11/09/2022
ጥንቃቄ !ጥንቃቄ!
AHA App እና መሰል አፕልኬሽኖችን በመንካት ለአፕልኬሽኑ ፈቃድ የሰጣችሁ ወንድም እና እህቶች
አቡ ዳውድ ኡስማን
ይህን ጠቃሚ ማሳሰቢያ ለሌሎችም ሼር በማድረግ ያሳውቁ
ሰሞኑን በዚህ በፌስብክ በስፋት AHA App የተሰኘ የአፕልኬሽን ሊንክ እየተዘዋወረ ይገኛል::
የዚህ መሰሉ የአፕልኬሽን ሊንክ አብዛኛው ጊዜ የማልዌር፣ ስፓይዌር፣ የፒሺንግ እና መሰል የግል አካውንት መረጃዎችን መስረቂያ እና መሰለያዎችን የያዙ ይሆናሉ::
በርካቶች በማወቅም ይሁን ባለማወቅ በሌሎች የፌስቡክ ጓደኞቻቸው ፌስቡክ ገፅ ላይ ተለጥፎ ያዩትን አፕልኬሽኑ በራሱ የሚለጥፈውን የጨዋታ ውጤት በማየት ጨዋታ ብቻ እየመሰላቸው እነሱም ሊንኩን በመንካት ሲሳተፉ ይታያል::
ጨዋታውን ለመጫወት ቅድሚያ ሊንኩን ስንጫን አፕልኬሽኑ የግል የፌስቡክ አካውንታችንን፣ ፕሮፋይላችንን እና ፎቷችንን መጠቅም እንዲችል ፈቃድ ይጠይቀናል:: ለጨዋታው ብቻ እየመሰለን Allow የሚለውን ምርጫ በመንካት ለአፕሊኬሽኑ ፈቃድ በመስጠት በራሱ ፍላጎት የፌስቡክ ገፃችን ላይ የጨዋታውን ውጤት እንዲለጥፍ እንፈቅድለታለን::
የዚህ ጊዜ በራሳችን ፈቃድ ከአካውንታችን ጋር እንዲገናኝ ፈቃድ የሰጠናቸውን አፕልኬሽኖች ፖስዎርዳችንን ጨምሮ የግል መረጃዎቻችን ለአፕልኬሽኑ አበልፃጊዎች በቀላሉ እያቀበልን ሊሆን እንደሚችል መዘንጋት የለበትም:
እዚህ ጋር መታወቅ እና መጠንቀቅ የሚያስፈልገው የዚህ መሰሉ የሶስተኛ ወገን አፕልኬሽኖች በፌስበክ ድርጅት እውቅና የሌላቸው ለግል መረጃዎቻችን የደህንነት ጥበቃ ፌስቡክ ሃላፊነቱን የማይወስድ መሆኑን ነው::
በብዛት በአፕልኬሽኖቹ መቼ ትሞታለህ/ሽ፣ ወደፊት ምን ትሆናለህ፣ መቼ ታገባለህ፣ በምን ምክንያት ትሞታለህ፣ ወደፊት ስታረጅ ምን ትመስላለህ፣ የትምህርት ደረጃህ ስንት ነው፣ ሀዘንህ ከምን እንደመጣ ለማወቅ እንቁላሉላ ንካ፣ ፊትህ የሚገባው የስራ ድርሻ ምን አይነት ነው ወዘተ የሚሉ ማህበራዊ ጥያቄዎችን በአፕልኬሽኑ በኩል ይጠየቃል:: እኛ ደግሞ ጨዋት ብቻ እየመሰለን ሌሎች የተሳተፉ ጓደኞቻችንን ስም ስለሚያሳየኝ እኛም ለመጫወት አፕልኬሽኑ በመንካት አፕልኬሽኑ የአካውንታችንን መረጃ እንዲጠቀም እየፈቀድን ለመንታፊዎች እና ለነጣቂዎች አካውንታችንን በቀላሉ እንዲጠቃ በር እየከፈትን እንደሚገኝ ማስታወስ ያስፈልጋል::
ባለማወቅ ይህን ካደረግን መፍትሄውስ ምንድን ነው??
ለጥንቃቄ ያህል ከዚህ ስጋት ለፃ ለመሆን የፌስቡክ Setting ላይ እንገባለን:: በመቀጠል Security የሚለውን በመጫን APPS and Websites የሚለውን እንጫናለን:: እዚህ ውስጥ ስንገባ የአካውንታችንን መረጃዎች እንዲጠቀሙ አውቀንም ይሁን ሳናውቅ ፈቃድ ሰጥተናቸው ከአካውንታችን ጋር የተያያዙ አፕልኬሽኖችን በዝርዝር ያመጣልናል:: እያንዳንዱን እየመረጥን Remove የሚለውን በመጫን ማጥፋት ይገባል::
የምንፈልገውን ሁሉንም ካጠፋን ቡኃላ ወደ ፖስዎርድ መቀየሪያው በመግባት ፖስዎርዳችንን መቀየር ያስፈልጋል:: ይህን ማድረጋችን ለሶስተኛ ወገን አፕልኬሽን ተላልፎ የተሰጠብንን የግል መረጃዎች ደህንነት ለማረጋገጥ ያግዘናል ማለት ነው::
ማስታወሻ:- ለቀጣይ ግን ምን ጊዜም ቢሆን መሰል የሚለቁቅ ሊንኮችን ጨዋታ ብቻ እየመሰለን መንካት እና መቀላቀል አካውንታችንን ለስርቆት ሊዳርግ ስለሚችል በውስጥ መልዕክትም ሆነ በአደባባይ የሚሰራጩ ሊንኮችን ከመክፈት መታቀን ያስፈልጋል::
ይህ መረጃ ጠቃሚ ነው ብለው ካሰቡ ለሌሎችም ይዳረስ ዘንድ ሼር በማድረግ ያካፍሉት