሱ ረመዳን የደረሰባቸው
=============================➫

#ጥያቄ፡-
አንዳንድ ሴቶች በአንዱ የረመዳን ፆም ያልዖሟቸውን ቀናት ሳያካክሱ ሌላኛው ረመዳን መጥቶ ያልፋቸዋል፡፡ በእነዚህ ሴቶች ላይ ያለባቸው ግዴታ ምንድን ነው?

#መልስ፡-
እነዚህ ሴቶች ያለባቸው በአስቸኳይ ተጸጽተውና ከዚህ ድርጊታቸው ለመጽዳት ለአላህ ቃል ገብተው ወደ እርሱ መመለስ ነው።ምክንያቱም አንድ ሰው ያልዖማቸውን የረመዳን ቀናት ያለ በቂ ሸሪዓዊ
ምክንያት ሳያካክስ እስከ ቀጣዩ ረመዳን መቆየት ስለማይፈቀድለት ነው::ይህም ዓኢሻ (ረድየላሁ ዐንሀ)ባወራችው በተከታዩ ሐዲስ ላይ የተመሠረተ ነው::
ዓኢሻ(ረድየላሁ ዐንሀ)እንዲህ ትላለች:- “በረመዳን ወር ያልዖምኩባቸውን ቀናት ቀጣዩ ረመዳን ከመምጣቱ በፊት በሸዕባን ወር ቢሆን እንጂ በሌላ ወር አልፆማቸውም ነበር:: "
ይህ የሚያሳየን የአንዱን ረመዳን ቀዷ ወደ ሌላው ረመዷን ማስተላለፍ የተከለከለ መሆኑን ነው:: ስለሆነም እነዚህ ሴቶች የልቅና ባለቤት ወደ ሆነው አላህ በመመለስ ለሠሩት ኃጢአት ምህረትን መጠየቅና ከሁለተኛው ረመዳን በኋላም ቢሆን ያባከኗቸውን ቀናት ማካካስ ይኖርባቸዋል።

ሸይኽ ሙሐመድ ኢብን ሷሊሕ አል-ዑሰይሚን

ሌሎች ፈታዋወች እንዲደርስወ ፔጃችንን ያድርጉ

የቴሌግራም ቻናላችንን ያድርጉ👇👇👇👇
https://t.me/Ftawa_Tube

ፎቶግራፍን ለማስታወሻነት ማስቀመጥ========================➫ #ጥያቄ፡- ፎቶግራፍን ለማስታወሻነት ማስቀመጥ አይፈቀድምን? #መልስ፡- ለወንድም ሆነ ለሴት ፎቶግራፍን ለማስታወሻነት...
25/03/2022

ፎቶግራፍን ለማስታወሻነት ማስቀመጥ
========================➫

#ጥያቄ፡-
ፎቶግራፍን ለማስታወሻነት ማስቀመጥ አይፈቀድምን?

#መልስ፡-
ለወንድም ሆነ ለሴት ፎቶግራፍን ለማስታወሻነት መያዝ አይፈቀድም።ይህም የአደምን ልጅ(ሰውን) እና የሌሎችንም ፎቶ ግራፍ ያጠቃልላል። እነዚህን ፎቶግራፎች ማስወገድ ያስፈልጋል፡፡
የአላህ መልእክተኛ ﷺ ይህን ጉዳይ በማስመልከት ለዓሊ ኢብኑ አቡ ጣሊብ የሚከተለውን ምክር ሰጥተዋቸው ነበር፡-
“ ማንኛውንም ምስል ሳታወድም እንዲሁም መቃብሮችን ደግሞ አንድ ስንዝር እስኪቀር ድረስ ሳታስተካክላቸው እንዳትተው::”
የአላህ መልዕክተኛ በተጨማሪም በካዕባ ግድግዳዎች ወይም በዙሪያው ላይ ማናቸውንም ምስሎች ማንጠልጠል አውግዘዋል፡፡ በዚሁ መሠረት መካ በተከፈተበት ጊዜ ካዕባ ውስጥ ሲገቡ በግድግዳዎቹ ላይ የተለያዩ ምስሉች ተስለው በማየታቸው ውሃና ቁራጭ ጨርቅ እንዲሰጣቸው በማዘዝ በዚያ ግድግዳውን አጽድተውታል:: ፎቶ ግራፍን አስመልክቶ ሌላ ሳናነሳው የማናልፈው ጉዳይ ዛፎችን፤ ተራሮችን፤ ሃይቆችንና የመሳሰሉትን ተፈጥሮአዊ ትዕይንቶች መያዝም ሆነ ግድግዳ ላይ መስቀል የሚፈቀድ መሆኑን ነው::

