Team Dawah Gonder

Team Dawah Gonder Calling peopl to Islam

21/02/2016

ሰዎች ልባቸው ይቀያየራል። ዛሬ የወደደህ ልብ ነገ ይጠላሀል። አላህ ከወደደህ የሰዎችን ዉዴታ ይለግስሀል።ስለሆነም፤ የሰዎችን ውዴታ ማግኘት ያንተ ግብ አይሁን። አንተ እንደፈለከው ሳይሆን፤ በአላህ እንደታዘዝከው ቀጥ በል!

09/12/2015

አንድ የአሜሪካ ፓርክ ውስጥ የሆነ አንበሳ የፓርኩን አጥር በማለፍ አንድን ጨቅላ ልጅ ሊነክስ ሲንደፈደፍ አንድ ያልታወቀ ሰው ያንን አንበሳ ግንባሩን ብሎ ይገድለዋል።… ከዛ ዜናውን ሚዲያዎች ተቀባበሉት« አንድ የሀገራችን ጀግና ጨቅላውን ልጅ ከአንበሳ ጥቃት አስጣለው!! » … ተብሎ ሲዘገብ ፣ ሰውዬው የሌላ አገር ዜጋ መሆኑን ተናገረ… ዜናው እንዲህ ተስተካከለ«አንድ ቱሪስት ጨቅላውን ልጅ ከአንበሳ ጥቃት አስጣለው!! »……… በዚህ መሃል ሰውዬው ስለሃይማኖቱ ሲጠየቅ "ሙስሊም ነኝ!" አለወዲያውኑ ዜናው እንዲህ ተዘገበ::::::::«አንድ መሳሪያ የታጠቀ ሙስሊም አሸባሪ ወደ ፓርክ ገብቶ ከልጆች ጋር ሲጫወት የነበረውን አንበሳ በአሰቃቂ ሁኔታ ረሸነው!! »

19/10/2015

ነብያችን (ሠ.አ.ወ) በቤታቸው እሳት ሳይነድ (ምግብ ሳይበስል)
ቀናት ያልፍ ነበር፡፡ ብዙ ጊዜያት እንደተራቡ ወደ መኝታቸው
ተጉዘዋል ፡፡ አንድ ቀን ኡመር (ረ.አ) ወደ ረሱል (ሠ.አ.ወ) ቤት
መጡ፡፡ ወደ ውስጥ ሲገቡም ነብዩ ከቴምር ቅጠል ከተሰራ
ፍራሽ ላይ ተኝተው ነበር፡፡ ደረቆቹ የቅጠል ጠርዞች በውድ
የነብያችን (ሠ.አ.ወ) ሰውነት ላይ ሰንበሮችን አውጥተዋል ፡፡
በአንድ ጥግ ትንሽ ደቄትና ውሃ አዩ፡፡ ከነዚህ ነገሮች በቀር
በቤት ውስጥ ፈፅሞ አንድም ነገር የለም፡፡ በዚህ ወቅት ታድያ
መላው አረቢያ በነብያችን (ሠ.አ.ወ) አስተዳደር ስር ነበረች፡፡
ኡመር እጅግ ደነገጡ፡፡ እምባቸውንም ማቆም አልቻሉም፡፡
ነብያችን (ሠ.አ.ወ) "ኡመር ሆይ! ለምን ታለቅሳለህ?” ሲለ
ጠየቁት፡፡ ኡመርም (ረ.አ) እንዲህ ሲሉ መለሡ፡- " እንዴት
አላለቅስ የአላህ መልዕክተኛ! የሮምና የፉርሺያ ንጉሶች በምቾት
ሲንደላቀቁ የአላህ መልዕክተኛ ከቴምር ዛፍ ቅጠል የተሰራ ደረቅ
ፍራሽ ላይ ይተኛል !” ነብያችን (ሠ.አ.ወ) እንዲህ አሉት ፡-
"ኡምር ሆይ! ቄሳርና የፋርስ ንጉስ በዚህች አለም ይደሰቱ፤ ለኛ
ግን የቀጣዩ አለም ደስታ በቂያችን ነው፡፡!" ቀጥለውም፡- "ይህ
አለም ለኔ ከቶ ምን ያደርግለኛል ! የኔና የዚህች አለም ግንኙነት
እንደ በጋ መንገደኛ ነው፡፡ ከዛፍ ጥላ ስር አረፍ ብሎ ሲነጋ
መልሶ እንደሚጓዘው፡፡" ( ቲርሚዝ)
ፊዳከ አቢ ወኡሚ ያረሱሉላህ

