EYOB BOOKS

EYOB BOOKS READING REALLY MATTERS!

«የእናቴ ሮሚዮ» መጽሐፍ “ስነ-ጽሑፍ ለካ ወዝ አለው!” ያስባለኝ፤ ከባባድ ሐሳቦችን የተሸከሙ ቃላት ያለድካም ሲጓዙ ያየሁበት ድንቅ መጽሐፍ ነው፡፡ እያንዳንዱ ታሪክ ስሜትን በሚኮረኩር፣ ፈገ...
19/08/2026

«የእናቴ ሮሚዮ» መጽሐፍ “ስነ-ጽሑፍ ለካ ወዝ አለው!” ያስባለኝ፤ ከባባድ ሐሳቦችን የተሸከሙ ቃላት ያለድካም ሲጓዙ ያየሁበት ድንቅ መጽሐፍ ነው፡፡ እያንዳንዱ ታሪክ ስሜትን በሚኮረኩር፣ ፈገግታን በሚጭርና ሳቅን በሚፈጥሩ ጭብጦች የተሞላ የሐሳብ ጅረት ነው፡፡

«የእናቴ ሮሚዮ» የማይሰለች፣ የማይጠገብ፣ የትዳርን ጓዳ እየፈተሸ በእያንዳንዱ ቤት የሚዘልቅ፣ ራስን የመታዘቢያና ደግሞም የማስተካከያ ዕድል የሚፈጥር መስታወት ነው፡፡ በእውቀት የተጻፈ፣ በማስተዋል የተዘጋጀና ማኅበራዊ መስተጋብራችንን የሚያስተካክል መዶሻ ነው ማለት ይቻላል፡፡

ለደራሲዋ ምስጋናና አድናቆትን መቸር ለቀጣይ መጽሐፍ መወለድ ስንቅ ነውና፤ መጽሐፉን እየገዛችሁ እንድታነቡት በአክብሮት እጋብዛለሁ፡፡
ኢዮብ ጽጌ
EYOB BOOKS

18/08/2026
በመደብራችን በማበረታቻ ቅናሽ ይገኛሉ
14/08/2026

በመደብራችን በማበረታቻ ቅናሽ ይገኛሉ

ልጆች ሊያነቡት የሚገባ በጥንቃቄ የተዘጋጀ መጽሐፍ። በመደብራችን በቅናሽ ይገኛል።
13/08/2026

ልጆች ሊያነቡት የሚገባ በጥንቃቄ የተዘጋጀ መጽሐፍ። በመደብራችን በቅናሽ ይገኛል።

የሀዋሳ ታነብባለች የሐምሌ ወር እንግዳ ዝግጅታችን በደመቀና ባማረ መልኩ ተጠናቀቀ። ብርቱ ካህን ፣ የጥንካሬ ምልክት ፣ የዓላማ ፅናት ማሳያ፣ የብርታትና የሰላማዊ ትግል አብነት፤ አክብረሽን ...
04/08/2026

የሀዋሳ ታነብባለች የሐምሌ ወር እንግዳ ዝግጅታችን በደመቀና ባማረ መልኩ ተጠናቀቀ። ብርቱ ካህን ፣ የጥንካሬ ምልክት ፣ የዓላማ ፅናት ማሳያ፣ የብርታትና የሰላማዊ ትግል አብነት፤ አክብረሽን ስለተገኘሽ ፣ስላካፈልሽን ግሩም መልእክት ፣ ስለሰጠሽን ድንቅ ጊዜ እናመሰግናለን።
ለዝግጅቱ መሳካት ሴንትራል ሆቴል አዳራሽ ፣ ኬራውድ ኢንተርናሽናል ሆቴል የእንግዳችንን ቆይታ በነፃ በመተባበር የሁልጊዜም የከተማችንን የኪነጥበብ ዝግጅቶች በማገዝ የተለመደ ድጋፋቸውን ሰጥተዋል። በየወሩ ደራሲያን እያመጣን እንቀጥላለን። ሀዋሳ ታነብባለች። ቀጣይ የነሀሴ ወር እንግዳችንን is loading.........

የሀዋሳ ታነብባለች የሐምሌ ወር እንግዳችንን ተቀብለናል። የማይታለፍ ፣ የማይቀርበት ዝግጅት ተሰናድቷል። ዛሬ እሁድ ሐምሌ 26 በ9:00 ሰዓት በሴንትራል ሆቴል እንገናኝ። መግቢያ ፈገግታ ብቻ...
02/08/2026

የሀዋሳ ታነብባለች የሐምሌ ወር እንግዳችንን ተቀብለናል። የማይታለፍ ፣ የማይቀርበት ዝግጅት ተሰናድቷል።
ዛሬ እሁድ ሐምሌ 26 በ9:00 ሰዓት በሴንትራል ሆቴል እንገናኝ። መግቢያ ፈገግታ ብቻ።

Address

Hawassa
1138

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when EYOB BOOKS posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category