ሸይኽ ዐብዱል ዐዚዝ ኢብን ባዝ

ሌሎች ፈታዋወች እንዲደርስወ ፔጃችንን ያድርጉ

የቴሌግራም ቻናላችንን ያድርጉ👇👇👇👇
https://t.me/Ftawa_Tube

ታዳጊ በሆነች ልጃገረድ ላይ ፆም ግዴታ የሚሆንባት መቼ ነው?---------------------------------------------------------------➫ #ጥያቄ፡-አንዲት ታዳጊ ልጃ...
22/03/2022

ታዳጊ በሆነች ልጃገረድ ላይ ፆም ግዴታ የሚሆንባት መቼ ነው?
---------------------------------------------------------------➫

#ጥያቄ፡-
አንዲት ታዳጊ ልጃገረድ ፆም መጀመር ያለባት ጊዜ መቼ ነው?

#መልስ፡-
ታዳጊ የሆነች ልጃገረድ ፆም መጀመር ያለባት ሌሎች ግዴታ የሆኑ የአምልኮት (ዒባዳ) አይነቶችን መጀመር በሚኖርባት ጊዜ ነው::አንድ ልጃገረድ ለአቅመ ሔዋን ደረሰች የሚባለው አንድም አሥራ
አምሰት ዓመት ሲሞላት፤የመራቢያ አካላቷ አካባቢ ጸጉር መውጣት ሲጀምር፤ የወር አበባዋ መፍሰስ ሲጀምር ወይም ስታረግዝ ነው::
ስለዚህም ከእነዚህ ከተጠቀሱት ነገሮች አንዱ በተከሰተ ጊዜ ይህች ልጅ የአሥር ዓመት ልጅ ብትሆን እንኳን ለአቅመ ሔዋን ደርሳለችና ፆም
በእርሷ ላይ ግዴታ ይሆንባታል፡፡ አሁን አሁን እንደሚታየው ብዙ ልጃገረዶች የመጀመሪያ የወር አበባቸውን የሚያዩት በአሥር ወይም በአሥራ አንድ አመታቸው ቢሆንም ወላጆቻቸው ይህን ሁኔታ ችላ
እያሉና ልጆቻቸው አሁንም ገና ለአካለ መጠን እንዳልደረሱ እያሰቡ እንዲፆሙ አያደርጓቸውም:: ይህ ፈጽሞ ስህተት ሲሆን ታዳጊ የሆነች
ልጃገረድ የመጀመሪያ የወር አበባዋን ካየችበት ጊዜ ጀምሮ ለአቅመ ሔዋን መድረሷና ሙሉ ሴት መሆኗ ተረጋግጦ ግዴታ የሆኑ የአምልኮት
ተግባራት ሁሉ በእርሷ ላይ ይፀኑባታል::

ሸይኽ ዐብደላህ ኢብን ጅብሪን

ሌሎች ፈታዋወች እንዲደርስወ ፔጃችንን ያድርጉ

የቴሌግራም ቻናላችንን ያድርጉ👇👇👇👇
https://t.me/Ftawa_Tube

የሸዕባን ከተጋመሰ በኋላ መፆም‼️=====================➫✍ «የሸዕባን ወር ከተጋመሰ በሗላ መፆምን በተመለከተ ሊቃውንት የተለያዩ አስተያየቶች አሏቸው። በርካታ የፊቅህ ሊቃውንት ሻ...
19/03/2022

የሸዕባን ከተጋመሰ በኋላ መፆም‼️
=====================➫

✍ «የሸዕባን ወር ከተጋመሰ በሗላ መፆምን በተመለከተ ሊቃውንት የተለያዩ አስተያየቶች አሏቸው። በርካታ የፊቅህ ሊቃውንት ሻዕባን ወር ከተጋመሰ በሗላ ለማንኛውም ሰው ግዴታ ፆም ያለበት ሰው ካልሆነ በስተቀር መፆም ይከለከላል የሚል አቋም አልላቸው። ሌሎቹ የወሩ መጀመሪያ ላይ መፆም ላልጀመረ ሰው ብቻ ነው የሚከለከለው ይላሉ፤ ነገር ግን የተመረጠው አቋም መፆም የሚከለከለው ከረመዷን አንድ ወይም ሁለት ቀን ቀደም ብሎ ብቻ ነው። ከዛ በፊት በየትኛውም ቀን ማንኛውም አይነት ፆም መፆም ይቻላል የሚለው ነው። ም/ቱም ነብዩ ﷺ ሸዕባንን ከጥቂት ቀናት በስተቀር ይፆሙት እንደነበር በትክክለኛ ሐዲሥ ተዘግቧል።

