Ahmed Getachew.አህመድ ጌታቸው

Directions

Ahmed Getachew.አህመድ ጌታቸው ኢትዮጵያ ሀገራችን ድሮም ታላቅ ሀገር ነበረች፤ አሁንም ታላቅ ሀገር ናት ፤ ወደፊትም ታላቅ ሀገር እንደሆነች ትቀጥላለች! ምክያቱም በውስጧ ጀግና ህዝብ ነው ያለው።

የሰላም አማራጭን በመምረጥ ከትጥቅ ትግል በመውጣት ላይ የሚገኙ አካላት እንቅስቃሴ በደባርቅ ወረዳ ተጠናክሮ ቀጥሏል በሰሜን ጎንደር ዞን በደባርቅ ወረዳ በጫካ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች የሰ...
15/09/2026

የሰላም አማራጭን በመምረጥ ከትጥቅ ትግል በመውጣት ላይ የሚገኙ አካላት እንቅስቃሴ በደባርቅ ወረዳ ተጠናክሮ ቀጥሏል

በሰሜን ጎንደር ዞን በደባርቅ ወረዳ በጫካ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች የሰላም አማራጭን በመቀበል እጅ መስጠትን ቀጥለዋል።

በወረዳው ከአሁን በፊትም በርካታ ህገ-ወጥ ታጣቂዎች የሰላም አማራጭን ተቀብለው መግባታቸው ይታወሳል። ዛሬም በወረዳው በምሥራቁ ቀጣና ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 34 ታጣቂዎች የሰላም አማራጭን ተቀብለው መግባታቸውን ተገልጿል።

የሰላም አማራጭ የተቀበሉትን ታጣቂዎች የሀገር መከለካያ ሠራዊት መሪዎች፣ የደባርቅ ወረዳ የሥራ ኀላፊዎች እና የሀገር ሽማግሌዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

የደባርቅ ወረዳ ዋና አሥተዳዳሪ አበባው አዛናው ታጣቂዎቹ ከራሳቸው ባለፈ ለሕዝብ እና መንግሥት የሚጠቅመውን መንገድ መርጠው በመምጣታቸው አመስግነዋል።

በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ገብተውበት የነበረው መንገድ የተሳሳተ መኾኑን ተረድተው ሰላምና ልማት እንዲረጋገጥ ቁርጠኛ በመኾናቸው ሊበረታቱ ይገባል ብለዋል።

አሁን የበደሉትን ሕዝብ ለመካስ የሚያስችል ትክክለኛው ምዕራፍ ላይ መኾናቸውንም ገልጸዋል።

በወረዳው ለሌሎች ወረዳዎች እና አካባቢዎች አርአያ የሚኾን ሥራ እየተሠራ መሆኑን ጠቁመው ይህ አርአያነት ደግሞ በሁሉም አካባቢዎች ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባው ገልጸዋል።

የሰላም አማራጩን የተቀበሉ ታጣቂዎች ሰላማዊ ሕይወት እንዲኖሩ፣ ከሕዝብ እና ከመንግሥት ጎን ተሰልፈው እንዲሠሩ ምቹ ሁኔታዎች እንደሚፈጠሩም ጠቁመዋል።

በአካባቢው የሚንቀሳቀሰው የሀገር መከላከያ ሠራዊት እዝ ዘመቻ መምሪያ ኃላፊ ኮሎኔል ዳምጠው ዘነበ የሰላም አማራጩን የተቀበሉ ታጣቂዎች ለሙያው ቅርበት ባለው መንገድ ተሰማርተው ማገልገል እንደሚችሉ አስገንዝበዋል።

የሰላም አማራጭን የተቀበሉ ታጣቂዎችም ሰላም እና ልማትን ለማረጋገጥ የበኩላቸውን እንደሚወጡ ተናግረዋል።

የህዝብና የሀገር ኩራት! የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት እና የለውጥ ጉዞውየኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የሀገሪቱን ሉዓላዊነትና ሰላም በጸኑ በመጠበቅ የህዝብና የሀገር ኩራት የሆነ ታላቅ ተቋም ነ...
15/09/2026

የህዝብና የሀገር ኩራት! የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት እና የለውጥ ጉዞው
የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የሀገሪቱን ሉዓላዊነትና ሰላም በጸኑ በመጠበቅ የህዝብና የሀገር ኩራት የሆነ ታላቅ ተቋም ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ሰራዊቱን በቴክኖሎጂ፣ በስነ-ልቦና እና በቁሳቁስ የተሟላና ዘመናዊ ሰራዊት ለመገንባት ትልቅ ትኩረት ሰጥተው እየሰሩ ይገኛሉ። የሰራዊቱን አቅም ማሳደግ የሀገርን ሰላም ዘላቂ ለማድረግ ቁልፍ መሆኑን በማመን፣ ተቋማዊ ማሻሻያዎች ተደርገዋል። ሰራዊቱም በውስጥም ሆነ በውጭ ተግዳሮቶች ጊዜ የህዝብንና የሀገርን ደህንነት በመጠበቅ ታላቅ መስዋዕትነት ከፍሏል። ዶክተር አብይ ሰራዊቱ በሰላም ማስከበር ተልዕኮዎች እና በሀገር ውስጥ የልማት ስራዎች ጭምር የነበረውን አርአያነት ያለው ተሳትፎ ሁልጊዜ ያወድሳሉ። የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ዛሬም የህብረ ብሄራዊ አንድነት እና የጽናት ምልክት ሆኖ ቀጥሏል። የዚህ ሀገር አዳኝ ሃይል ጥንካሬ የኢትዮጵያን የነገ ብልጽግና የሚያረጋግጥ ዋስትና ነው።
#ኢትዮጵያ

