Flying Pages - በራሪ ቅጠሎች

Flying Pages - በራሪ ቅጠሎች We are the bridge to fill the gap between where you are now and where you want to be!
እኛ አሁ?

በነጻ የምንሰጣቸው ዋና ዋና አገልግሎቶች:
 የግለሰባዊ ልህቅና መጽኃፍቶች ማጠቀላያ
 የስነልቦና መጽኃፍቶች ማጠቀላያ
 የአዕምሮ ማስተካከያ መጽኃፍቶች ማጠቀላያ
 በዙሪያችን የሚገኙ ስኬታማ ሰዎችን ተሞክሮ ማጋራት
 ብሪጅ የስኬት ጉርሻዎች
 የግለሰብ ገንዘብ አስተዳደር

https://youtu.be/VxhGyqLI-Nc
11/11/2022

https://youtu.be/VxhGyqLI-Nc

Authorized by the Napoleon Hill Foundation, these rare audio recordings were provided to us under license for exclusive distribution on YouTube. Financial pr...

01/11/2022

ሀብም ሰዎች ለህልማቸው ቁርጠኛ ሲሆኑ ድሃ ሰዎች ህልማቸውን ብቻ ያልማሉ፡፡
ድሃ አዕምሮ ስለህልሞች ብቻ እንዲያልም ተለማምዷል፡፡ ምክንያቱም ምንም አያስወጡትም፡፡ ግን በቁስ አካል ለመግለጥ ከፈለገ ዋጋው ጠንክሮ መስራት ነው፡፡
ሀብታም አዕምሮ ትልቅ ነገር ለማለም ብቻ ሳይሆን ወደ ህልሙ ለመድረስ ትለቅ ተግባራዊ ርምጃ ለመውሰድ ቁርጠኛ ነው፡፡