የምእመናን እናት ዓኢሻህ እንዲህ ብለዋል፦ "ነብዩ ﷺ የሸዕባንን ወር የበለጠ የሚፆሙት ወር አልነበረም -ከረመዿን በስተቀር- ሻዕባንን ከጥቂት ቀናት በስተቀር ሙሉውን ይፆሙት ነበር።" (ቡኻሪይና ሙስሊም)

በሌላም ቡኻሪይና ሙስሊም በዘገቡት ሐዲስ ነብዩ ﷺ የሚከተለውን ብለዋል፦ “ከረመዿን አንድ ወይም ሁለት ቀን ቀደም ብላችሁ አትፁሙ በቋሚነት ያስለመደው ፆም ያለበት ሰው ካልሆነ በስተቀር፤ እርሱ ፆሙን ይፁም”። (ቡኻሪይና ሙስሊም)

እነዚህና ሌሎችም ተመሳሳይ ሐዲሦች የሻዕባንን ወር አብዛሃኛውንና ከጥርጣሬ (ከሻዕባን 29ኛው) ቀን በፊት ያሉ የሻዕባን ወር ቀናቶችን መፆም እንደሚቻል በግልፅ ያሳያሉ። "ሻዕባን ከተጋመሰ በሗላ አትፁሙ" የሚለውን ሐዲስ በተመለከተ ኢማሙ አሕመድ፣ ኢብኑ መዒን፣ ኢብኑ መህዲና አቡ ዘርዕን ጨምሮ የተለያዩ አንጋፋ ቀደምት የሐዲሥ ሊቃውንት ትክክለኛ ሐዲሥ አይደለም ብለዋል። ኢብኑ ረጀብ አንዳንድ ሐዲሡ ትክክል ነው ያሉ ሰዎችን ስም ከጠቀሱ በሗላ "ከነዚህ የሚልቁና በዕውቀትም የሚበልጡ ሰዎች ሐዲሱን ዾዒፍ (ደካማ) ነው ብለዋል በማለት ከላይ የጠቀስኳቸውን ሊቃውንት ስም ጠቅሰዋል። የተወሰኑት ደግሞ ሐዲሡ ትክክለኛ ነው እንኳ ቢባል ሆን ብሎ ሻዕባን ከተጋመሰ በኋላ ለረመዷን ፆም ጥንቃቄ ለማድረግ በሚል ቀደም ብሎ ፆም ለጀመረ ሰው ነው የሚከለከለው ብለዋል። ሌሎች ደግሞ ይህ የተከለከለው ፆም ለሚደክመው ሰው ነው የሚል አቋም አላቸው። ኢብኑ ረጀብ በጥቅሉ ይህ ሐዲሥ እንደማይሰራበት በርካታ ሊቃውንት እንደገለፁ ተናግረዋል።»

(ከኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም የፆም ህግጋት መጽሐፍ የተወሰደ)

ሌሎች ፈታዋወች እንዲደርስወ ፔጃችንን ያድርጉ

የቴሌግራም ቻናላችንን ያድርጉ👇👇👇👇
https://t.me/Ftawa_Tube

ቁርኣን እያስተማሩ ደመወዝ መቀበል======================➫ #ጥያቄ፦ህፃናትን የከበረውን ቁርኣን በማሰሐፈዝ ደመወዝ መቀበል ብይኑ ምንድነው? "ይቻላል" የምትሉ ከሆነ ወርሃዊ ደመወ...
17/03/2022

ቁርኣን እያስተማሩ ደመወዝ መቀበል
======================➫

#ጥያቄ፦
ህፃናትን የከበረውን ቁርኣን በማሰሐፈዝ ደመወዝ መቀበል ብይኑ ምንድነው? "ይቻላል" የምትሉ ከሆነ ወርሃዊ ደመወዝ የሚቀበል አስተማሪ ከአላህ ዘንድ ምንዳ ይኖረዋል ወይ?

