Haim promotion

Haim promotion ሸመታ ሸመታ ይግዙ ይሽጡ

16/05/2021
18/12/2020

አንድ ወጣት የዩንቨርሲቲ ተማሪ ከፕሮፈረሰሩ አስማሪው ጋር መናፈሻው ላይ ቁጭ ብለው ያወራሉ። አስተማሪው ከተማሪዎች ሁሉ ይህን ተማሪ በጣም ስለሚወደው እንደጓደኛው አድርጎ ነው ሚያየው። ፊት ለፊታቸው ጫማውን አውልቆ የመናፈሻውን ፅዶችና ሳሮችን የሚያስተካክል ሰራተኛአለ ፤ ተማሪው የጵዳት ሰራተኛውን እያየ ለአስተማሪው “ቲቸር ዛሬ አንተም እኔም
ደብሮናል ፤ ለምን ያኛውን ሰውዬ ትሪክ አንሰራውም ? ያወለቀውን ጫማ ደበቅ እናርግበትና ጫማዎቹን ሲያጣቸው እንዴት
እንደሚበረግግ እኛም እዛጋ ደበቅ ብለን እንመልከተው” ይለዋል፡፡ አስተማሪውም “ወጣቱ ጓዴ ምንም እንኳ ቢደብረን ድሃዎችን እያሰቃየን እኛ መደሰት የለብንም ፡፡ ባይሆን እኛ ገንዘብ አለን
በገንዘባችን የበለጠ ደስታን ማግኘት እንችላለን ፤ ሂድና ቀስ ብለህ ሰውዬው ሳያይህ ባወለቀው ጫማዎች ላይ ገንዘብ ከተህበት ና ፤ ከዛም ተደብቀን የሚሆነውን እናያለን” አለው።
ተማሪው አስተማሪው እንዳለው ቀስ ብሎ የሰውዬው ጫማላይ በርካታ ገንዘብ ከቶበት መጣና ከአስተማሪው ጋርደበቅ ብለው የሰውዬውን ሁኔታ መከታተል ጀመሩ።
ሰውዬው ፅዳቱን ጨርሶ ኮቱን ለበሰና ጫማውን ለማድረግ ሲታገል ይቆረቁረውና ጎንበስ ብሎ ጫማውን ሲያራግፈው ብሮችን ያገኛል ፡፡ ሰውዬው ደነገጠ!! ዙሪያውን ቢያይ ማንም የለም ፤ ደግሞ ደጋግሞ ቀኝና ግራ ሲመለከት ማንም ሰው የለም፡፡ ሰውዬው በአግራሞት አንገቱን እየነቀነቀ ገንዘቡን ኪሱ ውስጥ ከከተተው በሗላ ሁለተኛ እግሩ ጫማውን ለማድረግ ሲያነሳ በተመሳሳይ ገንዘብ ያገኛል ፤ ሰውዬው አላመነም !! በጉልበቱ
ተንበረከከ አንገቱንም ወደ ሰማይ ቀና አደርጎ ጮክ ብሎ “ጌታዬ የሚስቴን መታመም አውቀህ ነው አይደል ፤ ካንተ ሌላ ማንም እንደማይረዳት አውቀህ ነው አይደል !! የልጆቼ ዳቦ ማጣታቸውን
አይተህ ነው አይደል !! ምስጋና ይግባህ ጌታዬ” አለ። ተማሪው የሰውዬውን ሁኔታ ሲመለከት ልቡን ነካው አይኑ እንቧ አቀረረች ፡፡ አስተማሪውም “ቅድም ካሰብከው ትሪክ ይልቅ አሁን የተሻለ ደስታ እንዳገኘህ አልጠራጠርም” አለው ፤ ተማሪው
እንባውን እየጠረገ “ፕሮፌሰር እስከዛሬ ካስተማሩኝ ሁሉ እንደዚህ ያለ ትምህርት አስተምረውኝ አያውቁም ፤ በህይወቴ የማረሳውን
ትምህርት ነው ያስተማሩኝ ፤ እውነትም ከመቀበል መስጠት የተሻለ ነው” በማለት መለሰላቸው ፡፡ "ደግ ደጉን እናስብ መልካምነት መልሶ ይከፍላልና"

Address

Debre Birhan

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Haim promotion posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share