21/10/2022

አስማታዊ ጤና
“ታላቁ ሀብት ጤና ነው፡፡”
ቪጊል “70 – 19 ዓ.ዓ.)
ሮማዊ ገጣሚ
ጤና በህይወት ውስጥ እጅግ በጣም ውዱ ነገር ነው፡፡ ይሁንና ከማንኛውም ነገር በላይ ጠናችንን ለስጦታ ወስደነዋል፡፡ ለአብዛኛዎቻችን፣ ስለጤናችን የምናስብበት ብቸኛው ጊዜ ስናጣው ብቻ ነው፡፡ ጤና ከሌለን ምንም ነገር የለን የሚለው ዕውነታ የራስ ምታታችን ይሆናል፡፡
ለብዙሃኑ ስለጤና የሚናገር አንድ የጣሊያን አባባል አለ፡ “ምንም እንኳ ባያውቀውም ጤና ያለው ሰው ሀብታም ነው፡፡” ጤናማ ሆነን አልፎ አልፎ ስለጠናችን ስናስብ፣ ቀለል ባሉ እንደ ጉፋን፣ ኢንፉሎይንዛ ስንያዝና አልጋ ላይ ስንውል፣ የእነዚህ ቃላት ዕውነታ ይሰማናል፡፡ ጤናማ ባልሆንክ ጊዜ፣ አብዝተህ የምትሻው ነገር እንዲሻልህ ብቻ ነው፡፡ ጤናህ ከመመለሱ በላይ የሚያሳስብህ ነገር አይኖርም፡፡
ጤና የህይወት ስጦታ ነው፡፡ በየቀኑ የምታገኘውና ማግኘትህን የምትቀጥለው ነገር ነው፡፡ ጤናማ ለመሆን ከምናደርገው ማንጫውም ነገር በተጨማሪ ጤናችንን ማግኘት እንድንቀጥል ስለጤናችን ማመስገን ይገባናል፡፡
አስታውስ፡
“ለእነዚያ ለሚያመሰግኑት (ስለጤናቸው) አብዝቶ ይሰጣቸዋል፤ የተትረፈረፈም ይኖረዋል፡፡ ለእነዚያ ለማያመሰግኑት (ስለጤናቸው) ካላቸው ተቀንሶ ላይ ይወሰድባቸዋል፡፡”
ምናልባትም ጤናማ የአኗኗር ስልት የመረጡ ግን ጤናቸውን ያጡ ሰዎችን ታውቅ ይሆናል፡፡ ለምታገኘው ጤና ምላሽ ምስጋና ማቅረብ ታላቅነት ነው፡፡ ስለጤናህ አመስጋኝ ስትሆን አሁን ባለህበት ጊዜ ብቻ ያለውን ጤናህ አይደለም የምታገኘው ግን በተመሳሳይ ሰዓት ወደ አንተ ያለውን የጤና ፍሰት የሚጨምረውን አስማት ወደ ስራ ታስገባዋለህ፡፡ የጤናህንም መሻሻል ሲጀምር በትክክል ታያለህ፡፡ ትንንሽ ምታቶችና ህመሞች፣ ቁርጠቶች፣ ጭረቶችና ምልክቶች በአስማቱ መጥፋት ሲጀምሩ ታስተውላለህ፡፡ ደስታህም በእጅጉ ይጨምራል፡፡
ቀጣይ ባለው ልምምድ የምትማረው ሆኖ በጤና የዕለት ተዕለት የምስጋና ለምምድህ ውስጥ ዕይታህን፣ የመስማት ችሎታህነን እና ሁሉንም የስሜት ህዋሳቶችህን፣ በመላ አካላትህ ውስጥ ያሉ ተግባራን ጨምሮ ማሻሻል ትችላለህ፡፡ ሁሉም ነገር የሚከሰተው እንደ አስማት ነው፡፡
“ምስጋና ቫክሲን ፣ አንቲቶክሲን እና አንቲስፕቲክ ነው፡፡”
ጆን ሄነሬ ጆወልት (1864 – 1923)
የፕረስባይተሪያን ሰባኪና ጸኃፊ
ጤናህ አስማታዊበሆነ መንገድ የሚጨምርበት መጠን ትክክለኛው መለኪያው ስለጤናህ በምታቀርበው ምስጋና የሚኖርህ የአመስጋኝነት ስሜት መጠን ነው፡፡ አምጋኝ ያልሆንክበት መጠን ደግሞ ጤናህ የሚቀንስበት ትክክለኛ ልኬት ነው፡፡ በየዕለቱ ከሚቀንስ ጤና ጋር መኖር ማለት ኃይልህ፣ ጥንካሬህ፣ በሽታን የመከላከያ ስርዓትህ፣ የሀሳብ ጥራትህ፣ በአካልህና በአዕምሮህ ውስጥ ያለ ሌላ ማንኛውም ተግባር እየተዳከመ ነው ማለት ነው፡፡
ስለጠናህ አመስጋኝ መሆን የምታመሰግንበት ተጨማሪ ጤና የምታገኝበትን ዋስትና ይሰጥሃል፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ በአካልህና በአዕምሮህ ውስጥ ያለ ጭንቀትና ውጥረት ያጠፋልሃል፡፡
ሳይንሳዊ ጥናቶች የሚያሳዩት ጭንቀትና ውጥረት የብዙ በሽታ ስሮች እንደሆኑ ነው፡፡ በተጨማሪም ጥናቶች ምስጋናን የሚተገብሩ ሰዎች በፍጥነት እንደሚደኑና ተጨማሪ ሰባት ዓመታትን እንደሚኖሩ አጋልጠዋል፡፡