17/10/2015

አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱ።
"የቂያማ ለት ማን ይሸከምልኛል"
አንድ ጊዜ ዑመር ቢን አልኸጧብ ዞር ዞር እያሉ የሙስሊሞችን ቤት እየጐበኙ ነው።መዲና ከተማ ውስጥ ከሩቅ እሳት ሲነድ ያዩና ሰው መኖር አለበት ብለው ወደዚያው ይሄዳሉ።አንዲት ሴትዬና ህፃናት ተቀምጠዋል።ህፃናቱ እያለቀሱ ነበር።ሴትየዋ ውሀ በእሳት ላይ ጥዳ እያፈላች ነው።ህፃናቱ ያለቅሳሉ ዑመር ጠጋ አሉና ሰዎች መምጣታቸውን እንዲያውቁ ጎሮሮቸውን እንደመጥረግ አድርገው ድምፅ አሰሙ።መልስ አላገኙም።ኡመር እንዲህ አሉ"ቤቶች!ቀረብማለት እችላለሁ?"አቤት ይቻላል" አለች ሴትየዋ "ምን ሆናችሁ ነው? ህፃናቱ ለምን ያለቅሳሉ?" ሲሉ ዑመር ጠየቁ ሴትየዋ ወላሂ እኛ መንገደኞች ነን ምንም የሚበላ የለንም አለቻቸው የተጣደው ውሀ ምንድን ነው ምንም ነገር የለውም ዝም ብዬ ልጆቹ እንቅልፍ እስኪወስዳቸው እያባበልኩበት ነው። ዑመር መሆናቸውን ስላላወቀች ቀጥላ እንዲህ አለች ዑመር ስለሁኔታችንቢያቁ ኖሮ እንዲህ አንሆንም ነበር።ዑመርም ጥቂት ጠቢቂኝ ብለዋት ሄዱ የረፈዕ የሚባል አገልጋያቸው የሆነ ትንሽ ልጅ ከዑመር ጋር አብሮ ተከተላቸው።እስኪ በይተልማል ድረስ ተከተለኝ አሉት ፈጠን ፈጠን እያለ ቢከተላቸውም ከርሳቸው እኩል መሪመድ አልቻለም።ዑመርም በይተል ማል ደረሱና በዱቄት የተሞላ ከረጢት አውጥተው በጀርባቸው ተሸከሙት። ምግብና ገብስ ጨምረው ያዙ።አሚረል ሙእሚን እኔ ልሸከምሎት አላቸው አገልጋያቸው ።ዑመርም "የቂያማ ቀን ማን ይሸከምልኛል" አሉ የረፈእ ና አብረህኝ ሁን ሁሉንም ነገር ሲያዘጋጁ አግዛቸዋለሁ በማለት እየተከታተሉ ወጡ።ከሴትየዋ ጋር ሆነው ምግብ በጋራ ያዘጋጁ ጀመር።የሚሰሩትን ስራ ሁሉ አገዟቸው።እሳት በትንፋሻቸው እንዲቀጣጠል እስከማድረግ ደረሱ።የተከበሩ ታላቁ ኡመር።ህፃናቱንም እያጎረሱ መገቧቸው።ይህን ሁሉ አድርገው ሲጨርሱ ለሴትየዋ እንዲህ አሏት ሲነጋ አሚረል ሙእሚኒን ዘንድ እንድትመጪ ምን አልባት እዚያ ታገኚኝ ይሆናል ብለዋትሊወጡ ሲሉ "ወላሂ! አንተ ከዑመር የተሻልክ ሰው ነህ ።ወላሂ ስልጣኑ ቢኖረኝ ኖሮ በዑመር ቢን አልኸጧብ ቦታ በሾምኩህ ነበር" ኡመርመሆናቸውንአላወቀችምነበር።
ያአላህ የነዚህን ምርጥ ትውልድ ፈለግ ምንከተል አድርገን አሚን !!!

28/08/2015

እናትህን ወይም አባትህን ሣትሣደብ በፍቅር እና በርህራሄ ከቢድዓ እንደምታስጠናቅቀው ሌሎች ወገንህን እንዲሁ ከቢድዓ አስጠንቅቃቸው።
እየሠደብክ ወይም ሥም
እየለጠፍክለት ከሡና አታስበርግገው።
ሡና የቡድን ስም ሣይሆን የነብዩ የህይወት ድርጊት ባጠቃላይ ነው።

  legna metkakmiya tefterchi gen negru teglbtena egna dunyan magelgel jemren   dunya ayedlchim ye Muslimoch hager allah ...
27/08/2015

legna metkakmiya tefterchi gen negru teglbtena egna dunyan magelgel jemren dunya ayedlchim ye Muslimoch hager allah lebariyawoch mert bota azgajitual alah yewfken ;( ;( ;( ;(

26/08/2015

አቡ ሁረይራ በዘገበው ሓዲስ የአላህ መልእክተኛ እንዲህ አሉ “አትመቀኛኙ፤ በውሸት አትጨራረቱ፤ አትጣሉ(በመካከላቹህ ጥላቻ አታምጡ)፤ ጀርባ አትሰጣጡ፤ በወንድማቹህ ገበያ ላይ አትሽጡ፤ ወንድማማቾች በመሆን የአላህ ባርያ ሁኑ፤ ሙስሊም የሙስሊም ወንድም ነው አይበድለውም፣ አይክደውም፣ አይዋሸውም እናም አያሳንሰውም ፤” ከዛም ወደ ደረታቸው(ልባቸው) ሶስት ግዜ እያመላከቱ የአላህ መልእክተኛ እንዲህ አሉ “ተቅዋ (የአላህ ፍራቻ) እዚህች ናት።” “አንድ ሰው መጥፎ ሰራ ለማለት ሙስሊሙ ወንድሙን አሳንሶ ማየቱ ይበቃል። ሁሉም ሙስሊም በሙስሊም ላይ ሓራም (እርም) ነው። ደሙም፣ ገንዘቡም፣ ክብሩም።” ሓዲሱን ሙስሊም ዘግቦታል።

26/08/2015

Over-thinking our problems is a sign we're spending too much time with the world and less time with Allah, exactly what the shaytan wants.

Address

Gonder
GONDER

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Team Dawah Gonder posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category