15/09/2026
 #ጀግናው ይችላል አባ መላ 👇👇
15/09/2026

#ጀግናው ይችላል አባ መላ 👇👇

የኢትዮጵያ የማይናወጥ ከፍታ በአለም ላይ እየታየ ነውኢትዮጵያ በታሪኳ አያሌ ውጣ ውረዶችን፣ የተፈጥሮና የሰው ሰራሽ ፈተናዎችን አልፋ የራሷን ማንነትና ነፃነት ጠብቃ የኖረች ታላቅ ሀገር ናት።...
15/09/2026

የኢትዮጵያ የማይናወጥ ከፍታ በአለም ላይ እየታየ ነው

ኢትዮጵያ በታሪኳ አያሌ ውጣ ውረዶችን፣ የተፈጥሮና የሰው ሰራሽ ፈተናዎችን አልፋ የራሷን ማንነትና ነፃነት ጠብቃ የኖረች ታላቅ ሀገር ናት። የታሪኳ ጥንካሬና የህዝቦቿ ህብረት በማንኛውም ማዕበል ውስጥ አልፈው ሀገራዊ ክብርን ማስጠበቅ እንደሚቻል ለዓለም ያረጋገጠ ነው። ይህ የማይናወጥ መሠረት በዓለም አቀፍ ደረጃ ሀገሪቱ ያላትን ልዩ ስምና ቦታ ሁልጊዜም ከፍ አድርጎ እንዲታይ ያደርገዋል።

በአሁኑ ወቅትም ሀገሪቱ በኢኮኖሚ፣ በዲፕሎማሲና ቀጣናዊ ተጽዕኖዋ በዓለም አቀፍ መድረኮች ላይ ጎልታ እየታየች ይገኛል። የተፈጥሮ ሀብቷን በመጠቀም፣ የውስጥ አቅሟን በማጎልበት እና በአፍሪካ ደረጃ ግንባር ቀደም ሚና በመጫወት የምታደርገው እንቅስቃሴ የከፍታዋ አንዱ ማሳያ ነው። ጥንታዊ ታሪኳ ከዘመናዊ የልማት ጥረቶች ጋር ተጣጥሞ ሲሄድ ሀገሪቱ በዓለም መድረክ ያላትን ተሰሚነትና ተፅዕኖ የበለጠ ያጠናክረዋል።

14/09/2026

የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር አቶ መሀመድ እድሪስ መልዕክት
-----------
ሀገር ለማሽገር በብልሃት መክሮ፣
ትውልድ አስተሳስሮ ሌላ ዓድዋ ሰርቶ፣
ማለፍ መታደል ነው ተከብሮ የመኖርን መሰረት አጽንቶ!

ውድ ኢትዮጵያውያን! ለዘመናት የቆዩ መሠረታዊ ሀገራዊ ችግሮቻችንን በሰለጠነ መንገድ በውይይት እና በምክክር ለመፍታት የተጀመረውን ታሪካዊ የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ሂደት በሰላም፣ በታማኝነት፣ በታላቅ የኃላፊነት ስሜት እና በኢትዮጵያዊ ጨዋነት በማጠናቀቃችን እንኳን ደስ አላችሁ! እንኳን ደስ አለን!

ሀገሬ የመከረችበት ጉባኤ የሕዝባችንን አሸናፊነት፣ የኢትዮጵያን ታላቅነት፣ የራስን ችግር በራስ የመፍታት ጥበብ እና የዓላማ አንድነትን በገሃድ ለዓለም ዳግም ያሳየ አዲስ የሽግግር ተስፋ ምዕራፍ አመላካች ደማቅ ድል ነው። ስለሆነም በምክክሩ የተገኙ የጋራ መግባባቶችን እና የሰላም ፍሬዎችን መንከባከብ እንዲሁም መጠበቅ የሁላችንም የጋራ ኃላፊነት ነውና ተባብረን የነገዋን ጠንካራ፣ የበለጸገች እና ሁለተናዊ ሰላሟ የተጠበቀ ኢትዮጵያን መሠረት እናጽና።

በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ! እንኳን ደስ አለን!

Wise dialogue moves a nation forward, connects generations, and builds a strong foundation for living with dignity. Creating another historic milestone like Adwa is a true blessing for us all.

My dear fellow citizens, Congratulations to everyone as we complete the historic National Dialogue Conference in peace, integrity, responsibility and Ethiopian civility. This effort successfully resolves our long-standing national challenges through peaceful and civilized discussion.

This national conference is a great victory that marks a new chapter of hope. It shows the world the triumph of our people, the greatness of Ethiopia, the wisdom to solve our own problems and our shared purpose. Protecting these agreements and the fruits of peace is our common duty. Let us work together to build a strong, prosperous and peaceful Ethiopia for tomorrow.

Once again, Congratulations to you and to us all!

Address

Dessie

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ahmed Getachew.አህመድ ጌታቸው posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category