ምን ያክል አመስጋኝ እንደነበርክ አሁን ባለህ የጤና ሁኔታ ማየት ትችላለህ፡፡ መጫጫን የሚሰማህና ህይወት ትግል መስላ ከታየችህ ወይም ከዕድሜህ በላይ የወጣትነት ስሜት ካልተሰማህ፣ እየኖርክ ያለኸው በሚቀቀንስ ጤና ነው፡፡ የዚህ የታላቅነት ስሜት ማጣት ዋናው ምክንያት አንዱ የምስጋና እጥረት ነው፡፡ ምንም እንኳ ለጤንነትህ የምስጋናን አስማታዊ ኃይል ብትጠቀምም ሁሉም ነገር የሚያወራው ስለ መለወጥ ነው፡፡
የጤና አስማታዊ ልምምድ የሚጀምረው ስለሰውነትህ ጤንነት የቀረበውን የሚከተለውን አንቀጽ በማንበብ ይጀምራል፡፡ ስለአንዱ የአካል ክፍልህ የቀረበውን መስመር ካነበብክ በኋላ አይንህን ጨፍንና የተሰመረውን ዓ/ነገር በአዕምሮህ ድገም፡፡ ለዚያ የሰውነትህ ክፍል የቻልከውን ያህል የአመስጋኝነት ስሜት ይሰማህ፡፡ በጣም ጠልቆ ከተሰማህ በሰውነትህ ላይ አስደናቂ ውጤቶችን በፍጥነት ማየትና ስሜቱም ሊሰማህ ይችላል፡፡
ስለግርህ አስብ፤ በህይወትህ ውስጥ ዋና የመጓጓዥያ ዓይነቶችህ ናቸው፡፡ እግሮችህን የምትጠቀምባቸውን ነገሮች በሙሉ አስብ፣ እነደ ሚዛንህን መጠበቅ፣ ለመቆም፣ ለመቀመጥ፣ እንቅስቃሴ ለመስራት፣ ለመደነስ፣ ደረጃ ለመውጣት፣ መኪና ለመንዳት፣ በአብዛኛው ለመራመድ ተዓምር . . .እግሮችህ በቤትህ ዙሪያ ለመሄድ፣ ወደ መታጠቢያ ቤት ለመሄድ፣ ወደ ኩሽና ገብተህ ለመጠጣት፣ እና ወደ መኪናህ ለመሄድ ያስችሉሃል፡፡ እግሮችህ ወደ መደብር፣ በመንገዱ ዳር፣ በአየር መንገድ ውስጥ፣ በወደቡ አካባቢ ለመሄድ ያስችሉሃል፡፡ የመራመድ ችሎታችን በህይወት ለመደሰት ነጻነት ሰጥቶናል፡፡ እግሮቼ አመሰግናችኋለሁ በል፡፡ የዕውነት በለው፡፡
ስለእጆችህ እና ምን ያህል ነገሮችን በአንድ ቀን ብቻ እንደምታነሳና እንደምትይዝ አስብ፡፡ እጆችህ በህይወትህ ውስጥ ዋና መሳሪያዎች ናቸው፡፡ እጆችህ ለመጻፍ፣ ምግብ ለመብላት፣ ስልክህን ወይም ኮምፒውተርህን ለመጠቀም፣ ገላህን ለመታጠብ፣ ልብስህን ለመልበስ፣ መጸዳጃ ቤት ለመጠቀም፣ ነገሮችን ለማንሳትና ለመያዝ፣ እና ነገሮችን በራስህ ለማድረግ ያስችሉሃል፡፡ እጆችህን ሳትጠቀም ነገሮችን እንዲያደርጉልህ በሌሎች ሰዎች ላይ ጥገኛ ትሆን ነበር፡፡ እጆቼ፣ ክናዶቼ እና ጣቶቼ አመሰግናችኋለሁ በል፡፡
ስለአስደናቂ የስሜት ህዋሳቶችህ አስብ፡፡ የመቅመስ ህዋስህ ቀኑን ሙሉ ስትመገብና ስትጠጣ ርካታን ይለግስሃል፡፡ በጉፋን ምክንያት የመቅመስ ስሜትን የማጣትን ነገር ታውቀዋለህ፡፡ ምግብና መጠጦችን ያለመቅመስ ስሜት የመብላትና የመጠጣት ደስታው ይጠፋል፡፡ ለአስደናቂው የመቅመስ ስሜቴ አመሰግናለሁ በል!
የማሽተት ስሜትህ የህይወትን አስደናቂ መዓዛ ለማወቅ ያስችልሃል፡፡ የአበቦች፣ የሽቶዎች፣ ምግብ ሲጠበስ፣ በበጋ ምሽት የሚነድ እሳት፣ በክረምት ወራትአየሩ፣ አድስ የታጨዱ ሳሮች፣ ከዝናብ በኋላ የመሬት ሽታ፣ … የህይወት ማዕዛዎች፡፡ ለድንቁ የማሽተት ስሜቴ አመሰግናለሁ በል፡፡
የመዳሰስ ስሜት ባይኖርህ ቀዝቃዛን ከሞቃት፣ ሸካራን ከለስላሳ፣ ወይም ጠንካራን ከደካማ መለየት አትችልም ነበር፡፡ ነገሮችን መረዳት፣ ፍቅርን አካላዊ በሆነ መንገድ መስጠትና መቀበል አትችልም ነበር፡፡ የመዳሰስ ስሜትህ የምትወዳቸውን ሰዎች በመዳሰስ ፍቅርህን/መውደድህን ማረጋገጥ ያስችልሃል፡፡ ከአንድ ሰው ወደ ሌላው ሰው የእጅ ዳሰሳን ስሜት መስማት በህይወት ውስጥ እጅግ በጣም ድንቁ ነገር ነው፡፡ ለድንቁ የመዳሰስ ስሜቴ አመሰግናለሁ በል፡፡