#መልስ፦
የከበረውን ቁርኣን መማርና ማስተማር - ኒያ ከተስተካከለ - ከትልልቅ ወደላቀውና ከፍ ያለው አላህ መቃረቢያዎች ውስጥ ነው። ነብዩም (ﷺ) {ከናንተ በላጫችሁ ቁርኣንን ተምሮ ያስተማረ ነው} በማለት ቁርኣንን በመማርና ማስተማር ላይ አነሳስተዋል።
የቁርኣን አስተማሪዎች በማስተማራቸው የተነሳ ደመወዝ መቀበላቸው ምንዳ ከመገኘቱ ጋር የሚቀረን አይደለም። ከአላህ - ጀለ ወዐላ - ምንዳ የሚገኘው ኒያው የጠራ (ለአላህ ብቻ የሆነ) ከሆነ ነው። ... "

ምንጭ [ፈታዋ ለጅነቲ ዳኢማህ፡ 15/ 99]
ፈትዋውን የሰጡት
1- ዐብዱልዐዚዝ ብኑ ዐብዲላህ ብኒ ባዝ
2- ዐብዱልዐዚዝ ኣሊ ሸይኽ
3- ዐብዱላህ ብኑ ጉደያን
4- ሳሊሕ አልፈውዛን
5- በክር አቡ ዘይድ

IbnuMunewor

ሌሎች ፈታዋወች እንዲደርስወ

የቴሌግራም ቻናላችንን ያድርጉ👇👇👇👇
https://t.me/Ftawa_Tube

ሁለት ብቻ ሆነው ሲሰግዱ ተከታዩ የት ነው የሚቆመው?አብዘሀኛው የማያውቀው ስህተት?===========================➫ከኢማም ጋር በምንሰግድበት ሰዐት ከተረሱ ሱናወች መካከል:-ሁለት...
16/03/2022

ሁለት ብቻ ሆነው ሲሰግዱ ተከታዩ የት ነው የሚቆመው?
አብዘሀኛው የማያውቀው ስህተት?
===========================➫

ከኢማም ጋር በምንሰግድበት ሰዐት ከተረሱ ሱናወች መካከል:-
ሁለት ብቻ (ከኢማሙ ጋር አንድ ተከታይ ብቻ)ከሆኑ ብቻውን የሆነው ተከታይ ከኢማሙ በቀኝ በኩል በሱ አቅጣጫ ሙሉ ለሙሉ እኩል ሆኖ ይቆማል:: አብዘሀኛው ሰው እንደሚያደርገው ከኢማሙ ወደኋላ ቀረት ሊል አይገባም።
ኢብኑ አባስ (ረዲየላሁአንሁማ) እንዲህ ይላሉ:-
"በመጨረሻው የሌሊቱ ክፍል ወደ ረሱለላህﷺ መጣሁ።እየሰገዱ አገኘኋቸው።እኔም ከኋለቸው ተከትየ መስገድ ጀመርኩኝ።እጄን በመያዝ ጓትተው በሳቸው አቅጣጫ (ሙሉ በሙሉ በሳቸው ትክክል) አቆሙኝ ።ወደ ሰላታቸው ሲገቡ ወደ ኋላ ተመለስኩ።ነብዩﷺ ሰላታቸውን እንደጨረሱ 'በኔ አቅጣጫ ሳረግህ ወደ ኋላ የምትመለሰው ምን ሆነህ ነው' አሉኝ''
ኢማሙ አህመድ በሙስነዳቸው ዘግበውታል ሀዲሱም ሶሂህ ነው።

ሸይኽ ኢማም አልባኒ እንዲህ ይላሉ:-
"ከዚህ ሀዲስ የምንወስደው ቁም ነገር:አንድ ሰው ብቻውን ከኢማም ጋር ተከትሎ ሲሰግድ ሱናው በሱ(በኢማሙ) አቅጣጫ ከኢማሙ ጋር እኩል ሆኖ በቀኝ በኩል መቆም ነው።ወደፊት ሊቀድምም ሆነ ወደኋላ ሊቀር አይገባም።''
سلسلة الصحيحة 2/ص159و160
ሴት ግን በማንኛውም ሁኔታ ከኢማሙ ኋላ ትቆማለች።
ወላሁአዕለም

ሌሎች ፈታዋወች እንዲደርስወ ፔጃችንን ያድርጉ

የቴሌግራም ቻናላችንን ያድርጉ👇👇👇👇
https://t.me/Ftawa_Tube

Address

Bahir Dar

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when AI-Ftawa/አል-ፈታዋ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share