17/07/2025
~~~መጻሕፍትን የማሰባሰብ ዘመቻ~~~
❤መጻሕፍቱ የሚሰባሰቡት ለማን ነው?
በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ በአዊ ሀገረ ስብከት በጓ/ሽ/ወረዳ የቲሊሊ ደብረ ብሥራት ቅዱስ ሚካኤል አርዕስተ አበው የመጻሕፍት ትርጓሜ ትምህርት ቤት ነው። ይህ ጉባኤ ቤት ከዚህ ዓመት ጀምሮ ደቀ መዛሙርትን ተቀብሎ በማስተማር ላይ ይገኛል።
❤ጉባኤ ቤቱ የተጀመረው በቲሊሊ ደብረ ብርሃን ቅዱስ ሚካኤል ሰበካ ጉባኤ አርቆ አሳቢነት ታሪክን ሀገርንና ቤተክርስቲያንን ለትውልድ ለመጠበቅና ለትውልድ ለማስተላለፍ ትውልድ ላይ መሥራት፣ ትውልድ ላይ ለመሥራት ደግሞ የመጻሕፍት ትርጓሜ ትምህርት ቤት አስፈላጊ መሆኑን በመገንዘብና ለወጣቶች፣ ለመንፈሳዊ ማሕበራትና ለቤተክርስቲያን የቁርጥ ቀን ልጅ የሆኑ ታላላቅ አባቶችን በማማከር ሲሆን ከጅማሮው ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ እንደ እግዚአብሔር መልካም ፈቃድ ያለ አቅሙን አሟጦ እየተንቀሳሰ ይገኛል።
❤ጉባኤ ቤቱ ጀማሪ እንደመሆኑ ያቀዳቸውን ዘርፈ ብዙ ጉዳዮችን ለማከናወን ዘርፈ ብዙ ግብአቶችም ያስፈልጉታል። ከእነዚህም መካከል
፩. መንፈሳዊ መጻሕፍት
፪. የታሪክ፣ የልብ ወለድ፣ የሥነ ልቡና መጻሕፍት
፫. የሳይንስ፣ የቅኔ፣ የዜማ መጻሕፍት
፬. ንጽጽር ለመሥራት እንዲያመች የሌላ እምነት ሰዎች የጻፏቸው መጻሕፍት
፭. የኤሌክትርኒክስ እቃዎች ኮምፒውተር፣ ፕሮጀክተር፣ ስልክና መሰል እቃዎች።
፮. ሌሎች ቁሳቁሶች፦ የመጻሕፍት መደርደሪያዎች፣ የቤተ መጻሕፍት ወንበሮችና የመሳሰሉት ቅድሚያ የሚሰጣቸው ናቸው።
❤ጉባኤ ቤቱን ለመደገፍ የምትፈልጉ በሙሉ በሚከተሉት አማራጮች መደገፍ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
1ኛ፦ በጉባኤ ቤቱ አካውንት መደገፍ የምትችሉትን ገንዘብ አስገብታችሁ ጉባኤ ቤቱ የሚያስፈልጉትን መጻሕፍት በቅናሽ ዋጋ ተስማምቶ መግዛት እንዲችል መርዳት፤
2ኛ፦ መጻሕፍትን መግዛትና አንብባችሁ ያስቀመጣችሁትን ማንኛውንም ዓይነት መጻሕፍት መስጠት
❤በጉባኤ ቤቱ ስም የተከፈቱ የባንክ ቊጥሮች፦
↪ ንግድ ባንክ፦1000708001094
↪ አቢሲኒያ፦227710489
↪ ዐዋሽ፦ 013201564641701
(አርዕስተ አበው የመጻሕፍት ትርጓሜ ቤት)