የምትወዳቸውን ሰዎችና የጓደኞችህን ፊት ማየት፣ መጽኃፍትን፣ ጋዜጦችን እና ኢሜይሎችን እንድታነብ፣ ቴሌቪዥን እንድታየ፣ የተፈጥሮን ውበት እንድታስተውል፣ እና ከሁሉም በላይ ደግሞ በህይወትህ ውስጥ ያሉ መንገዶችን እንድታይ ያስቻሉህን የአይኖችህን ተዓምር አስብ፡፡ በአይኖችህ ላይ የአይነርግብ (የማያሳይ) ለአንድ ሰዓት አድርግና ዘወትር የማተደርገውን ነገር ለማድረግ ሞክር፣ ከዚያም አይኖችህን ታደንቃቸዋለህ፡፡ ሁሉን ማየት ያስቻለኝን አይኔን አመሰግናለሁ በል፡፡
የራስህን እና የሌሎች ሰዎችን ድምጽ እንድትሰማና ከሰዎች ጋር እንድትግባባ ያስቻለህን ጆሮህን አስብ፡፡ ያለ ጆሮና ያለመስማት ስሜት ስልክ መጠቀም፣ ሙዚቃ ማዳመጥ፣ ሬዲዮ ማዳመጥ፣ የምትወዳቸውን ሰዎች ንግግር፣ ወይም በዙሪያህ ያሉ የዓለም ድምጾችን መስማት ፈጽሞ አይቻልህም ነበር፡፡ ማስማቴን አመሰግነዋለሁ በል፡፡
በእያንዳንዱ የስሜት ህዋሳትህ በሰከንድ ውስጥ የሚሰበሰበውን በሚሊዮን የሚቆጠር መለዕክት የሚተነትነው አዕምሮ ባይኖርህ ኖሮ አንዳቸውንም የስሜት ህወሳቶችህን መጠቀም አትችልም ነበር፡፡ በርግጥ ህይወትን እንድታውቅና እንድትኖር የሚያደርግህ አዕምሮህ ነው፡፡ አዕምሮን የሚመስል አንድ ኮምፒውተር በአለም ላይ የለም፡፡ ለድንቁ አዕምሮየ እና አንጎሌ ምስጋና ይገባው በል፡፡
ለጠናህ፣ ለአካልህና ለህይወትህ በማያቋርጥ ሁኔታ በቀን ለ24 ሰዓት በሳምንት ለ7 ቀናት የሚሰሩትን በትሪሊዮን የሚቆጠሩ ህዋሳቶችህን አስብ፡፡ ህዋሳቶቼ አመሰግናችኋለሁ በል፡፡ በሰውነትህ ውስጥ ማንኛውንም ነገር የሚያጣሩትን፣ የሚያጸዱትንና የሚያድሱትን፤ ህይወትህን የሚያስቀጥሉትን የአካል ክፍሎችህን አስብ፡፡ ስራቸውን ስለመስራታቸው እንኳ ሳታውቅ በራሳቸው ፈቃድ ሁሉንም ተግባራቸውን ስለመስራታቸው አስብ፡፡ በትክክል ስለምትሰሩ የአካል ክፍሎቼ አመሰግናችኋለሁ በል፡፡
ግን በሚያስደንቅ ሁኔታ በሰውነታችን ውስጥ ካለ የስሜት ህዋሳት፣ የአካል ክፍልና ስርዓት በላይ የልብ ስራን አስብ፡፡ ልብህ በሰውነትህ ውስጥ ያለውን ሁሉንም ክፍሎች ህይወት ያስተዳድራል፡፡ ምክንያቱም ልብህ በሰውነትህ ውስጥ ያለውን ስርዓት ህይወት ያቆያል፡፡ ጠንካራውና ጤናማው ልቤ አመሰግንሃለሁ በል፡፡
ቀጥሎ፡ ቁራጭ ወረቀት ወይም ካርድ ያዝና በወፍራሙና በትልቁ የሚከተለውን ጻፍ፡
የጤና በረከቶች በህይወት እንድቆይ ረድተውኛል፡፡
ዛሬ ካርዱን ከአንተ ጋር ያዘው፡፡ በአብዛኛው ልታየው ከምትችልበት ቦታ ላይ አስቀምጠው፡፡ በጠረንጴዛ ላይ የምትሰራ ከሆነ ከፊት ለፊትህ አስቀምጠው፡፡ ሹፌር ከሆንክ፣ በአብዛኛው ልታየው ክምትችልበት ቦታ ላይ ከመኪናህ ውስጥ አስቀምጠው፡፡ በአብዛኛው ቤት ውስጥ የምትቆይ ከሆነ እጆችህን የምትታጠብበት ቦታ፣ ወይም ስልክህ አቅራቢያ ማስቀመጥ ትችላለህ፡፡ የጻፍካቸውን ቃላቶች በአብዛኛው በግልጽ ሊያሳይህ የሚችል ቦታ ምረጥ፡፡
ዛሬ ቢያንስ በአራት የተለያዩ አጋጣሚዎች ቃላቶቹን ስታያቸው ቀስ ብለህ በአንድ ጊዜ አንድ ቃል አንብብ፡፡ ለተሰጠህ የጤና በረክት የቻልከውን ያክል የአመስጋኝኘት ስሜት ይሰማህ፡፡
ስለጤናህ አመስጋኝ መሆን ጤናህን ለመጠበቅ እጅግ በጣም ጠቃሚ ነው፡፡ ግን ደግሞ ጤናህ የተሻለ ሆኖ እንዲቀጥል፣ ከሚያድግ ኃይል እና ከህይወት ጣዕም ጋር ዋስትና ይሰጣል፡፡ ምስጋና ከተለመደው ህክምና ጋር አብሮ ጥቅም ላይ የሚውል ከሆነ የጤና አብዮት እናያለን፡፡ ከዚህ ቀደም ባልታየ ሁኔታ እንደማዕበል የማገገም ፍጥነትና ተዓምራት እናያለን፡፡

የአስማት ልምምድ ቁጥር አራት፡
አስማታዊ ጤና፡
1. የአስማት ልምምድ ቁጥር 1 - በረከቶችህን መቁጠር፡ ከ1 – 3 ያሉትን ቅደም ተከተሎች ድገም፡፡ የአስር በረከቶችን ዝርዝር አዘጋጅ፡፡ ስለምን ምስጋና ማቅረብ እንዳለብህ ምክንያቱን ጻፍ፡፡ ዝርዝርህን እንደገና አንብብ፡፡ በእያንዳንዱ በረከት መጨረሻ ላይ “አመሰግናለሁ፣ አመሰግናለሁ፣ አመሰግናለሁ” በልና ስለበረከቱ የቻልከውን ያህል የአመስጋኝነት ስሜት ይሰማህ፡፡
2. በአንድ ገጽ ወረቀት ላይ ወይም ካርድ ላይ “የጤና በረከቶች በህይወት እንድቆይ ረድተውኛል፡፡” የሚለውን ቃል ጻፍ፡፡
3. ቃላት የተጻፈባትን ወረቀት ዛሬ በአብዛኛው ጊዜ የምታይበት ቦታ ላይ አስቀምጥ፡፡
4. ቢያንስ ለ4 የተለያዩ አጋጣሚዎች ቃላቶችን ቀስ ብለህ አንብባቸው፡፡ ለተሰጠህ ውድ የጤና በረከት የቻልከውን ያክል አመስጋኝ ሁን፡፡ ስሜቱም ይሰማህ፡፡
5. ከመተኛትህ በፊት የአስማት ዓለትህን በአንድ እጅህ ያዝ እና በቀኑ ውስጥ ለተከሰተው መልካም ነገር “አመሰግናለሁ” የሚለውን የአስማት ቃል በል፡፡

20/10/2022

አንዳንድ ሰዎች አንተ የምትሰራው ነገር አልገባ ሲላቸው ሀሳብህን ለመበተን (Try to distract you) ይሞክራሉ፡፡ ነገር ግን ጅማሬህ የቱንም ያህል ትንሽ ቢሆን፣ መድረሻህ የቱንም ያህል ቢርቅ ጉዞህን አታቋርጥ! በእንደነዚህ ዓይነት እባቦች ሀሳብህ እንዳይበተን መዳረሻህ ላይ ትኩረት አድርግ! አንዳንዴ ስለማንነታቸው ስትጠይቅ ….. ከምታይባቸው ምግባር ጋር የሚጣጣም የኋላ ታሪካቸውን ታገኛለህ፡፡ ጉዞህ ወደፊት ብቻ ይሁን!
ምንጭ፡ ከህይወት ተሞክሮ
🤪🤪🤪🤪🤪🤪🤪🤪🤪🤪🤪🤪🤪🤪🤪🤪🤪🤪🤪🤪

ባህላዊ ህክምና ምን ያክል አስተማማኝ ነው ሀጂ ያሲን መልስ አላቸው! ለበለጠ መረጃ +251910038265 ላይ ይደውሉ! ከልብ እናገለግልዎታለን!!
19/10/2022

ባህላዊ ህክምና ምን ያክል አስተማማኝ ነው ሀጂ ያሲን መልስ አላቸው! ለበለጠ መረጃ +251910038265 ላይ ይደውሉ! ከልብ እናገለግልዎታለን!!

ሃጂ የባህል የባህል ህክምና በደሴ ከተማ፣ በመናፈሻ ክፍለ ሰሜን ካፌ ወደ ውስጥ 100 ሜትር ገባ ብሎ የሚገኝ የህክምና ማዕከል ነው፡፡ ይህ የህክምና ማዕከል በዘመናዊ ህክምና መፍትሄ ያልተ....

25/07/2022

🔥 Success doesn't happen by CHANCE. It happens by CHANGE. 🔥⁣⁣⁣⁣

Address

Dessie

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Flying Pages - በራሪ ቅጠሎች posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Flying Pages - በራሪ ቅጠሎች:

Shortcuts

Share

Category